Friday, 5 December 2025

የታይታ አገልግሎት የለንም!

Please read in PDF

ሽልማታችን ሰማይ፤ ዋጋችን ኹሉን በዓይኑ በሚቆጣጠር ጌታ ዘንድ እንደ ኾነ አውቀንና አምነን፣ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው የተከተሉ የጽድቅ መናንያን፤ የቅዱስ ቃሉን ሰማዕታት፤ እንደ ጨው በምድር ዳርቻዎች ኹሉ የተበተኑ ሐዋርያትን፤ እውነትና ፍትሕን እንደ ውኃ ከፈሰሰ ሕይወት ጋር የሰጡ ነቢያትን፤ ታርዶ እንደ ተወራረደ መሥዋዕት ኹለንተናቸውን የሰጡ ሰባክያንን፤ የምድረ በዳውን ዋዕይ፣ የበረሃውን ሚራዥ ታግሠው ሳይናወጡ የተጉና የኖሩትን እንደ ደመና ዙሪያችን ዘወትር የከበቡንን “ሕያዋን ጻድቃንን” አሠረ ፍኖታቸውን የምንከተል የተሰቀለው መሲሕ ማኅበረ ሰብ ነን። እናም መሲሑ እንዲልቅ፤ መንግሥቱ እንዲሰፋ፤ ለቤተክርስቲያን ጥቅምና መታነጽ እንጂ ለታይታ የምናደርገው አንዳችም የለንም።

Wednesday, 3 December 2025

ከዶክተር ገመቺስ ምክር ተጠበቁ!

 Please read in PDF

ከሰሞኑ ዶክተር ገመቺስ እንዲህ ብሎአል፤

ዳዊት ድሪምስ የወደቀውን የሰውን ሥነ ልቦና ለማነሳሳት የሚተጋ ሰው እንጂ የአዲሱ ዘመን ዕሳቤ አራማጅ አይደለም።”

ስለ አዲሱ ትውልድ እንቅስቃሴ አማኞችና ተከታዮች በሰፊውና በተከታታይ መጻፋችን ይታወሳል። ዶ/ር ገመቺስ ፈጽሞ እንደ ተናገረው ሳይኾን፣ እነ ዳዊት ድሪምስ፣ አሸናፊ ታዬ፣ ኤልያስ ገብሩ(ዶ/ር)፣ ግማዊት ክፍሌ፣ ነፃነት ዘነበ፣ ማንያዘዋል እሸቱና ሌሎችም በአገራችን የትምህርቱና የልምምዱ ዋና አቀንቃኞች መኾናቸውን አንስተን ጽፈናል፤ ዛሬ ደግሞ ዶክተሩ፣ ስለ ዳዊት ድሪምስ የተናገረውን በጥቂቱ እንቃኝ።