የምዩጣን ዐይን
ያወጣ ድፍረት!
ሰለሞን አቡበከርን በዝማሬዎቹ አውቀዋለኹ፤ ደጋግና ውዱድ መዝሙሮች አሉት፤ በትክክል ግን መዝሙሮቹን ርሱ ለመድረሱና ለመጻፉ እስክጠራጠር ድረስ “በሎዛ ሚዲያ” ያደረገውን ቃለ መጠይቁን ሰማኹት፤ በጣም በድፍረትና ባለማፈር ስለ ኦርቶዶክሳዊ ተሐድሶ አገልግሎት ሲናገርና የማያውቀውን ልክ እንደሚያውቅና ዋናው ሰው ርሱ እንደኾነ ሲናገር ሰምቼዋለኹ። ስለ ከንቱ ድፍረቱ ይህን አጭር ጽሑፍ መጣፍ ፈለግኹ!
ቃለ መጠይቅ የሚያደርግለት ሰው በግልጥ እንዲህ ብሎ ይጠይቀዋል፣
“… በጣም ማወቅ የምፈልገው፣ የምጓጓውና በጣም ብዙ ሰው ጠይቄ ሊመልስልኝ ያልቻለውና ተጨባጭ
መልስ ላገኝለት ያልቻልኩት፣ የኢትዮጵያ ተሐድሶ ኦሪጅናል ዋና ምንጩ የት ነው? ... ሰለሞን ይህን ጥያቄ ለመመለስ ታሪኩን ከአባ እስጢፋኖስ ሊጀምር
ሲል፣ ጠያቂው ርሱን አይደለም ልልህ የፈለግኹት፤ እዚህ አዲስ አበባ ላይ በዋናነት የተሐድሶን እንቅስቃሴ የሚመሩትን ዋና ዋና
ሰዎችን መጠየቅ ነው የፈለግኹ” ይለዋል።
ሰለሞንም “ፍኖተ አበውን እኛ ነን የመሠረትነው፤ ተሐድሶን የጀመርነው እኛ ነን” ይላል። ጠያቂውም
መልሶ፣ “ሰለሞን አንተ ከየት ታመጣዋለህ ተሐድሶን? መንፈስ ቅዱስ አልገለጠልህ?” ሲለው፣ ሰለሞን መልሶ፣ “ትምህርቱ
በነመሠረት ስብሐት ለአብ እንደ ተጀመረና ወደ ፊት ከተኼደ ደግሞ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብን የተቃወሙት እስጢፋኖስ የተባሉ ሊቀ ጳጳስ
ነበሩ” በማለት ይናገራል። አኹንም ግን ጠያቂው፣ “እስጢፋኖስ ሊቀ ጳጳስ ነበሩ እንዴ?” ሳይለውና ሳይጠይቀው፣ የሚፈልገውን
ጥያቄ እንዲመልስለት ሌላ ማብራሪያ ይሰጠዋል፤ “ለምሳሌ ሕወሐትን የመሠረቱት ሰባት ሰዎች ናቸው፤ ተሐድሶን የመሠረቱት እነማን
ናቸው?” ይለዋል። ነገር ግን ጠያቂው ጨርሶ የልቡ አልደረሰለትም። ጠያቂው በጣም የሚያሳዝን ሰው ነው፤ ማንን ምን እንደሚጠይቅ
እንኳ በትክክል አያውቀውም።
ጠያቂው ይቀጥላል፣ “... ለአንዴና
ለመጨረሻ ጊዜ በማያዳግም መልኩ የተሐድሶ እንቅስቃሴ መንኮታኮት፤ ማብቃት አለበት፤ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ መርዝ ሊነሰነስበት
ይገባል። ... አንተን የጸረ ተሐድሶ ኃላፊነት ቢሰጥህ ተሐድሶን ለማጥፋት ምን ያህል ርቀህ ልትሄድ ትችላለህ? እንቅስቃሴው
እንዴት ሊመታና ሊዳፈን እንደሚችል ታውቀዋለህ?” ሲለው፣ የአቡበከር ልጅ ትንሽ እንኳ አላሰላሰለም፣ “አዎን” ብሎ ይመልሳል።
እንዴት ለሚለው ግን ሲናገር፣ መነጋገር ከተቻለ ሊኾን እንደሚችል ያነሳል። ወደ ተሐድሶ ሄደዋል
የተባሉትን በመነጋገር መመለስና አገልግሎቱን መምታት እንደሚቻል በድፍረት ይናገራል። ያሳዝናሉ!
ግለ ምልከታዬ
ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ “ኦርቶዶክሳዊ ተሐድሶ ነበርን፣ ኦርቶዶክሳዊውን ተሐድሶ እናውቃለን፣
ኦርቶዶክስ ተሐድሶን እንወክላለን” ... የሚሉ በየአደባባዩና ሚዲያው ሲናገሩ[በተለይ ምዩጣኑና በብሽሽቅ የተጠመዱቱን] መስማት
እንግዳ ነገር አይደለም። አብዛኛዎቹ ኦርቶዶክሳዊ ተሐድሶ ምን ዐይነት ጥያቄ እንዳለውና ምን ዐይነት ሞጋች ሰነድ አቅርቦ፣
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሲኖዶስ ጭምር እንደ ተወያየበትና ሙግት እንደ ገጠመው አለማስተዋላቸው ይደንቃል። በተመሳሳይ መንገድ
ሰለሞንም፣ ተሐድሶ ከሚባለው ስም ውጭ የተሐድሶ ምንነቱን ሳያውቀው ብዙ መናገሩ አይደንቅም።
ደግመን ደጋግመን እንዳልነው፣ ተሐድሶ በገቢር ሲተረጐም፦
1.
የሚፈለግንና
የእግዚአብሔር የኾነውን መጠበቅ፣ መንከባከብ፣ ከጠላት መከላከል፣ እንዳይጎዳ ተገቢውን ቅጥርን መቅጠር ሲኾን፣
2.
እግዚአብሔር
የማይፈልገውን ነገር ደግሞ እንዲወገድ፣ እንዲቆረጥ፣ እንዲገረዝ ማድረግንም ይመለከታል።
ይኸው ተሐድሶአዊ ድርጊት በተገብሮ ሲተረጐምም፣ እኒህን ኹለት ነገሮችን ገንዘብ ያደርጋል።
እኒህም፦
1.
የእግዚአብሔር
ኾኖ የሚፈለገውን ነገር ማጥበቅ፣ እንዲንከባከቡ፣ ከጠላት እንዲከላከሉ ማድረግ ሲያመለክት፣
2.
እግዚአብሔር
የማይፈልገውን ነገር ፈጽሞ መወገዱን፣ መቆረጡን፣ መገረዙንም የሚያሳይ ወይም ማሳየትም ነው።
ይህን እውነታ እንኳን በትክክል ሊረዱና ሊያስረዱ ቀርቶ፣ በቅጡ እንኳ ሳያነብቡና ሳያውቁ
"የእኩያ ቡድንን ሰብስቦ" ተሐድሶ ነበርን ማለት እጅግ ያስደንቃል። ተሐድሶ የእግዚአብሔር ሥራ ብቻ ነው፤
ይኸውም በኀጢአት እርጅና የተጫጫነውን ፍጥረቱን በትክክልና ለክብሩ እንዲኾን አድርጎ ማደስ የሚቻለው ርሱ ብቻ ነውና።
እንግዲያስ ተሐድሶን ለማጥፋት ከታሰበ፣ እኒህን ድርጊቶች ደጋግሞ መተግበር ውጤታማ ሊያደርግ
እንደሚችል መምከር እንወዳለን።
1.
መጽሐፍ
ቅዱስ ከገጸ ምድ ማጥፋት፣
2.
የተሐድሶን
ጥያቄ መቀበል፣
3.
የማያቅርጠውን
የምንፈስ ቅዱስን ወቀሳና እቅስቃሴ መቋቋም መቻል፣
4.
ከመጽሐፍ
ቅዱስ ውጭ ካሉ መጻሕት ኹሉ የክርስቶስን ስምና ስለ ክርስቶስ ማዳን የሚናገሩ ዐሳቦችን ማጥፋት መቻልና ሌሎች ተመሳሳይ ተግራን
ማከናወን ተሐድሶን ለአንዴና ለማያዳግም ጊዜ “ሊያጠፋው” ይችላል!
ከዚህ በኋላ “የሚሄዱ” ምዩጣንም ኾኑ “ሄደው ያልሄዱትም” ጭምር ሊረዱት የሚገባው እውነት፣
“በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍ” ቢርቁ ይጠቅማቸዋል እንጂ አይጎዳቸውም!
“ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ለሚወድዱ ሁሉ ጸጋ ይሁን።” (ኤፌ. 6:24)
አሜን።
ሰዉ ልጅ ለማይረባ አዕምሮ ተላልፎ እንዳይሰጥ የሚል የእግዚአብሔር ቃል ማስታወሱ አሰፈላጊ ነው የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ይልቅ ነወይ ከአስቀድመው እንዲህ ይዋሻል ይህ ይጠበቃል
ReplyDeleteተሐድሶን ለማጥፋት ከታሰበ፣ እኒህን ድርጊቶች ደጋግሞ መተግበር ውጤታማ ሊያደርግ እንደሚችል መምከር እንወዳለን።
ReplyDelete1. መጽሐፍ ቅዱስ ከገጸ ምድ ማጥፋት፣
2. የተሐድሶን ጥያቄ መቀበል፣
3. የማያቅርጠውን የምንፈስ ቅዱስን ወቀሳና እቅስቃሴ መቋቋም መቻል፣
4. ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ካሉ መጻሕት ኹሉ የክርስቶስን ስምና ስለ ክርስቶስ ማዳን የሚናገሩ ዐሳቦችን ማጥፋት መቻልና ሌሎች ተመሳሳይ ተግራን ማከናወን ተሐድሶን ለአንዴና ለማያዳግም ጊዜ “ሊያጠፋው” ይችላል!