Sunday, 27 April 2025

ሚካኤል ስለ ሙሴ ሥጋ ከዲያብሎስ ጋር ለምን ተከራከረ?!

 Please read in PDF

ይሁዳ በመልእክቱ ውስጥ በሙሴ ሥጋ ምክንያት የሊቀ መላእክት ሚካኤልና የዲያብሎስ ክርክር መቅረቡን ይነግረናል። ስለ ሙሴ ሥጋ ጥቂት ብናነሣ፣ በዘዳ.  34፥5-6 እንደ ተጠቀሰው በሞዐብ ምድር እንደ ሞተና ከቤት ፌጎር አንጻር ባለው ሸለቆ ውስጥ እንደ ተቀበረ ይነግረንና የመቃብሩን ስፍራ ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሚያውቅ እንደሌለም ይነግረናል።

Saturday, 26 April 2025

Furiin dhugaa Yasuus malee hinjiru!

 Please read in PDF

Jechoota gurguddoo dubbii Waaqummaa keessaa inni tokko Furii dha. Kakuu duraa keessatti qabeenyi lubbuudhaaf furii ta'e caqasameera (Fkn. 13:8); warri Israa'el lafa ykn mana isaani erga gurguratan booda furii gochuudhaan deebisifachuu danda'u ture (Leewo. 25:24-34). Raajiin Muuseen ummata Israa'el gabrummaa Gibxi jalaa sababa bilisa baaseef furii ykn bilisa baasaa ta'eera ykn jedhamee yaamameera. (Ho. Erg. 7:35).

የትክክለኛ ቤዛ መስፈርቱ ይኸው!

Please read in PDF

በአጭር ቃል ስብከት፣ “... እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤” (1ቆሮ. 1፥23) እና “ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤" 1ጢሞ. 1፥15) የሚለው ብቻ ነው። ቅዱሳን ሐዋርያትም፣ የስብከታቸው ማዕከል፣ "መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” (ሐ.ሥ. 4፥12) የሚል ነበር።

Thursday, 24 April 2025

ሄኖክ ኃይሌ፣ “ሰባኪ” ከኾነ ከመጽሐፍ ለምን አይጠቅስም?

 Please read in PDF

ሄኖክ ሃይሌ፣ ለጳጳሱ አባ ገብርኤል በመለሰው መልስ ውስጥ እንዲህ የሚል ንግግር አለው፣

ያስተማሩት የታሰበበት ክህደት ነውና … ሙሴ ቤዛ በተባለበት መጽሐፍ ቅዱስ እያመኑ ድንግል ማርያም ቤዛ አትባልም ላሉት ጳጳስ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤዛ ሲሆናቸው ማየት አንፈልግም። ጠንከር ያለ ቀኖናዊ እርምጃ እንጠብቃለን።”

ነገሩን ግልጽ ለማድረግ፣ ሙሴ “ቤዛ” የተባለበትን ዐሳብ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማየቱ እጅግ መልካም ነው። በታላቁ መጽሐፍ ውስጥ በእስጢፋኖስ አንደበት፣

“ … ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።” (ሐ.ሥ. 7፥35)

ተብሎ ተጠቅሶአል። ስለ ሙሴ ጥቂት እንናገር፣ ሙሴ በግብፃዊቷ ልዕልት ቤት ያደገ ዕብራዊ ሰው ነበር (ዘጸአት 2፥1-10)። ለእኛ ባልተገለጠና የመጀመሪያው ዘገባ በማይገልጠው መንገድ፣ ሙሴ ሕዝቡን ከባርነት ነፃ ለማውጣት እግዚአብሔር እንደ ላከው ያውቅ ነበር (ሐ.ሥ. 7፥25)። በመጀመሪያ ሙከራው ሙሴ ዕብራዊውን እየደበደበ ያለውን ግብፃዊ ሰው ገደለ። በማግስቱ፣ እስራኤላውያን ረድኤቱንና ሥልጣኑን አለመቀበል ብቻ ሳይሆን ግድያውን እንደሚያውቁ ተገነዘበ። ፈርዖን ሳይገድለው ሙሴ ወደ ምድያም ምድር ሸሸ (ዘጸ. 2፥11–15)።

Wednesday, 23 April 2025

"ሊቃውንቱና መምህራኑ" እንዴት ከመጽሐፉ ተራራቁ?!

 

ደግሜ ቤዛ ለሚለው ቃል የተሰጠ ፍቺ ልጥቀስ፣ " ... ቤዛ ማለት፦ “... ካሣ፣ የደም ቤዛ፣ አንዱ ሰው የሰውን ደም ስለሚያፈስሰው ለውጥ ወይም ዋጋን፣ ገንዘብን፣ ካሣን መስጠት ወይም መዋጀት ማለት ነው።” ይላል የከሣቴ ብርሐን መዝገበ ቃላት። (ከሣቴ ብርሃን መዝገበ ቃላት፤  1951 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ገፅ 532)። ጌታችን ኢየሱስ ስለ ቤዝወት በተናገረ ጊዜ እንዲህ አለ፣ "የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።" (ማቴ. 20፥28፤ ማር. 10፥45) ብሎአል።


Tuesday, 22 April 2025

“ነይ ነይ እምዬ ማርያም… ቤዛዊት ዓለም … ስህ-ተ-ት ነው” (አባ ገብርኤል)

Please read in PDF

ከሰሞኑ በጣም ያከራከረ አንድ ርዕሰ ጉዳይ አለ፤ ነገረ ቤዝወት። “ቤዝወት” ታላቅ ነገረ መለኮታዊ ዕሳቤን በውስጡ የያዘ አስደናቂ ቃል ነው። በብዙዎች አንደበት የሚጠቀስ ቃል ቢኾንም፣ ቃሉ በትክክል ስፍራውንና ትርጕሙን አጊኝቷል ብዬ ግን አላምንም። ጥቂት ስለ ቃሉ እናውጋ እስኪ!

ቤዛነት ምንድር ነው?

“ቤዛ” የሚለው ቃል፣ ከግዕዝ ቋንቋ የተወሰደ ሲኾን፣ ሰውን ከባርነት ነጻ ለማውጣት የሚከፈል ዋጋ ወይም አንድን  የተያዘን ወይም የተወሰደን ነገር ለማስመለስ የሚከፈል ዋጋን፣ ካሳን አመልካች ነው። ቤዛን የመክፈል ሥራ ደግሞ፣ ቤዛነት ተብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሶአል። ቤዛነት፣ በበደለኛው ሰው የተወሰነውን ትክክለኛ ፍርድ ተመጣጣኙን ዋጋ ከፍሎ ነፃ ማውጣት ነው። ስለዚህም ቤዛ ማለት፣ “በቁሙ ዋጋ፣ ካሳ፣ ለውጥ፣ ምትክ፣ ዋቢ፣ ዋስ፣ መድን፣ ተያዥ … የመሰለው ኹሉ። [በደቂቅ አገባብ] ደግሞ፣ ስለ፣ ፈንታ፣ ምክንያት”[1] በማለት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ያብራሩታል። ከዚህ በመነሣት፦