Monday, 19 June 2023

“ጠላቶቻችሁን ውደዱ” (ማቴ. 5፥43-48)

 Please read in PDF

ጌታችን ኢየሱስ የሚመሠርታት መንግሥት፣ እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት አይደለችም፤ መንግሥቱ ለፍጹማንና እርሱን ለሚከተሉ ብቻ የምትገባና የምትሰጥ ናት። ጌታችን ኢየሱስ ስለ መንግሥቱና በመንግሥቱ ውስጥ ተከታዮቹ እንዴትና በምን መልኩ መመላለስ እንዳለባቸው ሊያስተምራቸው ወደደ፤ ትምህርቱ ባዶ ቃላት አይደሉም፤ ውብና የሕይወት ተስፋዎችን ጭምር የያዙና በምትመጣውም መንግሥቱ እንዴት መመላለስ እንዳለባቸው በንጉሣዊ ወርቃማ ቃሉ አስተምሮአል።

Sunday, 4 June 2023

የምንጠማው መንፈስ!

 Please read in PDF

ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ፦ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። … ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ፤ …” (ዮሐ. 7፥37፡ 39)

በአይሁድ ባህል መምህራን የሚያስተምሩት ተቀምጠው ነው፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን ከአይሁድ ባህልና ሥርዓት ወጣ ባለ መንገድ፣ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገር፣ ኹሉም ሰው እንዲሰማውና ትኵረት እንዲሰጠው ለማድረግ ፈልጐ ቆሞ ደግሞም “ጮኾ” (ቍ. 38) ተናገረ። ቆሞና ጮኾ በመናገሩ፣ ከበዓሉ በመጨረሻው ቀን የነበሩት ሕዝቦች ኹሉ እርሱን ለመስማት ችለዋል።