Sunday 30 January 2022

ይምረረው ፈጽሞ

Please read in PDF

ይቅለል አይወደድ

እንደ ወይን ወዳድ ይኹን ፌዝና ቀልድ

ተሳልቀው ያጠልሹት

ፈጥፍጠው ይናቁት

ያኔም...

መሰናከያና ነበረ ሞኝነት።

ዛሬ በኔ ዘመን ቃሌ ከጣፈጠ

ስብከቴ ተወ'ዶ እኔን ካስመረጠ

መስቀሉ ተዋርዶአል ኢየሱስ ተረግሟል

የኔ ቃል ሲወደድ ኢየሱስ ተንቋል።

እንኪያስ...

ስብከቴ መስቀሉን አድምቆ ሲሰብከው

ይምረረው ፈጽሞ የኢየሱስ ያልኾነው!


No comments:

Post a Comment