Thursday 11 November 2021

በደስታ ካልተገዛህለት!

 Please read in PDF

ቅጥር እንዳትቀጥር፣ እንዳታበጅ መስመር

ሚዛን ቱንቢው ይቅር፣ ብላ ጠጣ ጨፍር

በቅንብብ አትኑር፣ ባ’ጥር አትከበብ

ነጻ ኹን ተፈታ፣

ተፍነክነክ፤ ተደሰት፤ በሳቅና ፌሽታ …

ነጻነት ትርጉሙ ቅጥ አጣ፤ ጠነዛ

ሰው …

ከሚሻለው ሸሽቶ ለባሰው ተገዛ

ድንኳን አስቀርቶ ካስማ እየሸጠ

ቆሜያለሁኝ ይላል እየተለመጠ

የነጻ አርነቱን ለኃጢአት እየሰጠ!

እናም አማኙ ሆይ!

ነጻነት ለሰጠህ ላ‘ርነት ለዳረህ

ከባሪያ አሳዳሪ “ፈንግሎ” ላቆመህ

ለ‘የሱስ በደስታ ካልተገዛህለት

ገና ባሪያ እንጂ አላየህም ዕረፍት!

3 comments:

  1. ጌታን በታማኝነትና በቅንነት ስለምታገለግሉ እርሱ አብዝቶ ይባርካችሁ!!

    ReplyDelete
  2. የፀጋው ባለቤት ይባረክ! እግዚአብሔርን ስለናንተ ዘወትር አመሰግናለሁ! ተባረኩ!

    ReplyDelete
  3. God bless you my brother.

    ReplyDelete