Thursday 5 July 2018

ፊታችንን መልስ

Please read in PDF

ግፍ ደንደስ አወጣ፣ ዓመጽ ሥር ሰደደ፤
ቀንበር እንደ ጸና፣ መቃናት ሳይመጣ፣ ቀኑ ተዋገደ፤
ስል ኃጢአት ወረረን፣ ንቅዘታችን ታየ፤

በልብ ትምክህት፣ ንስሐው ዘገየ፤
ኤሎሄ ኤሎሄ፣ ለምን ተውከን ጌታ?
ደግ እያቃሳተ፣ ለኀጥዕ ሲኾን ደስታ?!
አንተ ቀን አውጪ ሆይ! የእስራኤል ቅዱስ፤
ፊትህን እንድናይ፣ ፊታችንን መልስ፤
መፈለግ ማድረግም፣ ካʼንተ ዘንድ ነውና፤
በክፉዎች ክፋት፣ በክፉ እንዳንቀና፤
አንተን መጠማትን፣ እስከ ለዘላለም፣ በልባችን አጽና
አሜን



1 comment: