Sunday, 18 January 2026

ተጠመቀ ጌታ!

 Please read in PDF

ርደተ ገሃነም ርደተ መቃብር

በመርገመ ሥጋም የነፍስ ሲጨመር

ጽሕፈተ ዕዳችንም ደልቦ ወርዝቶ

በእኛነታችን ላይ እንደ ለምጽ ነጥቶ

መቅረብ እንዳንችል ሰማዩ ተዘግቶ …

ሳለን ኀጢአተኛ ፍጹም ጠላቶቹ

ሊታረቀን መጣ የሱስ የናዝሬቱ፡፡

ከኀጢአት በቀር ሊኾን ከኛ እንዳንዱ

መጣ ክብሩን ትቶ ወዶ በፈቃዱ፤

በዕደ ዮሐንስ ልክ እንደ ኀጥዕ ሰው

ተጠመቀ ጌታ ዕዳችንን ሊሽር፤ ሰማዩን ሊከፍተው!

2 comments:

  1. ተጠመቀ ጌታ ዕዳችንን ሊሽር፤ ሰማዩን ሊከፍተው!

    ReplyDelete
  2. ተጠመቀ ጌታ ዕዳችንን ሊሽር፤ ሰማዩን ሊከፍተው!

    ReplyDelete