Friday, 21 November 2025

የትውልድ ነቀርሳ - የአዲሱ ትውልድ እንቅስቃሴ (የመጨረሻው ክፍል)

 Please read in PDF

የአዲሱ ትውልድ እንቅስቃሴ፦

6.    በልምምዱ ጥንቁልናና አስማትን ያበረታታል፦ ኮከብ ቈጠራ እና ጥንቈላ፡ ለራስ ለውጥ እና ማስተዋል የሚያገለግሉ ሟርት አክል መሣሪያዎችን በጽኑ ይደግፋሉ። በራሳቸው ይህን ቢደግፉና ቢቀበሉ ማንም አይቃወማቸውም፣ ምክንያቱም “የትኛውም ሰው የፈለገውን ሃይማኖት የመከተል መብቱ የተጠበቀ ነው። ነገር ግን የሮንዳ በርንን፣ የቦብ ፕሮክተርን፣ የድፓክ ቾፕራንና የኤካርት ቶልን፣ የማሪያን ዊልያምሰን፣ የባርባራ ማርክስ ሁባርድ፣ የኒሌ ዶናልድ ዋልሽ፣ የባርባራ ዴአንጀሊስ፣ የላቫር በርተን፣ የሪቻርድ ካርልሰን፣ የቤቲ ኢዲ፣ የኬን ፎሌት ወይም ደግሞ የእንቅስቃሴው አባቶች የሚባሉትን የአሊስ ቤይሊ፣ የቴይልሃርድ ዴ ቻርዲን፣ የሮበርት ሙለር፣ የዴቪድ ስፓንገር እና የቤንጃሚን ክሬም የአዲሱ ትውልድ እንቅስቃሴ አስተምህሮን እያቀነቀኑ የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ነኝ ማለት ፈፅሞ አይቻልም።”


Wednesday, 12 November 2025

የትውልድ ነቀርሳ - የአዲሱ ትውልድ እንቅስቃሴ ክፍል - ፯

 Please read in PDF

4.    እውነት አንጻራዊ ናት፦ በአዲሱ ትውልድ እንቅስቃሴ አስተምህሮ መሠረት ፍጹም እውነት የለም፤ ምክንያቱም ኹሉም እምነቶች ትክክልና ትክክለኛ ናቸው። ለምሳሌ፦ በክርስትና አስተምኅሮ አንድ ሰው ከጋብቻ ውጭ የሚያደርገው ማናቸውም ሥነ ምግባራዊ ርኩሰት አመንዝራነት ነው፤ ለአዲሱ ትውልድ እንቅስቃሴ ግን ርኩሰት ሳይኾን ትክክል ነው። በጋብቻ ውስጥም፤ ከጋብቻ ውጭም የሚደረግ አመንዝራት እውነትና ውሸት ቢኾንም፣ ለነርሱ ግን ኹለቱም እውነት ነው።

Friday, 7 November 2025

ቤን ሂንና ኑፋቄው!

 Please read in PDF

ሰውየው አስቀድሞ መጠሪያው “Faith World Church - የእምነት ዓለም ቤተክርስቲያን” በተባለ፣ በአኹን ወቅት ደግሞ World Healing Center Church - የዓለም የፈውስ ማዕከል ቤተክርስቲያን” የሚል ስያሜ የተሰጠው የግል “ቤተ ክርስቲያን” ያለውና “የብልጽግና ወንጌልን” አቀንቃኝ “ንጥጥ ባለጠጋ” ነው። ከባለጠግነቱና ከቅምጥልነቱ የተነሣ፣ የሂን የወንድም ልጅ የኾነው ፓስተር ኮስቲ ሂን በርሱ ቤት ተጠልሎ ሳለ ያየውን ሲናገር፣ ቅዱስ ጳውሎስና እነርሱ የሚለያዩበትን አንድ እውነት፣ “እኛ የጳውሎስን አይነት ወንጌል አንሰብክም ነበር።” በማለት ገልጦታል።[1] በምስክርነቱ ላይ ኮስቲ ሂን፣ እሱ እና ቤተሰቡ የያዙትን ውድ መኪናዎች እና ውድ ቤቶችን እና በጉዞው ዙሪያ ስላለው የቅንጦት ኹኔታ ገልጦአል።[2] ኮስቲ ሂን የአጎቱን የብልጽግና ወንጌል እና አስተምህሮ በመተቸት ብዙዎቹ ትንቢቶቹ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እንደሚቃረኑ ጽፎአል።[3]

Tuesday, 4 November 2025

ቃሉን የሚያነብብ ብፁዕ ነው!

 Please read in PDF

ቅዱስ ቃሉን ማንበብ መንፈሳዊና ታላቅ አምልኮ ነው፤ አቡቀለምሲሱ ቅዱስ ዮሐንስ፣ “[ቅዱስ ቃሉን] የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።” (ራእ. 1፥3) ይለናል። ሐዳሲው ቅዱስ ዕዝራ፣ “... ወንዶችና ሴቶች የሚያስተውሉም ሲሰሙ፥ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ አነበበው የሕዝቡም ሁሉ ጆሮ የሕጉን መጽሐፍ ለመስማት ያደምጥ ነበር።” (ነህ. 8፥3) እንዲል፣ ቃሉን ከእኩለ ቀን በላይ ማንበብ እጅግ ታላቅ አምልኮ ነው።