Saturday, 8 March 2025

12 ዓመታት በጡመራ መድረክ!

 

መልካሚቱም የአምላኩ እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና” እንዲል፣ ጌታ እግዚአብሔር በመልካምነቱ ባለፉት አሥራ ኹለት ዓመታት በረድኤቱ በጽሑፍ እንዳገለግል ረድቶኛል። በነዚህ ጊዜያቶች ከእግዚአብሔር ልጅ ከክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ለመስበክ አልተመኘኹም፤ ሰብኬውም ገና አልጠገብኩትም፤ ኢየሱስ ጽዋዬና ርስቴ ነውና ከርሱ በቀር ሌላ ምንም አያጓጓኝም፤ እግዚአብሔር አለኝ፤ በቂዬ ነው!

Saturday, 1 March 2025

“ … ውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶበታል።” (ሉቃ. 11፥39)

 Please read in PDF

ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን ሲጽፍልን፣ ትኵረት ካደረገባቸው ታላላቅ መንፈሳዊ ነገሮች አንዱ፣ ድኾችን በተመለከተ ነው። በወንጌሉ ውስጥ ኢየሱስ ቤት አልባ ድኻ ነው (9፥58)፣ አገልግሎቱ አምነው በተከተሉት ሴቶች ይደገፍ ነበር (8፥3)፣ አገልግሎቱ ለድኾች ወንጌልን በመስበክ እንደ ኾነ ተናገረ (4፥18)፣ ቅድስት ድንግል ማርያም ድኻ እናት መኾንዋን በመሥዋዕት አቀራረቧ አሳየ (2፥24)፣ “የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤” (1፥53) እንዲል፣ ድኾችን በብዙ እንደሚጐበኝና እንደ አልዓዛር ያሉ ድኾችን በሰማያት በብዙ ደስታ እንደሚያከበር ማስተማሩን ጽፎልናል (16፥19)፤ ይህ ብቻ ሳይኾን ሉቃስ፣ በኤልያስ ዘመን የነበረችውንም የሰራፕታዋንም ድኻይቱን መበለት አንስቶአል (4፥26)።