ጌታ እግዚአብሔር አምላካችን፣ ሊቀ ነቢያት ሙሴን ለመቅደስ
አገልገሎት የሚያስፈልጉ ንዋያተ ቅድሳት እንዲያዘጋጅ በዝርዝር ተናግሮታል። እንዲዘጋጁ ከተናገራቸው ንዋያተ ቅድሳት መካከል አንዱ፣
በአሮን ወይም በሊቀ ካህናቱ ጥምጣም ላይ በጕልህ መንገድ እንዲታይ ከወርቅ ሰሐን የተሠራው ጽሑፍ ነው። ጽሕፈቱ ጕልህ በመኾኑና
እይታን በመሳቡ ምንያት ለኹሉ የሚታይ ነው። “በመጠምጠሚያው ፊት በሰማያዊ ፈትል በመጠምጠሚያው ላይ የሚሰፋውና በአሮን ግንባር
ላይ የሚኾነው”፣ “ቅድስና ለእግዚአብሔር ወይም ለጌታ የተቀደሰ” የሚል ከንጹሕ ወርቅ ቅጠል ሥራ ወይም በወርቅ ሳህን ቅርጽ የተቀረጸና
በጥምጣሙ ላይ የሚደረግ ነው።
Wednesday, 25 February 2026
“ቅድስና ለእግዚአብሔር” (ዘጸ. 28፥36)
Thursday, 19 February 2026
ከዝሙት ሽሹ!
ከሰሞኑ የአሜሪካን ምድር የናጠ አንድ በአብላጫው “የዝሙት መረጃን” ያጨቀ፣ ከአንድ ግለሰብ የመረጃ ቋት “አፈትልኮ” ወጥቶአል፤ መረጃው ከአሜሪካ እስከ አፍሪካ፤ ከአውሮፓ እስከ ኤስያ የሚገኙ የአገር መሪዎችን፣ “የታወቁ ሰዎችን”፣ ለምድር የከበዱ የሚባሉትን ኹሉ በአንድም በሌላም መንገድ የሚነካካ ነው። እጅግ አሳዛኙ ተግባር፣ ለነዚህ ሰዎች የዝሙት ማገዶነት የሚቀርቡት ሴቶች ኹሉም ማለት በሚያስደፍር መልኩ “አካለ መጠን” ያልደረሱና ሕጻናነት ናቸው፤ ነገሩ አባት ከገዛ ልጁ ወይም አያት ከሚኾናት ሕፃን ጋር የ”መተኛት” ያህል ነው።
Sunday, 15 February 2026
ጾምን በራብ እንጹም!
በሥጋችን ምግብና ውኃ ስናጣ መራብና መጠማት የጤነኝነት ምልክት ነው፤ እኒህን ስናጣቸው አለመራብና አለመጠማት ጤነኝነት አይደለም። ራብና ጥም የሌለው ሰው፣ በጽኑ ደዌ ወይም ለሞት በሚያበቃ ሕመም ለመያዙ ምክንያት ሊኾን ይችላል። ስለዚህ ራብና ጥም ለሰውነታችን አንዳች ረብ ያለው ነገር እንደሚያስፈልገን ኹነኛ ምልክት ነው።
Friday, 6 February 2026
ነነዌ ተቀጥታለች!
የዮናስን የትንቢት መጽሐፍ ስናነብ፣ የነነዌ ኀጢአት ይቅር መባሉን እናውቃለን። የናሆምን የትንቢት መጽሐፍ ስናነብ ደግሞ የነነዌ የታወቁ ኀጢአቶች ምን፤ ምን እንደ ኾኑ እናስተውላለን። ነቢዩ ናሆም የነነዌ ኀጢአት በዝርዝር ሲገልጥ፣ በእግዚአብሔር ላይ ማሴር ወይም በክፉ ማሰብ (1፥9፡ 11)፣ ጣዖትን ማምለክ በተለይም ምናሴ የጣዖትን አምልኮ ከነርሱ ወርሶአል (1፥14)፣ የተለያዩ የሰዎችን አካላት በመቁረጥ ጭካኔ የተሞላባት ቅጣትን መፈጸም(3፥19)፣ ውሸት፣ ንጥቂያ ወይም ቅሚያ (3፥1)፣ አስማት፣ ጥንቆላና ዝሙት[ግልሙትና] (3፥4) የታወቀችበት ኀጢአቷ ነበር። ይህ ኹሉ ሲኾን የአሶርዋ ነነዌ ምንም ነገር እንደማያገኛት አስባ ተዘልላና ኮርታ ተቀምጣ ነበር።
Sunday, 1 February 2026
እንቅልፋሙ ዮናስ!
ወደ አሕዛባዊቷ ነነዌ የተላከው ዮናስ፣ ሕጋዊ ታሪፍ
ከፍሎ ወደ ተርሴስ ኮበለለ። ቀለል አድርገን ካየነው፣ ዮናስ ሕጋዊ ክፍያ ፈጽሞ መሄዱ ችግር ላይኖርበት ይችላል፤ ነገር ግን ወደ
እግዚአብሔር ፈቃድ አላደረሰውም። እንዲያውም የተሳሳተን ነገር በትክክለኛው መንገድ ለመሥራት መጣር ነገሩን ትክክል ካለማድረጉ ባሻገር
አደገኛ ያለመታዘዝ ምልክት ነው። የእግዚአብሔርን ፈቃድና ትእዛዝ የሚቃረን ማናቸውም ነገር እጅግ ትክክል በተባለ መንገድ ቢደረግም
ኀጢአት ነው። ይህ የዮናስ አደገኛ መንገድ ነው።


