በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የ“ተሐድሶ አገልጋዮች” ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል፤ ዕዝራ፣ ነህምያ፣ ዘሩባቤልና ኢያሱ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። ሕዝቡና እነርሱ በምርኰ ሳሉ፣ የእስራኤልን ጥልቅ ውድቀትና መንፈሳዊ ቅዝቃዜ በማየት፣ እስራኤል ዘሥጋ ትነቃቃና ታበራ፤ ትጌጥና ትፈካ ዘንድ የነቢያቱን የተስፋ ቃል በማወጅ፤ እንደገና በማስታወስና አጽናንቶ በማበረታታት ይታወቃሉ።
Thursday, 18 June 2026
Sunday, 7 June 2026
ወንድምነት ረክሶ አገልግሎት ሲመለክ!
በዘመናዊው ዓለም ኢየሱስ በኪደተ እግሩ ከሰማርያ እስከ ኢያሪኮ የሚፈልጋቸው ሳምራዊቷ ሴትና የጤሜዎስ ልጅ በርጠሚዎስ፣
ወይም በቅፍርናሆም ያገኛት ደሟ ቀጥ ያለላት ሴት፣ ለዚህ ዘመን አገልጋዮች ጥሩ የስብከት ርዕስ እንጂ በወንድምነት ወይም በእህትነት
የሚፈለጉ አይመሰለኝም። በቀላል ንግግር ሰውነት በዚህ ዘመን ከአገልግሎት አይበልጥም የተባለ ይመስላል።
Friday, 5 June 2026
ጳውሎስ የሰማው የሞት ድምጽ! (2ቆሮ. 1፥9-11)
ቅዱስ ጳውሎስ ኹለተኛውን ቆሮንቶስ እየጻፈ ያለው፣ በአንደኛ መልእክቱ ላይ በታላቅ ተግሳጽ የገሰጻቸውንና ንስሐም
በመግባት የንስሐ ፍሬ ያሳዩትን ቅዱሳን ወገኖቹን ለማጽናናትና ለማበረታታት ነው።
አንደኛውን መልእክት ሲዘጋ፣ የወንጌል ሥራ በር እንደ ተከፈተለትና ነገር ግን የዚያኑ ያህል ደግሞ እጅግ ተቃዋሚዎች እንደ ተነሱም ተናግሮአል (1ቆሮ. 16፥8-9)፤ ምናልባት ተቃዋሚዎቹ ከባድ ስደት አልያም ከፍ ያለ እንግልት አድርሰው ሊኾን ይችላል።
Monday, 25 May 2026
በሥጋው ያረገ ጌታ!
ክርስቶስ ኢየሱስ ከቅድስት ድንግል በነሣው ሥጋና ከሙታን
መካከል ሲነሣ በለበሰው ፍጹም ሰውነቱ ወደ ሰማያት አርጓል። ምክንያቱም የመጣበት ዋነኛ ዓላማ፣ “የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን ነውና”
(ሉቃ. 19፥10)። ደግሞም ሰውን ለማዳን ክርስቶስ እንከን አልባ ሰው መኾን ያስፈልገው ነበር። ከዚህም የተነሣ ሊያድነን በፍጹም
ሰውነቱ የተሰቀለው ያው መሲሕ፣ በሰማያት መግቢያ በር ይኾነን ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ።
Tuesday, 19 May 2026
Monday, 18 May 2026
Thursday, 14 May 2026
“በወንጌል ሕይወታችን ኾነ” ከሚለው ጉባኤ የተወሰዱ ቊልፍ አባባሎች፣
-
“… አኹን ያለንበት ጊዜ ስብከተ
ወንጌል በዋና ዓላማነት ያልያዘበት፣ ሊቃውንትን በማፍራት ብቻ ቤተ ክርስቲያን የተጠመደችበት ጊዜ ቢኖር አኹን ያለንበት ጊዜ ነው።
…”
- “… ወንጌል እንደ ቅዱስ ጳውሎስ መሥዋዕታዊ ሕይወትን ዘወትር ይፈልጋል። …”
Saturday, 2 May 2026
“በወንጌል ሕይወታችን ኾነ” ከሚለው ጉባኤ የተወሰዱ ቊልፍ አባባሎች፣
-
“… የሰው ልጅ ኹለተኛ ባሕርይ
ረቂቅ ነፍስ ናት፤ ለረቂቅ ነፍስ ደግሞ የሚሰዋላት ሕያው መስዋዕት ወንጌል ነው።”
- “… የወንጌል ሰባኪው ራሱ ሕያው ወንጌል ነው፤ ብዙ ጊዜ ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ወይም ሃይማኖታቸውን በጥልቀት የማይመረምሩ፣ ለማንበብ ጊዜ የሌላቸው ምእመናን ሁልጊዜ የሚያነብቡት የአገልጋዩን ሕይወት ነው። …”
Wednesday, 29 April 2026
“በወንጌል ሕይወታችን ኾነ”
“በወንጌል
ሕይወታችን ኾነ” በሚል መሪ ቃል፣ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገር አቀፍ የወንጌል ቀን ለሦስተኛ ጊዜ ባለፉት ኹለት
ቀናት አክብራ አሳልፋለች። ይህም በዋናነት ትኵረት ያደረገው፣ የወንጌልን ትምህርት በቋንቋ ተደራሽ ለማድረግ ከቀደሙት ዓመታት ይልቅ
በተለየ ኹኔታ በማሰብ እንደ ኾነ ተገልጦአል። የቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ እንዳሉትም፣ “የቤተ
ክርስቲያን መሠረታዊ ዓላማ ምዕመናንን በቃለ እግዚአብሔር ወንጌል አንፆ ለክርስቶስ ዳግም ምጽአት ማዘጋጀት እንደ መኾኑ መጠን፣
ሰባክያን ምሳሌ ባለው ሕይወት ሊያገለግሉ ይገባል።” ብለዋል። ተያያዥነት ባለው መልኩ፣ በተለይም ወንጌል ለሚያገለግሉ ሰባክያን
ልዩ ትኵረት እንዲሰጥና፣ ሰባክያኑም አገልግሎታቸው “ተልእኮ ተኰር” እንዲኾን ከታዳሚው በተደጋጋሚ ተጠቅሶአል።
Sunday, 26 April 2026
Thursday, 23 April 2026
“በመንፈስ ተመላለሱ” (ገላ. 5፥16)
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፣ “የሥጋ ምኞት በመንፈስ ላይ፣ መንፈስም በሥጋ ላይ ነውና፤ ልታደርጉ የምትወዱትን እንዳታደርጉ እነዚህ እርስ በርሳቸው ይቃረናሉ” ይላል። በዚህ በወደቀው ዓለም ውስጥ ስንመላለስ፣ ምንም እንኳ በክርስቶስ ኢየሱስ በደሙ ቤዝወት ከኩነኔና ከዘላለም ሞት ድነን፣ “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ የታጠብን፣ የተቀደስን፣ የጸደቅን" (1ቆሮ. 6፥11) ብንኾንም፣ በውስጣችን ግን የእግዚአብሔር በኾነውና በኀጢአት መገኘት ምክንያት ታላቅ ጦርነት አለ። በአንድ ማንነት ውስጥ ያሉ፣ ርስ በርሳቸው ደግሞ የሚቀዋወሙ ባላንጣዎች! የሥጋ ምኞታችን በማናቸውም መንገድ ለእግዚአብሔር አይታዘዜና እንዳንገዛ ከልካይ ነው።
Monday, 20 April 2026
Sunday, 12 April 2026
“ተነሥቶአልና…፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ” (ማቴ. 28፥8)
በክርስትና ታሪክ ውስጥ “ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ” እንደሚለው ያለ አስደናቂና አጽናኝ ቃል ጨርሶ የለም። ማቴዎስ ወንጌሉን ሲጽፍልን፣ ትንሣኤውን በልዩትነት መንገድ ነው። ይኸውም ስቅየቱንና መከራውን እንደ ዘገበ ወዲያው የትንሣኤውን ነገር ይነግረናል። ትንሣኤውንም የሚያቀርበው ልክ ክርስቶስን የሕግ ፍጻሜ ነው ብሎ (ማቴ. 5፥17) እንደሚያቀርበው እንደዚያው፣ ትንሣኤውንም የምድር አገልግሎቱ ማብቂያና መክተቻ፤ ፍጻሜ አድርጐ በውበት ያቀርበዋል።
Friday, 10 April 2026
“እነሆ ሰውዬው” (ዮሐ. 19፥6)
ይህን ቃል
የተናገረው ጴንጤናዊው ጲላጦስ ነው። የተናገረውም ስለ ስቁዩ ሎሌ መሲሕ ኢየሱስ ነው። የተናገረበትም ምክንያት፣ ቊ. 1 ላይ
እንደምናነበው፣ ጲላጦስ ራሱ ኢየሱስን ገርፎታል፤ የያዙትም ሰዎች “ይዘብቱበትና ይደበድቡት ነበር፤” (ሉቃ. 22፥63) እንዲል፤
መግረፉንና “ለመግረፉ ድጋፍ ለማግኘት” የተናገረው ይመስላል፡፡ ክፍሉ በክርስቶስ ሕማማት ትረካ ውስጥ ወሳኝና ጌታችን በገዛ ወገኖቹ ፍጹም አለመቀበልን እንደ ገጠመው
እንመለከታለን። ከምንም በላይ ደግሞ ሰዎች ኢየሱስን አሳልፈው ሲሰጡ፣ ምን ያህል ለጥቅማቸውና ለክብራቸው፤ ለሥልጣናቸው እንደሚጨነቁና
አብ የተወደደ ልጁን በሚሰጠው ፍቅሩ ውስጥ ሰው ምን ያህል ኀጢአተኛ እንደ ኾነ በጥልቀት የምናይበት ነው።








