የሐሰት መምህራን ክርስትና ከመጀመሩ በፊትም የነበሩና ያሉ፣ በእኛም
ዘመን እንግዳ ኾነው የተከሰቱ ያይደለ ሲኾን፤ ትምህርታቸውም ከታየበትም ጊዜ ጀምሮ እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሐሰት ትምህርታቸውን
ሳይታገሱ ፊት ለፊት የተቃወሙ መኾናቸውን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ይነግረናል፡፡ ሐዋርያት በዘመናቸው ይሠራጭ የነበረውን የሐሰት ትምህርትና
አስተማሪ መምህራንን ትምህርታቸውንና ስማቸውን ጠቅሰው ተቃውመዋል፤ የሰማርያው ጠንቋዩ ሲሞን (ሐዋ.8፥9)፣ ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ[እስክንድሮስ
የተባለው ምናልባት የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ ሊኾን ይችላል (2ጢሞ.4፥14)] (1ጢሞ.1፥20)፣ ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ (2ጢሞ.2፥17)፣
ዴማስ(2ጢሞ.4፥10)፣ ዋናቸው ሊሆን የሚወድ ዲዮጥራጢስ (3ዮሐ.9) እና ሌሎችንም “ሐዋርያት ነን የሚሉቱን መርምረው ሐሰተኞች
ሆነው ባገኟቸው” ጊዜ እንደለዩዋቸው ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክርልናል፤ (ራእ.2፥2)፡፡
በኋለኛውም በቤተ ክርስቲያን አባቶች ዘመን፣ ቤተ ክርስቲያን የተነሡባትን
የኑፋቄ ትምህርቶች እንደጉባኤ ኒቂያ፣ ቁስጥንጥንያ፣ ኤፌሶንና ሌሎችንም ጉባኤያትን በመሥራት ከኢቦናውያን እስከ ግኖስቲካውያን፣
ከሲሞን መሠርይ እስከ አርዮስ፣ መቅዶንዮስ፣ አቡሊናርዮስ፣ አውጣኪ፣ ንስጥሮስ፣ ቫሲለደስ፣ መርቅያን … ድረስ ያሉትን መናፍቃንን
በየዘመኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መዝና ትቃወም፤ አልመለስ ያሉትንም አውግዛ ከመካከሏ ትለይ[ለሰይጣን አሳልፋ ትሰጥ (1ቆሮ.5፥5)]
እንደነበር ታሪክ ምስክራችን ነው፡፡
ስለዚህ እኛም በዘመናችን ያለምንም ከልካይ የአማኞችን ቅድስና ከሚያረክሰው፤
ከአዳኛቸው፣ ከጌታቸውና ከአምላካቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጽሞ የሚለያያቸውን[ሊለያያቸው ያለውን] ማናቸውንም የሐሰት ትምህርት እንቃወምና
“ልንቀበለው አይገባንም” ብለን እንሞግት፣ እንሔስ፣ በመጽሐፍ ቅዱስና በቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን አባቶች ትምህርት እናፈርሰው ዘንድ፣
ታላቅ ምስክርና ዋቢ አለን፡፡ ይህን የምናደርገው ከእውነት መተባበራችንንና ሐሰትንና ሐሰተኞችን ለመታገስ የማይቻለን መኾኑን ለማሳየትም
ጭምር ነው፡፡
በተለይም “የእምነት[ቃል] እንቅስቃሴ” የተባለው ኑፋቄ በመካከላችን አቆጥቁጧል፤
መጽሐፍ፣ “ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ
ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ፤” (ሐዋ.20፥29-30)፣ “ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ
መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤” (2ጴጥ.2፥1) እንዲል፣ ከመካከላችን መነሣታቸውና
ብዙ ተከታይ ቢያገኙ[ምናልባት ወደፊት] አንደነቅም፤ ቀድሞ የተነገረ የትንቢት ቃል አለና፡፡ ነገር ግን ያቆጠቆጠው ተስፋፍቶ “ብዙዎችን”
እንዳይወርስና ፍሬ አፍርቶ እንዳይጐመራ፣ ስለዚህ ፍልስፍናዊና ምልክት ናፋቂ ኑፋቄ አስፍተንና አበክረን ለመጻፍ ተነሣሣን፡፡ ምክንያቱም
አፍንጫችን ሥር በመምጣት ብዙ ወንድሞችና እህቶችን ስለነጠቀንና ራሳቸውን እስከማጥፋት በሚያደርስ የከፋ ኃጢአት እንዲወድቁ ስላደረገ
ነው፡፡ በእርግጥ እኒህን ወንድሞችና እህቶች እንዲመለሱ በብዙ ብንጥርም፣ ነገር ግን የእኛ መዘግየትና[ችላ ማለት ጭምር] ይመለሳሉ
የሚለው ተስፋችንን እንደመዘግየት[እንደተላላነት] በመመልከት በትምህርታቸው ገፍተው ወጥመዳቸውን በአማንያን ዙርያ ሲያረብቡ መታገሳችንን
“እንደታላቅ ዕድል ቆጥረውት” ተጠቅመውበታል፡፡ እናም ትምህርታቸው መጽሐፍ ቅዱስንና ጌታችን ክርስቶስን ፍጹም ያስክዳልና ያመኑት
በተላላነት እንዳይወድቁና እንዳይሳሳቱ፣ አገልጋዮችም በእረኝነታቸው እንዲተጉና በጐችን ከተኩላ የመጠበቅ ሥራቸውን አጽንተው እንዲገፉበት
ስለእምነት እንቅስቃሴ ትምህርት ክህደትነት ለመጻፍ ተገደድን፡፡ አዎን!
መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ
የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት
ነው፥ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው፤
(1ቆሮ.1፥22-24)
|
የእምነት
እንቅስቃሴ አመሠራረትና መሥራቾቹ
የእምነት እንቅስቃሴ እምነትን ጀምሮታል፤ መሠረተ እምነቱንም ጥሎታል፤
አስፋፍቶታልም ተብሎ የሚታመነው የኒውዮርኩ ተወላጅ፣ የሜቶዲስት ቤተ ክርስቲያን ዲያቆን የነበረው ኤሴክ ዊሊያም ኬንዮን[1]
(1879-1948 ዓ.ም) ሲኾን፣ የእምነት እንቅስቃሴውን ስያሜም “ተጽዕኖ አምጪ እምነት” ብሎ ሰይሞትም ነበር፡፡ ትምህርቱ እንዲፈጥን፣
በችኮላ ወደሌሎች ክፍላተ ዓለም እንዲደርስ አድርጐታል ተብሎ የሚታመነው
የእምነት እንቅስቃሴ ዋና ሰው ደግሞ፣ በኦክላሆማ የፔንታኮስታል “አገልጋይ” የነበረው ኬኔት ሔጌን(1917-2003 ዓ.ም) ነው፡፡[2]
ከዚህም ባሻገር ኬነት ኮፕላንድ፣ ሜሪ ቤከር ኤዲ፣ ኦራል ሮበርትስ፣ ጆይል ኦስቲን፣ ጆሴፍ ፕሪንስ፣ ቤን ሂን፣ ጂም ቤከር[3]
እና የሚባሉ ሌሎችም … ሰዎች በአጋርነት ትምህርቱን በትጋት አሠራጭተውታል፡፡
ከእምነት እንቅስቃሴ መሥራቾች አንዱ
ኬነት ኢ.ሔገን
የምዕራቡ ዓለም ብዙ የነገረ መለኰት ምሁራን፣ የእኒህን መናፍቃን ትምህርቶቻቸው
ሁሉ ከፍልስፍናና ከአጋንንት በቀጥታ የተቀዱ መኾናቸውን እጅግ ብዙ ጥናታዊ ጽሁፎችንና መጻሕፍት በመጻፍ አጋልጠዋቸዋል፡፡[4]
በእኛ አገርም በተለይ በወንጌላውያኑ አብያ ክርስቲያናት አማኞች ዘንድ፣ የዚህ ትምህርት አስተማሪዎች በግልጥም በስውርም ብቅ ብቅ
ያሉ ሲኾን፣ በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አከባቢ ደግሞ በጋሻው ደሳለኝና ከእርሱ ጋር በአንድነት የሚሠሩ አንዳንዶች ይህንን
ትምህርት ሲያንጸባርቁ ተስተውለዋል፡፡
ቃሉ፣ “ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፤” እንዲል
ቃሉ(ዕብ.13፥9)፣ በእግዚአብሔር ጸጋ በመታመን መቆም ይገባናል እንጂ፣ እንግዳ በኾነ፣ ከእግዚአብሔር በሚለይ፣ በክርስቶስ ሞትና
ትንሣኤ ላይ ከሚሳለቅ ምድራዊ ትምህርት ከመታለል ልንጠበቅ፤ እንዳንወሰድም በብዙ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ
ክርስቶስ ኢየሱስን በልባችን እንድንሾመው፤ እንድናከብረው፤ እንድናመልከውም ይርዳን፤ አሜን፡፡
ይቀጥላል …
[1]
“የእምነት እንቅስቃሴ”[ቁሳዊና
ምድራዊ ባዕለጠግነትም አዎንታዊ የኾነውን ቃል በማወጅ ወይም በመናገር ይገኛል ስለሚባል በሌላ ስሙ ትምህርቱ የብልጥግና ወንጌል]
በመባል የሚታወቀውን መናፍቃዊ ትምህርት ጠንሳሽ ናቸው፡፡ ኬኒየን በ1892 ዓ.ም ላይ ዲበ አካላዊ መናፍቃን
(Metaphysical Cults) በመባል የሚታወቁት መናፍቃዊ እንቅስቃሴዎች ከፈለቁበትና ቦስተን ከተማ ከሚገኘው ኤመርሰን ኮሌጅ
በመግባት፣ “አዲሱ አስተሳሰብ” (New Thought) በመባል የሚታወቀውን ትምህርት ተማረ፡፡ ይህ ትምህርትም መሠረት ያደረገው፣
“በቁሳዊ ነገሮች ላይ ለሚከሠቱት ነገሮች ሁሉ ምንጫቸው፣ በመንፈሳዊው
ዓለም ውስጥ እውን የሆነው ነገር ሲሆን … አዎንታዊ ቃል በመናገር እንደጤንነትና ሀብት ያሉትን ቍሳዊ ጥቅሞች እውን ማድረግ(ማግኘት)
ይቻላል፡፡”
|
በሚል አስተምህሮ ላይ ነው፡፡
(Charles E. Hummel, Fire in the Fire Place (Ivp, 2nd ed,1993), 5. እናም አስተምኅሮው
ሲተነተን፣ “መንፈሳዊው ዓለም ማለት በውስጣችን ያለው ሲኾን፣ በምንናገረው ንግግራችን ወደዚህ ዓለም ልናመጣውና ልንተገብረው፤
ልናዝዘውም እንችላለን፤ ውስጣችንን ማድመጥና ከዚያ የምንሰማውን ነገር በመከተል ማዘዝ የምንፈልገው ማንኛውም ነገር ኹሉ ሊመጣ ይችላል፤”
የሚል ጽኑ እምነት አለው፡፡
የኬንየንን ፍልስፍናዊ ትምህርት በመከተል የ“New thought” ፍልስፍናን
ይበልጥ ያዘጋጀውና በሚገባ ያሰናዳው ፊንሐስ ቁ[ኩ]ምቢ ሲኾን፣ የክርስቲያን ሳይንስ አስተማሪዋ ሜሪ ቤከር ኤዲ(Merry
Beker Eddy) ደግሞ፣ ይህንኑ ፍልስፍናዊ ትምህርት የምትጋራና የምትደግፍ ናት፡፡ ይህች ሴት በግልጥም፣ “የኢየሱስ ሞትና ስቃይ
ከደኅንነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፣ ምክንያቱም አይሁድ ትምህርቱን እንዲያቆም በነገሩት ጊዜ ማቆም ነበረበት፣ ራሱንም ከእግዚአብሔር
ጋር እንዲያስተካክል ነግረውት … ትዕዛዛቸውን ስላልተቀበለና እንቢ በማለቱ ምክንያት አግባባዊ ቅጣትን ተቀበለ እንጂ እኛን በተመለከተ
ምንም የከፈለው ዋጋ የለም፤ ስለዚህም ከእኛ መዳን ጋር በተያያዘ አልሞተም፤ ከሙታን መካከልም አልተነሣም” በማለት ታስተምራለች፡፡
[2]
ኬኔት ሔጌን(1917-2003 ዓ.ም)፣ ጌታ ኢየሱስ ከስምንት ጊዜ በላይ እንደተገለጠለትና
ከዚያን ጊዜ ጀምሮም፣ “ልዩ መገለጥና የማስተማር ጸጋ እንደተቀበለ”፣ ነገር ግን ትምህርቱም ኾነ ጽሑፎቹ ከቀደምት የእምነቱ ጠንሳሽ
ከኾኑት ከኬንየን ጽሑፎች የተገለበጡና ምንጭ ሳይጠቅሱ የተሠረቁ መኾናቸውን፣ ብዙ ጸሐፍት የሁለቱን ጽሑፎች ጎን ለጎን በማስቀመጥ
በሚገባ ይተቻሉ፡፡ ሔገን የነገረ መለኮት ትምህርት ቤትን ገብቶ ያልተማረ ሲኾን፣ [ … ምናልባትም ድፍረታቸውና ገብተን ተምረናል
ለሚለው ንግግራቸው፣ “መረዳታቸውን በመደበኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ስላልጐለበተ አልተፈተሸም፡፡ የአገልግሎት ዝግጅታቸው
ዝቅተኛ ኾኖ ሳለ፣ ለመጫወት የሚፈልጉት ሚና ትልቅ ነው፤ ራሳቸውን የተሃድሶ መሪዎች ሲሉ ይጠራሉ፡፡
አብዛኛዎቹ መምህራን
መደበኛ ትምህርት አለመቅሰማቸውን ስትሰሙ፣ ከመካከላቸው ራሳቸውን ዶ/ር ብለው የሚጠሩ መኖራቸው ግራ ያጋባችሁ ይኾናል፡፡ ነገሩ
ሌላ ነው፡፡ መምህራኑ የመዓረግ ስያሜ የተጐናጸፉት የእነርሱ አመለካከት ካላቸው ትምህርት ቤቶች ዶክትሬት ስላገኙ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ
የትምህርት ማስረጃዎች፣ የትምህርት ማስረጃን ከሚቸበችቡ ተቋማት የተገዙ ናቸው፡፡ ፈረንጆቹ ተቋማቱን የዲፕሎማ ወፍጮዎች ይሉዋቸዋል፤
የአገሩን የእውቅና መስፈርትም አያሟሉም፡፡ በግዢ የተገኙ ማስረጃዎች በቅጡ ማገናዘብ የሚያስችል ውስጣዊ አቅም አይጐናጽፉም፡፡ የከበረ
ስማቸውን የማይመጥኝ አላዋቂነት ይታይባቸዋል፡፡ (Cecil M. Robeck, Montanism and Present Day
“Prophets”, Pneuma 32(2010); [ተካልኝ ነጋ፤ የጸሎት
- የንግድ ቤት?!፤ ዓ.ም እና የታተመበት ሥፍራ ያልተጠቀሰ፤ ርኆቦት አታሚዎች የታተመ፤ ገጽ.53-54)]
በእርግጥ ለዚህ ማሳያነት
እንደኃይሉ ዮሐንስ፣ ዘላለም ጌታቸው፣ በጋሻው ደሳለኝንና ሌሎችንም መጥቀስ በቂ ማሳያ ነው፡፡ የዚህ መሸፈኛቸው ደግሞ “ጌታ ተገልጦ አስተማረኝ” የሚልና በመገለጥ ያገኙት
የማስተማር ክህሎታቸውም መጽሐፍ ቅዱስን በልዩ ኹኔታ እንደሚገልጥና እንደሚያስረዳ ደጋግመው በመናገር ይታወቃሉ፡፡ ነገር ግን ተገለጠልኝ
የሚሉት እግዚአብሔር፣ ለምን ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጋር እንደማይስማማ በትክክል ለመመረመረ፤ ወደላይና ወደታች አበጥሮ በልበ ሰፊነት
ቅዱስ ቃሉን በማስተዋል ላጠና፣ ሐሰተኝነታቸው ፍንትው ብሎ የሚታይ ነው፡፡
[4]
በተለይም D.R.
McConnell የተባሉት አሜሪካዊ ዓቃቤ እምነት፣ “A Different Gospel፡ A Bold and Revealing Look at the Biblical
and Historical Basis of the Word of Faith Movement(Hendrickson publishers;
1998; USA)” በተባለ መጽሐፋቸው፣ የእምነቱ መምህራንን “ሌብነት”፣ በዋናነትም ኬኔት ሔገን የጻፏቸው ጽሑፎች የራሳቸው እንዳልኾኑና
ቃል በቃል ከእምነቱ ዋና መምሀር ከነበሩት ከኬንየን እንዴት እንደገለበጡትና የራሳቸው አድርገው እንዳቀረቡት በሠፊው አስፍረውት
እናገኛቸዋለን፡፡
አንተ ልጅ ግን በዚህ ትምህርት በጣም የተቆጣህ ይመስላል፡፡መቆጣትህ መልካምነው፡፡ያስመሰግናል፡፡ አደራህን አጥምደው እንዳይጥሉህ ተጠንቀቅ፡፡የምናውቃቸው ብዙ አባቶችና ወንድሞች ይን ትምህርት አስመልክተው ዝም ማለታቸው ይደንቃል፡፡ እግዚአብሔር ባንተ በኩል ይህን ትምህርት እየተበቀለው መሆኑን ሳስብ ጌታን እባርከዋለሁ፡፡አደራ በምንም እንዳያታልሉህ በርታ፡፡ ጌታ በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ፡፡ እውነትን ከሚወዱ ወንድሞች መካከል ጻፍኩልህ፡፡
ReplyDeleteወንድሜ እንዲህ ያሉ መንፈሳዊ አገልግሎትን ከሚደግፉ መካከል አንዱ ነኝ፡፡ሌሎችም ከኔ ጋር አሉ፡፡አድራሻህን ማግኘት ብንችል እጅግ ደስ ይለናል፡፡በግሌ ደቡብ አፍሪካ በነበርኩበት ጊዜ ይህ ትምህርት ብዙዎችን አጥቅቶ ነበር፡፡ አሁን ባለሁባትም ከተማ ብዙዎችን ሲነካካ እያየሁ ነው፡፡ እባክህን በዚህ ዙርያ የተሰሩ ስራወችን በግል ባገኝ ደስ ይለኛልና ባወራህ ደስ ይለኛል፡፡ ተባረክ ሳልልህ ማለፍ ግን አልፈልግም፡፡ በርታ ብዙ ነገር አስተምረኸናል፡፡
ReplyDeleteygeermal Lib yistachew
ReplyDeleteእባክህ የተወደድክ ወንድሜ በጋሻው ከኦርቶዶክስ አትበል እሱ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ አይደለም። እመቤታችን ማርያም የአምላክ እናት አትባልም,ክርስቶስ ከድንግል አልተዋሀደም ብለው ሲሰብኩ በእውነት አልሰማህም። የብልጽግና ወንጌል ትንሹ ነው ለማያነብ እና ለማያስትውል ትውልድ። ስንቱን ሰማን,አየንም አመንዝራ ትውልድ ምልክትን የሚሹ በቀትታ ስርጭት ስናይ። እየሱስ በመለኮቱ አልተገለጸም በስጋ ነው እያሉ። ያውም ወንጌል በራልን እውነት ተገለጠልን ከሚሉ ,እየሱስ ጌታ ነው በሉና እመኑ ትድናላቹ,ሌላው የምትሰሩት ብስጋቹ ነው ሲሉን። እሱን ባላወቁት ቁጥር ለማይገባ አይምሮ ተላልፈው ተሰጡ እንዳንል ወንጌል የገባው ከኛ በላይ አሉ። ወገኔን የልጅነት ጸጋ ካገኘበት ቤተመቅደስ እና ስብእና አውጥተውት በባዶ ስፍራ አንከራተቱት። ያላረፋ ህዝብ። ምን እንላለን ማራናታ ብለን ዘውትር እንጮሀለን ።አው ጌታ ሆይ ቶሎ ና። እረኛው ለበጉ የማይሬ ሆነዋል.ነፍሳችን አንተን ናፍቃለች ጌታ ሆይ አንተ ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ፍጹም ስጋ ፍጹም መለኮት በተዋህዶ እንደከበርክ ,ፍጹም ሰው እና አምላክ እንደሆንክ እናምናለን።ጌታ ሆይ በዚ እውነት ላይ ስላሳረፍከኝ አመሰግናለው። በእኛ መረዳት ለሳቱትም አንተ ወደ ልቦናቸው መልሳቸው። አሜን!! ለወንድሜም ዲ/አቤነዘር የድንግል ምልጃ አይለይህ አምላክ ጸጋውን ያብዛልክ 30,100 ከዛ በላይ የምታፈራ ሁን።
ReplyDeleteehte begashaw ortodox neber gn ahun tesasate enji. Kedmo yeserawn mekad agbab aydelm.esu tru bayseram egna gn tru linhon yigebal.geta eyesu yirdaw.
Deleteአይ ወንይድሜ እሱን አንተ አልክ።በጋሻው እኮ ቤተክርስቲያን ናት የውሽት ትምህርት አስተምር ብላ የላከቸኝ እንጅ ከየት መንፋስ ቅዱስ አገኝውት አለ። ማስመሰልና መሆን እንደኔ አረዳድ ይለይይል።አየህ እኔና አንተ እንካን ስለሱ እንከራከራለን የቆምንበትን እውነትን አንመረምርም።እየሱስ ጌታ ነው ያለ ሁለ እረኛ ይመስለንና ስንሄድና ስንከተል የምንኖረው። በእሱ ውድቀት ልቤ ቢያዝንም የድንግል ምልድጃ ባለበት እንዲረዳው የዘውትር ጸሎቴ ነው። ለኛም አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ አምላክ እንደሆነ እና ከድንግል ማርያም በተዋህደው ስጋ ፍጹም ሰው እና አምላክ እንደሆነ ካመንና በዚ እውነት ላይ ከቆምን,የትኛውም እውነት የሚመስል የሀሰት ትምህርት እና መምህራንን የምናውቅበት እውቀት ከእግዚያብሔር እናገኛለን።
DeleteBegashawn ahun balebet huneta aldegfewm gn litazenlet yigebal.አቤኔዘርም ያለው ይህኑ መሰለኝ፡፡ትምርቱን አንደግፍም ግን ልናዝንለት ይገባል ነው ያለው፡፡እና ታድያ እንዳልሽው እሱን ርዕስ መድረጋችን ስህተት ነው፡፡ ኑፋቄ ግን ኑፋቄ ነው፡፡ እና በዚህ መስማማት ጥሩ ነው፡፡
Deleteወንድሜ ሆይ በርታ የጌታ ፀጋ እና አብርሆት ከአንተና ለእግዚአብሄር ህዝብ ከሚራሩ ጋር ይሁን
ReplyDeleteWendmachn tru neger new yaschebetken.melktu melkam new.slezih faith movement betam tsere wengel endehone ene bebekule teredichalw
ReplyDeleteEgziabher bemelkam asnesitohal berta
ReplyDeleteበጋሻው ደሳለኝ ቀስ ቀስ ክርስቶስን የሚያስክድ ትምህርት የሚያሰርፅ ከሆነ ማንም የሚሰማው የለም... እናመሰግናለን ስለጥቆማው!
ReplyDelete