Showing posts with label ዘጠነኛው የዓቢይ ጾም ሳምንት - ትንሣኤ. Show all posts
Showing posts with label ዘጠነኛው የዓቢይ ጾም ሳምንት - ትንሣኤ. Show all posts

Sunday, 26 April 2020

በሕማሙና በትንሣኤው ዙርያ የነበሩ ምስክሮች (ክፍል አምስት)


3. ትንሣኤውን በመመልከት ኹሉን ትቀድማለች፦ ባለፉት ጊዜያት ጌታ መንፈስ ቅዱስ እንዳስተማረን፣ በመግደሎሟ ሴት ኹለት ነጥቦችን አንስተን፤ ሰባት አጋንንት ያወጣላትና እንዲሁም የጌታ ኢየሱስን ሕይወትና ትምህርት ተመልክታ፣ ፍጹም የተከተለችው መኾኑን አንስተናል። ከዚሁ ቀጥለን የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ምስክሮች ስለ ኾነችው ሴት በጥቂቱ እንመለከታለን።


Wednesday, 22 April 2020

ተነሥቶአል!

Please read in PDF
ይህ ታላቅ ምስክር የተሰጠው ለታላቁ መሲህ ለክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው፤ ሞት ብርቱ ሥጋ ለባሽን ኹሉ አሸንፎ ገዝቶአል፤ በጦር ሜዳ ጀግኖች የነበሩትን አርበድብዶ፣ “በውኑ ሞት እንደዚህ መራራ ነውን?” (1ሳሙ. 15፥32) በማስባል፣ በፊቱ አንበርክኮአል። ሞት ያልገዛው ብርቱ፣ ያልሻረው ኃያል፣ ያልጠቀለለው ጎበዝ፣ ያልዋጠው አለቃ፣ ያልሰበረው ጠንካራ … በምድር ላይ ከቶ አልነበረም። ሞት ወደቀውን ዓለም ተከትሎ፣ በሰው ልጆች ኹሉ ነግሦ ኖሮአል፤ “በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል” ወደ ሥጋ ለባሹ ዓለም ሰተት ብሎ ገባ፤ (ሮሜ 5፥17) እንዲል።


Thursday, 30 May 2019

በሕማሙና በትንሣኤው ዙርያ የነበሩ ምስክሮች (ክፍል አራት)

  2.  ክርስቶስ ኢየሱስን ሕይወት አይታለች፦ ጌታችን ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ የእርሱን ሕይወት ከእርሱ ጋር ውለው፤ አድረው እንዲያዩ ደግሞም አብረውት እንዲኖሩ ፈቅዶአል፤ (ዮሐ. 1፥40)። ከዚህም ባሻገር ጌታችን ኢየሱስ ራሱ ሌሊቱን ሙሉ ሲጸልይ ካደረ በኋላ ደቀ መዛሙርቱን ሲመርጥ “ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው፥” ወዶ እንደ ኾነ ቅዱሳት መጻሕፍት በግልጥ ይመሰክራሉ፤ (ማር. 3፥13-14)።
   ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኀጥአንን ተቀባይ መኾኑን ቅዱሳት መጻሕፍት ደጋግመው ገልጠዋል፤ ግብዞችንና አስመሳዮችን፣ የሕይወት ቲያትረኞችን እጅግ ይጠየፍ የነበረው ጌታ ኀጥአንን ግን በአደባባይ ሳይታዘባቸው ተቀብሏል፤ አብሮአቸው ተመግቦአል፤ ሳይጠየፋቸው በአንድነት ከእነርሱ ጋር አሳልፎአል። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከኀጢአተኞች ጋር ማሳለፉ ለብዙዎች አይሁድ የማይዋጥላቸው ተግባር ነበር፤ ምክንያቱም በግልጥ እንደ ሕጉ መለየትና መወገዝ እንጂ ተቀባይነትን ማግኘት አለባቸው ብለው ያምኑ አልነበረምና።

Monday, 20 May 2019

በሕማሙና በትንሣኤው ዙርያ የነበሩ ምስክሮች (ክፍል ሦስት)

 Please read in PDF

3. ማርያም መግደላዊት፦ የክርስቶስ ከሙታን ትንሣኤ መካከል በእውነት መነሣት የክርስትና ዋና ማዕከል ነው፤ በመስቀል ላይ ቤዛ ኾኖ መሰቀሉ በእውነት ለኃጢአተኞች መኾኑና የቤዛነት ክፍያውም መረጋገጡን የሚያበስረው ከሙታን መካከል መነሣቱ ነው፤ “እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ” ክርስቶስ ከሙታን መካከል ተነሥቶአል፤ (ሮሜ 6፥4፤ 7፥6፤ ሐዋ. 2፥24፤ 2ቆሮ. 5፥17፤ ኤፌ. 4፥22፤ ቈላ. 3፥10)። ጌታ ኢየሱስ ከሙታን መካከል ባይነሣልን፣ “ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት፤ እስከ አሁን ድረስ በኃጢአታችሁ አላችሁ” (1ቆሮ. 15፥17) እንደ ተባለ፣ ከኃጢአታችን ሳንላቀቅ እስከ አኹን እንደ ተጣባን፣ የሙጥኝ ብለን እየኖርን አለን ማለት ነው። ክብር ይኹንለትና እርሱ ግን የኀጢአት ዋጋችንን በሥጋው መከራ በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶ ከፍሎልን፣ ዋጋችንም የጸደቀና የተረጋገጠ መኾኑን በትንሣኤው አጽንቶልናል።