የታሪክ ጸሐፊው ጆሴፈስ፣ በዘመኑ ይፈጸም የነበረውን የስቅላት ሞትን “እጅግ
አሳዛኝ ሞት” በማለት ገልጦታል፤[1] ስቅላት አስከፊና እጅግ የሚሰቀጥጥ የመሞቻ መንገድ
ነበርና። ስቅላትን ለዓለም ያስተዋወቁት ፋርሳውያን ቢኾኑም፣[2]
አይሁድ፣ ሮማውያንና ሌሎችም ግን ወደውና ፈቅደው ስቅላትን እንደ ተቀበሉ የታሪክ መዛግብት ይመሰክራሉ፤[3] ይህም የመቀጣጫ መንገድ እጅግ ከባድና አስከፊ
ከመኾኑ የተነሣ፣ በአገር ክህደት የተያዙ ወንጀለኞች፣ ወንበዴዎች፣ ቄሣርን የሚቃወሙ ፖለቲከኞች ወይም እስረኞች ኹሉ የሚቀጡበት
ቅጣት ነው። ቅጣቱ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ወይም የሚቀጣው ሰው እስኪሞት ድረስ በመስቀሉ ላይ መቈየቱ አስከፊነቱን ከማሳየቱ ባሻገር፣
በሕዝብ ፊት የሚፈጸምና ከፍ ያለ ውርደትንም ጭምር በውስጡ የያዘ ነው።[4]
Saturday, 26 September 2026
የውርደቱ መስቀል - የዘላለም ክብራችን
Monday, 21 September 2026
የዐዲስ ዘመን መሠረት!
Source - https://www.mahibereahaw.org.et/
በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ፥ ኀጢአት የተባለ ዕድፈት ሲገባ፥ በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረውን ክቡሩን ሰው እርጅናና ጉስቁልና ተጠናወተው። የሥጋ እርጅና ብቻ ያይደለ፥ የነፍስ ከጽድቅ ዕውቀት መጉደልና ባለማስተዋል የፊት መጨማደድ ተያዘች። ከዚህ የተነሣ፥ በሰው ልጅ የታሪክ አንጓ ላይ ውድቀት፤ መሸነፍ፤ መታረዝ፤ መራቆት፤ መጃጀት ... የየዕለት ዜና፤ የዘወትር ክሥተት ኾነ።
Saturday, 12 September 2026
“አይሰማ” ወይም “ስማቸው እንኳ አይነሳ”!
ምንጭ - https://www.mahibereahaw.org.et/
በቅዱሳን አማኞች መካከል ጨርሶ
እንዳይሰማ ወይም ስሙ እንኳ እንዳይነሳ የሚገባ ነገር አለ፤ ኀጢአት፡፡ በዚያው ትይዩ ደግሞ፣ “ርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ
ተናዘዙ።” እንዲል፥
ቅዱሳን አማኞች ርስ በርስ ኀጢአታቸውን መናዘዝ የሚገባቸው ጊዜ አለ። ኀጢአታችንን በግልጥ ለእግዚአብሔር የምንናዘውን ያህል፥ ደግሞም፥ ለበደልናቸውም ሰዎች በደልና
ስህተታችንን በግልጥ መናዘዝ ይገባናል።
Tuesday, 25 August 2026
“በአርባምንጭ ተሐድሶ ሙሉ ለሙሉ መቀጠል አይችልም” (“ዲያቆን” አበባው ምስክር)
የተሐድሶ ባለቤት ራሱ እግዚአብሔር እንጂ ሰውም ኾነ አንዳች ተቋም አይደለም። እግዚአብሔር አምላክ
ይህን የሚያደርገው ደግሞ በምሕረቱ ብዛት ነው። በባቢሎን ምርኰ ሳሉ እግዚአብሔር በተሐድሶ እንዴት ያለ ጕብኝት ለእስራኤል እንዳደረገላቸው፣
ነቢይና ካህን የነበረው ዕዝራ ሲናገር፣ “ … አምላካችን ግን በባርነታችን አልተወንም የሕይወት
መታደስን ይሰጠን ዘንድ፥ የአምላካችንንም ቤት እንሠራ ዘንድ፥ የተፈታውንም እንጠግን ዘንድ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም ቅጥር ይደረግልን
ዘንድ …” (ዕዝ. 9፥9) በማለት፣ የሕይወትን መታደስ ወይም የሕይወት ተሐድሶ የሚሰጠው ራሱ እዚአብሔር ብቻ እንደ ኾነ ገልጦአል።
Wednesday, 5 August 2026
ፍልሰታን ለጌታ እንዋጅ!
ቅድስት
ድንግል ማርያም፣ ጌታችን ኢየሱስን በመውለዷ ቅድስትና ብጽዕት ናት። የጌታ መልአክ መልአኩ ገብርኤል መጥቶ እግዚአብሔር ሊሠራ
የወደደውን ጅማሮ በርሷ መሥራት እንደሚጀምር ሲያበስራትም በመረዳት መታዘዝዋ ስለተጻፈልን፣ ለአዲስ ኪዳን አማኞችም ለጌታ ቃል
ጥንቅቅ ባለ መንገድ መታዘዝና በትክክል መረዳትም እዳለብን ከሕይወትዋ እንማራለን። ይህ ብቻ ሳይኾን፣ በዕብ. 11 ላይ እንደ
ተጠቀሱት የእምነት አርበኞች፣ የእግዚአብሔር ቃል ዕውቀትዋ በጸሎትዋ፤ ልምምድና ሥራዋ ደግሞ በተጋድሎዋ ፍንትው ብሎ
ይታያል።
Friday, 24 July 2026
“ጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል… አለች።”
ጽዮን በባቢሎን ምርኰ በተያዘችና ለሰባ ዓመታት ያህል በግዞት በዘገየች ጊዜ የተረሳችና የተተወች መሰላት፤ በተለይም
የመቅደሱ መፍረስና ከቅድስቲቱ ምድር ሙሉ ለሙሉ መነቀላቸው ተስፋቸውን ይበልጥ አጨለመው። እግዚአብሔር ግን ሕዝቡ ተስፋ እንዲቈርጥ
አይፈልግም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ታማኝ፤ ጽኑ ፍቅር፤ የማያቋርጥ ኪዳናዊ ቊርኝት ያለው፤ ጨርሶ ሊዘነጋ የማይችል
ልብ አለውና። ይህን እውነት እግዚአብሔር በበደልና በኀጢአት ለወደቀችው ለጽዮን፣ በነቢዩ አንደበት በግልጥ ይናገራል፤ እንዲህ
በማለት፣
“ጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ጌታም ረስቶኛል አለች። በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ
ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም። እነሆ፥ እኔ በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለሁ፥
ቅጥሮችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ።” (ኢሳ. 49፥14-15)
Friday, 17 July 2026
ለባህለ ትምህርት አልባ “ተሐድሶዎች”
ወንጌል የማይለወጥና ዘላለማዊ መልእክት ቢኖረውም፣ የራሱ ባህል ግን የለውም፤
ወንጌል ለየትኛውም ሕዝብ፤ ለኹሉም ነገዶች፤ በኹሉም ቋንቋዎችና ባህሎች መሰበክና መነገር ያለበት የእግዚአብሔር መንግሥት ታላቅ
ምሥራች ነው። ለዚህ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ዋና ምሳሌአችን ነው። ጌታችን ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለገሊላና ለይሁዳ መንደሮች
ያቀረበበት መንገድ፣ እጅግ ጠቃሚ የኾኑ የባህል ተዛማጅ መመሪያዎችንና ልምምዶችን ያስተምረናል።
Monday, 13 July 2026
የዋልድባ የግድያና የዘረኝነቱ ጦስ!
“... በኹለት ዐመቱ ጌታችን በእናቱ እቅፍ መጥቶ ባረካት[ዋልድባን]። ዋልድባ በአራቱ ወንዞች ትከበብ ብሎ፣ የሰው
ብቻ ሳይኾን የእንሰሳ ሴት አይግባባት ብሎ ጌታችን ኢየሱስ የውግዘት ቃል አሳልፎባታል። ሴቶች እንዳይገቡ በግዝት ቃል ተነግሮባታል።
... ስውር ቅዱሳን ክንድ ከስንዝር ከፍ ብለው የቀደሱበት ስፍራ ነው።... ዳልሻ ዋልድባ ቤተ ደናግል የሚባል የሴቶች ገዳም ጨርሶ የለም። ... ገዳሙ ጨርሶ የእርሻ ስፍራ እንዳይኾን እንኳ ተከልክሎአል።...
በዋልድባ ጳጳስ እንኳ ቢመጣ 40 ቀን ቋርፍ ሳይጨብጥ በዋልድባ ቀጥታ መቁረብ አይቻልም።…” የሚሉ አያሌ “ተረቶች” በገዳሙ “አባቶች”
ሲነገር መደመጡ እንግዳ ነገር አይደለም።
Thursday, 18 June 2026
ተሐድሶ የቅሬታዎች አገልግሎት ነው!
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የ“ተሐድሶ አገልጋዮች” ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል፤ ዕዝራ፣ ነህምያ፣ ዘሩባቤልና ኢያሱ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። ሕዝቡና እነርሱ በምርኰ ሳሉ፣ የእስራኤልን ጥልቅ ውድቀትና መንፈሳዊ ቅዝቃዜ በማየት፣ እስራኤል ዘሥጋ ትነቃቃና ታበራ፤ ትጌጥና ትፈካ ዘንድ የነቢያቱን የተስፋ ቃል በማወጅ፤ እንደገና በማስታወስና አጽናንቶ በማበረታታት ይታወቃሉ።
Sunday, 7 June 2026
ወንድምነት ረክሶ አገልግሎት ሲመለክ!
በዘመናዊው ዓለም ኢየሱስ በኪደተ እግሩ ከሰማርያ እስከ ኢያሪኮ የሚፈልጋቸው ሳምራዊቷ ሴትና የጤሜዎስ ልጅ በርጠሚዎስ፣
ወይም በቅፍርናሆም ያገኛት ደሟ ቀጥ ያለላት ሴት፣ ለዚህ ዘመን አገልጋዮች ጥሩ የስብከት ርዕስ እንጂ በወንድምነት ወይም በእህትነት
የሚፈለጉ አይመሰለኝም። በቀላል ንግግር ሰውነት በዚህ ዘመን ከአገልግሎት አይበልጥም የተባለ ይመስላል።
Friday, 5 June 2026
ጳውሎስ የሰማው የሞት ድምጽ! (2ቆሮ. 1፥9-11)
ቅዱስ ጳውሎስ ኹለተኛውን ቆሮንቶስ እየጻፈ ያለው፣ በአንደኛ መልእክቱ ላይ በታላቅ ተግሳጽ የገሰጻቸውንና ንስሐም
በመግባት የንስሐ ፍሬ ያሳዩትን ቅዱሳን ወገኖቹን ለማጽናናትና ለማበረታታት ነው።
አንደኛውን መልእክት ሲዘጋ፣ የወንጌል ሥራ በር እንደ ተከፈተለትና ነገር ግን የዚያኑ ያህል ደግሞ እጅግ ተቃዋሚዎች እንደ ተነሱም ተናግሮአል (1ቆሮ. 16፥8-9)፤ ምናልባት ተቃዋሚዎቹ ከባድ ስደት አልያም ከፍ ያለ እንግልት አድርሰው ሊኾን ይችላል።
Monday, 25 May 2026
በሥጋው ያረገ ጌታ!
ክርስቶስ ኢየሱስ ከቅድስት ድንግል በነሣው ሥጋና ከሙታን
መካከል ሲነሣ በለበሰው ፍጹም ሰውነቱ ወደ ሰማያት አርጓል። ምክንያቱም የመጣበት ዋነኛ ዓላማ፣ “የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን ነውና”
(ሉቃ. 19፥10)። ደግሞም ሰውን ለማዳን ክርስቶስ እንከን አልባ ሰው መኾን ያስፈልገው ነበር። ከዚህም የተነሣ ሊያድነን በፍጹም
ሰውነቱ የተሰቀለው ያው መሲሕ፣ በሰማያት መግቢያ በር ይኾነን ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ።
Tuesday, 19 May 2026
Monday, 18 May 2026
Thursday, 14 May 2026
“በወንጌል ሕይወታችን ኾነ” ከሚለው ጉባኤ የተወሰዱ ቊልፍ አባባሎች፣
-
“… አኹን ያለንበት ጊዜ ስብከተ
ወንጌል በዋና ዓላማነት ያልያዘበት፣ ሊቃውንትን በማፍራት ብቻ ቤተ ክርስቲያን የተጠመደችበት ጊዜ ቢኖር አኹን ያለንበት ጊዜ ነው።
…”
- “… ወንጌል እንደ ቅዱስ ጳውሎስ መሥዋዕታዊ ሕይወትን ዘወትር ይፈልጋል። …”






.jpg)



