ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንና የ“ዲያቆን” ዳንኤል ክብረት የክፋት ሸፍጥ (ክፍል ፩)
መግቢያ
ለዚህ ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የኾነኝ “ቀሲስ” ዳንኤል ክብረት የተባለ ሰው፣
በebs tv በአርአያ ሰብ(Who is Who) ፕሮግራም ላይ፣ በቀን 19/9/2010 ማታ 2፡00 ሰዓት ገደማ ላይ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንን
በተመለከተ በሰጠው ቃለ ምልልስ፣ ፍጹም ሸፍጥና ክፋት የተሞላበትንና ከታሪክ እውነታ ያፈነገጠ ሃሳብን በማቅረቡ፣ እውነታውን ከቤተ
ክርስቲያኒቱ መጻሕፍትና ከአባቶቿ አንደበት ማሳወቅ አስፈላጊ ኾኖ በመገኘቱና ነው።
ስለዚህም ጽሑፉ ከደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ታሪካዊ ዳራ ይልቅ እጅግ በአመዛኙ
በእነርሱ ላይ የተፈጸመውና ቤተ ክርስቲያን በመጻሕፍቶቿ የያዘቻቸው እውነት ከቅዱሳት መጻሕፍት[1][ከመጽሐፍ
ቅዱስ] አንጻር እንዴት ይዳኛል? ዳንኤል ክብረትስ ምን የተለየ ሃሳብን በደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ዙርያ ይዞ ብቅ አለ? ይዞ ብቅ
የማለቱ እሳቤስ ምን መዘዝ አለው? ቅዱሳት መጻሐፍትስ እንዴት ይዳኙታል? ዳንኤልና ቅዱሳት መጻሕፍት ምን ያህል ጥብቅ ዝምድና አላቸው?
ዳንኤል በማናቸው ምክንያትስ ቢኾን የሰው በአሰቃቂ ኹኔታ መገደል የሚገደው ነውን? … የሚሉና ሌሎች ተያያዥ ኹኔታዎችን በአጭሩ
ለመዳሰስ እንሞክራለን።
ከታሪካዊ ዳራ ይልቅ መንፈሳዊ ነገሩ ላይ የማመዘኔ ምክንያትም፣ (1) ታሪካዊ
ዳራው በተለያዩ ምሑራንና [ለምሳሌ፦ ፕሮፌሰር ታምራት ታደሰ፣ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌና ሌሎችም)፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች ለምሳሌ፦
በካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔር፣ በብሩክ ገብረ ሊባኖስና በግርማ ኤልያስ እንዲሁም በተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች] በመዳሰሱና በመሠራቱ
ምክንያት ነው ማለፉን መርጫለኹ። በታሪካዊ ዳራው ላይ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ኾነች ምሑራን ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን
ላይ የተፈጸመው ተግባር በዓላውያንና በአረመኔዎቹ የሮማ ነገሥታት ዘመን ከተፈጸመው ኢ ክርስቲያናዊና ሥነ ምግባራዊ ጭፍጨፋና መከራ
በማይተናነስ መልኩ ስለመፈጸሙ ሳያስተባብሉ ይናገራሉ፤ (2) ነገር ግን ድርጊቱን ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር የፈተሹ ምሑራንም ኾኑ
የቤተ ክርስቲያን አባቶች [በተወሰነ ረገድ ካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔርና ብሩክ ገብረ ሊባኖስ እጅግ በጥቂቱ ካልኾኑ በቀር] አልገጠሙኝም።
(3) መሠረታዊውና በትክክልም መታየት ያለበት ጉዳይ ይህ ነው ብዬ ስላመንኩኝ ይህን አጭር ጽሑፍ ለመጻፍ አስቤያለሁ።
እንዳለመታደል!
ያለፈንና በትክክል የተፈጸመን
ታሪክ ጥላሸት ለመቀባት መሞከር፣ አኹን ላይ ቆሞ በልበ ሰፊነት የኋላውን በቅንነትና በማሰላለሰል የሚያይን ትውልድ መናቅ ነው። በእርግጥ እኛ አገር ታሪክንና
በትክክል የሚታይ እውነታን መደባበቅና ማንቋሸሽ፣ ለመቅበር መሞከርና እንዳይወጣ አፍኖ መያዝ ከፍ ሲል ደግሞ በክፋት ልብ ሸፍጥነትን
መፈጸም እንግዳ ተግባር አይደለም። አሁን ኢትዮጲያን እየመራ ካለው መንግሥት ጀምሮ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች [ምሑራን] የኢትዮጲያን
ታሪክ አንድ መቶ ዓመት የማይሞላ አድርገው ሲያቀርቡ እናያለን፤ ከእነርሱ ውጭ ሌላ አዋቂና መርማሪ እንደ ሌለ አድርገውም በማቅረብ
ይታወቃሉ። ነገር ግን ይኸው መንግሥት አሁን ባለው ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አማካይነት መቶ ዓመት አይሞላትም ያላትን አገር፣ ዛሬ ብሔራዊ
አንድነቷን ለማስከበር ከዓመታት በኋላ ሲነሣ የኢትዮጲያን ጥንታዊነት ሳይወድ ሲናገር ሰማነው። የደቂቀ እስጢፋኖስም ነገር በተካደው
ትውልድ አንደበት በክብር እንደሚነሣ አንጠራጠርም።
በምድራችን
ላይ ከሚከሰቱ ታላላቅ ስህተቶች የመጀመርያው፣ ከታሪክ ስህተት መማር አለመቻል ወይም የተፈጸመና ሕያው የኾነን ታሪክ ለመቅበር ሌላ
የታሪክ ስህተት መፍጠር ነው። አንድ የተለመደ ብሒል አለ፤ “ስትሄድ ያደናቀፈህ ድንጋይ መልሶ ከመታህ፣ ድንጋዩ እርሱ ሳይኾን
አንተ ነህ” የሚል(ብሒሉን አሳስቼ ከኾነ ይቅርታ እጠይቃለሁ)፤ በሌላ ንግግር ትላንት ያደናቀፈን ዛሬም መልሶ ካደናቀፈን እኛ ተደናቃፊዎች
ብቻ አይደለንም ማለት ነው። እንዳለመታደል የወደቅንባቸው አቀበቶችና ስህተቶች የትየለሌዎች ናቸው።
ዳንኤል
በፕሮግራሙ ላይ እጅግ ብዙ አሳፋሪ ንግግሮችን ሲያደርግ ሰምተነዋል፤ ዳንኤል እንዲህ ያሉ ተግባራትን ሲያደርግ ይህ የመጀመርያው
አይደለም፤ ሕሊና አዘዘ ፕሮግራሙን አቅርባ ሃሳቡን እንዲህ በማጋለጧ ሳላመሰግናት አላልፍም።
የደቂቀ እስጢፋኖሳውያን የክርክር ምክንያት ምንድር ነው?
“ … ከስግደት ጋር የተያያዙ ሦስት ሃሳቦች አሉ፤ እጅ መንሳት፣ ሰላምታ
መስጠት፤ መስገድ። የነበረው ክርክር ሦስቱ ለእነ ማን ይገባሉ ነው፤ ስግደትን እንደ አጠቃላይ ካየነው ሦስቱም ስግደት ናቸው፤ ስግደት ያስፈልጋል አያስፈልግም አልነበረም ክርክሩ፤ ግን ለማን ነው የሚሰገደው፤ ማንን ነው እጅ የምንነሣው
እና ማንን ነው ሰላም የምንለው የሚል ነው። … እመቤታችንን
ሰላም ለኪ ልንል ብቻ ነው የሚገባ የሚል አቋም ነበራቸው፤ … ስለዚህ ስግደት የሚለውን ለፈጣሪ እንስጥ፣ ሰላምታ የሚለውን ለቅዱሳን፣
እጅ መንሳት የሚለውን ለእኩዮቻችን ለሰዎች እንስጥ አሉ፤ ሌሎቹ ሊቃውንት ግን ሦስቱም ስግደት ናቸው ከአመለካከት ነው እንጂ፤ ስግደት
ነው አይደለም የሚያሰኘው ሦስቱም ስግደት ነው። ስለዚህ ስግደት በዚህ መልኩ ሳይኾን መከፈል ያለበት የአምልኮት የአክብሮት የጸጋ
ብለን ነው መክፈል ያለብን እንጂ፣ እገሌን እጅ ነሳሁት፣ እገሌን
ሰላም አልኩት፣ እገሌን ሰገድኩለት የሚባል ነገር የለም፤ ይኼ በውስጥ በነገረ መለኮት ላይ የተነሣ ክርክር ነው እንጂ ጠቅላላ ስግደት አያስፈልግም የሚለው ጉዳይ አይደለም፤ ... (ዳንኤል ክብረት)[2]
(አጽንኦት የእኔ)
፳፬ኛ ተአምር
ለመስቀልና ለእመቤታችን ስግደት እንደሚገባ
... ክብርት እመቤታችን
ያደረገችው ተአምር ይህ ነው። ልጅዋ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገው የመስቀሉ ተአምር ይህ ነው።
በክርስቲያን
አገር አንዲት ታላቅ አገር ነበረች። ነገሥታቷም ጳጳሳቷም በውስጧ የሚኖሩ ክርስቲያንም ሁሉ ይወድዋት ነበር። አምላክን የወለደች
በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የክብርት እመቤታችንን በዓሏንም ያከብሩ ነበር። እየሰገዱ ይገዙላት ነበር። ሁለተኛም የልጅዋን የመስቀሉን በዓል ያከብሩ ነበር። ለሱም
እየሰገዱ ይገዙለት ነበር። እጅ ይነሱትም ነበር። ያድነናል ብለው አምነው ይሸከሙት ነበር። በዚያችም አገር ሐሳዊ መሲሕን የመሰለ
በስም ክርስቲያን ነኝ የሚል ጽኑዕ ከሐዲ ተነሣ። ሰውየውም ቄስና መነኩሴ ነኝ ይል ነበር። በሥራው ግን ፍጹም አይሁዳዊ ነበር የዲያብሎስ
የግብር ልጅ ነበርና።
ያም ከሐዲ
አይሁዳዊ የሚሆን እኔ ለማርያም አልሰግድም። ለልጅዋም መስቀል አልሰግድም አለ። ለብዙ ሰዎችም ከውሾች ይልቅ የሚያጸይፍ ይህን ጥፉ
ትምህርቱን አስተማራቸው። ... ከዚያ ከርጉም ከጽኑዕ ከሐዲ ከሰይጣን ልጅ በኋላ የቀሩትም ልጆቹ ለድንግል ማርያም ለልጅዋ መስቀልም
አንሰግድም አሉ። ጥፉ ክፉ ትምህርት በሚሆን በትምህርታቸው ብዙ አመኑ። ንጉሥና ባገርም ያሉ ሰዎች ሰምተው ፈጽመው አዘኑ። ጌታችን
የኒህን የከዳተኞች አይሁድ ጥፋታቸውን አሳየን እያሉ በፍጹም አልቅሰው ወደ እግዚአብሔር አመለከቱ። ንጉሣችን ዘርዓ ያዕቆብም ከዳተኞች
የሚሆኑ እኒህን ሰበሰባቸው። ... ጠየቃቸው ... አንሰግድም አሉ።
... የክርስቲያን ማኅበርም
ባፋቸው እኛ ክርስቲያን ነን ለሚሉ ለኒህ ሞት ይገባቸዋል እያሉ ይሙቱ በቃ ብለው ፈረዱባቸው። ... ንጉሡም አፍንጫቸውን መላሳቸውንም
ቁረጧቸው ብሎ አዘዘ። ሌሎቹ ይፈሩ ዘንድ ቆረጧቸው። እንደዚህም ሁኖ እኒህ ከዳተኞች የሥራቸውን ክፋት አልተውም ነበር። ከዚህ በኋላ
የክርስቲያን ወገኖችም ተሰብስበው እኒህ ከዳተኞች አይሁድን ምላሳቸውንና አፍንጫቸውን ብቻ በመቁረጥ ለምን ተዋችኋቸው? አሉ። አገባብስ
በደንጊያ ወግረው ሊገድሏቸው ይገባ ነበር፤ ... ለእመቤታችንና ለልጅዋ መስቀል አንሰግድም ብለዋልና። ...
የክርስቲያንም ማኅበር ሁሉ በደንጊያ ተወግረው ሊሞቱ ይገባል አሉ። ፍርድም በተፈጸመ ጊዜ እኒህን ከሐዲያን በደንጊያ ይወግራቸው ዘንድ
ንጉሥ አዘዘ። በየካቲት በሁለት ቀን በዕለተ ዓርብ ወግረው ገደሏቸው። ... እኒህን ከሐዲያን ከወገሯቸው ወዲህ ሠላሣ ስምንት ቀን
በሆነ ጊዜ ... ስለእናቱ ስለእመቤታችን ስለከበረ መስቀሉም የክርስቶስ
መስቀል በሚከበርበት በመጋቢት ዐሥር ቀን ሰኞ ሌሊት እግዚአብሔር ድንቅ ተአምር አደረገ። በንጉሡ ድንኳን ላይ ፍጹም ብርሃን ወጥቶ
እንደጎርፍ ፈሰሰ። ... የዚያ ብርሃን መልኩም እንደ እሳት ላንቃ ይመስላል። ነገር ግን አያቃጥልም ነበር። ወደ ሰውም በቀረበ
ጊዜ ፊት ያበራል የብርሃኑም መታየት ልቡናን ደስ ያሰኛል ... (ተአምረ ማርያም)[3]
... ዜና መዋዕላቸው
እንደሚለው ደቂቀ እስጢፋ የሚባሉ ለእመቤታችንና ለቅዱስ መስቀል ስግደት አይገባም የሚሉ መናፍቃን እንደ ተነሱ ይጽፋል። ... እነዚህን
መናፍቃን ንጉሡ ባሉበት ሊቃውንቱ ተከራክረው ረቷቸው። ከዚህ በኋላ እነ ደቂቀ እስጢፋኖስ ለፍርድ ወደ ንጉሡ ቀረቡ። ንጉሡም ፍርዳቸውን
ከምዕመናን እንዲቀበሉ የተሰበሰቡትን ምዕመናን ጠየቁ። ሁሉም በሞት ቅጣት እንዲቀጡ በየነባቸው። በመጨረሻም አፍንጫቸውን ተፎንነው
ምላሳቸውን ተቆረጠ፣ በደንጊያ ተወግረው በየካቲት ሁለት ቀን ሞቱ፤ በ፴፰ኛው ቀን መጋቢት ፲ ቀን የመስቀል ዕለት በዚያ ቦታ ብርሃን
ወርዶ ታየ። ስለዚህም ይህችን ቦታ ደብረ ብርሃን ብለው ሰየሟት። (አባ ጐርጐርዮስ(ሊቀ ጳጳስ)[4]
እንግዲህ ከእነዚህ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሰነዶችና ከዳንኤል ንግግሮች እኒህን
ጥያቄዎች ብናነሣና በልበ ሰፊነት ከቅዱሳት መጻሕፍትና ከታሪክ አንጻር ብንመዝናቸውስ?
1. የዳንኤልን ሃሳብ
መጽሐፍ ከተአምረ ማርያምና ከአባ ጐርጐርዮስ አንጻር እንየው እስኪ? የዳንኤልን ሃሳብ ተቃራኒ ተአምረ ማርያምና የአባ ጐርጐርዮስ
መጽሐፍ በውስጡ ይዟልና፤ ዳንኤል በግልጥ ወይ ተአምረ ማርያምንና አባ ጐርጐርዮስን አይቀበልም፣ አልያ ደግሞ ተአምረ ማርያምንና
አባ ጐርጐርዮስን መንቀፉና አለ መቀበሉን ሊነግረን እየፈለገ ይኾናል፤ ዳንኤል እስጢፋኖሳውያን የመገደላቸው ምክንያት ለንጉሥ ክብርን
ባለመስጠታቸው ብቻ እንጂ ለመስቀሉና ለማርያም ስግደት ይገባል አይገባም የሚል ክርክር አላነሡም እያለን ነው፤ በሌላ ንግግር ይህን
ጥያቄ ቀለል አድርገው ለንጉሡ ክብርን ሰጥተው[ሰግደው] ማለፍ ነበረባቸው ይለናል።
እነዚህ
ሐሳቦች በውስጣቸው ብዙ ቁም ነገሮችን ማስነሣት የሚችሉ ናቸው፤
1.1.1. ታድያ ተአምረ
ማርያምና አባ ጐርጐርዮስ እስጢፋኖሳውያን “ለማርያምና ለመስቀሉ አልሰግድም” በማለታቸው በአሰቃቂ ኹኔታ መገደላቸውን የሚነግረን
ከወዴት አምጥቶ ነው? ለመኾኑ የቆየውና ምስክር መኾን የሚችለው ማን ነው? ዳንኤል ወይስ ተአምረ ማርያም? ዳንኤል ወይስ ሊቀ ጳጳስ
ጐርጐርዮስ? ተአምረ ማርያምና ሊቀ ጳጳስ ጐርጐርዮስ እኮ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን “ለማርያምና ለመስቀሉ አልሰግድም” በማለታቸው ምክንያት
የመከራ ዓይነት እንዳስተናገዱና በዚህ ምክንያትም መገደላቸውን፣ እግዚአብሔርም ይህንን አረመኔያዊ ድርጊት “ደግፎ” ብርሃን እንዳወረደና
ብርሃን የወረደበትም ሥፍራ “ደብረ ብርሃን” ተብሎ እንደ ተሰየመ ይነግረናል እኮ? እንኪያስ ማናቸው እውነተኞች?
በዳንኤል ንግግር ስግደት ያስፈልጋል አያስፈልግም ክርክር ካልነበረ፣ ተአምረ
ማርያም ፈጽሞ ተአማኒነት የለውም ማለት ነው፤ ምክንያቱም ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን የመገደላቸው ምክንያት በግልጽ ተአምረ ማርያም
“ለማርያምና ለመስቀሉ አልሰግድም” በማለታቸው ምክንያት እንደ ኾነ ይነግረናል። ስለዚህ ከኹለት አንዳቸው፣ አንዳች ሸፍጥ እየሸፈጡብን፣
ሴራ እየጐነጐኑብን ነው ማለት ነው። ይህ ማለት ደግሞ አንዳቸው እየዋሹ ታሪክ እያልኮሰኮሱ፤ እያረከሱ ነው ማለት ነው። አንዳቸው
ሕያው የኾነ ታሪክ እየቀበሩ እንዳይታወቅ በብርቱ እየታገሉ ነው ማለት ነው።
1.1.2. ዳንኤል እስጢፋኖሳውያን ለንጉሡ አለመስገዳቸውን የጥበብ መጉደል፣ የእልኸኝነት
ሥራ እንደ ኾነ ይናገራል። ለንጉሡ ሰግደው ቢኾን ኖሮ ይህ ኹሉ የመከራ ዓይነት ባልደረሰባቸው ነበር ይለናል። ለመኾኑ ዳንኤል እስጢፋኖሳውያን
ክብርን መስጠት አለባቸው ሲል ለንጉሡ መስገድ እንዳለባቸው ያምናል ማለት ነው?[ለካ ወዶ አይደለም ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያን የመሰለ
የሰላ ትችትና ጉድ አሽጐድጉዶ ሰንዝሮ፣ መልሶ እጥፍ ብሎ ማኅበሩ ሥር ተጣጥፎ የገባው?!]።
ለመኾኑ
ለእግዚአብሔር ብቻ እንጂ ለሌላ ለማንም አልሰግድ ማለት ከጥበብ መጉደል፣ የእልኸኝነት መንገድ ነውን?
1.1.3. ከእግዚአብሔር በቀር ለሌላ አልሰግድም ማለት ነገረ መለኮታዊ ክርክር ነው
ወይ? የእስራኤል ልጆች፦ “ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት
አይሁኑልህ። በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም
ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት
በልጆች ላይ የማመጣ፤ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ
ቀናተኛ አምላክ ነኝና።” (ዘጸ.20፥2-6) የሚለውን ሕግ ከያህዌ ሲቀበሉ ውስጣዊ የነገረ መለኮት ክርክሩ ምንድር ነበር? እግዚአብሔርን
ብቻ ከማምለክና ለእርሱም ብቻ ከመስገድ ውጪ ምን ሌላ ትንታኔና ሐቲት ነበረው?
1.1.4. ሌላው ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንን
ለማራከስና ለማልኮስኮስ የገባው ፈሊጥና አሽሙር ነው። አንዳንዴ አይሁዳውያን ናቸው ይባሉና ደግሞ መናፍቃን ናቸው ይሉናል፤ ለመኾኑ
አይሁዳዊነት ነባር እምነት(Monotheism) ነው ወይስ ኑፋቄ ነው? አይሁዳዊነትን መናፍቅነት ለማለት ምን ነገረ መለኮታዊ እሳቤ
አለ? ይሁዲነት ራሱን የቻለ ታላቅ የብሉይ ኪዳን እምነት አይደለምን? መናፍቅነት ራሱ ትርጉሙ ምንድር ነው? እስጢፋኖሳውያን መናፍቃን
ናቸው ወይስ አይሁዳውያን? እርግጠና ኾኖ መናገር የሚቻለው ኹለቱንና ሌሎችንም ስያሜዎች ሰጥቶ አለመርካታቸውን የሚያሳይ ነው።
ዳንኤል ልክ እንደ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ የእስጢፋኖሳውያን ነገር ከመቃብር እንዲዳፈን ከሚፈልጉ ሰዎች ዋነኛው ነው። እነርሱን
በመቃወሙ ስሙ ከእነርሱ ይልቅ እንዲያገነግን ይፈልጋል፤ ከእነርሱም በላይ ራሱን ጥንታዊ አድርጐ ልክ በዚያ ዘመን እንዳለ ሰው ኾኖ የእኔን ብቻ እመኑኝ
ሌላውን ልታምኑ አይገባም የሚል “ታባይ ድምጹን” ያስተጋባል። የቤተ ክርስቲያኒቱ መጻሕፍትና አባቶች ግን እስጢፋኖሳውያን በዚያ
ዘመን በነበረው ንጉሥና በክርስቲያኑ ማኅበረሰብ መገደላቸውን ቅንጣት ታህል አታስተባብልም፤ ይልቁን “እግዚአብሔራዊ የጽድቅ ተግባር
እንደ ኾነና ራሱ እግዚአብሔርም እጁ እንዳለበት ትናገራለች እንጂ!” ዳሩ ግን ይህ ኹኔታ ከቅዱሳት መጻሕፍት አስተምኅሮ አንጻር እንዴት ይመዘናል?
እንዲህ ስላለው ተግባር መጽሐፍ ምን ይላል?
ይቀጥላል …
[3]
ተአምረ ማርያም ግእዝና አማርኛ፤ 111 ተአምራትን የያዘ፤
1989 ዓ.ም 3ኛ እትም፤ አዲስ አበባ፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ ገጽ.94-101፤ ከቁ.1-76
diakon slebete krstian tarik mawek efelgalehu metshaf be pdf kaleh laklgn
ReplyDeleteአመሰግናለሁ የሚፈለጉትን መጻሕፍትና ኢሜይል አድራሻ ላክልኝ፤ ካለኝ ሁሉንም ልልክልህ ቃል ገባለሁ!
Deleteበኢቢኤስ ቲቪ ስለደቂቀ እስጢፋኖስ የቀረበውን ዝግጂት በጥቂቱ አይቻለሁ የደቂቀ እስጢፋኖስን የወንጌል ተጋድሎ ማለትም ለወንጌል የከፈሉትን ዋጋ እነ ዳንኤል ክስረት አና መሰሎቹ በዚያን ግዜ ከነበረው ፓለቲካ ጋር አይናቸውን በጨው አጥበው ቢያጠጋጉትም እውነት በውሸት ለመሸቃቀጥ እነ ዳንኤል ክስረት ቢሞክሩም ደቂቀ እስጢፋኖ ለክርስቶስ ወንጌል ዋጋ ከፋለዋል። ለጣኦት አንሰግድም ዘርያቆብ ለጻፈው የአጋንንት ተረተረት አንገዛም ብለው ሰለክርስቶስ ዋጋ ከፋለዋል። አነ ዳንኤል ክስረት አሁን እነሱ አልፈዋል አሁንም ቢሆን ተረተረት ከማውራት ወንጌልን መስክርበት ዳ/ን የታሪክ ተመራማሪ ተብየው ሙያውን አክብረው አንተ እንደፈለክ አትራገጥበት ነገሩ አንተና መሰሎችህ ከመጸሐፋ ቅዱስ እውቀት ነጻናችሁ። እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን። ኢየሱስ ያድናል አሜን
ReplyDeleteእውነት ነው የተናገረከው
ReplyDeleteእስኪ መጀመሪያ ስለ ራስክ ራስህን መርምር አንተ ጊዜ አመጣሽ ሃይማኖት ውስጥነክ ያለኸው መጽሃፍ ቅዱስ አይለወጥም አይታደስም በአሁኑ ሃይማኖታችሁ የተዋህዶን ዶግማ ቀነና ትውፊቷን ለመበረዝ የምትጥሩት ነገር ነው የሚገርመኝ ስለ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መጽሃፍች ብዙ ታወራለክ የሱ ብቻ አይደለም በጣም ብዙ ነገር ስታወራ አይካለሁ እውነት በውሸት አይሸፈንም ደቂቁ እስቲፋኖስ ነብሱን ሳይሰስት ለእውነተኛውና ለትክክለኛው አምላኩ ለድንግል ማርያም ልጅ ሂወቱን ሰውቷል ስለዚህ ጠብ ካለክ ዲያቆንን በግሉ ማናገር ትችላለክ ይህ ሳማእቱን እያነሳክ የምትፈለስፍበት አይደለም ወንድም አቤኔዘር
ReplyDeleteዳንኤል እኮ መንፈሳዊ ሰው አይደለም ክርስቶስ ይድረስለት
ReplyDeleteወዳጄ አሁን አላዋቂነትህን ተረዳው ለካ ሳታውቅ ነቃፊ ነህ ? በል ተወት አድርገን በተዋህዶ ስም አትነግድ ፡፡
ReplyDeleteከስርሀል በናትህ አልተሳካልህም.....ሌላ ጊዜም ይህን ኪሳራ ደግመህ እንዳትሞክረው!!!
ReplyDeleteዳንኤል ክብረት ቃለ ምልልሱን አይቼዋለሁ ስግደት 3 አይነት ነው ለፈጣሪ የአምልኮ ስግደት ለመላዕክት እና ለፃድቃን የፀጋ ስግደት ለሰው የአክብሮት ስግደት ታዲያ ስህተቱ ምን ላይ ነው እርግጠኛ ነኝ ሊያስተምርህ ፈቃደኛ ነው ጠይቀውና ተማር የማያልቅ እዉቀትና ጥበብ አለው
ReplyDeleteyehe page yetawageze yetahadaso page naw salazih sela ORTHODOX astemaro haseb mestat ayechelem menafek selahone yedekone Abinezer yemilaw page lay yemitelalafut managnawanam haseb ORTHODOXEN ayemeleketem.
ReplyDeleteደሞ በሱ መጣችሁ ብንጨፈለቅ አንድ እሱን አንሆንም ከብት ዶማ
ReplyDeleteዳንኤል እኮ ነገሮችን የሚያበላሸው ሆን ብሎ ነው በተለይ ደግሞ መንፈሳዊ ነገሮችን እያወቀ ሆን ብሎ ነው
ReplyDeleteአቤንኤዘር ተባረክ በርታ አስደናቂ ሥራ ነው፡፡ ብዙ ተቃውሞ ስለተነሳብህ አትደንግጥ
ReplyDeleteአልተማረም እንጂ ዘርዓ ያዕቆብ ቢማር ኖሮ እስጢፋኖስን ለሥዕል ለመስቀል ለሕንፃ ስገድ ብሎ አይጠይቀውም ነበር ። ደግሞም ያን ያህል ስቃይ ማድረስ ባልፈለገ ነበር ። ይባስ ብሎ ለመስቀልና ለማርያም የፈጣሪ ክብር ይገባቸዋል በክብራቸው ከፈጣሪ ጋራ ተካክለዋልና ብሎ ባልካደ ነበር ።
ReplyDeleteሲጀምር እስጢፋኖስ ክርስትናን አያውቅም አልተቀበለምም
ReplyDeleteለምን ቢባል ክርስቲያን ይሞታል ስለክርስቶስ
ስለእውነት ይሞታል እንጂ በሃይማኖት ሰበብ ሰውን አይገድልም
ክርስትና በስም ብቻ ሳይሆን በተግባር የሚገለጥ ነው
ዮሐንስ 13 (John)
13፤ እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።
14፤ እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል።
15፤ እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።
16፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።
17፤ ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።
1 ጴጥሮስ 2 (1 Peter)
20፤ ኃጢአት አድርጋችሁ ስትጎሰሙ ብትታገሡ፥ ምን ክብር አለበት? ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራን ስትቀበሉ ብትታገሡ፥ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ይገባዋል።
21፤ የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።
22፤ እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤
23፤ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤
24፤ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ (* በግዕዝ እንዲህ ተጽፎአል፡— ወበእንተ ኃጣውኢነ ውእቱ ተሰቅለ ዲበ ዕፅ በሥጋሁ ከመ ያውፅአነ እምኃጣውኢነ ወበጽድቁ ያሕይወነ። *)
ማቴዎስ 10 (Matthew)
24፤ ደቀ መዝሙር ከመምህሩ፥ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም።
25፤ ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!
26፤ እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና።
27፤ በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ።
28፤ ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።
ከእነዚህ ነገሮች አጼ ዘርዓያዕቆብ አንድም የፈጸመው የለም
ይልቁንም የሻረው እንጂ
ስገዱልኝ ተበርከከኩልኝ
ለፍጡራን
ለእጽዋት
ለቅርጻቅርጽ ስገዱ የሚል ክርስቲያን በፍጹም ክርስቲያን ሊሆን አይችልም
ክረስቲያንም አይደለም
ሥራው ይገልጠዋልና !!!!!
በመጀመርያ ይህ ዳንኤል። ክብረት የሚባል ሰው እንጀራ በልቶ። ለመሞት። የወሰነ ሰው ንው ስለ እግዚአብሔር። ክብርና እውነት ምንም ግድ የለውም ሰለዚህ። እንደዚህ። ላሉ። ታሪካዊ እውነቶች ለሱ ም ትርጉም። አይሰጡትም ለምን ስለ እውነት ቢናገር የእንጀራ ገምዱ ይበጠስበታል ሰለዚህ። ለዚች። አላም ሊኖርላት ብሎ ነው ከርሱ ከዚህ። የተሻለ። ነግር ባንጠብቅ?
ReplyDeleteየደናቁርት ሥብሥብ መናፍቃን ይፈጥራል አማሳኝ
ReplyDeleteሙሉ ንግግሩን ብትጽፈው ኖሮ መልካም ነበር ማለት የዲያቁን ዳንኤል ንግግርን ማለቴ ነው ሆኖም አንተ ከማን ወገን ነህ? "በወይራ ዘይት ብልቃጥ ውስጥ ሌላ ነገር ይታየኛል" በነገራችን ላይ የነገሩትን ብቻ በመስማት የሚነዳ የማያውቅ የዋህ ብቻ ነው። ስለ ደቂቀ እስጢፋ በብዘ መልኩ የሐስት የክስ በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ የማቅረብ አባዜ የተጠናወታችሁ አላችሁ ለምን ቢሉ እውነት የሚመስል ሐሰት የዋሁን ለማጥመድ ስለሚጠቅም
ReplyDeleteDniel kbret yhuda metshaftoch bemesrk ymtawek
ReplyDeleteWorship only belongs to Jesus who died in the cross
ReplyDeleteምን ማለት ነው ?ድቁንናህ ግን ኦሪጅናል
ReplyDeleteነው ወይስ በእርቀት የተቀበልኸው ነው?
ምን ማለት ነው ?ድቁንናህ ግን ኦሪጅናል ነው ወይስ በእርቀት የተቀበልኸው ነው?
ReplyDeleteአንተ አለህ አድል ምንም ሳትሰራ የሰሩትን ቁጭ ብለህ የምትተች አንተን ብሎ ዲያቆን❗
ReplyDeleteተዋህዶ ኦርቶዶክስን የማትከስበት መንገድ የለህም በቃ ጥላቻ ውስጥህ ዘልቋል::
ReplyDeleteንጉስ እንጂ ቅዱስ ብለን አልጠራነውም:: ዘርዓያዕቆብ የኢትዮጵያ ንጉስ ነበር:: ጣኦት አምልኮትን በግልጽ የተቃወመ ነው:: በኢትዮጵያ ልዕልና እንደ ንጉስ ካሌብ የሚጠቀስ icon ነው:: ምሁር እንደነበረም መጽሐፍቱ ምስክሮች ናቸው::
Banda mn takaleh sil...hhhhh waybandonat endekebaronew miyadergew
ReplyDeleteዘርዓያዕቆብን የሚጠላ አጋንንት የሰፈረበት የአጋንንት ዘር ብቻ ነው ።
ReplyDeleteተቃጠል !! ከኃዲው ጴንጤ።
እንደዛነው ሚያዝህ የያዝከው መጽሐፍ ቅዱስ ንቃ የተኛኸው በባዶ ሜዳ ላይ ያለ እንቅልፍ የቃዠኸው
ReplyDeleteበረከት ፀጋ ይብዛልህ !
ReplyDelete