Showing posts with label አራተኛው የዓቢይ ጾም ሳምንት - መጻጉዕ. Show all posts
Showing posts with label አራተኛው የዓቢይ ጾም ሳምንት - መጻጉዕ. Show all posts

Sunday, 15 March 2020

ልበ መጻጉዕ!

Please read in PDF

   የዓቢይ ጾም አራተኛው ሳምንት ስያሜው መጻጉዕ ነው፤ ትርጉሙ በ ቁሙ ጐባጣ ማለት ነው። የስያሜው ታሪክ በቀጥታ የተያያዘው በዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 5 ላይ ያለውን ታማሚ ሰውን ማዕከል ያደረገ ነው። ታማሚው ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ያህል ሕመምተኛ የነበረ ሰው ነው። ሕመሙ ምን እንደ ኾነ አልተጠቀሰም፤ ነገር ግን ጽኑ ሕመም መኾኑ አይካድም። በኢየሩሳሌም፣ በበጐች በር አጠገብ፣ አምስት ባለ መጠለያ መመላለሻዎች የነበሯት፣ በአራማይክ ቋንቋ ቤተ ሳይዳ ወይም ቤተዛታ ተብላ በምትጠራው የመጠመቂያ ስፍራ፣ ይህ መጻጉዕ ሰው ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ያህል ፈውስን ሲጠብቅ ኖሮአል።


Sunday, 24 March 2019

መጻጉዕ - ፈዋሹ እግዚአብሔር

Please read in PDF
“እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና” (ዘጸ. 15፥26)
   እስራኤል ከግብጽ ምድር ሲወጡ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በጸናች እጁ በተዘረጋች ክንዱ፤ በተአምራት አሻግሮአቸዋል፤ ባሕሩን ከተሻገሩ በኋላ ሙሴ ሕዝቡን ይዞ ለሦስት ቀናት የተጓዘው ወደ ሱርም ምድረ በዳ ነው፤ በዚያ ምድረ በዳ ላይ ሕዝቡ ውኃ ማግኘት አልቻሉም፤ ቀጥለው ወደ ማራ ቢመጡም የማራ ውኃ እጅግ መራራ ነበርና መጠጣት አልቻሉም፤ ከዚህ የተነሣ ታላቁን ተአምራት፣ ድንቁን ነገር በኤርትራ ባሕር ዳርቻ ላይ የተመለከቱት እስራኤል፣ ባዳናቸውና በታደጋቸው አምላክ መታመንን ትተው፣ “ሕዝቡም፦ ምን እንጠጣለን? ብለው በሙሴ ላይ አንጐራጐሩ” (ዘጸ. 15፥24)። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ለመነ፣ ያህዌ ኤሎሂም እንዳዘዘውም አደረገ፤  ውኃውም ጣፈጠ።