Showing posts with label ሦስተኛው የዓቢይ ፆም ሳምንት - ምኩራብ. Show all posts
Showing posts with label ሦስተኛው የዓቢይ ፆም ሳምንት - ምኩራብ. Show all posts

Monday, 9 March 2020

ምኩራብ - ሦስተኛው ቤተ መቅደስ

Please read in PDF

  ያለንበት የዓቢይ ጾም ሳምንት በማኅሌታይ ያሬድ ስያሜ፣ “ምኩራብ” ተብሎአል፤ ምኩራብ አይሁድ በምርኮ ወደ ባቢሎን በተወሰዱ ወራት፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማንበብና የሕጉን ቃሎች ለማሰብ፣ በየጥቂት አባወራ በመሰባሰብ የጀመሩት ነው። ወደ አገራቸው ሲመለሱም ይኸንኑ በመቀጠል፣ ከዋናውና መሥዋዕት ከሚቀርብበት መቅደስ ባሻገር፣ በየመንደራቸው አቅራቢያ ምኩራብ በመሥራት፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማጥናትና ማንበብን በዚያ ጀመሩ። እንግዲህ ማኅሌታይ ያሬድ፣ ምኩራብን ለዓቢይ ጾም ሦስተኛው ሳምንት ሲሰይም፣ በሳምንቱ ውስጥ ከሚነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ደግሞ፣ ዮሐ. 2፥12-22ን በመመደብ ነው። ክፍሉም በቀጥታ በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ ጋር በማያያዝ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ስለ መኾኑ የታመነ ነው።

Tuesday, 19 March 2019

ምኩራብ

  Please read in PDF
  አይሁድ ወደ ባቢሎን በምርኰ በወረዱ ጊዜ የቀደመው ኪዳን “የአምልኮ ማዕከል” ከኾነው ከመቅደሱ ተለያዩ፤ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር በሦስተኛው ዙር የምርኰ ማጋዝ በአካል ወደ ኢየሩሳሌም በመምጣት ኢየሩሳሌም ገለበጣት፤ መቅደሷንም አፈረሰ፤ ከመቅደሱ ንዋየ ቅዱሳቱንም ዘረፈ፤ እስራኤልን ሙሉ ለሙሉ ባድማ አደረጋት።
   እናም የኪዳኑ ሕዝብ እስራኤል በምርኰ ሳሉ አምልኮ “ናፈቁ”፤ ከኢየሩሳሌም በቀር በሌላ ስፍራ [በባቢሎን ጭምር] መቅደስ መሥራት ባይቻላቸው፣ በዚያው በምርኰ ባሉበት ምድር ኾነው የሚሰባበሰቡበትንና በዋናነትም ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚያነቡበትን፣ በንባብም የሚያመልኩበት ምኩራብ፣ በቁጥር አነስ ያሉ ሰዎችን ሊይዝ በሚችል መልኩ በሕዝቡ መካከል ሠሩ፤ እናም በምርኰ ምድር ኾነው በንባብ እግዚአብሔርን ለማምለክ፣ ሊታዘዙትም ምኩራብን ለሕዝቡ አቅራቢያ በኾነበት ስፍራ ተግተው ሠሩ።