-
“… አኹን ያለንበት ጊዜ ስብከተ
ወንጌል በዋና ዓላማነት ያልያዘበት፣ ሊቃውንትን በማፍራት ብቻ ቤተ ክርስቲያን የተጠመደችበት ጊዜ ቢኖር አኹን ያለንበት ጊዜ ነው።
…”
- “… ወንጌል እንደ ቅዱስ ጳውሎስ መሥዋዕታዊ ሕይወትን ዘወትር ይፈልጋል። …”
-
“… የችግራችን ዋና ምንጭ ወይም መሠረት የሥርዓተ ትምህርት ክፍተት ነው፤
ለዚህ ኹሉ ነገር የዳረገን ይህ ነው፤ ይህም ማለት ጉባኤ ቤቶችም ይኹኑ ሌሎችም የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ የተሸከሙ አይደሉም፤
የቤተ ክርስቲያን ተልእኮዎች ሐዋርያዊነት፣ ኖላዊነትና ዕቅበተ እምነት ናቸው። ከነዚህ ከሦስቱ ውጭ ሌላ ተልእኮ ቤተ ክርስቲያን
የላትም። ሐዋርያዊነት እስከ ዓለም ዳርቻ ወንጌሉን እየሰበኩ መሄድ ነው፤ ኖላዊነት በበረት ያሉትን አምላካዊ መልክ እንዲይዙ ማድረግ
ነው፤ ዕቅበተ እምነት ደግሞ በሃይማኖት የሚቃጣውን ነገር መክቶ ማምከን፤ ማስቀረት ነው። ከነዚህ ከሦስቱ ውጭ ቤተ ክርስቲያን ሌላ
ዓላማ የላትም። ጉባኤ ቤቶቻችን ከነዚህ ጋር የተጣበቁ አይደሉም ነው ዋና መልእክታችን። …”
- “ … ከጉባኤ ቤት ስንማር ወንጌል ታደርሳለህ፣ ወገንህን ታጠምቃለህ … ተብሎ
የተላከ አለ? … እኔ አልተባልኩም እንግዲህ። ትኵረታችን ሊቅ ወይም የሚራቀቅ ማፍራት ብቻ ኾነ እንጂ ተሰድዶ ሄዶ ወንጌል ማድረስ
የለም። ይህ ጉባኤ ቤቶች ሲቀረጹ ያመጣው ክፍተት ነው። …”
-
“… አብነት ትምህርት ቤቶች
ታላቅ የዕውቀት መከማቻ ቢኾኑም ውጤታቸው ግን በተቋማዊ ግብ ሐዋርያዊነትን፣ ኖላዊነትንና ዕቅበተ እምነትን ሳይኾን በግለሰብ ፍላጎት
ላይ የተመሠረተ ዓላማን ቀረጹ። ያላመኑትን አሳምኖ ማጥመቅ፣ በረቱ ውስጥ ያሉትን ለቅድስና ማብቃት፣ በሳይንስ በመጤ ፍልስፍናና
በልዩ ልዩ ምንፍቅናዎች የበቀሉ አረሞችን መከላከል መኾን ነበረበት ግን አልኾነም። …”
-
“… ቤተ ክርስቲያን የተሰጣትን
ተልእኮ ትታ፣ ራሳቸውን ብቻ የሚያኖሩ አገልጋዮችን በመመገብ ተጠምዳለች። ይህ በጣም ታላቅ ሸክም ደግሞም ውርደትም ነው። በዚህ
ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተቀጥሮ ራሱን የሚያኖር አገልጋይ ቁጥሩ ቀላል አይደለም። ከዚህም የተነሣ አገልጋዩ ከዚህ በታች
ያሉትን የተቀጣሪነት መገለጫ ጠባያት አሉት፦
·
አገልጋዩ በምዕመኑ መንፈሳዊ
ዕድገት ላይ ከመጨነቅ ይልቅ፣ ከምዕመኑ በሚገኝ ጥቅም ላይ ራሱን ጥገኛ ያደርጋል፣ ይህ ደግሞ ስልጡን ለማኝነትን ያመጣል፣
·
አዳዲስ ተግዳሮቶችን መጋፈጥ
አይፈልግም፣ ይህ የግል ጥቅሙን ይነካዋል፣
·
በደመወዝና በአበል ጥያቄዎች
ሲወዛገብ ይውላል፣ ቤተ ክርስቲያንም ከተልዕኮ ተኮር ወደሙያ ተኮር ፍልሰት ነው የገጠማት ማለት ነው፣
-
“… መንፈሳዊ ተልእኮን በbusiness
management መርሖዎች ለመምራት መሞከር፤ ማለትም ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደ ኩባኒያ፣ ምዕመኑ እንደ ደንበኛ ሰባኪው ደግሞ እንደ
marketing ኾኖ እየተወነ ይገኛል። ይህ እጅግ የናረ የቁስ ፍላጎት በአገልግሎቱ ውስጥ እንዲሰፍን አድርጎአል ማለት ነው፤…”
ይቀጥላል …

ቃል ሕይወት ያሰማል ተስፋ መንግስተ ሰማያት ያውርስልን
ReplyDelete