Showing posts with label ጌና (የኢየሱስ ልደት). Show all posts
Showing posts with label ጌና (የኢየሱስ ልደት). Show all posts

Monday, 6 January 2020

የእግዚአብሔር ቅንአት!

Please read in PDF
የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።”
   ነቢየ ልዑል ኢሳይያስ፣ ሕጻኑ ወንድ ልጅ ጌታ ኢየሱስ ከርስቶስ ለእኛ በውድ ስጦታነት እንደ ተሰጠ ይነግረናል። “ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤” በማለት አብ ብዙ ስጦታዎችን ለእኛ ሰጥቶናል፤ ኢየሱስን የሚያህል ስጦታ ግን አልሰጠንም፤ ወደ ፊትም አይሰጠንም፤ የተሰጠን የትኛውም ስጦታ ከኢየሱስ አይበልጥምና። አስቀድሞ በራሱ መልክና ምሳሌ ፈጥሮን፣ የራሱን መልክና አምሳል በእኛ በማኖር ክብሩንና ጽድቁን፣ ዕውቀቱንና አለመሞትን ለኹላችን አድሎናል። እግዚአብሔር ሰውን ቅዱስ አድርጎ በመፍጠሩም፣ ከሌሎች ፍጡራን በተለየ መልኩ፣ ሰው የእግዚአብሔርን ቅድስና ተካፋይ ኾነ።


Saturday, 19 October 2019

በልብ መጠበቅ

Please read in PDF

ነገርን በልብ ስለ መጠበቅ በመጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ምዕራፍ ኹለት ጊዜ የተነገረላት እናት የኢየሱስ እናት ቅድስት ማርያም ናት። ቅድስት ድንግል ማርያምን በተመለከተ ከኹለት ልዩ ልዩ አካላት የሚሰነዘሩትን ነገሮች በጥሙና ለሰማ ሰው ዲያብሎስ ሐሳቡ የተሳካለት ይመስላል። (አንዱ ቤት ከአምላክ እንድትስተካከል አድርጎ፣ ሌላው ቤት ደግሞ ፈጽሞ እንድትጠላ በማድረግ)። ኹለቱም ወገኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ አድራሻ ለመራቃቸው እማኙና የመጀመርያው ማስረጃ ያው ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። (ስለነዚህ ወገኖች ሌላ የብዕር ቀጠሮ ልያዝና በቀጥታ ወደ ዛሬው ዐሳቤ ላቅና)።

Saturday, 5 January 2019

ሕጻኑና እናቱ


Please read in PDF
    የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከቅድስት ድንግል የመወለዱን ነገር ከጻፉልን ወንጌላውያን አንዱ ቅዱስ ማቴዎስ ነው፤ መሲሑ ተናፋቂው ማስያስ፣ በነቢያት ትንቢትና በአበው ምሳሌ የተነገረለትና የዘመናት ናፍቆት የነበረው ሕጻንና ጌታ፣ አባትና ልዑል ምጡቅ ከኾነው ከአባቱ ከሰማይ ወጥቶ ወደ ሰው ልጆች ኹሉ[ወደ እኛ] በመምጣቱ ተገለጠ፤ ቅዱስ ማቴዎስ ይህን እውነታ የመሲሑን ነገረ ልደት ከአይሁድና ከአሕዛብ የትውልድ ሐረግ ቈጥሮ በመምዘዝ፣ በመዘርዘርም መሲሑን ዘላለማዊ ነገር ግን በሥጋ ዕድሜ የተወሰነ ጊዜ ሊቈጠርለት እንዳለው (1ጢሞ. 2፥6) በመንፈስ ቅዱስ ተነድቶ ጻፈልን።  
   ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ስለሕጻኑና እናቱ ሲናገር፣ ሕጻኑን ቀዳሚና አቻ የሌለው በማድረግ ኹል ጊዜ ያቀርበዋል። በምዕራፍ ኹለት ላይ ብቻ ይህን እውነታ በጕልህ መመልከት እንችላለን፤ “ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት”፣ “ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ”፣ “እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና …”፣ “ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ”፣ (ማቴ. 2፥11፣ 13፣ 14፣ 21) በማለት በማናቸውም ስፍራ ላይ ከእናቱ በፊት ሕጻኑን በማስቀደም፣ ፊተኛ በማድረግ፣ በማግነን፣ በማላቅ ያስቀምጠዋል[በእርግጥስ ሕጻኑ ያልላቀ ማን ሊልቅ፣ መሲሑ ያልገነነ ማን ሊገንን፣ ኢየሱስ ፊተኛ ያልኾነ ማን ሊቀድም …?]።

Wednesday, 15 August 2018

በሥጋ የተገለጠ አምላክ


    የክርስትና ትምህርት የመገለጥ ትምህርት ነው። የመገለጡ ምንጭ መለኮት ከኾነው ከራሱ ከእግዚአብሔር እንጂ፣ በሰው ወይም ከሰው አይደለም። ይህ መገለጥም “ከጥንት ጀምሮ በብሉይ ኪዳን ታሪክ እግዚብሔር በልዩ በልዩ መንገድ ለአበውና ለነቢያት በቃልም ሆነ በድርጊት፣ በራእይም ሆነ በሕልም በተአምራዊ ሁኔታ የገለጠላቸውን ሁሉ ያካትታል፤ በተለይም በኋለኛው ዘመን በሥጋ የተገለጠውን ክርስቶስንና የማዳን ሥራውን ሁሉ ይመለከታል።”[i]

ከዋናው መገለጥ በፊት የነበረው “መገለጥ”
     ብሉይ ኪዳን ታላቁን መገለጥ ፍለጋ ብዙ የመቃተት ድምጾች፣ ሕልሞች፣ ራእዮች፣ ትንቢቶች … የተሰማበት የምጥ መጽሐፍ ነው። እኒህ ብዙ መቃተቶችና ፍለጋዎች ለረጅም ዓመታት የተደረጉ ናቸው። በእኒህ ረጅም ዘመናት መላእክት ሊያዩት የሚመኙትንና ሰዎች ሊያገኙት ያላቸውን መዳን፣ ቅዱሳን ነቢያት “…ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤” (1ጴጥ. 1፥10-11)፣ ታላቁ ነቢይ ሙሴ፦ “የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ ነቢያት ቢሆኑ፥ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ መንፈሱን ቢያወርድ አንተ ስለእኔ ትቀናለህን?” (ዘኊል. 11፥29) በማለት፣ ታላቁ መገለጥ ለሕዝቡ ኹሉ እንዲገለጥና እንዲያገኛቸውም አብዝቶ ተመኘ። እጅግ የሚደንቀው ነገር የዘኊልቅ መጽሐፍን ሲጽፍ እንኳ፣ እጅግ የበዛውን ትውልዶች በመቁጠር ሲደክም ትልቁ ዓላማው ሊያርፍበት ያለውን ዋናውን መሲህ ፍለጋ ነበር። እርሱን ስላላገኘም በብዙ ፍለጋ ውስጥ ማለፉን እናስተውላለን።
    አንድ አባት ይህን እውነት በመጽሐፋቸው እንዲህ ብለው ገልጠዋል፦

Thursday, 15 February 2018

አንተ ባትወርድልኝ

ከመላእክት ዓለም ወደእንሰሳት በረት
ከመለኮት ሳታንስ ወደሰው ልጅነት

Tuesday, 5 January 2016

“ …ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ” (ማቴ.1፥21)


Please raed in PDF

እንኳን ለበዓለ ልደቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ አሜን፡፡
      ለሁለት ሺህ ዓመታት ያልተዘነጋ ፤ ለአንድም ቀን ሳይነሳ የተዋለበት ቀን የሌለ ድንቅ ስም፤ ክርክር ፣ ሙግት ፣ ክህደት ፣ ፍልስፍና ፣ ነቀፋ ፣ ስድብ ፣ ትችት ፣ መሸቃቀጥን ድል ነስቶ ያሸነፈ ፤ ነቢያት ሊሰሙትና ሊያዩት የወደዱት፣ መላዕክት በምስጋና ያደነቁት ግሩም ስም ፤ ባለፈው ፣ ባለውና ገና በሚመጣው ትውልድ ተወዶ ያልተጠገበ ስም ቢኖር ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡
    ኢየሱስ የሚለው ቃል “የሹዋ” ለሚለው የዕብራይስጥ ቃል አቻ የግሪክ መጠሪያ ስም ሲሆን፥ ትርጉሙም “እግዚአብሔር ያድናል ፤ እግዚአብሔር ድኅነት ነው” ማለት ነው፡፡ በሌላ ንግግር ኢየሱስ በግሪኩ ሲሆን በዕብራይስጡ ኢያሱ ነው፡፡ ትርጉሙም አንድ ነው፡