Showing posts with label ነገረ ነነዌ. Show all posts
Showing posts with label ነገረ ነነዌ. Show all posts
Thursday, 13 February 2020
Tuesday, 19 February 2019
“ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ” (ማቴ. 12፥41)
Please read in PDF
የአይሁድ መሪዎችና ሕዝቡም የክርስቶስን መሲሕነት ለማረጋገጥ ምልክትን [ተአምራትን] በተደጋጋሚ ጠይቀውታል። የጠየቁት መሲሕነቱን ለማመንና እርሱን ለመከተል አይደለም፣ ይልቁን መሲሕነቱን ለማወቅ የመጡበት መንገድ ጠማማና ያለማመን መንገድ ነው። በዚህ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 12 ላይ ብቻ እንኳ ሊፈታተኑ በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበዋል፤ (ቁ. 2፤ 14፤ 24፤ 38)፤ ፍጹምና ጻድቅ የኾነውን መሲሕ ሊፈትኑት እርሱ የሚያሳየውን ምልክት በተደጋጋሚ ጠይቀዋል። የፈለጉት ተአምራት በጉልህ የሚታይና አሁን በሰማያት ላይ የሚደረገውን ነበር፤ (ሉቃ. 11፥16)።

ምልክቱን የፈለጉት ራሳቸው እንደሚሹት ነው እንጂ ሊታነጹበትና እግዚአብሔርን
የተአምራት ድንቅ አምላክ ብለው ለማመስገንና ለማምለክ አይደለም፤ ይልቁን ሊነቅፉት፣ ሊፈትኑት፣ በእርሱም ላይ ሊሳለቁ ነበር። በቀጥታ
ንግግራቸውም ኢየሱስ ተአምራትን ያደርግ የነበረው በሰይጣን ኃይል እንደ ኾነ በግልጥ በመናገር ንቀታቸውን አሳይተዋል። በዚህ ንግግራቸው
ይህን ብቻ የሚያደርጉ አይደሉም። እግዚአብሔር የዘለላም አምላክ መኾኑን የሚቃወሙ ናቸው። ምክንያቱም እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን
የሠራቸው ሥራዎቹ፣ ተአምራቶቹ፣ ምልክቶቹ የሚያረጁና የሚያልፉ አይደሉምና። ይህን ባለማስተዋል በፍጹም ስተዋል።
Sunday, 1 February 2015
ከነቢዩ የተሻሉት አህዛብና ግዕዛን
ትንቢተ ዮናስን ስናጠና የእግዚአብሔር
አስተማሪነትና ታጋሽነትን በእውነት ልብ የሚነካ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚንቀው አንዳች ሥነ ፍጥረት እንደሌለ ስናይ ደግሞ የዮናስን
መጽሐፍ ይበልጥ ደጋግመን ባለመሰልቸት በትኩረት እንድናየው ያደርገናል፡፡ ምንም እንኳ አህዛብ ቢሆኑም እግዚአብሔር የታላቂቱን ከተማ
የነነዌን ክፋት ወደፊቱ መውጣቱ ባየ ጊዜ ከፍርድና ከቁጣ ይልቅ ይመለሱ እንደሁ በማለት የንስሐ ዕድል ሊሰጥ ነቢዩ ዮናስን ወደነነዌ
“ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ ክፉታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቶአልና በእርስዋ ላይ ስበክ።” አለው፡፡(ዮና.1፥2)
እግዚአብሔር ሳያስተምር ፣ ሳይመክር ፣ ሳይዘክር ፣ ሳይገስጽ ፣ ሳያስጠነቅቅ
… ለፍርድ አይቸኩልም፡፡ እግዚአብሔር የኃጢአታችን ብዛት አያስጨንቀውም ፤ የትኛውም የኃጢአት ብዛት ትንሹን የእርሱን ምህረት እንደማይበልጥ
ያውቀዋልና፡፡ ስለዚህ ነነዌን በፍርድ ከማስተማር በፍቅር ሊያስተምር ታላቁን ነቢይ ላከላት፡፡ ሥልጣን ከኃይል እንዲበልጥ በፍቅር
ማስተማርም በፍርድና በተግሳጽ ከማስተማር እጅጉን ይበልጣል፡፡ ጌታ እግዚአብሔር ነነዌን ማስተማር የፈለገው በምህረትና በፍቅር ነው
፤ ዮናስ ግን እግዚአብሔር ከተማይቱን በፍርድና በቁጣ እንዲያስተምር እንጂ በፍቅር ከማስተማርና “ንስሐ ግቡ” ከሚለው ጀምር መባሉን
አልወደደውም፡፡ ስለዚህም ከእግዚአብሔር ፊት መሸሽን እንደመፍትሔ በመቁጠር የዚያን ጊዜ የአለም ዳርቻ ናት ተብላ ወደምትታመነው
ከነነዌ ማዶ ሊሄድ ተነሳ፡፡ ዳዊት “ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? … ”(መዝ.138፥7) ያለውን ዘንግቶት
ነበር፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)