Showing posts with label ጥምቀት. Show all posts
Showing posts with label ጥምቀት. Show all posts

Sunday, 19 January 2020

በጥምቀቱ ከኀጢአተኞች ጋር ተቈጠረ!

Please read in PDF
 
   ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጠመቁን ነገር በየዓመቱ በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት “ታስቦ” ይውላል፤ መታሰቡ “መልካም” ቢኾንም፣ የሚታሰብበት መንገድ ግን ፈጽሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ መራቁ፣ እጅግ የሚደንቅ የሚያሳዝንም ነው። በአገራችን “በዓለ” ጥምቀት አብዛኛውን ጊዜ ከመንፈሳዊ ነጸብራቅነቱ ይልቅ፣ ባሕላዊና ʻሃይማኖታዊ ሥርዓት መከናወኛ ብቻ ኾኖ ሲከበርʼ እናስተውላለን። ጭፈራ፣ ሽለላ፣ ʻታቦትʼ እጀባ፣ ሎሚ ውርወራ፣ የአዳዲስ ልብስ ማሳያና … ሌሎችም ተግባራት፣ ልኩንና ገደቡን በጣሰ መልኩ የሚቀርቡት በዚሁ በጥምቀት “በዓል” ቀን ነው። ቤተ ክርስቲያን ወደ ኢየሱሳዊ መንፈሳዊነት ፍጹም አለማዘንበልዋ እንዲህ ላለ ሰፊ ተላላነት ተላልፋ መሰጧን ማስተዋል አያዳግትም።

Sunday, 5 February 2017

ጌታ ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ? (የመጨረሻ ክፍል)

Please read in PDF
4.   ድቅን ሁሉ ለመፈጸም   ጽድቅ የሚለው ቃል፣ ቀጥታ ከዕብራይስጥ የተቀዳ ሲሆን ትርጉሙ፥ ፍጹም ትክክለኛነት፣ ቀጥተኛ፣ ፍትሓዊ፣ በጐ ምግባር ማለት ነው፡፡  ይኸውም ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ግንኙነት “በትክክለኛ ሁኔታ” ላይ ሆኖ መገኘት ማለትን በግልጥ ያሳያል፡፡ እግዚአብሔር ከመጀመርያው ለሰው ያለው ሃሳቡ እንዲህ ነበር፡፡ ፍጹም ጻድቅና መልካም እንዲሆን፥ ሰው ግን በእግዚአብሔር ፊት በመልኩና በአምሳሉ ሊገኝ አልቻለም፡፡ ወደገዛ መንገዱም በማዘንበል በምሳሌው እንደ መልኩ ማንነቱን በመያዝ (ዘፍ.5፥3) በኃጢአት ተሰነካክሎ ወደቀ፤ ከትክክለኛነትም ተሰናከለና በዕድፈት ረከሰ፡፡
    መጥምቁ ዮሐንስ አስቀድሞ ጌታ ኢየሱስን ለማጥመቅ ፈቃደኛ አልነበረም፤ ምክንያቱም ጌታ ኢየሱስ ምንም በደልና ኃጢአት የሌለበት ፍጹም ጻድቅ መሆኑን አስተውሏልና፡፡ ስለዚህም አብረውት ስለኃጢአታቸው ሊጠመቁ ከቆሙት እንደአንዱ ሊቆጥረው አልደፈረም፤ ይልቁንም ጌታ ኢየሱስ ከሁሉ የተለየ ልዩ መሆኑን የአዋጅ ነጋሪው ሰው ተገነዘበ፡፡ “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?” በማለት፣ ራሱን ከኢየሱስ ጋር በማስተያየት፣ ዮሐንስ ራሱ መጠመቅ የሚያስፈልገው ፍጹም ኃጢአተኛ መሆኑን መሰከረ፡፡ በእርግጥም፣ ሰው ከሆነው ከኢየሱስ በቀር አንዳች ፍጹምና ጻድቅ ከምድር ስለጠፋ ክርስቶስ ጽድቃችን ሊሆን መጣ፡፡ እርሱ አንዳች በደልና ነውር ያልተገኘበት ነውና ጽድቅን  በመሥራት ለእግዚአብሔር አቀረበን፤ (ዕብ.4፥14 ፤ 1ጴጥ.2፥22-23)፡፡

Wednesday, 25 January 2017

ጌታ ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ? (ክፍል ሦስት)

Please read in PDF
3.    ሰው ኃጢአትና ውድቀት ጋር ራሱን ይደምር ዘንድ ይህ ሃሳብ በመንፈስ ቅዱስና በቃሉ ማስተዋል ካልሆንን በቀር፥ ብዙዎች ተሰነካክለው እንደወደቁበት ልንሰነካከልና ልንወድቅበት እንችላለን፡፡ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትስብእትነት ላይ ብዙዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊውን እውቀት ባለመያዛቸው ምክንያት ከጥንት ዘመን ይስት እንደነበር ዛሬም ብዙዎች ሲስቱ እያየን ነው፡፡

Friday, 20 January 2017

ጌታ ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ? (ክፍል ሁለት)

Please read in PDF
2.   ገረ ሥላሴን ለማብራራትና ለዓለም ሁሉ ለመግለጥ፦ ትምህርተ ሥላሴ በመጽሐፍ ቅዱስ በምልዐት የተብራራ ትምህርት ነው፡፡ በተለይም ትምህርቱ በግልጥ የተሰበከው፤ በጉልህ የታየውና የተረዳው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሲሐዊ መገለጥ[በጥምቀቱ] ጊዜ ነው፡፡

Wednesday, 18 January 2017

ጌታ ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ? (ክፍል አንድ)

    ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመሲሕነቱን አገልግሎት በግልጥ የጀመረው በጥምቀቱ ዋዜማ ነው፤ በነቢዩ ኢሳይያስ አንደበት መሲሑ እንደተነገረው፥ “የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ፡፡ ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና” (ኢሳ.40፥3-5) ተብሎ የተነገረው ትንቢት በተፈጸመ ማግስት ነው፡፡