መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ብቻ መናገር አስተዋይነት፤ ያልተናገረውን ደግሞ አለመጨመር ፍጹም ታማኝነት ነው። እኛ ሰውን ደስ ለማሰኘት የተናገርነው “እውነት”፣ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ያልተናገረው ሐሰት ሊኾን የሚችልበት አንዳች ሚዛን የለም፤ የእውነት እውነተኛው ሚዛን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ከኾነ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ያልተናገረውና ያላለው ኹሉ ሐሰት፣ እርሱ የተናገረውና በእርሱ ያለው ብቻ እውነት ነው። ሚዛንን ስቶ ሚዛናዊ መኾን ፈጽሞ አይቻልምና።
Showing posts with label መረጃና ተግሳጽ. Show all posts
Showing posts with label መረጃና ተግሳጽ. Show all posts
Saturday, 15 August 2020
Tuesday, 4 August 2020
ክርስቲያኖች ወደ ቄሳር ሲጠጉ እፈራለሁ!
ለምንኖረው ሕይወትና ለማናቸውም የክርስትናችን የኑሮ ዘይቤ፣ ማዕከሉ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ያልተኖረ የሕይወት አብነት የለንም፤ የተኖረና በድል የተጠናቀቀ የሕይወት አብነት ግን አለን፤ እርሱም የክርስቶስ። ክርስቶስ ያልኖረውን ሕይወት ኑሩ አላለንም፤ “ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤” (ማቴ. 11፥28) ያለን ጌታ፣ “ፍለጋውን እንድንከተል ምሳሌ ትቶልናል” (1ጴጥ. 2፥21) ስለዚህ የማይጨበጥ፣ በንግግር ብቻ የሚተረክ፣ በተመስጦአዊ ስብከቶች የሚሰበክ ብቻ ያይደለ፤ የሚኖር፣ የሚሻተት፣ የሚቀመስ፣ የሚጣጣም ቅዱስ ሕይወትን ሰጥቶናል።
Thursday, 21 May 2020
የሐሰት መምህራን የማይነኳቸው ርእሶች (ክፍል ፭)
Please read in PDF
ከዚህ ቀደም የስህተት መምህራን የማይነኳቸውን ሦስት ርዕሶችን
ማለትም ኀጢአትን፣ ንስሐን፣ የእግዚአብሔርን ፍርድና ቊጣ መመልከታችን ይታወሳል፤ ዛሬ ደግሞ
ቀጣዩን ርእስ እንመለከታለን።
4. ስለ ቅድስና፦ ቅድስና በብሉይም ኾነ በአዲስ ኪዳን ውስጥ እጅግ የከበረ ዐሳብ ነው። በብሉይ ኪዳን በተለይም ከሕጉ መሰጠት በኋላ፣ ከቅድስና ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጠንካራው ቁልፍ ቃል፣ “ቅድስና ለእግዚአብሔር” የሚለው ነው። ይህም በጥሩ ወርቅ በተሠራው አክሊል ላይ፣ እንደ ማኅተም ቅርጽ ተሠርቶ፣ ኹሉም ሰው ሊያየው በሚችል መልኩ፣ በራሱ ላይ አክሊሉን ይደፋዋል፤ (ዘጸ. 39፥30)። በማኅተም ቅርጽ ያለውን “ቅድስና ለእግዚአብሔር” የሚለውን ጽሕፈት ማንም ይሸሽገው ዘንድ አይችልም። ከእግዚአብሔር ጋር በመኾን፣ የተካፈልነውን ቅድስና እኛ ራሳችን እንኳ መሸሸግ አንችልም፤ ልክ ሙሴ የፊቱን ብርሃን መሸፈን እንዳልቻለው፤ (ዘጸ. 34፥29)።

Sunday, 17 May 2020
የኅዳር በሽታ፤ ኮሮና፤ ዝሙት!
ከ50 ሚሊየን በላይ ሕዝብ
የቀጠፈው፣ ዓለም ዓቀፉ ብሪትሽ
ፍሉ፣ በአገራችን ሲከሰት "የኅዳር በሽታ" መባሉንና የመጣበት ምክንያትም "ዘማዊ በምድሪቱ
ስለ በዛ ነው"፣
ተብሎ ይታመን እንደ ነበር ስንቶች
ሰምተን ይኾን? [በእርግጥ በአገራችን አንድ ጥፋት
ሲከሰት፣ ወዲያው ከመቅሰፍትና ከመዓት ጋር ማያያዙ የተለመደ ቢሆንም፣ በዚያ ዘመን
ዝሙት የተስፋፋ መኾኑን በሚገባ ያሳብቃል]። እግዚአብሔር ግን ምሕረቱ
ብዙም፤ ለዘላለምም ነው!
የሐሰት መምህራን የማይነኳቸው ርእሶች (ክፍል ፬)
Please read in PDF
3. የእግዚአብሔርን ቊጣና ፍርድ አይናገሩም፦ ዓይን ያወጡ ሃሳውያን አገልጋዮች ብቻ ሳይኾኑ፣
በአከባቢያችን ያሉ አንዳንድ ለቀቅተኛ እንኳ፣ “የእግዚአብሔርን ፍቅር ብቻ ማውራት አይበቃምን?” ሲሉ፣ በተደጋጋሚ እንሰማቸዋለን።
ነገር ግን ከተነገረውና በግልጥ ከተቀመጠው ከእግዚአብሔር ዐሳብ መራቅ አደጋ አለው፤ ደግሞም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነተኛነትና
አይሻሬነትን ማቃለል
ነው።
Wednesday, 13 May 2020
የሐሰት መምህራን የማይነኳቸው ርእሶች (ክፍል ፫)
Please read in PDf
2. ንስሐ፦ የስህተት መምህራን የማይነኩትና የማይደፍሩት ሌላው ርእስ ቢኖር ንስሐ ነው። ከእግዚአብሔር ለተለየው ዓለምም፤ በቤቱ ኖሮ ለሚበድለው አማኝም ንስሐ ዕለታዊ ተግባር ነው። በብሉይ ኪዳን ዐሳብ የአንድን ሰው ከኀጢአት ወደ እግዚአብሔር መመለስን የሚያመለክት ሲኾን (ኢሳ. 9፥13፤ ኤር. 4፥22፤ 5፥3፤ 26፥3፤ ሆሴ. 5፥4፤ 7፥10)፤ የአዲስ ኪዳን ምንባባት ደግሞ ኹለንተናዊ መመለስን የሚያመለክቱ ናቸው፤ ለምሳሌም፦ የነነዌ ሰዎች ኹለንተናዊ በኾነ ዝንባሌአቸው ንስሐ መግባታቸውን፣ “በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፥” በማለት ጌታ ኢየሱስ ተናገረ (ዮና. 3፥5-9፤ ማቴ. 12፥41)፣ ነነዌ ዮናስን ከተቀበለች፣ አይሁድም ከዮናስ የሚበልጠውን ጌታ አምነው ሊቀበሉ ይገባ ነበርና።

Friday, 8 May 2020
የሐሰት መምህራን የማይነኳቸው ርእሶች (ክፍል ፪)
Please read in PDf
·
ኀጢአት፦ በስህተት መምህራን ዘንድ ትርጉማቸው ከተበላሹ ወይም እንደ ገና ከተተረጐሙት መካከል፣ ኀጢአት
አንዱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ኀጢአትን በማያሻማ ትርጉም፣ “የአንድ ሰው አለመታዘዝ” (ዘፍ. 3፥17፤ ሮሜ 5፥12፡ 15፡ 18፡
19)፣ ከእግዚአብሔር ክብር መጉደል ወይም እግዚአብሔር ወዳሰበልን እውነተኛ ግብና ክብር አለመድረስ (ሮሜ 3፥23)፣ በራስ መንገድና
ዝንባሌ መሄድ (ኢሳ. 53፥6)፣ ማመጽ (1ዮሐ. 3፥4) የሚሉና በሌሎችም ትርጉሞች በግልጥ ተርጉሞት እንመለከታለን።
Sunday, 3 May 2020
የሐሰት መምህራን የማይነኳቸው ርእሶች (ክፍል ፩)
Please read in PDF
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ቅዱሳን ደቀ መዛሙርት፣ ከእነርሱ መሄድ በኋላ ሐሰተኛ መምህራን ሊመጡ እንዳላቸው በግልጥ ተናግረዋል። የሐሰት መምህራን ሁል ጊዜ የእውነተኛ ደቀ መዛሙርት አለመኖርን ይመኛሉ ወይም የእውነተኛ ደቀ መዛሙርትን ቸለተኝነት እንደ መግቢያ በር ይጠቀሙበታል። ስለዚህም ሁልጊዜ ባለመታከት አንገታቸውን ከማስገግ አያርፉም። አሳቻ ቦታ ቆመው ምቹ ጊዜ እንዲመጣላቸው ተግተው ይጠብቃሉ።

Friday, 24 April 2020
ቅንነት ጥሎ፤ ዘፈን አንጠልጥሎ!
Please read in PDF
ተኩላው
ወደ በጐች ጐረኖ መሰስ ብሎ ሲገባ፣ ዝም ማለት ወይም ባላየ ማለፍ “ተለመደ”፤ የእግዚአብሔርን ምሕረት አስታክኮ፣ ኀጢአትን “ምን
አለበት?” እያሉ ማላመድ የለቀቅተኛ ነገረ መለኮታዊያንና በሰልን ባይ አማኝና አገልጋዮች መገለጫ ኾነ፤ ኀጢአትን መጠየፍ አጉል
አክራሪነት ተባለ፤ ኀጢአተኝነትን መካድና መቃወም ተቃዋሚነትና ከሳሽነት ተብሎ ተፈረጀ፤ ግብረ ሰዶማዊው አገልጋይ ሲሰብክ፣ “መጀመሪያ
ንስሐ ግባ!” ማለት ግብዝነትና ማካበድ ኾነ፤ በተቃራኒው ደግሞ ዘፋኝነት ከመዝሙርነት ሲጣባ መንፈሳዊ ግልጋሎት፣ ኢየሱስን የሚጋርድ
ተግባር ትክክል፣ የተሰቀለውን ክርስቶስ የሚሸቅጥ ተግባርና ዐሳብን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማድረግ ጥቅሶችን ማስጨነቅ ተወደደ፤ ተኩላውን
ከመንጋው ማላመድ “ካውንስል” ተብሎ ተሞገሰ፤ ኢየሱስ ሳይኾን ቡድንና አገልጋይ ነኝ ባይ በሰው ልብ ገነነ፤ ለቀቅተኞች ቤተ ክርስቲያንን
ንብ የማር ቀፎን እንደሚከብብ ከበቡአት።
Thursday, 9 April 2020
የ“ዲያቆን” አሸናፊ መኮንን፣ አዲሱ ድርሳነ ማርያም (ክፍል ፪ እና የመጨረሻ)
Please read in PDF
የወንጌሉን ዓላማ በመሳት፣ በአሸናፊ የተተረጐሙ “ትርጓሜያት”
1. የሰርጉ ተቀዳሚ ዓላማ “የእመቤታችንን የድንግል ማርያምን የእምነት ጸሎት ለማብራራት ነው”[1] የሚለው፣ የዮሐንስ ወንጌል ተቃራኒ ዐሳብ ነው። “ዲያቆን” አሸናፊ፣ እመቤታችን የጸለየችው ጸሎት ተራ ጸሎት አይደለም ቢልም፣ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ኹለት ውስጥ ጸሎት መኖሩን አናነብም ወይም ወንጌላዊው ዮሐንስ፣ ቅድስት ማርያም ጸሎትን መጸለይዋን አልጻፈልንም። ይህን ለማለት አስግጎ ወይም ወደ ቃሉ በማሰገባት የተረጐመው ክፍል፣ “የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፦ የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው።” የሚለውን አንቀጽ ነው፤ (2፥3)።[2] ጸሎት ነው ከማለት ባለፈ፣ አስደናቂ ልመና፣ የቃና ዘገሊላው ጸሎት፣ የድንግል ጸሎት እያለ ሲያሞጋግሰው እናስተውላለን። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ጸሎት ያለውን አንቀጽ፣ “እንደ ፈቃዱም የቀረበ፣ የጌታን ልብ ያወቀ ጸሎት” በማለትም ያሞካሸዋል።

የ“ዲያቆን” አሸናፊ መኮንን፣ አዲሱ ድርሳነ ማርያም (ክፍል ፩)
Please read in PDF
መግቢያ
“ዲያቆን” አሸናፊ መኮንን፣ የዮሐንስ ወንጌልን እያንዳንዱን ምዕራፍ በመተርጐም፣ የዮሐንስ ወንጌልን ምዕራፍ ኹለትን፣ ኹለተኛ መጽሐፍ በማድረግ አቅርቦታል፤ ለምዕራፍ ኹለቱ መጽሐፍ፣ የሰጠው ርእስ “ቃና ዘገሊላ” የሚል ሲኾን፣ መጽሐፉ 252 ገጻት፣ አሥራ አምስት ክፍሎች[ምዕራፍ ሳይኾን] አሉት። መጽሐፉ የተጻፈው የዮሐንስ ወንጌልን ማዕከል በማድረግና “የለዘብተኞችን ንቅናቄ አራማጆችን ትምህርታቸውን እየነቀፈ” መተርጐምና ትችትን ማቅረብ እንደ ኾነ ጠቅሶአል፤ በተጨማሪም መጽሐፉ ራሱ የተወለደው፣ ከዮሐንስ ወንጌል ጥልቅ ምስጢር እንደ ኾነም ጭምር በድፍረት በመናገር።1

Monday, 30 March 2020
የገነነ ምሕረት!
በምድራችን ላይ እጅግ አያሌ ተላላፊ በሽታዎች ተነስተዋል፤ እስካሁን ግን ከ1918 እስከ 1919 ዓመተ እግዚእ፣ የዓለማችንን 50 ሚሊየን ሕዝብ ቅርጥፍ አድርጎ የበላ፤ እንደ ቅጠልም ያረገፈ፤ በH1N1 Virus መነሻነት የተነሳውና “Spanish flu” በመባል እንደሚታወቀው መረርሽኝ ያህል የተነሣ የለም፡፡ በጊዜው የዓለማችን አንድ ሦስተኛው የሚያህለው ማለትም፣ 500 ሚሊየን ሕዝብ ገደማ በቫይረሱ ተጠቅቶ ነበር፤ ከዚህ ቁጥር ውስጥ ደግሞ 50 ሚሊየን ገደማ ሕዝብ ሞቶ ነበር፤ የዚያኔ በአሜሪካ ብቻ 675 ሺህ ሕዝብ ያህል አልቆባት ነበር፡፡
Friday, 27 March 2020
በቫይረሱ ብንያዝስ?

በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ ወይም ተይዣለው ብለው ከጠርጠሩ ምን ማድረግ ይችላሉ ?
ሳል፣ ትኩሳት፣ ትንፋሽ ማጠር እና ተያያዝ ምልክቶች በራስዎ ላይ ከተመለከቱና በኮቪድ-19 እንደተጠቃ ከሚጠረጥሩት ወይም ከተረጋገጠ ሰው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ከነበርዎት ወይም በኮቪድ19 ወደተጠቁ አገራት/አካባቢዎች ተጉዘው ከነበረ ምን ማድረግ አለብዎት?
Monday, 23 March 2020
ስለ ተላላፊ በሽታ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
Please read in PDF
መግቢያ
ጌታችን ኢየሱስ መድኀኒት አስፈላጊነቱ ለበሽተኞች መኾኑን ተናገረ (ማቴ.
9፥12)፤ ስለዚህም ሰዎች ከበሽታ ለመዳን መድኀኒትን መጠቀማቸውን እናስተውላለን፤ “በጥንት ዘመን ሰዎች በመድኃኒት ሲያምኑ
በነፍስ ሊበረቱ ይችላሉ። ጥቅሙ ከእምነት እንጂ ከመድኃኒት አልነበረም። ዛሬ ግን ብዙ ጊዜ በመድኃኒት ቢያምኑም ባያምኑም
መድኃኒቱ ፍቱን ነውና ይሠራል”። ከፊት ዘመን ይልቅ በዛሬ ዘመን ሰዎች በመድኃኒት አብዝተው የሚታመኑ ይመስላል፤ ለዚህም
ይመስላል በምድራችን ላይ እጅግ ዝቅተኛ ከሚባሉት እስከ ቅንጡ መታከሚያ ቤቶች የተበራከቱት። ነገር ግን ይህ ኹሌ ስሙርና የመጨረሻ
መፍትሔ ኾኖ አይታይም።
Wednesday, 18 March 2020
ተጽናኑ፤ አጽናኑም!
Please read in PDF
አዲስ ኪዳን በአጭር ቃል፣ ከሥጋ ሕመምና ሞት፤ ከበሽታም ይልቅ ከእግዚአብሔር
አባትነት መለየትና መነጠልን የዘላለም ሞትና ፍርድ እንደሚያስከትል ያስተምራል። የሥጋ ሕመምና ሞት በአዲስ ኪዳን ትምህርት፣ ጊዜያዊና
ሰው የመኾናችን ውጤት መኾኑን ብቻ የሚያመለክትም ነው። ከዚህ ባሻገር ሰዎች ባለመታዘዝ በጸኑ ልክ፣ ለኀጢአት፣ ለዓመጻና
ለማይረባ አእምሮ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ።
Friday, 4 October 2019
እሬቻን የማላከብርበት ክርስቲያናዊ ምክንያቴ
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ “የፖለቲካው ጡዘት አገራዊ መልኩን በመልቀቁ፣ ብሔርና ሃይማኖት ተደጋፊ” ከመኾን ጋር ተያይዞ፣
የበአላትን ፉክክር ሃይማኖታዊ መልክ ሲያለብሱ እየተመለከትን ነው። ይህ ደግሞ ውል አልባ የኾነ መጠዛጠዝንና መገፋፋትን፣ “እኔ
እበልጥ እኔ እበልጥ!” የሚል ሥጋዊ መቀናናትን ሲያስከትልና ትውልድ የሚመርዙ ተግባራት “ሃይ ባይ” ማጣታቸውንም እንድንመለከት
አድርጎናል። ልክ እንደ ዘመነ መሣፍንት፣ “በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፤ ሰውም ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ
የታየውን ያደርግ ነበር።” (መሣ. 16፥7) ተብሎ እንደ ተነገረው፣ የትኛውም ሰውና ብሔር መልካም መስሎ የታየውን ከማድረግ
ከልካይ የሌለበትና እግዚአብሔር የተገፋበት የተናቀበት ዘመን ላይ ነን።
Monday, 2 September 2019
ሐዋ. 2 ላይ የብሔርተኞቹ ሸቃጭነት!
በቃሉ ውስጥ
ባዕድ ዐሳብ ቀላቅሎ ማቅረብና መሸቀጥ ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የማይታዘዙ ሰዎች ኹነኛ መገለጫ ነው (2ቆሮ. 2፥17፤ 4፥2)፤
ከሰሞኑ የተነሡት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም፣ ዝቅ ብለውና ወርደው “በክልል ደረጃ፣ በአንድ ብሔር
ስም” ክርስትናን “እንመስርት” ባዮቹ አካላት፣ እጅግ ድፍረት በተሞላበት ንግግር መጽሐፍ ቅዱስን ጠቅሰው፣ ይህን እኩይና እቡይ
ድርጊታቸውን እንደሚደግፋቸው ሲጠቅሱ ሰምተናቸዋል፤ በቋንቋና በብሔር ክርስትናን ለመደራጀት እንደሚፈቅድላቸው ከጠቀሱት ጥቅስ
አንዱ ደግሞ የሐዋርያት ሥራ ኹለትን ነው።
Friday, 30 August 2019
የቄሳር ተላላኪ “ቀሳውስት” - ሠርግና ምላሽ
ቤተ ክርስቲያን ከመንግሥት ጋር “ተቃራኒ” በነበረችባቸው ዘመናት፣ ማለትም
ነገሥታት ጸረ ክርስትና አቋም ይዘው ተነሥተው በነበሩባቸው ዘመናት፣ ቤተ ክርስቲያን ከሩቅ የሚታይ አብረቅራቂ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋን
ተጐናጽፋ ነበር፤ ከአንድ መቶ ሃምሳ ዓመታት በላይ ከኔሮን ቄሣር እስከ ዲዮቅልጥያኖስ የዘለቀው ጽኑ የመከራ ዘመን ቤተ ክርስቲያን
እንደ ቦኸር በዐለት ላይ ተከላት እንጂ፣ ፈጽሞ ካመነችው እውነትና ከመንፈስ አንድነቷ አላነወጣትም፤ አልከፋፈላትም፡፡ መከራ ማጥሪያዋ
ብቻ ሳይኾን መጽናኛዋም ጭምር ነበር፡፡
Saturday, 3 August 2019
የእምነት እንቅስቃሴ አማኞች መጽሐፍ ቅዱስን በዐውድ አያውቁትም!
Please read in PDF
ዐውድ አንድን
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለመረዳት ወሳኝ ነው፤ ዐውድን አለመረዳት ጠቅላላ የመጽሐፉን ዐሳብ አለመረዳት ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ቀድሞ
የተናገረውን ያብራራልናል ይገልጥልናል እንጂ፣ አዲስ መገለጥም ኾነ ኢየሱስ ከተናገረው የተለየ የሚነግረን ምንም ነገር የለውም፤
ይህም በዐውድ ውስጥ ልንረዳው እንችላለን ማለት ነው፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ቀጥሎ፣ ዐውድ የቀደመው መልእክት ለዝንተ ዓለም ዘመን ዘለቅ
ኾኖ እንዲሻገር ኹነኛ አጥር ነው ማለት እንችላለን፡፡
Monday, 22 July 2019
ከክርስቶስ ይልቅ “ቄሣርን” አወዳሽ “ነቢያት”! (የመጨረሻ ክፍል)
Please read in PDF
“ወንጌላውያን” ነቢያትና ቤተ
መንግሥታዊ ማስታወቂያነታቸው
“ወንጌላውያን” ነቢያትና ጥቂት የማይባሉ ኦርቶዶክሳውያን አገልጋዮችም
ጭምር ቤተ መንግሥቱ በሕዝብ ዘንድ ዕውቅና ያገኝ ዘንድ ተግተው “እያገለገሉ” ይመስላል፤ ለዚህም ለምሳሌ፦ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ
መወቀስ አይገባቸውም እስከሚለው ጥግ የሄዱ አገልጋዮችን አይተናል፤ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያን ከቤተ መንግሥት ባነሰ ማንነት
መኖሯን ራሳቸውን ጭምር በመስደብ ያቀረቡትን ሰምተናቸዋል። ለዚህም ለከት አልባ በኾነ መንገድ ግልጥ ፖለቲካዊ ቃላትን በመጠቀም
ሲወርዱ ተመልክተናቸዋል።
ለምሳሌ፦
- “አርበኝነት
በደሙ የተዋሐደው” ኢትዮጲያዊነት፣
- ሃያ
ሰባት ዓመታት መብታችን ተጥሶ … ፣
- የኢትዮጵያ
… የጠላቶቿ ድንጋይ አቀባዮች (የማርሲሉ ዮናታን አክሊሉ)፣
- ኢትዮጵያን
እግዚአብሔር በቃል ኪዳን ጠብቆአታል፣
Subscribe to:
Posts (Atom)