ጽዮን በባቢሎን ምርኰ በተያዘችና ለሰባ ዓመታት ያህል በግዞት በዘገየች ጊዜ የተረሳችና የተተወች መሰላት፤ በተለይም
የመቅደሱ መፍረስና ከቅድስቲቱ ምድር ሙሉ ለሙሉ መነቀላቸው ተስፋቸውን ይበልጥ አጨለመው። እግዚአብሔር ግን ሕዝቡ ተስፋ እንዲቈርጥ
አይፈልግም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ታማኝ፤ ጽኑ ፍቅር፤ የማያቋርጥ ኪዳናዊ ቊርኝት ያለው፤ ጨርሶ ሊዘነጋ የማይችል
ልብ አለውና። ይህን እውነት እግዚአብሔር በበደልና በኀጢአት ለወደቀችው ለጽዮን፣ በነቢዩ አንደበት በግልጥ ይናገራል፤ እንዲህ
በማለት፣
“ጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ጌታም ረስቶኛል አለች። በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ
ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም። እነሆ፥ እኔ በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለሁ፥
ቅጥሮችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ።” (ኢሳ. 49፥14-15)


.jpg)