1. አትናናቁ፦በማንኛውም የኑሮ ዘይቤ የሚኖሩ ሰዎችን ስታከብሩ፣ ሠሪያቸውን ወይም የፈጠራቸውን ያህዌ ኤሎሂምን ነው የምታከብሩት። እግዚአብሔር ሰውን ወደዚህ ምድር ሲያመጣው በትልቅ ዓላማና ለክብሩ መገለጫ ይኾን ዘንድ ነው። እኛ እንደ ሳይንቲስቶች ወይም እንደዚህ ምድር ጠቢባን በፈጠረው ዓለምና ሰው እጅግ በመደነቅና በመመሰጥ የምንዋጥና በዚህ ብቻ የምንቀር አይደለንም፤ ይልቁንም እግዚአብሔር ዓለምንና ሰውን የፈጠረው ያህዌ ኤሎሂም ከሰው ጋር ግላዊና ኅብረታዊ ግንኙነትን ሊመሠርት እንዳለው እናምናለን።
Showing posts with label ትምህርት. Show all posts
Showing posts with label ትምህርት. Show all posts
Thursday, 6 February 2020
Wednesday, 5 February 2020
ንቀት (ክፍል ፱)
ጌታችን ኢየሱስ ፍጹም ተንቆአል!
በአንድ ወቅት በክርስቶስ ኢየሱስ ጉዳይ በአይሁድ ሸንጐና ሕዝብ ክርክር መደረጉን፤
በመካከላቸው መለያየት በተደጋጋሚ መከሰቱንም የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ይነግረናል፤ (7፥43፤ 9፥16፤ 10፥19)።ለዚህ ምላሽ እንዲኾንም የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን ለማስያዝ
ያደረጓቸው ተግባራት ለኢየሱስ የነበራቸውን ንቀት ፍንትው አድርጐ ያሳያል። ዮሐንስ ይህን በሚገባ ይገልጠዋል፤ አስቀድሞ እነርሱ
ከሚያከብሩአቸው ሰዎች ታላላቅ ሰዎችን በመላክ ለኢየሱስ ያላቸውን አክብሮት ቢያሳዩም፣ በኋላ ላይ ግልጹ ዐሳባቸው ታውቆአል፤ ይኸውም
ለኢየሱስ ያላቸውን ንቀት ለማሳየት ጠባቂዎችንና ዝቅተኛ ሥልጣን ያላቸውን ሰዎች ልከዋል፤ ነገር ግን ከፊተኞቹ የኒቆዲሞስ ማመን
ከኋለኞቹም ጠባቂዎች “እንደዚህ ሰው ማንም እንዲሁ ከቶ አልተናገረም” የሚል ምስክርነት መገኘቱ እጅግ የሚደንቅ ነው፤ (ዮሐ. 7፥45-52)።
Sunday, 2 February 2020
ንቀት (ክፍል ፰)
Please read in PDF
1.
በአገራችን አስተዳደጋችን ምንታዌነት አለው፦
በመጀመሪያቱ ቤተ ክርስቲያን ቤተሰቦች ውስጥ የነበሩት ባሪያዎች፣
አንዳንዶቹ በጌታ ኢየሱስ ያመኑ ነበሩ፤ ስለዚህም እኒህን
ባሪያዎች እንደ ወንድሞቻቸው እንጂ እንደ ቤት አገልጋዮቻቸው እንኳ አይመለከቱአቸውም ነበር፤ ነገር ግን እኒህ ባሪያዎች
በተቃራኒው ጌቶቻቸውን መናቅ ጀመሩ፤ የክርስትናው ነጻነት ይበልጥ ሊያከብሩአቸውና ሊሠሩላቸው እንዲገባ ማዘዙን ዘነጉት፣ እነርሱ
ግን በተቃራኒው አደረጉ። አንድ አገልጋይ በግዴታ ያገለግል በነበረበት ወራት ይሠራ የነበረውን ሥራ ኹሉ፣ አኹን ግን በፍቅር
መሥራት ተሳነው። ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ፦
“የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለሆኑ አይናቁአቸው፥ ነገር ግን በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የሚያምኑና የተወደዱ
ስለሆኑ፥ ከፊት ይልቅ ያገልግሉ።” (1ጢሞ. 6፥2)
Wednesday, 22 January 2020
ንቀት (ክፍል ፯)
ለምን ግን እንናናቃለን?
አንዳንዶች
በመልካቸው ብቻ ይናቃሉ፤ ለምሳሌ፦ በዓረብ ማኅበረ ሰብ ውስጥ ያሉ ጥቁር ዓረቦች፣ ጥቁር ስለኾኑ ብቻ የተናቁ እንደ ኾኑ
ይናገራሉ፤[1]
አንዳንድ “ቤተ እምነቶች” ንቀትን የማበረታታት ትምህርቶች አላቸው፤ ለምሳሌ፦ ከእነርሱ ቤተ እምነት ውጪ ያሉትን ወይም የቤተ
እምነታቸውን ቀኖናና ዶግማ የማይቀበሉትን ማናቸውንም ቤተ እምነቶች መናቅ እንደሚገባቸው ያምናሉ፤ ልክ አብዛኛዎቹ የፕሮቴስታንት
አብያተ ክርስቲያናት ወይም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አንዳቸው ሌላውን እንደሚንቁ። እንዲያውም እንደ እስልምና[2]፣
ጅሖቫ፣ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት፣ የእምነት ቃል አገልግሎት፣ ሞርሞንና ተመሳሳይ “ቤተ እምነቶች”፣ ማንኛውም ሰው የእነርሱን
ቤተ እምነት ቀኖናና ዶግማ ካልተቀበለና ከእነርሱ ውጭ ካለው ማናቸውም ኅብረት ጋር፣ ኅብረት ቢያደርግ “ከርኩሱ ዓለም ጋር
ግንኙነት እንዳደረገ ወይም እንደ ተካፈለ” አጥብቀው ያስተምራሉ።
Tuesday, 31 December 2019
ንቀት (ክፍል ፮)
Please read in PDF
ሌሎችን በመናቃቸው ምክንያት የወደቁ ሰዎች
መጽሐፍ ቅዱስ አያሌዎች ሌላውን በመናቃቸው ምክንያት መውደቃቸውንና
መንኮታኮታቸውን በግልጥ ያስተምረናል፤ በዓለም ላይ ከተከናወኑ ጥቂት ያይደሉ ታሪኮች ውስጥ እንኳ፣ ገናና የተባሉትንና ያልተጠበቁትን ሲያዋርድ ተመልክተናል፤ አንብበናል። በተለይም “ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት
በጽድቅም ላለው ምክር” የተጻፈልን ሕያው የእግዚአብሔር እስትንፋስ የኾነው መጽሐፍ ቅዱስ፣ በንቀታቸው ምክንያት ስለወደቁት ሰዎች
እንዲህ ያስተምረናል፦
1.
የጎልያድ ንቀት
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጎልያድ የጦር ትጥቅ እንዲህ በማለት ይናገራል፤ “… የጌት ሰው ጎልያድ፥ ቁመቱም ስድስት
ክንድ ከስንዝር የሆነ፥ ዋነኛ ጀግና መጣ። በራሱም የናስ ቍር ደፍቶ ነበር፥ ጥሩርም ለብሶ ነበር፤ የጥሩሩም ሚዛን አምስት ሺህ
ሰቅል ናስ ነበረ። በእግሮቹም ላይ የናስ ገምባሌ ነበረ፥ የናስም ጭሬ በትከሻው ላይ ነበረ። የጦሩም የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅልያ
ነበረ፤ የጦሩም ሚዛን ስድስት መቶ ሰቅል ብረት ነበረ።” ጎልያድ እንዲህ ያለ አለባበስ በመልበሱና የውጊያ ትጥቅን በመታጠቁ፣ ከፍልስጥኤማውያን
ኹሉ አንደኛ አድርጎታል፤ በዚህ ሳይበቃ እስራኤልንና ንጉሡ ሳኦልንም ጭምር በማንቀጥቀጡ የሚደርስበት ፈጽሞ አልተገኘም።
Thursday, 12 December 2019
Tuesday, 3 December 2019
ንቀት (ክፍል ፬)
Please read in PDF
የአይሁድና የሳምራውያን መናናቅ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር በመጣበት ጊዜ የአይሁድና
የሳምራውያንን ኹኔታ ወንጌላዊው ዮሐንስ እንዲህ በማለት ይገልጠዋል፤ “አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና።” (ዮሐ. 4፥9)።
በጥንት ታሪክ ሳምራውያን ከአይሁድ ጋር አንድ ነበሩ፤ ነገር ግን ከአሦር ምርኮ በኋላ፣
“የአሦርም ንጉሥ ከባቢሎንና ከኩታ ከአዋና ከሐማት ከሴፈርዋይም ሰዎችን አመጣ፥ በእስራኤልም ልጆች ፋንታ በሰማርያ ከተሞች አኖራቸው፤ ሰማርያንም ወረሱአት፤ በከተሞችዋም ተቀመጡ። በዚያም መቀመጥ በጀመሩ ጊዜ እግዚአብሔርን አይፈሩትም ነበር፤ እግዚአብሔርም አንበሶች ሰደደባቸው፥ ይገድሉአቸውም ነበር። ስለዚህም ለአሦር ንጉሥ። ያፈለስኻቸው፥ በሰማርያም ከተሞች ያኖርኻቸው የአገሩን አምላክ ወግ አላወቁም፤ የአገሩን አምላክ ወግ አላወቁምና አንበሶችን ሰድዶባቸዋል፥ እነሆም፥ ገደሉአቸው ብለው ተናገሩት። የአሦርም ንጉሥ። ከዚያ ካመጣችኋቸው ካህናት አንዱን ውሰዱ፤ ሄዶም በዚያ ይቀመጥ፥ የአገሩንም አምላክ ወግ ያስተምራቸው ብሎ አዘዘ። ከሰማርያም ካፈለሱአቸው ካህናት አንዱ መጥቶ በቤቴል ተቀመጠ፥ እግዚአብሔርንም እንዴት እንዲፈሩት ያስተምራቸው ነበር። በየሕዝባቸውም አምላካቸውን አደረጉ፥ ሰምራውያንም በሠሩት በኮረብታው መስገጃዎች ሕዝቡ ሁሉ በሚኖሩበት ከተሞቻቸው አኖሩአቸው። … ከመካከላቸውም ለኮረብታው መስገጃዎች ካህናት አደረጉ፥ በኮረብታውም መስገጃዎች ይሠዉ ነበር። እግዚአብሔርንም ሲፈሩ ከመካከላቸው እንደ ፈለሱት እንደ አሕዛብ ልማድ አምላካቸውን ያመልኩ ነበር። እስከ ዛሬ ድረስ እንደ ቀደመው ልማድ ያደርጋሉ፤ እግዚአብሔርንም አይፈሩም፥ እግዚአብሔርም እስራኤል ብሎ የጠራውን የያዕቆብን ልጆች እንዳዘዛቸው ሥርዓትና ፍርድ ሕግና ትእዛዝም አያደርጉም። ” (2ነገ. 17፥22-29፤
33-34)።
Wednesday, 20 November 2019
ንቀት (ክፍል ፫)
Please read in PDF
ጌታ ኢየሱስ ማንንም አልናቀም!
“… በተስፋ የተጠበቀው መሲሕ ሌላ ዐይነት ክብር፣ ማለትም የትሕትናን
ክብር ለብሶ ነበር በመካከላቸው የተገኘው። አባ ኔቪል ፈጊስ የተባሉ ካህን እንደ ተናገሩት፣ ‘እግዚአብሔር ታላቅ ነው የሚለው
የሙስሊሞች እወጃ እውነትነቱ ጉልህ በመሆኑ ያለልዕለ ተፈጥሮአዊ ህልው እገዛ ሰው ሊረዳው ይችላል። እግዚአብሔር ትንሽ ነው
የሚለውን ግን ኢየሱስ ለሰው ልጆች ያስተማራቸው እውነት ነው።’ …”[1]
ጌታ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበት መንገድ እጅግ አስደናቂና ልብን
በመደነቅ የሚመላ ነው። የመጣበት መንገዱና ዓላማው ለብዙዎች የሚጥምና የሚጣፍጥ አይደለም፤ በአዲስ ኪዳንም አገላለጥ ጠባብ
መንገድ፣ የግመል መርፌ ቀዳዳ ታህል፣ እስከ መስቀል ሞት መታዘዝ፣ የራስ ክብርንና መብትን መተው፣ ባልንጀራን እንደ ራስ መውደድ … በሚል ውብ ሕይወትና ዝንባሌዎች
የተመላ ነው።
Wednesday, 13 November 2019
ንቀት (ክፍል ፪)
Please read in PDF
እግዚአብሔር አይንቅም!
እግዚአብሔር
አምላክ በክብር የተከበበና በፍቅር የተትረፈረፈ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር ፍጥረትንም ሲፈጥረው በድንቅና በግሩም ክብር ነው፤ “ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።” (መዝ. 139፥14) እንዲል፣ ሰው በግሩም፤ በድንቅ አድናቆት ተመልቶ የተፈጠረ ነው። መዝሙረኛው እንዲህ
ሲል የፈጠርከውን ሰው የምታውቀው አንተ ነህ፤ እኔንም የፈጠርኸኝ አንተ ነህና በሚገባ ታውቀኛለህ፤ ምክንያቱም በእናቴ ማኅፀን ያበጃጀኸኝና
በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ ንቁ ኾነህ የተንከባከብኸኝ አንተ ነህ እያለ ነው፣ ያህዌ ኤሎሂምን!
Monday, 4 November 2019
ንቀት (ክፍል ፩)
Please read in PDF
መግቢያ
ቅዱስ ጳውሎስ ዘርዝሮ ካልጨረሳቸው(ገላ.
5፥19-21) እና ተዘርዝረው ከማያልቁት የሥጋ ሥራዎች አንዱ ንቀት ወይም ሰዎችን መናቅ ነው፤ የሥጋ ሥራዎችን እንዘርዝራቸው
ብንል ዳርቻው ኹሉ እንደማይበቃቸው እናውቃለን፤ ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀሉ ኃይል እኒህንና ሌሎችንም ኃይላት ደካማ
በሚመስል መንገድ ሰብሮና በመስቀሉ ጠርቆ አስወግዶአቸዋል። አለቅነት፣ ሥልጣን፣ ኃይል፣ ጌትነት ኹሉ በክርስቶስ ጌትነትና ኃይል
ተሽሮአል፤ (ኤፌ. 1፥20-21፤ 3፥10፤ ፊልጵ. 2፥9)። ክርስቶስ በመስቀል ሞቱ የተወደደና ቅዱስ ሕይወት እንኖር ዘንድ
በደሙ ፉጨት ጠርቶናል።
Sunday, 6 October 2019
ሾላኮቹ (የመጨረሻ ክፍል)
Please read in PDF
ምን እንድርግ?
በባለፉት ጊዜያት እጅግ መልካም ነገሮችን በማንሣት በዚህ ርእስ ሥር ስናጠና
ቆይተናል፤ ሾላኮችን ጠባያቸውንና ኹለንተናዊ ባሕርያቸውን አንስተንም ተመልክተናል፤ ከዚህ በመቀጠል ደግሞ እኛ ምን ማድረግ እንደሚገባን
በማንሣት የእግዚአብሔርን ቃል እንጫወታለን።
1.
ወደ ቃሉ
እንመለስ፦ የሾላኮቹ ያላሳለሰ ተግባራቸው እኛን ከቃሉ መነጣጠል ነው፤ ወደ ቃሉ ልንመለስና ዘወር የምንልባቸውን ማናቸውንም
ምክንያቶችና መንገዶችን ጨርሰው ነው የሚዘጉት። ብንመለስ እንኳ ለገዛ ራሳቸው እንዲመች አድርገው ቃሉን ያጣምማሉ እንጂ በትክክል
እንድንመለስ አያደርጉም፤ አይፈልጉምም።
Wednesday, 25 September 2019
Monday, 23 September 2019
ሾላኮቹ (ክፍል ፬)
Please read in PDF
ባለፈው በተመለከትነው ክፍል ሾላኮቹ ማንን ያስታሉ? ብለን በቀዳሚነት
ከቅዱሳት መጻሕፍት ጠቅሰን “እውነትን ማወቅ የማይወዱ
ሞኞች ሴቶችን” እንደሚያስቱ ተመልክተናል፤ ዛሬ ደግሞ የዚኹን ቀጣይ ክፍል እንዲህ እንድታነቡት ጋብዛችኋለሁ፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ፤
አሜን።
2.
አዳዲስ አማኞችን፦ አዳዲስ
አማኞች ለቃለ እግዚአብሔር ጥማት የተጋለጡ ናቸው፤ ከቃለ እግዚአብሔር ጋር የተያያዘ ማናቸውንም ትምህርቶች ለመስማት ይቸኩላሉ።
በተለይም ሾላካ መናፍቃን የሚጠቅሷቸውንና እውነተኛ መምህራን የሚጠቅሷቸውን እውነተኛ ትምህርት ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር በማነጻጸር
የትኛው እውነተኛና የትኛው ደግሞ ሾልኮ እንደ ገባ የመለየትና የማስተዋል እንከን አለባቸው።
Wednesday, 18 September 2019
ሾላኮቹ (ክፍል ፫)
Please read in PDF
በባለፉት ኹለት ክፍሎች የመናፍቃንን የሾላካነት ጠባይ መመልከታችን አይዘነጋም፤ ከዚያ በመቀጠል ዛሬም
እንመለከታለን፤ የጌታ ጸጋና ሰላም ከኹላችሁ ጋር ይኹን፣ አሜን፡፡
4.
ልዩነትን ወይም
እንግዳ ዘርን ለመዝራት፦ ጌታችን ኢየሱስ እንክርዳድ ዘሪው ክፉ፣ ማንም ሳያየው በሌሊት ወይም ጨለማን ለብሶ በመሹለክ
ተግባር እንዳደረገው ነግሮናል፤ ጠላት እንክርዳድ የዘራው በዚያው መልካሙ ዘር በተዘራበት እርሻ ላይ ነው፤ አበቃቀሉም ኹለቱም በአንድነት
በቀሉ፤ የስንዴውም የእንክርዳዱም አበቃቀላቸው ተመሳሳይና አንዱን ከሌላው ለመለየት እጅግ አዳጋች እንደ ኾነ፣ “እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም” (ማቴ. 13፥29) ከሚለው ከጌታችን ኢየሱስ
ንግግር እናስተውላለን።
Tuesday, 27 August 2019
ሾላኮቹ (ክፍል ፪)
Please read in PDF
2.
ለመስረቅ፦ ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጐች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤” በማለት ሲናገር ሾላኮቹ ራሳቸውን በማመሳሰልና በመደበቅ የተካኑ መኾናቸውን
እየነገረንም ጭምር ነው፤ (ዮሐ. 10፥1)። ሌባ በባሕርይው ተደብቆ ወይም ሾልኮ እንጂ በግልጽ መግባትን አያውቅም። ይህንም የሚያደርገው
ተቀዳሚ ዐላማው የእርሱ ያልኾነውን ነገር፣ ለራሱ ጥቅምና ፍላጎት ለመስረቅና ለመውሰድ ነው።
Monday, 12 August 2019
ሾላኮቹ (ክፍል ፩)
Please read in PDF
መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ
ቃል ሐራጥቃ[1] የኾኑ መናፍቃንን
ጠባያቸውን ሊገልጥ በሚችል መንገድ፣ ሾላኮች ወይም ወደ ቤቶች ሾልከው የሚገቡ በማለት ይጠራቸዋል፤ (ገላ. 2፥4፤ 2ጢሞ. 3፥6፤
ይሁ. 4)። ቅዱስ ጳውሎስ ወደ እግዚአብሔር አደባባይና ወደ አማኞች የሚገቡት እንደ ሰላይ ነው ይለናል፤ ጌታችን ኢየሱስ ደግሞ
ከአማኞች ጋር ልዩነት የሌላቸው እስኪመስሉ ድረስ “እንደ ተኩላ” (ማቴ. 7፥15) ነው ይለናል፤ ሰላይ መመሳሰልን ገንዘብ ያደርጋል፤
ተኩላም ኹለ ነገሩ ከበግ ጋር አንድ ዓይነት መኾንን ይመርጣል፤ ይህን ተፈጥሮአዊ ተመሳስሎታቸውን የሚጠቀሙት ግን የሚፈልጉትን ለማግኘት
ወይም በጭካኔያቸው ለመንጠቅና በግን በሕይወቱ ቦጫጭቀው ለመብላት ነው።
Saturday, 20 October 2018
Tuesday, 24 April 2018
Namni nama malee Hafuraa miti! (kutaa 3ffaa)
Please read in PDF
Waaqayyoon “akka bifa keenyaatti, akkaa
fakkaattiis nama ni umna” dubbi jechuu isaa(Uma.1:26-31)
Kutaan kitaaba
Qulqulluu kun namni bineensa lubbuu qabu irraa “haa ta’u, haa ta’u” jedhee Waaqayyon
akka hin uumne agarsiisa. Inumayyuu kabajaafi jaalala guddaan harka isaatiin
kan tolchee, kanas immoo bifa fi fakkaatti isaatiin uumu isaa ni agarra. Waaqayyoon
akkeenya(dhaqna Hafuraa) isaa akka callaqisnu uumama keenya keessatti ibsuun fedha
isaa ibseera. Kanaanis namni bineensa kamiyyuu irraa adda ta’u isaa hubachuu
dandeenya. Sagalee Waaqayyoo sirritti hubbachuudhaaf sagalicha warri dura
dhaga’e maal akka hubatee sakkata’uun bayyee barbaachisaa dha. Warri dura
hubatee waan hubateen alatti; nutis addatti wanti haarayatti hubannu tokkoleen
hinjiru.
Friday, 13 April 2018
“ዓለም ያለድንግል ማርያም አማላጅነት አይድንም” ማለት፥ የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ ማክፋፋት ነው! (ክፍል ፪)
Please read in PDF
ሊያድነን አንድያ ልጁን ላከ፤
አዳነንም!
ቅዱሳት መጻሕፍት በአንድ ቃል ተስማምተው እግዚአብሔር አምላክ ዓለሙን እንዲያድን አንድያ ልጁን መላኩንና አንድያ ልጁም
ዓለሙን ሁሉ በደሙ ከኃጢአት ሁሉ እንዳነጻ ይመሰክራሉ፡፡ “እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና”
(ዮሐ.3፥16) የሚለው ቃል፣ ሰውን ለመውደድ መነሻውና ምንጩ አንድያ ልጁን በፈቃዱ የሠጠን ራሱ አብ አባታችን መሆኑን ነው፡፡
አስተውሉ! አዳም በወደቀ ጊዜ ቅድስት ሥላሴ “ወዴት ነህ?” ብሎ ፈለገው፡፡ አሁንም ከሥላሴ አንዱ አካል አብ “ውድ ልጁን እስኪሰጠን
ያለምክንያት በእንዲሁ ፍቅር” ወደደን፡፡ ክብር ይግባው፡፡ አሜን፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በፈቃዱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሊያድነን
“አማኑኤል” ሆነ፤ ተወለደም (ማቴ.1፥23)፡፡ “ሥጋ ያልነበረው እግዚአብሔር አምላክ ቃል ወደእኛ መጥቶ በፈቃዱ ከቅድስት ድንግል
ማርያም ነፍስ ዕውቀት ያለው ሥጋን ተዋሐደ” (ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ ምዕ.25 ክፍል 4 ቁ.37፡፡ ገጽ.60) እንግዲህ ጌታችን
ከሰማያዊ ዙፋኑ ወደእኛ የመጣው በፈቃዱ ነው፡፡
Tuesday, 3 April 2018
“ዓለም ያለድንግል ማርያም አማላጅነት አይድንም” ማለት፥ የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ ማክፋፋት ነው! (ክፍል ፩)
Please read in PDf
የስህተት ትምህርቶች በየዘመናቱ
የየራሳቸው መልክና ጠባይ አላቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ ለሚነሱ ኑፋቄያትና የተዛነፉ አስተምኅሮዎች እንደቀደሙት ቅዱሳን
አባቶች መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ መክራ ዘክራ፣ አስተምራ ሞግታ፣ የሳተውን አቅንታ፣ በስህተቱ የጸናውንና ሊመለስ ያልወደደውን
ለይታ በቅዱስ ቃሉ ማዕከልነት ማስተካከል ይገባታል፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተሰጣት መለኮታዊ ሥልጣን አለ፤ ይህን
ባታደርግ ደግሞ ከአምላካዊ ወቀሳ ፈጽሞ ላታመልጥ ትችላለች፤ (1ዮሐ.4፥1፤ ራእ.2፥2)፡፡
ከላይ በርእስነት በተናገርነው ሃሳብ ዙርያ፣ ማኅበረ ቅዱሳን የተባለው
ማኅበር እየፈራና እየተባ፣ በግልጥ ከመቃወምና ካለመቃወም መካከል ቆሞ እንዲህ መናገሩ “ይደንቃል”፦
“አንዳንድ ባሕታውያን ነን የሚሉ ሰዎች መናፍቃን ጸረ ማርያም በሆነ ትምህርታቸው ስለሚታወቁ ከዚያ በተቃራኒው በመቆም
የበለጠ ተወዳጅነትን ለማትረፍ ሲሉ እመቤታችንን ያከበሩ በሚመስሉ ስሕተትና ኑፋቄ አዘል ትምህርቶችን ያስተምራሉ፡፡ በዚህ ዓይነት
መልኩ በአንድ ግለሰብ የተጀመረ መፈክር መሰል ትምህርት ባጭር ጊዜ ውስጥ ተሰራጭቶ ብዙዎች የሚደጋግሙት በቤተ ክርስቲያን ዐውደ
ምሕረት ሳይቀር የሚደመጥ፣ በታላላቅ ጉባኤዎች ላይ በጉልህ ተጽፎ ብዙ ሰዎች ሊመለከቱት በሚችሉት መልኩ ሲሰቀል ማየት ተለምዷል፡፡
አባባሉ የአምላክን ሁሉን ቻይነት የሚፃረር መሆኑን፣ አምላክ እርሱ በፈቀደው መንገድ ዓለምን ማዳን የሚችል መሆኑን ገልጠው የተናገሩ
ሰዎች ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡
አምላካችን ዓለምን ሲያድን እመቤታችንን ለተሰግዎት ቃል መረጣት እንጂ እርሷ አልመረጠችውም፡፡” [1]
|
Subscribe to:
Posts (Atom)



