Please read in PDF
ሊያድነን አንድያ ልጁን ላከ፤
አዳነንም!
ቅዱሳት መጻሕፍት በአንድ ቃል ተስማምተው እግዚአብሔር አምላክ ዓለሙን እንዲያድን አንድያ ልጁን መላኩንና አንድያ ልጁም
ዓለሙን ሁሉ በደሙ ከኃጢአት ሁሉ እንዳነጻ ይመሰክራሉ፡፡ “እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና”
(ዮሐ.3፥16) የሚለው ቃል፣ ሰውን ለመውደድ መነሻውና ምንጩ አንድያ ልጁን በፈቃዱ የሠጠን ራሱ አብ አባታችን መሆኑን ነው፡፡
አስተውሉ! አዳም በወደቀ ጊዜ ቅድስት ሥላሴ “ወዴት ነህ?” ብሎ ፈለገው፡፡ አሁንም ከሥላሴ አንዱ አካል አብ “ውድ ልጁን እስኪሰጠን
ያለምክንያት በእንዲሁ ፍቅር” ወደደን፡፡ ክብር ይግባው፡፡ አሜን፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በፈቃዱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሊያድነን
“አማኑኤል” ሆነ፤ ተወለደም (ማቴ.1፥23)፡፡ “ሥጋ ያልነበረው እግዚአብሔር አምላክ ቃል ወደእኛ መጥቶ በፈቃዱ ከቅድስት ድንግል
ማርያም ነፍስ ዕውቀት ያለው ሥጋን ተዋሐደ” (ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ ምዕ.25 ክፍል 4 ቁ.37፡፡ ገጽ.60) እንግዲህ ጌታችን
ከሰማያዊ ዙፋኑ ወደእኛ የመጣው በፈቃዱ ነው፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር በመምጣቱ የሰው ልጆች ሁሉ
የናፍቆትና የእርዳን ጩኸታቸው ፍጹም መልስን አጊኝቷል፡፡ በተለይም በጽድቅ ሕይወቱ ያለነቀፋና ያለነውር፤ አንዳች ኃጢአት ሳይገኝበት
ተመላልሶ (1ጴጥ.2፥22-23 … ) ለሁላችን ያለነቀፋ መኖርን ኣሳየን፡፡ ሊያድነን ቤዛ በሆነበትና ብዙ መከራን በተቀበለበት በሐሙስ
ማታ መከራና በአርቡ የችንካር መስቀሉም አንዳች ተንኰል ሳይገኝበት አዳነን፡፡
እግዚአብሔር አምላክን ማግኘት ከዘለዓለም በፊት የሰው ልጅ ጥማትና ረሃብ
ነበር፡፡ ነገር ግን ሰው በራሱ ወደአምላኩ መቅረብ እንዳልተቻለው ያየው እግዚአብሔር፥ አንድ ልጁን ልኮ የራቀውን የሰውን ልጅ በልጁ
በኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ አቀረበው፡፡ ውድ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔርና በእኛ መካከል መካከለኛ ሆኖ ፍጹም አቀረበን፡፡
ብዙዎች ክርስቶስን እርሱ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለ መካከለኛ ነው የሚለውን የቅዱስ መጽሐፍ እውነት (1ጢሞ.2፥5፤ ዕብ.8፥6
፤ 9፥15 ፤ 12፥24) ክርስቶስ ወደፍጡር የሚያወርድ ትምህርት ይመስላቸዋል፡፡ ይህ ግን ከባድ ድንዛዜና አለማስተዋል ነው፡፡
ድንግል ማርያም መካከለኛ ኾና የክርስቶስ መካከለኝነት ለምን ተነቀፈ?
ሰዎች በክርስቶስ መካከለኝነት የረኩ አይመስልም፡፡ ለዚህም አንዳንዶች ከፍጡራን
ቅዱሳን ሰዎች ወይም ከቅዱሳን መላእክት መካከል የታወቁትንና ያልታወቁትን በመጥራት መካከለኞቻቸው እንደኾኑ በመታመን የሚጠሩትና
የሚማጠኑት፡፡ ይህንን ሃሳብና የክርስቶስ መካከለኝነት የመነቀፉን ምክንያት ቄስ ኮሊን ማንሰል እንዲህ በማለት ገልጠውታል፦
“ሰው ክርስቶስን እንደካህኑ ሊቀበለው አይፈልግም፡፡ የተሰቀለው ክርስቶስ
“ለአይሁድ ማሰናከያ፣ ለአሕዛብ ሞኝነት ነው”፤ (1ቆሮ.1፥23)፡፡ ከሕግ በታች ሆኖ ራሱን ለማጽደቅ ይፈልጋል፤ (ገላ.4፥21
፤ ሮሜ.10፥3)፡፡ በወገኑ፣ በሃይማኖቱ ሥርዐትና ሕግን በመጠበቁ ሊኰራ ይወዳል፤ ፊል.3፥4-7)፡፡ በዚህ ዐይነት ሰው ከእግዚአብሔር
ጋር ጠበኛ መሆኑ ከታየ፣ በእርሱና በእግዚአብሔር መካከል አስታራቂ እንደሚያስፈልገው ያስባል፡፡ ወይም ደግሞ አስታራቂ (መካከለኛ)
እንደሚያስፈልግ ቢያስብም፣ እግዚአብሔር ያዘጋጀለትን አንድ ብቻ አስታራቂ ነቅፎ ለራሱ ልዩ ልዩ አስታራቂዎች እንዲኖሩት ይፈልጋል፤
1ጢሞ.2፥5፡፡ ሰው ወደእግዚአብሔር እንዲቀርብ ክርስቶስ አስፈላጊውን ሁሉ የፈጸመለት መሆኑን አይቀበልም፤ እንዲውም በጸጋ እንዲጸድቅ
አይፈልግምና በራሱ ጽድቅ በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት ተስፋ ያደርጋል፤ 1ጴጥ.3፥18 ፤ ሮሜ.3፥24 ፤ 10፥3 ፤ 1ቆሮ.1፥30
፤ 2ቆሮ.5፥21፡፡[1]
|
መካከለኝነቱ
ለምን ተነቀፈ?
1.
“ጌታ የማስታረቅ አገልግሎቱን በዕለተ ዓርብ ስለፈጸመ ዛሬ ያማልዳል፣ አማላጅ ነው ማለት ከአብ አሳንሶ ማየት ስለሆነ የጌታን የባሕርይ አምላክነት የሚጻረር በመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ቤተ ክርስቲያን አጥብቃ ታወግዘዋለች” በማለት መካከለኝቱን
ለመንቀፍ በዋነኝነት እንደምክንያት ይጠቅሱታል፡፡ ይህንንም ትምህርት ከቤተ ክርስቲያኒቱ አባት አንዱ፣ “ ... ነቢረ የማን(በአብ
ቀኝ መቀመጥ) ክርስቶስ ግብረ ትስብእት ከፈጸመ በኋላ እንደገና የሰውነትን ሥራ የማይሠራ፣ ነገር ግን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር
በክብር መለኮታዊ ሥራውን እየሠራ የሚኖር መኾኑን የሚያስረዳ ቃል ነው፡፡” በማለት ገልጠዋል፡፡[2]
ይህ ቃላቸው ግን “ሰው በመኾኑ መከራን ተቀበለ እንጂ ለዘላለሙ ሥጋን ተዋሕዶ ይኖራል”[3]
ከሚለው ቃሉ በግልጥ ይቃረናል፡፡
ይህ ሃሳብ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የጸና መኾኑን በሌላ ቦታ እንዲህ
በቃለ መጠይቅ መልክ ተገልጧል፤ “ምንም እንኳ ጌታችን የሰውን ሥጋ በመልበስ ከአብ አንሶ የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ግን የሆነው እስከመስቀል
ድረስ ብቻ ነው፡፡ ጌታችን በሥጋ ሊፈጽመው የሚገባውን ሞት ቀምሶ ከሞት ከተነሣ በኋላና አሁን በትንሣኤ አካል በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ
ባለበት ጊዜ ሰብአዊ ባሕርይ በመኮታዊነቱ ላይ አይንጸባረቅም ብላ ታምናለች፡፡ ጌታችንም በመጨረሻ ሲጸልይ “አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር
በነበረኝ ክብር ልጅህን አክብረው” ብሏልና እንዲህ አድርጎ ማመን ትክክለኛ እምነት ነው ብዬ እወስዳለሁ፡፡”[4]
መካከለኝነት ምንድር ነው?
የኢትዮጲያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር ያሳተመው፤ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት መካከለኛነትን፣ “በሁለት ወገኖች መካከል ለማስታረቅ የሚቆም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መካከለኛለት በእግዚአብሔር ፊት ለበደለኞች የሚማልድና
ከእግዚአብሔር ምሕረትን የሚያስገኝ ነው፤ ኢዮ.9፥31 ፤ 1ሳሙ.2፥25፡፡ በብሉይ ኪዳን ካህናትና ነቢያት በእግዚአብሔርና በሕዝቡ
መካከል የመካከለኛነት ሥራ ይሠሩ ነበር፤ ዘሌ.9፥7 ፤ ዘዳ.18፥18-21 ፤ 28፥1 ፤ ዕብ.5፥1-4፡፡ ሙሴ የብሉይ ኪዳን መሥራች
ስለነበር የብሉይ ኪዳን መካከለኛ ሆነ፤ ዘጸ.19፥3-8 ፤ ሐዋ.7፥37-39፤ ዕብ.9፥19-20፡፡ ሙሴ በመካከለኛነቱ ከኢየሱስ
ክርስቶስ ጋር ተነጻጽሯል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው፤ ዮሐ.1፥17 ፤ ዕብ.7፥27-28 ፤ 8፥6 ፤ 9፥15፤ 23-24 ፤ 10፥1 ፤ 12፥24፡፡ ኢየሱስ
ክርስቶስ የካህናትን፣ የነቢያትንና የሙሴን መካከለኛነት በመፈጸሙ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለ መካከለኛ እርሱ ብቻ ነው፤
1ጢሞ.2፥5፡፡”[5] በማለት በሰፊው ይፈታዋል፡፡
†
ሌላና ልዩ መካከለኛ ለምን አስፈለገ?
·
የነበሩትን ሞት ስለገዛቸውና
ደካሞች ስለነበሩ፤
·
ኃጢአተኞችና የተኰነኑ ስለኾኑ፡፡
መካከለኝት በአዲስ ኪዳን
መካከለኛ “Mediator” ወይም በግሪኩ “መሲቲስ”
የሚለውን ቃል ይወክላል፤ ቃሉ ግን በትክክል ሃሳቡን አይተረጉምም፡፡ “መሲቲስ” በተለያዩ ሁለት በተለያዩ ሰዎች[ወገኖች] መካከል
የሚቆም አገናኝ፣ አቅራቢ ወይም አስታራቂ ነው፡፡ “መሲቲስ” በአዲስ ኪዳን ስድስት ጊዜ ብቻ ተጽፎ እናገኘዋለን፤ ቃሉ ጌታችን ክርስቶስ ኢየሱስ ለሰው በሚያስፈልገው አቅጣጫ ሁሉ በእግዚአብሔርና
በሰው መካከል የሚቆም አገናኝ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ራሱን ቤዛ አድርጐበመስጠቱ ካህናችን ነው፤ ደግሞም ነቢያችንና
ንጉሣችን በመኾኑ ካህናችን ብቻ አይደለም፡፡
አገናኝ ኾኖ እንደነቢይ አብን በትምህርቱ ገልጦልናል፤
“መቼም ቢሆን
እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው” (ዮሐ.1፥18) ማቴዎስም በማቴ.11፥27
ላይ፣ “ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።” በማለቱ
ከሰው መካከል፣ ከመልአክም ቢኾን ማንም ሊፈጽም ያልቻለውን በአስተምኅሮቱ ነቢይነቱን፣ በአገናኝነቱና ስለእግዚአብሔር ግልጡን በመናገሩ
መካከለኝነቱን ገለጠ፡፡
ሰው ኃጢአትን በመሥራቱ ከአምላኩ እግዚአብሔር ተለየ፤
ኀጢአት እንደግድግዳ ለዪና የማያሰማማ ኾነ፤ (ኢሳ.59፥2)፡፡ ስለዚህ በደለኛውን ሰውና ቅዱሱን እግዚአብሔር አምላክ የሚያገናኝ
መካከለኛ ግድ የሚያስፈልግ ኾነ፡፡
በአዲስ ኪዳን ብቸኛው መካከለኛ ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ነው፡፡ ምክንያቱም ለተለያዩ ወገኖችና ነገዶች ተሰጥተው የነበሩትን ማዕረገ ክህነት፣ ንግሥናና ነቢይነትን “ክርስቶስ”
በሚለው “የሹመት ስም” ጠቅልሎ ወርሶታልና፡፡
ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ ስለሁለት ነገር መካከለኛ ነው እንለዋለን፦
1.
ስለለበሰው ሥጋ ፦ እርሱ ፍጹም አምላክ ብቻ ያይደለ ፍጹም ሰውም ነው፡፡ በፍጹም ሰውነቱ ከእኛ ጋር ነው ብንልም፥ በአምላክነቱ ደግሞ
በሥላሴ መካከል ያለ ነው፡፡ ስለዚህ ለእኛ የቀረበንና ወደአባቱ ፣ ወደእርሱና ወደባሕርይ ሕይወቱ የሚያቀርበንና የሚያዛምደን ከእርሱ
የሚበልጥ ማንም “የሥጋ ዘመድ” የለንም ፤ እርሱ ብቻ አማኑኤል ነውና፡፡
2.
በመስቀሉ
ሥራ ፦ እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እንዲህ አለ፥ “እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ”
(ዮሐ.12፥32) ጌታ በዚህ ቃሉ የመስቀል ሞቱ በእኛና በእግዚአብሔር መካከል መካከለኛ ወይም ድልድይ መሆኑን አስተማረን፡፡ የሞተው ለእኛ ነውና በሞቱ የገዛ ገንዘቦቹ አደረገን፡፡ ትላንት አዳም በወደቀ ጊዜ “ወዴት ነህ?” ያለው እርሱ ራሱ፥ ዛሬም
በሞቱና በትንሣኤው መካከለኛችን ሆኖ ፈልጐ ያገኘናል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፥
“ሰው የሆነም ዘመድ ሊሆነን ብቻ አይደለም ፤ ፈጽሞ ይቅር አለን
ኃጢአታችንን ለማስተስረይ ከአብ ጋር ለማስታረቅ ሊቀ ካህናትም ይሆነን ዘንድ ወደደ እንጂ፤ ስለዚህም ሰዎችን ሊመስላቸው ይገባል
ባለው ነገሩ ላይ ጨምሮ በሁሉ አዛኝ የሕዝቡንም ኃጢአት ለማስተስረይ በእግዚአብሔር ዘንድ የታመነ አስታራቂ ይሆናቸው ዘንድ ነው
አለ ዕብ.2፥17፡፡
ባሕርያችንን ስለተዋሐደ ሰው የመሆኑን ነገር ያስተምረን ዘንድ ይኸን
ተናገረ ሰው ለመሆን ያበቃው ለማስታረቅ ኃጢአትን ለማስተስረይ ብቻ ነው እንጂ ሌላ ምክንያት የለውም ፤ ከእርሱ በቀር ራሱ ብቻውን
ኃጢአት ማሥተስረይ የሚቻለው የታመነ አስታራቂ ማነው? ለማስታረቅ ኃጢአትን ለማስተስረይ ያቀረበው መሥዋዕትስ ምንድር ነው? መሥዋዕት
ለመሆን የነሣው ሥጋው ነው እንጂ፡፡
… ከዚህም
በኋላ የምናምንበትን አስታራቂ ሐዋርያ እርሱን አብነት አድርጉት አለ አብ ከወዲያ ዓለም ወደዚህ ዓለም ስለላከው ሐዋርያ
አለው ፤ ስለ አመንበት በጎ ሥራ ለመሥራት የምንቀና ደግ ወገን አድርጎ ገንዘብ አደረገን ለእኛ ማልዶልናልና የምናምንበት ሊቀ
ካህናት (አስታራቂ) አለው፡፡ ዮሐ.17፥1-26፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ሊቀ ካህናት በአደረገው በአብ ዘንድ የታመነ
እውነተኛ ነው አለ ለወገኖቹ በጎ ማገልገልን እንዲያገለግል ይጐዱም ዘንድ ቸል እንደማይላቸው እኛ እንድናውቅ መናገሩ ነው፡፡”
[6]
“ቀድሞ ሊቀ ካህናት ይለምን እንደነበረ ዛሬስ ለለመነ አምላክ ይለምናል ብለህ አታድንቅ፡፡ ሊቀ ካህናት እንደመሆኑ ስለለመነ አታድንቅ፡፡ … ስለምን ሰው ሆነ ሰው ካልሆነ አያድንምን የሚል ሰው ቢኖር አዎን ሰው ካልሆነ አያድንም ብለን እንመልስለታለን” [7]
“ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ሊቀ ካህናት በአደረገው በአብ ዘንድ የታመነ እውነተኛ ነው አለ፤ ለወገኖቹ በጐ ማገልገልን እንዲያገለግል ይጎዱም ዘንድ ቸል እንደማይላቸው እኛ እንድናውቅ መናገሩ ነው፤”[8]
"እርሱ እኛን መጠበቅ
አልተወም በማይለወጥ ፍቅር ስለሚወደን አርሱ ስለእኛ ዘወትር ይማልድልናል... አማላጅነቱም ከአባቱ ማነሱን አያሳይም ይልቁን
አፍቃሪነቱን ያሳያል እንጅ፡፡" "ዮሐንስ አፈ. ድር. 15 ሮሜ 8:34ን በተረጎመበት ድርሳኑ)
“ሰው ዓለምን ለማዳን አይችልም፡፡ የሰው መሞትም ከኀጢአት አያነጻም፡፡ ... ዳዊት ‘ሕያው ኾኖ የሚኖር ሞትንም
የማያይ ሰው ማነው? ከሲኦል እጅስ ነፍሱን የሚያድን ማነው? ሲል
እንደተናገረ፣ ሞትን ያጠፋ ዘንድ ሕይወትንም ያበራ ዘንድ የሚቻለው ከሰዎች ይገኛልን? ነፍሱን ለማዳን ያልቻለ ከኾነማ ሌላውን
ለማዳን እንዴት ይችችላል? አንዱን ለማዳን ካልቻለስ መላውን ዓለም እንዴት ሊያድን ይችላል? ኀጢአት በሰው ውስጥ ዐድሮአልና፤
ሞትም ይከተዋል፡፡ ... አዳም በበደለ ጊዜ ሰውን የወለደው በራሱ አምሳል ነው፡፡”[9]
“ዛሬም ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ተገለጠ፤ ሰው ከመሆኑ በፊት ለምን አልተገለጠም? እርሱማ በሕልውና ያለ፤ ያለድካም ሁሉን የፈጠረ ሁሉ የተፈጠረበት የአብ ጥበቡ ነው እንጂ፡፡ ዛሬስ በምን ሥራ፤ በምን ነገር በእግዚአብሔር ፊት ተገለጠ፤ አምላክ ቃል እንደእኛ ሰው ሆኖ በአዲስ ሥራ ተገለጠ፡፡ ዓለም ሳይፈጠር ሥጋን ሳይዋሐድ በመለኮቱ በአብ ዘንድ ሕልው ሲሆን ዛሬ ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት በእኛ ባሕርይ በአስታራቂነት ተገለጠ፡፡ ዛሬ ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት እንደተገለጠ የምንናገረው ነገር ይህ ነው፤ …”[11]
|
ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለም፥
“ክርስቶስ ስለኃጢአታችን
መሥዋዕት በመሆኑ እውነተኛ አስታራቂያችን ሆኗል፡፡ … ስለዚህ ነው ክርስቶስ “ከጥንት ጀምሮ እስከዘላለሙ ድረስ አስታራቂ ሆነን”
ተብሎ የተጻፈው፡፡
… ከኦሪት በኋላ የመጣው
የእግዚአብሔር የመሐላ ቃሉ ግን ዘለዓለም የማይለወጥ ፍጹም ወልድን ካህን አድርጐ ሾመልን” (ዕብ.7፥20-28 የግእዙን ትርጉም
ተመልከት)” [14]
በማለት ተናግረዋል፡፡
|
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ”መካከለኛ የተባለበት አዳምና ልጆቹ ሁሉ በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር
ጋር ተጣልተዉ ተለይተዉና ርቀዉ የነበሩትን በማስታረቁና በማቅረቡ ነዉ፡፡” በማለትም ሊቀ ጉባኤ አባ አበራም በግልጥ አስቀምተዋል፡፡
(141-142) እንዲሁም ”… እንግዲህ ክርስቶስ በእግዚአብሔርና በሰው መካከለኛ እንደመሆኑ ስለኃጢአት ምሕረትን የመለመንና የማስታረቅ
ሥራውን አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ መሥዋዕት በመሆን ፈጽሞታል (ዕብ.7፥25 ፤ 9፥12 ፤ 10፥10-25)፡፡ በማለት ያስረግጡታል፡፡
በሌላ ሥፍራም፥
“አባታችን ያዕቆብ ወደሜሶፖታምያ በሚጓዝ ጊዜ፣ በሕልሙ እርሱን(ወልድን) አየው፡፡ መሰላል ቆሞ
(ዘፍ.28፥10-15) ፤ እርሱም ከምድር እስከሰማይ የተዘረጋ ዛፍ ነው፡፡ በእርሱም ምእመናን ሁሉ ወደመንግሥተ ሰማያት ይደርሳሉ፡፡
የእርሱ መከራ መስቀል ለእኛ ወደላይ መውጫ መንገዳችን ሆኗልና፡፡” [15]
ተብሏል፡፡
|
በእርሱ መካከለኛነት አለሙ ድኗል፤ እየዳነም ነው፤ ደግሞ ገና ፍጹም
ይድናል፡፡ ይህን የምንለው በመስቀል ላይ የተሠራው የቤዛነት ሥራው ዛሬም ሕያውና ያልሞተ፤ አሁንም ስለፍጥረት ሁሉ የሚታይ ትኩስ
ደም ስለሆነ ነው (ዕብ.9፥24) ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ታላቅ መገለጥና እውነት ያለመጠራጠር ታምናለች፤ ትቀበላለችም፡፡
ነገር ግን ይህን እውነተኛ የወንጌል ትምህርት የሚቃወምና ቤተ ክርስቲያንን
የሚያስነቅፍና የክርስቶስን ሞት የሚያክፋፋ ትምህርት ከቀደመው ዘመን በከፋ ሁኔታ በየአውደ ምሕረቱ ሲያስተጋባ፤ ጥቂት በማይባሉ
“ሰባክያን” አንደበት በድፍረት ሲለፈፍ እየሰማን ነው፡፡ ነገሩን ቀለል አድርጐ እንዳናይ የሚያደርገን ነገር ደግሞ ክህደቱ ትምህርት
ሊበጅለት መከጀሉንና መጽሐፍ ቅዱሳዊ “ለማድረግ” መታሰቡ ነው፡፡
“ያለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም” የሚለው የክርስቶስን
ቤዛነት የሚክድ የተገለጠ ክህደት መነገር ከተጀመረ ዓማታትን ወስዷል፡፡ በየታክሲው በስቲከር መልክ፣ በቲሸርት ታትሞ ለሽያጭ ከመታደሉ
አልፎ ክህደቱን እውን ለማድረግ መጽሐፍ ጭምር ታትሞ በቤተ ክርስቲያን ስም በቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ተባዝቶ ተሰራጭቷል፡፡[16]
ከታሪክ እንደተማርነውና አሁን በሚገባ እንደምናስተውለው በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ጊዜ በድንግል ማርያም ስም በእግዚአብሔርና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የሚደረጉ ማንኛቸውም
የንቀት፣ የድፍረት፣ የማክፋፋት ሥራዎች ሲሠሩ ብዙ ጊዜ የሚቃወሙ ወይም “ይህ ትክክል አይደለም” የሚሉ አካላት ሲነሡ ማየት የተለመደ
አይደለም፡፡ በእኔ አመለካከት ይሕ የሆነበት ሁለት ዋና ምክንያቶች ያሉ ይመስለኛል፦
1.
በድንግል ማርያም ስም የሚደረጉ ነገሮች ብዙ ጊዜ ከመናፍቅነት ያስቆጥራሉ
የሚል እምነት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ “ያለድንግል ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም” የሚለው ዋናና ትልቅ ማሳያ ነው፡፡
ምክንያቱም ይህ አባባል ሙሉ ለሙሉ የክርስትናን ስም የሚቃወምና የሚክድ ነውና፡፡ ከዚህ ባሻገር ስለድንግል ማርያም ከነገረው አልፎ
መናገርና መለፈፍ የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡
2.
አንድ ሰው ደግሞ ይህ ነገር ክህደት መሆን ቢገባው እንኳ ለመቃወምና ትክክል
አይደለም ብሎ ቢናገር ሊደርስ የሚችልበትን “ሲኖዶሳዊ” ውግዘት፤ ከማኅበረሰቡ የሚደርስበትን መገለልና መተቸት ፤ ከፍ ሲል የቤተ
ክርስቲያኒቱ አገልጋይ ከሆነ ደግሞ ከቤተ ክህነት “የእንጀራ ገበታቸው” መፈናቀሉና ቤተሰቡን መበተኑን እያሰበ ከሚመጣበት ተቃውሞና
ስደት ዝምታን መምረጡ ነው፡፡
ነገር ግን ይህ ትምህርት ፍጹም ቤተ ክርስቲያንን የማይወክልና ክህደት
መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ቃል ይነግረናል፡፡
ይቀጥላል …
[12]
ድጓ 113
[16] እዚህ ላይ ቢያንስ አንድ መጽሐፍ
መጥቀሱ መልካም ነው፡፡ ደምሰው ዘውዴ፤ ያለ ድንግል ማርያም
አማላጅነት አለም አይድንም፤ 2000 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤
አሳታሚው ያልተገለጠ፡፡ ይህ መጽሐፍ 45 ገጽ ያለው ሲሆን በተቻለ መጠን “መንፈሳዊ ለመሆን” የጣረ መጽሐፍ ነው፡፡ በሚያስገርም
ሁኔታ በመጽሐፉ ቀዳሚ ገጽ ላይ “ይህ መጽሐፍ በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ዶግማ፣ እምነት፣ ሥርዓና
ደንብ መሠረት የተዘጋጀ ነው” የሚል ትሑት አልባ ትዕቢታዊ ድፍረትን ያዘለ መግለጫ በውስጡ አለው፡፡ እንግዲህ የዚህም መጽሐፍ ጭብጥ
ስናስተውል ከርእሱ ብዙ ርቆ ውሸትን በውስጡ ያጨቀ ቢሆንም፣ ማንም አካል ግን ይህን ሰው ምንም አላለውም፡፡ እንግዲህ ተሐድሶ ያስፈልጋል
ስንል እንዲህ ለውን እንክዳድ ትምህርት በመቃወም ነው፡፡
ReplyDeleteበእውነት ጸጋውን ያብዛlk እግዚአብሔር ይባርkh ከanተ ብዙ እየተማርን ነው በርta::
“ቀድሞ ሊቀ ካህናት ይለምን እንደነበረ ዛሬስ ለለመነ
ReplyDeleteአምላክ ይለምናል ብለህ አታድንቅ፡፡ ሊቀ ካህናት እንደመሆኑ
ስለለመነ አታድንቅ፡፡ … ስለምን ሰው ሆነ ሰው ካልሆነ
አያድንምን የሚል ሰው ቢኖር አዎን ሰው ካልሆነ አያድንም
ብለን እንመልስለታለን” amen amen
yemigerm difret! ©✔✔ berta Abeni ♥ Geta Yesus tsegawn yabzalh.amen.
ReplyDeleteMasetewale yaxa tewuled abatun kalakun axerun ayinekeniku, "amilakine ina ye amelakin maderiya yisadeb zende awurew af tesexew".tinbit mefetsemiya kemehon igezer yixebiken. Filb.3:18 indenezi yalut sewech kiberachew newurachew hodachew amilakache silxane yalachewun yisadebalu.kedusan behaleme layi indemiferedu atakumini? Yilale metsaf kidus masetewale yisxen amen.
ReplyDeleteMamaled endihu kelal aderegachihut manew sewn lemadan, Ke egzabhar gar lemastarek be Meskel memot Ena Demun mafises alebet, One God and One mediater b/n God and man , That is Jesus the son of God. Manin lemastarek Dem alfesesem Mariam meche Meskel lay motech
ReplyDelete“ዓለም ያለድንግል ማርያም አማላጅነት አይድንም” የሚለውን መደበኛ ሐረግ የፈጠሩት አዛብተው ነው፥“ዓለም በድንግል ማርያም አማላጅነትም ይድናል”የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤን ፍፁም ማክፋፋት አያደርግም።
ReplyDeleteድንግርግሮሽ Equivocation/ስርቅ/ድብልቅልቅ ማለት የሌላን ሰው ሀሳብ አጣሞ በመወከል፣ ይህን የተጣመመ ሀሳብ በማጥቃት፣ ዋናውን ሀሳብ ያጠቁ ማስመሰል ነው፤ይህ ጥሩ ምሳሌ ነው።
እንዳይደለ ታውቃለህ፤ አንተም ያልከው ዐሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ሲመዘን፣ ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ እንደ ከኾነም ጭምር። "ያለ" የሚለው አጫፋሪ ቃል በማናቸውም መልኩ ማርያምን አጉልቶ፣ ኢየሱስን እንደሚጋርድ ጥቂት ላሰበው ሰው የተሰወረ አይደለም።
Deleteእንደዚያ ሲባል ሰምቼ አላውቅም ። ግን አንተ በቅዱሳን አማላጅነት ታምናለክ?
DeleteRevaluation 6:9,10,11
DeleteFrdn yileminalu enji.