Showing posts with label ጰራቅሊጦስ. Show all posts
Showing posts with label ጰራቅሊጦስ. Show all posts

Sunday, 16 June 2019

አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ

Please read in PDF

   ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል ከተነሣ በሃምሳኛው ቀን፣ ወደ ሰማያት ባረገ ደግሞ በአሥረኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ገባላቸው ተስፋ ቃል ከአባቱ ዘንድ በመላክ የቤተ ክርስቲያን ልደት አብስሮአል።
   ከግሪኩ “ፓራክሊቶስ” ወይም ከዕብራይስጡ “ፕራቅሊጥ” ከሚለው ግስ የተገኘው፣ “ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል ትርጉሙ፦ “አማላጅ፣ አስታራቂ፣ አፍ፣ ጠበቃ፣ ትርጁማን፣ አምጃር፣ እያጣፈጠ የሚናገር፣ ስብቅል ካፉ ማር ጠብ የሚል።…፤ ናዛዚ፣ መጽንዒ፣ መስተፈስሒ፤ መንፈስ ቅዱስ” በማለት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ተርጉመውታል። [1]

Saturday, 26 May 2018

በቤቱ የተዘነጋ አባ ወራ

   ጽሐፍ ቅዱስ ወንድ አባ ወራ እንደ ኾነ ይነግረናል፤ “ባል የሚስት ራስ ነውና።” (ኤፌ.5፥23፤ 1ቆሮ.11፥3)፣ እንዲል። እናም ወራውን(ቤተሰቡን) በአግባቡ ማስተዳደር አለበት፤ “ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤ ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል?” (1ጢሞ.3፥4-5)። አባ ወራነት አስቀድሞ የወራ[በኦሮሚኛ ቤተሰብ ማለት ይኾንን?] ምስክርነት ያሻዋል፤ ቤተሰቡን የማይወድና ለቤተሰቡ ምንም ከበሬታ የሌለው አማኝም ኾነ አገልጋይ በውጭ ያለውን ዓለም በመላው እንደ ሚወድ ቢናገር ወይም ቢያሳይ ግብዝ ወይም አርቲስት እንጂ ሌላ ምንም ሊኾን አይችልም።
   የባል አባወራነቱ አስተዳደራዊ ነውና፣ ትልቅ ፍቅር የሚጠይቅ ነው። በትልቁም በትንሹም ውድ የኾነውን የባሎቻቸውን ፍቅር ያዩ ሚስቶች፣ ለባሎቻቸው እስከ ሞት በሚያደርስ ፍቅር እንደ ሚታመኑ ጥርጥር የለውም። ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን ፍቅር ዓይታ ለነፍሷ እንደ ማትሳሳ እንዲሁ፣ ሚስቶችም የአባ ወራቸውን “ደማቅ” ፍቅር ዓይተው ለባሎቻቸው የማይታመኑበት፣ ልጆችም አባታቸውን እንደ “ንጉሥ” የማያዩበትና የማያከብሩበት አንዳች ምክንያት አይኖርም።

Sunday, 19 June 2016

ጰራቅሊጦስ - ሌላ አጽናኛችን


Please read in PDF

     “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤” (ዮሐ.14፥15-16)
     መንፈስ ቅዱስ ለሰው ልጆች የሚሰጥ የአብ ውብና ድንቅ ስጦታ መሆኑን በመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመርያ ጊዜ የምንመለከትበት ክፍል ይህ ከላይ ያየነው ነው፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የመሰጠቱ ተስፋ ከኢየሱስ መሔድ ወይም ማረግ በኋላና እርሱም በዚያ ሆኖ በሚለምነው ልመና እንደሆነ፥ “እኔም አብን እለምናለሁ ... ” የሚለውን የጌታ ቃል አብነት በማድረግ ቅዱስ ያሬድ በድጓው፥ “ ... ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን የእኔ ስለሆኑት ምሕረትን ወደምለምንበት ወደአባቴ ወደሰማይ ዐርጋለሁ አላቸው” በማለት በገጽ.113 ሲያሰፍር፥ እንዲሁም “ ... ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደአባቴ ዐርጋለሁ ስለእናንተ እለምነዋለሁ አላቸው” (ድጓ ገጽ 291) በማለት በግልጥ ይደግመዋል፡፡