Wednesday, 5 August 2026

ፍልሰታን ለጌታ እንዋጅ!

 

ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ጌታችን ኢየሱስን በመውለዷ ቅድስትና ብጽዕት ናት። የጌታ መልአክ መልአኩ ገብርኤል መጥቶ እግዚአብሔር ሊሠራ የወደደውን ጅማሮ በርሷ መሥራት እንደሚጀምር ሲያበስራትም በመረዳት መታዘዝዋ ስለተጻፈልን፣ ለአዲስ ኪዳን አማኞችም ለጌታ ቃል ጥንቅቅ ባለ መንገድ መታዘዝና በትክክል መረዳትም እዳለብን ከሕይወትዋ እንማራለን። ይህ ብቻ ሳይኾን፣ በዕብ. 11 ላይ እንደ ተጠቀሱት የእምነት አርበኞች፣ የእግዚአብሔር ቃል ዕውቀትዋ በጸሎትዋ፤  ልምምድና ሥራዋ ደግሞ በተጋድሎዋ ፍንትው ብሎ ይታያል።

Friday, 24 July 2026

“ጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል… አለች።”

 

ጽዮን በባቢሎን ምርኰ በተያዘችና ለሰባ ዓመታት ያህል በግዞት በዘገየች ጊዜ የተረሳችና የተተወች መሰላት፤ በተለይም የመቅደሱ መፍረስና ከቅድስቲቱ ምድር ሙሉ ለሙሉ መነቀላቸው ተስፋቸውን ይበልጥ አጨለመው። እግዚአብሔር ግን ሕዝቡ ተስፋ እንዲቈርጥ አይፈልግም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ታማኝ፤ ጽኑ ፍቅር፤ የማያቋርጥ ኪዳናዊ ቊርኝት ያለው፤ ጨርሶ ሊዘነጋ የማይችል ልብ አለውና። ይህን እውነት እግዚአብሔር በበደልና በኀጢአት ለወደቀችው ለጽዮን፣ በነቢዩ አንደበት በግልጥ ይናገራል፤ እንዲህ በማለት፣

“ጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ጌታም ረስቶኛል አለች። በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም። እነሆ፥ እኔ በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለሁ፥ ቅጥሮችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ።” (ኢሳ. 49፥14-15)

Friday, 17 July 2026

ለባህለ ትምህርት አልባ “ተሐድሶዎች”

 

ወንጌል የማይለወጥና ዘላለማዊ መልእክት ቢኖረውም፣ የራሱ ባህል ግን የለውም፤ ወንጌል ለየትኛውም ሕዝብ፤ ለኹሉም ነገዶች፤ በኹሉም ቋንቋዎችና ባህሎች መሰበክና መነገር ያለበት የእግዚአብሔር መንግሥት ታላቅ ምሥራች ነው። ለዚህ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ዋና ምሳሌአችን ነው። ጌታችን ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለገሊላና ለይሁዳ መንደሮች ያቀረበበት መንገድ፣ እጅግ ጠቃሚ የኾኑ የባህል ተዛማጅ መመሪያዎችንና ልምምዶችን ያስተምረናል።

Monday, 13 July 2026

የዋልድባ የግድያና የዘረኝነቱ ጦስ!

 

“... በኹለት ዐመቱ ጌታችን በእናቱ እቅፍ መጥቶ ባረካት[ዋልድባን]። ዋልድባ በአራቱ ወንዞች ትከበብ ብሎ፣ የሰው ብቻ ሳይኾን የእንሰሳ ሴት አይግባባት ብሎ ጌታችን ኢየሱስ የውግዘት ቃል አሳልፎባታል። ሴቶች እንዳይገቡ በግዝት ቃል ተነግሮባታል። ... ስውር ቅዱሳን ክንድ ከስንዝር ከፍ ብለው የቀደሱበት ስፍራ ነው።... ዳልሻ ዋልድባ ቤተ ደናግል የሚባል የሴቶች ገዳም ጨርሶ  የለም። ... ገዳሙ ጨርሶ የእርሻ ስፍራ እንዳይኾን እንኳ ተከልክሎአል።... በዋልድባ ጳጳስ እንኳ ቢመጣ 40 ቀን ቋርፍ ሳይጨብጥ በዋልድባ ቀጥታ መቁረብ አይቻልም።…” የሚሉ አያሌ “ተረቶች” በገዳሙ “አባቶች” ሲነገር መደመጡ እንግዳ ነገር አይደለም።

Thursday, 18 June 2026

ተሐድሶ የቅሬታዎች አገልግሎት ነው!

Please read in PDF

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የ“ተሐድሶ አገልጋዮች” ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል፤ ዕዝራ፣ ነህምያ፣ ዘሩባቤልና ኢያሱ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። ሕዝቡና እነርሱ በምርኰ ሳሉ፣ የእስራኤልን ጥልቅ ውድቀትና መንፈሳዊ ቅዝቃዜ በማየት፣ እስራኤል ዘሥጋ ትነቃቃና ታበራ፤ ትጌጥና ትፈካ ዘንድ የነቢያቱን የተስፋ ቃል በማወጅ፤ እንደገና በማስታወስና አጽናንቶ በማበረታታት ይታወቃሉ።

Sunday, 7 June 2026

ወንድምነት ረክሶ አገልግሎት ሲመለክ!

Please read in PDF

በዘመናዊው ዓለም ኢየሱስ በኪደተ እግሩ ከሰማርያ እስከ ኢያሪኮ የሚፈልጋቸው ሳምራዊቷ ሴትና የጤሜዎስ ልጅ በርጠሚዎስ፣ ወይም በቅፍርናሆም ያገኛት ደሟ ቀጥ ያለላት ሴት፣ ለዚህ ዘመን አገልጋዮች ጥሩ የስብከት ርዕስ እንጂ በወንድምነት ወይም በእህትነት የሚፈለጉ አይመሰለኝም። በቀላል ንግግር ሰውነት በዚህ ዘመን ከአገልግሎት አይበልጥም የተባለ ይመስላል።

Friday, 5 June 2026

ጳውሎስ የሰማው የሞት ድምጽ! (2ቆሮ. 1፥9-11)

 Please read in PDF

ቅዱስ ጳውሎስ ኹለተኛውን ቆሮንቶስ እየጻፈ ያለው፣ በአንደኛ መልእክቱ ላይ በታላቅ ተግሳጽ የገሰጻቸውንና ንስሐም በመግባት የንስሐ ፍሬ ያሳዩትን ቅዱሳን ወገኖቹን ለማጽናናትና ለማበረታታት ነው።

አንደኛውን መልእክት ሲዘጋ፣ የወንጌል ሥራ በር እንደ ተከፈተለትና ነገር ግን የዚያኑ ያህል ደግሞ እጅግ ተቃዋሚዎች እንደ ተነሱም ተናግሮአል (1ቆሮ. 16፥8-9)፤ ምናልባት ተቃዋሚዎቹ ከባድ ስደት አልያም ከፍ ያለ እንግልት አድርሰው ሊኾን ይችላል።

Monday, 25 May 2026

በሥጋው ያረገ ጌታ!

 Please read in PDF

ክርስቶስ ኢየሱስ ከቅድስት ድንግል በነሣው ሥጋና ከሙታን መካከል ሲነሣ በለበሰው ፍጹም ሰውነቱ ወደ ሰማያት አርጓል። ምክንያቱም የመጣበት ዋነኛ ዓላማ፣ “የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን ነውና” (ሉቃ. 19፥10)። ደግሞም ሰውን ለማዳን ክርስቶስ እንከን አልባ ሰው መኾን ያስፈልገው ነበር። ከዚህም የተነሣ ሊያድነን በፍጹም ሰውነቱ የተሰቀለው ያው መሲሕ፣ በሰማያት መግቢያ በር ይኾነን ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ።

Monday, 18 May 2026

ያላንተ!

 

እንደ ጢቢኛ የምገላበጥ

እንደ አሽከር ዐይን የምቀላውጥ

Thursday, 14 May 2026

“በወንጌል ሕይወታችን ኾነ” ከሚለው ጉባኤ የተወሰዱ ቊልፍ አባባሎች፣

 

-     “… አኹን ያለንበት ጊዜ ስብከተ ወንጌል በዋና ዓላማነት ያልያዘበት፣ ሊቃውንትን በማፍራት ብቻ ቤተ ክርስቲያን የተጠመደችበት ጊዜ ቢኖር አኹን ያለንበት ጊዜ ነው። …”

-     “… ወንጌል እንደ ቅዱስ ጳውሎስ መሥዋዕታዊ ሕይወትን ዘወትር ይፈልጋል። …”



Saturday, 2 May 2026

“በወንጌል ሕይወታችን ኾነ” ከሚለው ጉባኤ የተወሰዱ ቊልፍ አባባሎች፣

 Please read in PDF

-     “… የሰው ልጅ ኹለተኛ ባሕርይ ረቂቅ ነፍስ ናት፤ ለረቂቅ ነፍስ ደግሞ የሚሰዋላት ሕያው መስዋዕት ወንጌል ነው።”

-     “… የወንጌል ሰባኪው ራሱ ሕያው ወንጌል ነው፤ ብዙ ጊዜ ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ወይም ሃይማኖታቸውን በጥልቀት የማይመረምሩ፣ ለማንበብ ጊዜ የሌላቸው ምእመናን ሁልጊዜ የሚያነብቡት የአገልጋዩን ሕይወት ነው። …”

Wednesday, 29 April 2026

“በወንጌል ሕይወታችን ኾነ”

 Please read in PDF

“በወንጌል ሕይወታችን ኾነ” በሚል መሪ ቃል፣ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገር አቀፍ የወንጌል ቀን ለሦስተኛ ጊዜ ባለፉት ኹለት ቀናት አክብራ አሳልፋለች። ይህም በዋናነት ትኵረት ያደረገው፣ የወንጌልን ትምህርት በቋንቋ ተደራሽ ለማድረግ ከቀደሙት ዓመታት ይልቅ በተለየ ኹኔታ በማሰብ እንደ ኾነ ተገልጦአል። የቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ እንዳሉትም፣ “የቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ ዓላማ ምዕመናንን በቃለ እግዚአብሔር ወንጌል አንፆ ለክርስቶስ ዳግም ምጽአት ማዘጋጀት እንደ መኾኑ መጠን፣ ሰባክያን ምሳሌ ባለው ሕይወት ሊያገለግሉ ይገባል።” ብለዋል። ተያያዥነት ባለው መልኩ፣ በተለይም ወንጌል ለሚያገለግሉ ሰባክያን ልዩ ትኵረት እንዲሰጥና፣ ሰባክያኑም አገልግሎታቸው “ተልእኮ ተኰር” እንዲኾን ከታዳሚው በተደጋጋሚ ተጠቅሶአል።

Thursday, 23 April 2026

“በመንፈስ ተመላለሱ” (ገላ. 5፥16)

 

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፣ “የሥጋ ምኞት በመንፈስ ላይ፣ መንፈስም በሥጋ ላይ ነውና፤ ልታደርጉ የምትወዱትን እንዳታደርጉ እነዚህ እርስ በርሳቸው ይቃረናሉ” ይላል።  በዚህ በወደቀው ዓለም ውስጥ ስንመላለስ፣ ምንም እንኳ በክርስቶስ ኢየሱስ በደሙ ቤዝወት ከኩነኔና ከዘላለም ሞት ድነን፣ “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ የታጠብን፣ የተቀደስን፣ የጸደቅን" (1ቆሮ. 6፥11) ብንኾንም፣ በውስጣችን ግን የእግዚአብሔር በኾነውና በኀጢአት መገኘት ምክንያት ታላቅ ጦርነት አለ። በአንድ ማንነት ውስጥ ያሉ፣ ርስ በርሳቸው ደግሞ የሚቀዋወሙ ባላንጣዎች! የሥጋ ምኞታችን በማናቸውም መንገድ ለእግዚአብሔር አይታዘዜና እንዳንገዛ ከልካይ ነው። 

Sunday, 12 April 2026

“ተነሥቶአልና…፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ” (ማቴ. 28፥8)

 በክርስትና ታሪክ ውስጥ “ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ” እንደሚለው ያለ አስደናቂና አጽናኝ ቃል ጨርሶ የለም። ማቴዎስ ወንጌሉን ሲጽፍልን፣ ትንሣኤውን በልዩትነት መንገድ ነው። ይኸውም ስቅየቱንና መከራውን እንደ ዘገበ ወዲያው የትንሣኤውን ነገር ይነግረናል። ትንሣኤውንም የሚያቀርበው ልክ ክርስቶስን የሕግ ፍጻሜ ነው ብሎ (ማቴ. 5፥17) እንደሚያቀርበው እንደዚያው፣ ትንሣኤውንም የምድር አገልግሎቱ ማብቂያና መክተቻ፤ ፍጻሜ አድርጐ በውበት ያቀርበዋል።

Friday, 10 April 2026

“እነሆ ሰውዬው” (ዮሐ. 19፥6)

 Please read in PDF

ይህን ቃል የተናገረው ጴንጤናዊው ጲላጦስ ነው። የተናገረውም ስለ ስቁዩ ሎሌ መሲሕ ኢየሱስ ነው። የተናገረበትም ምክንያት፣ ቊ. 1 ላይ እንደምናነበው፣ ጲላጦስ ራሱ ኢየሱስን ገርፎታል፤ የያዙትም ሰዎች “ይዘብቱበትና ይደበድቡት ነበር፤” (ሉቃ. 22፥63) እንዲል፤ መግረፉንና “ለመግረፉ ድጋፍ ለማግኘት” የተናገረው ይመስላል፡፡ ክፍሉ በክርስቶስ ሕማማት ትረካ ውስጥ ወሳኝና ጌታችን በገዛ ወገኖቹ ፍጹም አለመቀበልን እንደ ገጠመው እንመለከታለን። ከምንም በላይ ደግሞ ሰዎች ኢየሱስን አሳልፈው ሲሰጡ፣ ምን ያህል ለጥቅማቸውና ለክብራቸው፤ ለሥልጣናቸው እንደሚጨነቁና አብ የተወደደ ልጁን በሚሰጠው ፍቅሩ ውስጥ ሰው ምን ያህል ኀጢአተኛ እንደ ኾነ በጥልቀት የምናይበት ነው።

Tuesday, 31 March 2026

ገማልያላዊ ማስተዋል

 Please read in PDF

“ … በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የከበረ የሕግ መምህር ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ በሸንጎ ተነሥቶ ሐዋርያትን ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ፥ እንዲህም አላቸው፦ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ስለ እነዚህ ሰዎች ምን እንደምታደርጉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። … ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ። ሰሙትም፥…” (ሐ.ሥ. 5፥34-35፡ 39-40)

“… በዚችም ከተማ በገማልያል እግር አጠገብ ያደግሁ፥ የአባቶችንም ሕግ ጠንቅቄ የተማርሁ፥ ዛሬውንም እናንተ ሁሉ እንድትሆኑ ለእግዚአብሔር ቀናተኛ የሆንሁ አይሁዳዊ ሰው ነኝ።” (ሐ.ሥ. 22፥3)