ሰው ታርዶ ብርሃን ከሰማይ ይወርዳልን?
ተአምረ
ማርያም እስጢፋኖሳውያን በንጉሡ ዘርዓ ያዕቆብ በመታረዳቸው ምክንያት ብርሃን መውረዱን ሲናገር እንዲህ ይላል፦
“... እኒህን
ከሐዲያን ከወገሯቸው ወዲህ ሠላሣ ስምንት ቀን በሆነ ጊዜ ... ስለእናቱ
ስለእመቤታችን ስለከበረ መስቀሉም የክርስቶስ መስቀል በሚከበርበት በመጋቢት ዐሥር ቀን ሰኞ ሌሊት እግዚአብሔር ድንቅ ተአምር አደረገ።
በንጉሡ ድንኳን ላይ ፍጹም ብርሃን ወጥቶ እንደ ጎርፍ ፈሰሰ። ... የዚያ ብርሃን መልኩም እንደ እሳት ላንቃ ይመስላል። ነገር
ግን አያቃጥልም ነበር። ወደ ሰውም በቀረበ ጊዜ ፊት ያበራል የብርሃኑም መታየት ልቡናን ደስ ያሰኛል ...” (ተአምረ ማርያም)[1]
“… ከዚህ በፊት ከቤተ
ክርስቲያን የተቀበሩትን ቅዱሳንም (ከመቃብር) አውጥተው በድንጋይ እንዲወግራቸው አዘዘ። ወታደሮቹ እንዳዘዛቸው አደረጉ። በዚህ ምክንያት በመንግሥቱ ብሔሮች ሁሉ ትልቅ
ፍርሃት ሆነ። ንጉሡ ለነዚህ ጥቂት መንጋ በሆኑ በቅዱሳን ዘንድ በቀር ክህደቱን እንደ ከሐዲው እንደ ዲዮቅልጥያኖስ አልገለጠም።
“እግዚአብሔር አማሌቅን ዘር ማንዘራቸውን በድብቅ እጅ ይመታቸዋል” ተብሎ እንደ ተጻፈው እግዚአብሔር ሲመታ አይገልጽም። እግዚአብሔር
እንዴት እንደ መታ (እነሆ)፤ ቅዱሳኑን ባሠቃያቸው ጊዜ እንደ ሚበተን የወናፍ ምድጃ እሳት ዓይነት እሳት አመጣ፤ በድንኳኑ ላይም
ታየ፤ እሱና ሠራዊቱ ግን ተደስተው፥ “ብርሃን በእኛ ላይ ወረደ” አሉ። ከሊቃውንቱ አንዳንዶቹ፥ “ብርሃን አይደለም፤ ይህ እንዲያውም
የእግዚአብሔር የቁጣው ምልክት ይመስላል። ይኽ ሰው የእግዚአብሔርን ባሮች ስላሠቃያቸው በላያችን ላይ የሚመጣብንን መቅሠፍት እንዴትና
ምን (እንደሚሆን ምን) እናውቃለን?” አሉ።” [2]
ዳንኤል፣
እኒህን ኹሉ ምክንያቶች በማቅረብ ለማምታታት የሚፈልገው ለምን እንደ ኾነ ሃሳቡ ግልጥ ነው፤ በእስጢፋኖሳውያን ላይ ያለውን ጥላቻ
በግልጥ ማሣየት ነው። ይህንም ታሪኩን አልኰስኩሶ በማቅረብ ይታወቃል፤ እስጢፋኖሳውያንን “አላዋቂና ጥበብ አልባ” አድርጐ ሲያቀርብ፣
ንጉሡን ግን “ስህተት አልባ፣ የዕውቀት መሠረት ያላቸው፣ መጻሕፍትን የደረሱና የዕውቀት ሽግግር ያደረጉ፣ ዕውቀትን ያስፋፉና ወደር
የማይገኝለት ተመራማሪ እንደ ነበር ይነግረናል”። አንድ ነገር እውነት ነው፤ ንጉሡ ዓለማዊና “ዘመናዊ” ትምህርትን ፍልስፍናዎችን
በጊዜው አስፋፍቷል፤ አንዳንድ መጻሕፍትን አስተርጉሟል፤ “ዘመናዊ መልክ እንዲይዙም” አድርጓል።
ነገር ግን ይህ ቅዱሳንን ከማሳደድ፣
ሰማዕታትን ከማረድ፣ ዓለማውያንና ሆድ አደር መነኰሳትን ወድዶና አቅርቦ እውነተኞች መነኰሳትን ማዋረዱ፣ ማረዱ፣ ማንገላታቱ፣ ደማቸውን
እንደ ውኃ ማፍሰሱ፣ ጽሕማቸውን መንጨቱ፣ የጭካኔና የአረመኔነት ተግባሩን መፈጸሙን መሸፋፈኛ አድርገን ልናቀርበው አይገባንም። ደግሞም ይህን ክፉ ሥራውን ለመደገፍ፣ ለዚህ ተግባራቸው “ብርሃን ከሰማይ
ወረደላቸው” ማለት፣ እግዚአብሔርን የክፋታቸው ተባባሪ ለማድረግ መቋመጥን ያሳያል።
እግዚአብሔር ኃጢአተኛ እንኳ እንዲገደል ፈቃዱ አይደለም፤ (ሕዝ. 18፥32፤
33፥11)። እኛ በሕይወት ያለነው እንኳ አኹኑኑ ንስሐ እንድንገባ እንጂ ባንገባ፣ በድንገተኛ ፍርድ የምንወሰድ ነን፣ ደግሞም ሌሎችን
ለመግደል መብት ያለን አይደለንም፤ (ሉቃ. 13፥1-5)። ሰውን በመግደል ብርሃን ከሰማይ ወርዷል ማለትም፣ የገዛ ሕይወቱን በማካፈል
በመልኩና በአምሳያው የፈጠረውን ሰው፣ ሌላው ሰው እንዲገድል ፈቅዷል ያስብላል። ይህ ግን ሐሰት እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታን
ያዘለ አይደለም።
የአፄ
ዘርዓ ያዕቆብ ቅዱሳንን መግደል፣ “ትክክል ነው” ለምትሉ!
ወንድሙን
በመግደል የታወቀና በተገለጠ ክፋት በመያዝ ከቃየል የባሰ በምድር ላይ አልነበረም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክ እርሱ እንዲገደል
ፈጽሞ አልወደደም፤ ፈቃዱና ሃሳቡም ኃጢአተኛ እንዲሞት ፈጽሞ አይደለም፤ “በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ
እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?” (ሕዝ. 18፥23) ብሎ በመናገሩ የቃየልን መሞትም ፈጽሞ
አልፈቀደም፤ “እንግዲህ ቃየንን የገደለ ሁሉ ሰባት እጥፍ ይበቀልበታል። እግዚአብሔርም ቃየንን ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት
አደረገለት።” እንዲል (ዘፍ. 4፥15)።
ማንም
ይኹን ማን ሰውን የመግደል መብት የለውም፤ ቃሉ በግልጥ፣ “አትግደል” (ዘጸ. 20፥13)፣ “የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ደሙ ይፈስሳል፤
ሰውን በእግዚአብሔር መልክ ፈጥሮታልና።” (ዘፍጥ. 9፥6)፣ “ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን
ያፈርሰዋል” (1ቆሮ. 3፥17)[3]፣
ደግሞም፦ “ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና” (ማቴ. 26፥52) ተብሎ ተነግሯል። ስለዚህም ማንም በሌላ ሰው ላይ እጅን ቢያነሣ
ባነሣበት መንገድ ብድራቱን ያገኛል።
ደቂቀ
እስጢፋኖሳውያንን አንዳንዶች ከፖለቲካው አንጻር፣ ሌሎች ደግሞ ሃይማኖትን ከመጠበቅ አንጻር ንጉሡ መግደሉ ትክክል ነው የሚል እሳቤን
ያንጸባርቃሉ። በኹለቱም መንገድ ግን ሰውን ለመግደል መልስ የሚሰጥ ነገር የለውም። እንኳን መንፈሳውያን፣ “መልካም ስብእና” ያላቸው
የዚህች ምድር አንዳንድ መሪዎች ሰውን መግደል ፈጽሞ የሚደግፉ አይደሉም። ሰውን ለመግደልም ኾነ ወደ ራሱ ለመውሰድ ሥልጣንና ችሎታ
ያው እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ (ዘፍጥ. 6፥7፤ 17፤ ዘዳግ. 28፥63፤ ሕዝ. 33፥28፤ ሶፎ. 1፥2-3፤ 18)።
ደግሞም ባሕርያቱ
ይህን ይመሰክሩበታል፤
1. እንደ ሮማውያን አላውያን ነገሥታት ሰዎችን እያታገለ በእነርሱ ይዝናና ነበር፤
ለዚህ አንድ ማስረጃ መጥቀሱ አስፈላጊ ሳይኾን አይቀርም።
“የንጉሣችን ዘርአ ያዕቆብ ባለቤት፤ የበእደ ማርያም እናት ዣን ከለላ ይባሉ
የነበሩት ንግሥት ከዕለታት አንድ ቀን፤ ኃጢአታቸውን ተናዘው ንስሐ ለመግባት ፈለጉና፤ በዘመናቸው የነበሩትን መንፈሳዊ አባት አባ
ተክለ ሐዋርያትን ወደ ቤተ መንግሥት አስጠሯቸው። መንፈሳዊው አባትም ጥሪውን ተቀብለው ወደ ቤተ መንግሥት ሄዱ። ንግሥቲቱን መክረው
አስተምረው ተገቢውን ንስሐ ሰጧቸው። ንግሥቲቱም በእደ ማርያም ይባል የነበረውን ልጃቸውንም እንዲመክሩላቸው እንዲያስተምሩላቸው መንፈሳዊውን
አባት ጠየቋቸው። በእደ ማርያም በእናቱ ምክር ተስማምቶ ከመንፈሳዊው አባት ቡራኬ ለመቀበል ፈቀደ። መንፈሳዊው አባትም መጻሕፍትን
እየጠቀሱ በእደ ማርያምን መክረው አጽናንተው ባረኩት።
ከዚያ በኋላ መንፈሳዊውን አባት ወደ ንጉሡ አቀረቧቸውና ከንጉሥ ዘርአ ያዕቆብ
ጋራ ተገናኙ። ንጉሡም የመንፈሳዊውን አባት ብቃትና ችሎታ ለማወቅ ፈልገው፤ ጥያቄዎችን አቅርበውላቸው በሰጧቸው መልስ ብቃታቸውን
ከተረዱ በኋላ፤ ከቤተ መንግሥቱ በር አጠገብ በነበረችው በእመቤታችን ስም በተሰየመችው ቤተ ጸሎት (ኒቆታ) ውስጥ እንዲቀመጡ ፈቀዱላቸው።
መንፈሳዊው አባትም በቤተ መንግሥቱ ጸሎት ቤት ለሦስት ወራት ቆዩ።
በቤተ መንግሥቱ ፊት ለፊት በነበረው ሜዳ ላይ፤ የመስቀል በዓል በየዓመቱ
ሲከበር በሚደረገው ሥርዓ የንጉሡ ጭፍሮች በፈረስ ግልቢያ በመወዳደር እስኪ ጎዳዱና እስኪ ገዳደሉ ድረስ እርስ በእርሳቸው በዱላ
ባጥንት በዘንግ ሲደባበደቡ ሲቀጣቀጡ መንፈሳዊው አባት ዐዩ። መንፈሳዊው አባትም፤ ንጉሡ ይህን አረማዊ ባህል ከማረም ይልቅ እንዲካሄድ
በመፍቀዳቸው በጣም አዘኑ። መንፈሳዊው አባትም “ይህን ያረመኔ ተግባር እያየሁ በቤተ መንግሥት ውስጥ በምቾት በመቀመጥ ጊዜዬን በከንቱ
ማባከን ነው። ንጉሡን መክሬ አስተምሬ ይህንን አረማዊ ልማድ እንዲያቆሙ ማድረግ አለብኝ” ብለው ወሰኑ።
በመጀመርያ በማስቆሙ እንቅስቃሴ ላይ ካህናቱ እንዲተባበሯቸው ጠየቁ። ካህናቱ
ግን ከፈለጉ እራስዎ ያድርጉት እንጂ እኛ ንጉሡን እንፈራለን ብለው ሊተባበሯቸው አልፈለጉም። መንፈሳዊው አባትም፤ ካህናቱ “ባይተባበሩኝ፤
ንጉሡ ምክሬንና ተግሳጼን ባይቀበሉም፤ ሊገድሉኝ ቢፈልጉም ይግደሉኝ እንጂ፤ ይህን አረማዊ ተግባር ዕያየሁ ዝም ብዬ ዘመኔን በከንቱ
አላሳልፈውም” ብለው ወሰኑ። ወደ ንጉሡ ከመቅረባቸው ነፊት ለሦስት ቀናት ከአምላካቸው ኃይልና ድፍረት እንዲያገኙ ጾሙ ጸለዩ።
ከሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት በኋላ ለግርማዊነትዎ የማቀርበው ትልቅ ጉዳይ አለኝና
ይፍቀዱልኝ ብለው መስከረም 21 ቀን ወደ ንጉሡ ላኩ። ንጉሡም ታማኝ አገልጋዮቻቸው ከነበሩት ከደብሮች አለቆች አንዱ ገብረ ኢየሱስ
በሚባለው በኩል “ለዛሬ አይመቸኝም” ብለው መለሱላቸው። መንፈሳዊው አባትም ለንጉሡ ማቅረብ ያሰቡትን ለደብተራ ገብረ ኢየሱስ አካፈሉት።
ማቅረብ ያሰቡትም፤ “በቤተ መንግሥት አደባባይ ላይ ሰዎች እርስ በእርሳቸው እየተደበደቡ እስከ መጋደል መድረሳቸው ለሰው ልጅ ክብር
ተስማሚ አይደለም” የሚል ሲሆን፤ በቤተ መንግሥት በቆዩበት ወቅት የታዘቧቸውን ሌሎችንም ስህተቶች “መታረም ይገባቸዋል” ብለው ለደብተራ
ገብረ ኢየሱስ አካፈሉት። ደብተራ ገብረ ኢየሱስ መንፈሳዊው አባት ለንጉሡ እንዲያደርሱላቸው የነገሩትን መልእክት ለንጉሡ ሊያደርስ
ይቅርና፤ ራሳቸው ይህን ድፍረት የተሞላ አቀራረብ ለንጉሡ ለማቅረብ በማሰባቸው እጅግ ተገረሙ።
ደብተራ ገብረ ኢየሱስ “ነቢየ አምላክ ሆይ” ንጉሡ ሠራዊቱ የሚያደርገውን
አረማዊ ባህል እንዲያስቆሙ ሊያስደርጉ ይቅርና፤ እርስዎንስ ከጭፍራው ተቀላቅለው ይደባበደቡ ብለው ግርማዊነታቸው ቢያዝዝዎ ምን ሊሉ
ነው? ብሎ መለሰላቸው። ከዚያ በኋላ ደብተራው፣ “ይዘልፍዎታል፤ ይንቅዎታል” እያለ መንፈሳዊውን አባት ከንጉሡ ጋራ የሚያራርቅና
የሚያጋጭ፤ የሚያስቆጣ ነገር እየጨመረ ለንጉሡ ነገራቸው። ንጉሡም ደብተራው ነበገራቸው የተጋነነ ነገር በመንፈሳዊው አባት ላይ ቁጣቸወ
ነደደ። “አፍቅሬና አክብሬ በቤተ መንግሥቴ ባስቀምጣቸው እንዴት ይህን ያል ሊንቁኝና ደፍሩኝ በቁ? በፍጥነት አምጧቸው” ብለው ንጉሡ
ወታደሮችን አዘዙ። ወታደሮችም መንፈሳዊውን አባት እያዳፉ ወደ ንጉሡ አቀረቧቸው። ንጉሡም “ግርማዊነታችንን እየዘለፉ ለደብተራው
የነገሩት እውነት ነውን? ከሕግ ውጭ ማንን ስንገርፍና ስንገድል ዐዩ? እንዴት ስማችንን ያጠፋሉ? ብለው በመንፈሳዊው አባት ላይ
የቁጣ ቃል አወረዱባቸው። መንፈሳዊው አባትም የንጉሡን ቁጣና ግልምጫ አልተቀበሉም። ይልቁንም “ንጉሥ ሆይ!” በቁጣ የተናገሩትን
ልስማዎና ልቀበልዎ ይቅርና፤ የቁጣዎ ቃል ካንደበትዎ በሚጐርፍበት ቅጽበት፤ ከርስዎ ቁጣ በድፍረት ለንጉሡ መለሱላቸው። ቀጠሉና
“ባካባቢዎ የሚፈጽሙት የፍርድ መዛባት፤ ዝሙትና ግርፊያ መቆም ይኖርባቸዋል” ብለው በድፍረት ተናገሩ።
ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብም መንፈሳዊው አባት በድፍረት በመናገራቸው አፋቸውንና
አፍንጫውን እንዲደበድቡ አዘዙ። ካፍንጫቸውና ካፋቸው ደም ጐረፈ። ይህ የሚደርስባቸው ስቃይ ሳይገታቸው መንፈሳዊው አባት ለንጉሡ
ሊነገር የሚገባውን ተግሳጽ መናገራቸውን ቀጠሉ። … ወደ ጽኑ እስር ቤትም እንዲወስዱ ወታደሮችን አዘዙ። ከጥቂት ዓመታት በኋላ ንጉሥ
ዘርዓ ያዕቆብ መንፈሳዊውን አባት ከእስር ቤት አስመጧቸው። መንፈሳዊው አባትም ከቀድሞው እጅግ በጠነከረ መንፈስ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብን
ገሰጿቸው። ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብም በመንፈሳዊው አባት ላይ ቁጣቸው የበለጠ ነደደ። አስደበደቧቸው፤ ወደ ጽኑ እስራትም እንዲመለሱ
አዘዙ። የመንፈሳዊ አባት መንፈሳዊ ኃይላቸው እየጋለ ቢሄድም፤ ከበትሩና ከእንግልቱ ጽናት የተነሣ ሰውነታቸው ደከመ።”[4]
እንግዲህ
ይህንን የሚያነብ የትኛውም መንፈሳዊ ሰው፣ ንጉሡ መንፈሳዊ ዕውቀትና ሕይወት ነበራቸው ብሎ ለመሞገት አንዳች የሚደፍረው ነገር የለውም።
ንጉሡ እንደ መጽሐፈ ብርሃን፣ እግዚአብሔር ነግሠ፣ ክህደተ ሰይጣን እና ሌሎችም ድርሰቶችን ቢጽፍም በሕይወት የተተገበረና እውነተኛ
ዕውቀት ነበር ብሎ ለመናገር አያስደፍርም። ሰይጣን ከማወቅም አልፎ፣ በመንቀጥቀጥ ያምናል፤ (ያዕ. 2፥19)፤ ነገር ግን የሚያውቀውንና
በመንቀጥቀጥ የሚያምነውን ነገር በመልካም ልብ አይታዘዘውምና ከእግዚአብሔር ዘንድ እድል ፈንታ የለውም።
2.
ንጉሡ ኹለት “ሕጋዊ” ሚስቶች ነበሩት፤ የአንዷ ስም በአልቲሐት- ዕሌኒ ወይም ጽዮን ሞገሳ ስትኾን ኹለተኛዋ ደግሞ
በአልቲሓት - ፍሬ ማርያም ወይም ዣን ኃይላ ትባል ነበር።[5]
በእውኑ በአዲስ ኪዳን ከአንዲት ሴት በላይ በሚስትነት መያዝ አመንዝራነት
አይደለምን? እንኳን እንዲህ በግልጥ አግብቶ መኖር መጽሐፍ ቅዱስ የልብ አመንዝራነትን በግልጥ የሚቃወም አይደለምን? ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ፦ “ወደ
ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።” (ማቴ. 5፥28) ብሎ እንዳስተማረን። በግልጥ ቃልስ የእግዚአብሔር
ቃል፦ “ ... ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ
ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች
ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።” የሚል አይደለምን?
3.
እጅግ ነፍሰ ገዳይ[6]
ከመኾኑ የተነሣ በምድር ላይ ማንንም ለማመን ተቸግሮ ነበር፤
“አቡነ
ቅዱስ እስጢፋኖስ ትክክለኛዋን ሃይማኖት ስላስተማረና እንደ ነቢዩ ቃል፥ “የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሱ፤
የአሕዛብ ነገዶች ሁሉ በፊቱ ይስገዱ፤ መንግሥት የእግዚአብሔር ነችና” ስላለ፥ በዚህ ምክንያት ገረፈው፤ ብዙም ቀጣው። (ሰማዕትነቱን)
እዚያው እስኪፈጽም ድረስ በእስር ቤት ዘጋበት። ከሱ በኋላ ልጆቹንም ብዙ ተንኮል ሠራባቸው፤ ለንጉሥ መስገድ እምቢ ስላሉ አይሁዳውያን
እያስመሰለ ፀረ ማርያም አላቸው። በዚህም ይገድላቸው ጀመር።
ይኸንን
በእግዚአብሔር ባሮች ላይ ሲሠራ፥ ጻድቃንንም ሲሰድብ፥ ንጹሕ ደም ሲያፈስ(ስለኖረ) በሰው እጅ የሚሞት ስለመሰለው በሕይወቱ ዘመን
ሁሉ ጥርጣሬ አደረበት፤ ስለዚህ ከሚያምናቸው ከጥቂቶች ባሮች በቀር ሌላ ወደሱ አያስገባም ነበረ።”[7]
አንዳንዶች ንጉሡ በመንፈሳዊው ዓለም ስም ገብቶ ያደረጋቸውን
አስቀያሚ ነገሮችን ለመሸፋፈን ረጅም መንገድ ሲሄዱ እንመለከታለን፤ ዳንኤል ክብረት ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዱና ዋናው ነው።
ለዚህም እንደ መሸፋፈኛ ንጉሡ ይህን ያደረጉት የመንግሥታቸውን ዙፋን ለመጠበቅ ነው የሚል “ሌላ አመክንዮ” ሲያቀርቡም እናስተውላለን።
ነገር ግን ይህ ሃሳባቸውም ቢኾን ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም። ምክንያቱም ንጉሡ በማናቸውም ክርክሮቹ ውስጥ ያነሣ የነበረው፣ ራሱን
እንደ ቤተ ክርስቲያን ተወካይና ጠበቃ አድርጐ በማቅረብ እንደ ኾነ ታሪኮቹን ስናጠና እንረዳለን፤ ለምሳሌም እኒህን በጥቂቱ መጥቀስ
ይቻላል፤
1. ራሱ ያጻፈው ተአምረ
ማርያም ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን የተገደሉበትና ከፍ መከራ ውስጥ እንዲልፉ ምክንያቱ ለማርያምና ለመስቀሉ አለመስገዳቸው እንደኾነ ይናገራል፤
2. ራሱ ንጉሡ ስለመሃላ
ተከራክሯል፤ ወይም አከራክሯል፤[8]
3. የቁርባን ጥያቄ
ተነሥቷል፤[9]
4. ራሱም የጻፋቸው
መጻሕፍት [መጽሐፈ ምስጢር፣ መጽሐፈ ባሕርይ፣ ጦማረ ትስብእት ... ] ለሃይማኖት ጥያቄዎች ራሱም መልስ መስጠቱን ያወሳሉ፤
5. ንጉሡ ከደቂቀ
እስጢፋኖሳውያን ውጪ ያደርስ የነበረው መከራና ስቃይ [ለማርያም፣ ለመስቀሉና ለእኔ ስገዱልኝ በሚል] በሌሎች ላይ መድረሱን የሚያሳይ
የታሪክ ሰነድ አናገኝም፤
6. የእስጢፋኖሳውያን
ምላሽ ኹሌም
መልሳቸው አንድና ግልጽ ነው፤ ከእግዚአብሔር ውጪ ለማንም አንሰግድም የሚል ነበር፤ እርሱም ስገዱልኝ ለማለት ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅስ ነበር።
7.
ኹሌም መናፍቃን አንዳንድ ሥፍራ ላይ ደግሞ አይሁዳውያን እንጂ የንጉሥ
ዓመጸኞች ተብለው ተጠቅሰው አይታወቅም፤ በንጉሥ ላይ ስለማመጻቸውም የሚያሳይ መረጃ ወይም በምን ምክንያት እንዳመጹ የሚያሳይ መረጃን
አንመለከትም።
ዘርዓ ያዕቆብን ፍጹም መልአካዊ አድርጐ ለማቅረብ ማሰብ ከአዲስ ኪዳን ትምህርት ጋር ፍጹም በተቃርኖ ያቆማል። ንጉሡ
ዘርዓ ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ቃል አንጻር ስተዋል፤ ተሳስተዋል፤ ወድቀዋል፤ ተንኮታኩተዋል። በመካከለኛው ዘመን ታሪክ ይኹን፣ ከዚያ
በፊትና በኋላም በቅዱሳን ሰማዕታት ላይ መፈጸም የሌለባቸው እጅግ አስፈሪ፣ አሰቃቂ፣ “የቤተ ክርስቲያንን ቤተ ክርስቲያንነት” ጥያቄ
ውስጥ ሊያስገባ የሚችሉ በርካታ ጸያፍ ተግባራት ፈጽመዋል። ይህን ከእስጢፋኖሳውን ውግዘት ጋር ብቻ አያይዞ እንደዋዛ ለማለፍ ማሰብ
በዚህ ዘመን ቀላል ይሆናል ብሎ ማሰብ ተላላነት ሳይኾን አይቀርም።
“በደቂቀ እስጢፋኖስ እንቅስቃሴ ትረካ በብዙኃን የቤተ ክርስቲያኗ ሰዎች ዘንድ
እንቅስቃሴውን ምንጊዜም ከውግዘቱ ጋር ብቻ አያይዞ የማየት ዝንባሌ አለ። ከአባ እስጢፋኖስ ህልፈት በኋላ በአፄ ናዖድ ዘመን ስለ
ተፈታው ግዝትና ስለተፈጸመው እርቅ እምብዛም አይነሣም። … ”[10]
ንጉሡ የሠሩትን አስተዳደራዊና ሥነ ጽሑፋዊ [ቤተ መንግሥታዊ] ሥራን እንደ
ፍጹም መንፈሳዊ ሥራ ማቅረብ ለፍርደ ገምድልነት ይዳርገናል። ከመንፈሳዊነት አንጻር ንጉሡን ቅንጣት ታህል ለማክበር አንዳች ምክንያት
የለንም። “ለንጉሡም ኾነ ለሌላ ለማናቸውም ፍጡር መስገድ አለባችሁ” በማለት፣ እስጢፋኖሳውያንን የገደሉበትንም መንገድ በማናቸውም
መንገድ አንደግፍም። ንጉሡም መንፈሳዊነትን ተገን በማድረግ መግደሉ ፈጽሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ ያለውም አይደለም።
እነ ዳንኤል ክብረት ይህን ደፍረው መናገር አለመቻላቸውና ይህን ለመሸፋፈን ማሰባቸው እጅግ “የብእር ሆድ አደርነታቸውን”
ዓሳይተዋል። በእርግጥ ዳንኤል ብቻ ሳይኾን፣ በዚህ መርሐ ግብር ላይ ካህሳይ ገብረ እግዚአብሔርም በመጽሐፋቸው ላይ ያላቸውን ጥንካሬ
ፈጽመው አጥተው ታይተዋል። በመጽሐፋቸው ላይ የንጉሡን ኢ መንፈሳዊነት ደፍረው የገለጹበትን አቅም እጅግ አላልተው በሚያሳዝን መልኩ
ሃሳባቸውን “ሲያጣጥፉ” ላያቸው “ሳያሳዝኑ” አይቀሩም[11]።
ምናልባትም ከቤተ ክርስቲያን ወይም በሥራ ገበታቸው ላይ የሚመጣባቸውን መገለልና መፈናቀል ፈርተው ሊኾን እንደ ሚችል እሙን ነው።
ማጠቃለያ
አባ እስጢፋኖስም ኾኑ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ይዘው የተነሡት ጥያቄ መንፈሳዊና
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ይህን ትምህርታቸውንም በድፍረት መስክረውታል። በቃል ብቻ ሳይኾንም በሕይወት ምስክርነትም ገልጠውታል፤ በመልካም
ተጋድሎም ደምድመውታል። እንደዚህ ዘመን አንዳች ወንጌል ሳይሰብኩ “የሰው እጅ ተመልካች ምንኩስናም” ሳይኾን፣ ወንጌል ያስተምሩ፣
ይመሰክሩ፣ ያውጁ፣ ይጸልዩ፣ ደግሞም በገዛ እጃቸውም ይሠሩ ነበር፣ ከሥራቸውም ጥረት የተነሣ እጅግ አስደናቂ “የዚያ ዘመን ቴክኖሎጂያዊ”
ሥራዎችን አበርክተዋል። ለሚያሙበት ትምህርታቸውም እስከ ሞት ድረስ በመታመንም ዋጋ ከፍለዋል። ይህንም ጨክነው በሕይወታቸው ሲያደርጉ
አንዳች አልተከፉም፤ በደስታ ተጐነጩት እንጂ።
ንጉሡ ዘርዓ
ያዕቆብ ግን ከዚህ በተቃራኒ እኒህን ቅዱሳን አሳደዱአቸው፤ ገደሏቸው፤ እጅግ በብዙ መከራ ውስጥ እንዲያልፉ አደረገ። ብዙ “ትምህርቶችን”
በመጥቀስ አባ እስጢፋኖስንና ደቀ መዛሙርቱን ቢከራከርም እነርሱ ግን በሚበልጥ የወንጌል ትምህርት ድል የነሡትም ለዚህ ነው። ንጉሡ
በወንጌል ትምህርትም ኾነ ሕይወት ከአባ እስጢፋኖስና ደቀ መዛሙርቱ ፈጽሞ የሚያንስ ነበር። እናም ንጉሡ በአባ እስጢፋኖስና በእስጢፋኖሳውያን
መበለጡ እጅግ ሳያበሳጨው እንደ ማይቀር ማስተዋል ይቻላል።
እስጢፋኖሳውያንን ዛሬም እንደ ተወገዙ ተአምረ ማርያም ቢነግረንም፣ ከግዝታቸው መፈታታቸውን ግን የቤተ ክርስቲያን
ታሪክ ደግሞ ይነግረናል፤ መወገዛቸው በራሱ ስህተት ኾኖ ሳለ፣ ተፈትተው እንደ ገና እንደ ተወገዙ አድርጐ ማቅረብ፣ አንድ ያልታወቀ
አካል[ነገር ግን ከዲብሎስ ወገን የኾነ] ከዚህ ሥራ ትርፍ ለማግኘት እየጣረ ለመኾኑ አያስተባብልም። እነ ዳንኤል እንዲህ እንደ
ሚቀልዱበት ሳይኾን የሰማዕታቱ ምስክርነት በቤተ ክርስቲያን አንደበት ሙሉ እውቅና እንደ ሚያገኝ፤ ነፍሰ ገዳዮቹ ደግሞ እንደ ቅዱስ
ቃሉ አንድ ቀን እንደ ሚወቀሱ እናምናለን። ደግሞም ይህ ባይኾን የአባ እስጢፋኖስንና ተከታዮቻቸውን የወንጌል ምስክርነት የሚያስተባብል
አንዳች ነገር የለውም።
ተፈጸመ።
[1]
ተአምረ ማርያም ግእዝና አማርኛ፤ 111 ተአምራትን የያዘ፤
1989 ዓ.ም 3ኛ እትም፤ አዲስ አበባ፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ ገጽ.98፤ ከቁ. 66-76።
[6] ፍስሐ ያዜ
ካሣ፤ የኢትዮጲያ የ5ሺ ዓመት ታሪክ፤ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግ
መጽሐፍ ፩፤ 2003 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ሕትመት አልፋ አታሚዎች፤ ገጽ 259፡፡
[7] ዝኒ ከማሁ ገጽ 222፤ ንጉሡ ከዚህም ባሻገር ብዙ መኳንንትን መግደሉን፣ የሚጠራጠራቸውን ኹሉ ከገዛ ቤተሰቡ ጀምሮ
እጅግ ብዙዎችን ማስፈጀቱን የታሪክ ድርሳናት በሚገባ ያስረዳሉ፡፡
ዳንኤል በዚህ ከቀጠልክ ሰዎችን እውነተኛ መዳን ከሚገኝበት ሰዎችን ሁሉ ወደ እውነት ከሚመራው መንገድ ፈቀቅ ማድርግህን ከቀጠልክ አንገትህ ላይ የወፍጮ ድንጋይ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባህር መወርወር ይቀልሃል።እባክህ ትውድ አታጣም። ምሁር እንደሆንክ አውቃለው ግን ለህይወት ተጠቀመው።የሰውን ሳይሆን ከቃሉ ብቻ በል።ካላለ አትበል።ያለዚያ ስተህ አሳች ከሆንክ ፍርድህ ብዙ ነው።የፍቅር ምክር!!!!
ReplyDeleteስለስግደት የበለአምን አህያ ጠይቋት ዘሁ 22:27 ታላላቆችን ማክበር ራስን ዝቅ ማድረግ ጣኦት ማምለክ ከተባለ እነ ሎጥ እነኢያሱ እነ ወንጌላዊው ዮሐንስ ጣኦት አምላኪዎች ነበሩ ማለት ነው??? ጌታም ጎንበስ ብሎ እግር ማጠቡም ስህተት ነው? እያላችሁን ነው? ከበለአም አህያ ያነሳችሁ ምስኪኖች ናችሁ።
ReplyDeleteውይ ውይ ውይ ውይ ዳንኤልን ለመናገር እና ለመተቸት ቅድሚያ ከራሥ ጋር መነጋገርና እራሥን መተቸት ያሥፈልጋል
ReplyDeleteተሃድሶ ቀፋፊ ሌላ ወሬ ኣጣህ?
ReplyDeleteዳንኤል እውነት ቢለማመድ ቢያወራ ትልቅ ሰው መሆን ይችል ነበር ማህሌተ ጽጌ እራሱ በቂ ነው ስለነ እስጢፋኖስ ግን ግእዝ ማውራት እና መተርጎም ይለያል
ReplyDeleteegzio marne Kristos
ReplyDeleteይህ ማለት በአለም የመጀመርያው የተሀድሶ እንቅስቃሴ ነው ከሉትራን ይቀድማል:: ወገኔ ጉንዳጉንዶ ማርያም ላይ ያለው ያልተበረዘ ትምህርት ነው እኛ ታሀድሶዎች የምንቀበለው::
ReplyDeleteasafari nigus
ReplyDeleteasafari nigus
ReplyDelete
ReplyDeleteዳንኤል እኮ ጽዱ መናፍቅ ነው
የወደቀ ነገራችንን ያነሳ ፀጋ ፤ይህ እንዲሆን አምላኬን ለምኜው ነበር፤ ማን ይመልስለት እያልኩ ስብሰከሰክ ነበር ተባረክ አቤኒ
ReplyDeleteይቅርታ አልገባኝም
ReplyDeleteጌታን መቀበል እንዴት?
ReplyDeleteበጭብጨባ ወይስ በእምነት?
የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል እምነት ቢኖረን፡-
-ሁለት ያለን ለሌለው እናካፍል ነበር
-30000 በላይ የእምነት ድርጅቶች አይኖሩንም ነበር
-ሴት የወንድ ልብስ አትለብስም ነበር(ከቃሉ ይልቅ ውበታችን አይበልጥብንም ነበር)
-እርስ በርሳችን እንዋደድ ነበር
-ኪሳችንን ደብቀን ጌታ ይባርክህ አንልም ነበር
… አንሸነጋገልም ነበር
ጌታ አይዘበትበትም!
kebatari
ReplyDeleteDeniale mene agebewe sela zara yakobe sela tareki ayegebeweme aketeri sejamere setete eyawete matsefe kafelega ka shiwe yajemere yane yagnem enekebelelan
ReplyDeleteእንዲይ የሚያስቀባጥርሽ ዳንኤል ክብረት ላይ ተይዘሽ ነው ፕሮፋይል ያደረግሻቸው ይዘውሽ ነው ስትቀይሪው ወደ ጤንነትሽ ትመለሻለሽ
ReplyDeleteቆይ ግን ትንሽሽሽ እኳን እግዚአብሔርን አትፈሩም ?????ብድግ እያላችሁ የራችሁን ኃጢአት ደብቃችሁ ሌላውን ስትወንጀሉ
ReplyDeleteበቃ የእናንተን ፍላጎት ካልተናገረ አትረኩም???,
የነ ዛራ ያይዕቆብ ጉድ ብዙ ነው ! ለምስል ለመስቀል ስገዱ ብሎ የማይስግዱትን ከወገብ በታች ቀብሩዋቸው በላይላቸው ፈረስ አስጋልቧል ዘመናት ያስረስው ብዙ የተደበቀ በክርስቶስ ወንጌል የተገለጠ ብዙ ምስጥር አለ ለምን ይዋሻል???
ReplyDeleteደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ንፁህ ኢትዮጵያዊ የተዋህዶ ልጆች ነበሩ፡፡ንጉሡ ዘረያዕቆብ ከደቀ እስጢፋኖስ ከመወገን ይልቅ ከኮፕቲክ ከመጡት የኢትዮጵያ ጠላት ፍናፍንት ጳጳሳት ጋር ወግኖ አስፈጅቷቸዋል፡፡እግዚአብሔር ብርሃን ያወረደው ለነዚህ ሰማዕታት ነው፡፡በርሃኑ ከወረደ በኃላም በሐገሪቱ ከባድ የተቅማጥ በሽታ መቶ ብዙ ህዝብ አልቋል፡፡የበለጠ በመሪራስ አማን በላይ የተጻፈውን "መጽሐፈ አብርሂት እና የጥንቷ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ታሪክ ማንበብ ነው፡፡ባብዛው በቤተክህነት ያሉ ከኢትዮጵያ ሊቃውንት ቅዱሳን ወጠቢባን ይል ለኮፕቲክ ግብፅ የሚያቃጥሩ ፍናፍንቶች ናቸው ዳንኤል ክብረትን ጨምሮ፡፡ስለዚህ የተዋህዶ ልጆች የሆንን ሁሉ ቅዱሳን አባቶቻችንን ሊቃውንቱን እንወቃቸው እንዘክራቸው፡፡የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ሐገራችንን ኢትዮጵያውያን ፣በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተዋጀችውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ቅዱሳን አባቶች የተጋደሉላት ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅል፡፡የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፤የጻድቃን የቅ.መላእክት ተራዳኢነት አይለየን አሜን!!!
ReplyDeleteፖለቲካና ኀይማኖት የየራሳቸው መስመር አላቸው በስመ ሀይማኖት ፖለቲካ አትነግድ አስመሳይ
ReplyDeleteቆናጽል! ስለ ደቂቀ እስጢፉኖስ ሳይገባህ የምትደናበር ደንባራ!
ReplyDeleteዳንኤል ክብረት (ዲ/ን) የሰጠው ሀሳብ ማዛናዊነት ያለው ሀሳብ ነው፡፡
one question for you, as a christian we believe that God, the son died for us when even were sinners. So how can this religion permit killing people that are made in his image and those that he has died for. In the Gospel Jesus said you have not helped me, you have not visited me when I was sick. And he was talking about the people that he has created rather than himself. So as a person who believes in Christ who has died in cross for all sinners, would not it be killing one sinner be killing Jesus him self?
Deleteአቤኔዘር ተክሉ ዋና ተሀድሶና የተሀድሶ ሰባኪ መሆኑን እንዲሁም የዲያቆን አቤኔዘር ተክሉ ብሎግ በሚል በከፈተው ብሎግና የፌስቡክ ፔጅ በመክፈት ስዎችን ሲያምታታ የነበረ መሆኑን እናውቃለን፤ ዛሬ ደግሞ ተሀድሶዎች መልስ የሚያሳጣቸውን ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን እንደልማዳቸው የሀሰት ውንጀላ በመወንጀል ከሰው ልብ ውስጥ ለማውጣት እየተራወጡ ነው። ሰይጣን ዛሬም በተሀድሶዎች ላይ አድሮ ይህችን ቤተክርስቲያን በአዲስ መልክ እየተዋጋት እንዳለ የሰሞነኞቹ በዲያቆን ዳንኤል ላይ እየቀረቡ ያሉ የውሸት ክሶች ማስረጃዎች ናቸው። እግዚአብሄር ልቦና ይስጣችሁ።
ReplyDeletebel bel sewya atemtsdk mecham danieln yemngr bkat ayenorhim afhin...sheft mnmn telalhi enda sheftam
ReplyDeleteYenebiye Geta amotshin metsafn silehatiyat yetsafewn degmeh degagmeh eyw ...aratu nebiyat beandnet yemiserutm chimr temelke
ReplyDeleteዳንኤልን ክብረት እውነተኛ የተዋህዶ ልጅ ነው እንጀ አንተ አይነቱ ጥራዝ ነጠቅ እሱን መተቸት አይችልም ፕሮቴስታንት ስለሆንክ ነው የጠላሀው እመነኝ በአንተ ንግግር ማንም አይታለልም
ReplyDelete