Friday, 30 November 2018
Sunday, 25 November 2018
ነገሌ አርሲ ኪዳነ ምሕረት ዛሬም የስብከት ርዕሳቸው እኛ ነን!
ከነጌሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ባሻገር፣ በኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን በግልጽ በከሳሾቻችን “አእላፋት” ክስ ተከሰን የቀረብነው 2005 ዓ.ም ነበር፤ ከዚያኔ ክሶች
የማይዘነጋኝ፦ “ኢየሱስን መካከለኛችን ነው” ብሎ ኮርስ ላይ አስተምሯል ብለው፣ ያስተማርኩበትንና ለተማሪዎች የሰጠኹትን የራሴኑ
ማስተማርያ አቀረቡ፤ በተመሳሳይ መልኩ ይኸንኑ ትምህርት ያስተማርኳትን “ጓደኛዬን” ምስክር አቁመው አስመሰከሩ፤ ያሳቀኝ ግን ከዚህ
በኋላ የተናገሩት ነው፤ “እኛ ጐጃምና ጐንደር ከሚገኙ ከታወቁ ጠንቋዮች ጋር ጥብቅ የትምህርት ቁርኝት እንዳለን በጊዜው የኪዳነ
ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የስብከተ “ወንጌል” ኀላፊ ተናገረ። እንግዲህ በእነርሱ አመክንዮ “ጐጃምና ጐንደር ውስጥ ʻኢየሱስ መካከለኛዬ ነውʼ
የሚል ጠንቋይ አለ ማለት ነው? …”፤ ለምን እንዲህ እንዳሉ ይገባኛል። ክሳችን ከወንጌል ውጪ እንደ ኾነ ሰዎች እንዲያምኑላቸው!!!
ዳሩ ከከንቱና ከውሸት ልፍለፋ አይዘልም! ያንን ኹሉ አልፈን ዛሬም በምሕረቱ አለን! ነገንም የምንመካው በጌታችን ኢየሱስ ብቻ ነው!
አንዳንዶች አብረውን ጀምረው ዛሬ ስለ ክርስቶስ ጨክነው አብረውን ባይቆሙም!
Friday, 16 November 2018
የሚጤስን ክር የማያጠፋ እውነተኛ ብርሃን! (ኢሳ. 42፥3)
Please read in PDF
የሚጤስ ክር ምኑ ነው የማይጠፋው? ራሱስ ሊጠፋ የሚጤስ አይደለምን? የተቀጠቀጠ ሸንበቆ ምኑ ነው የማይሰበር? ያልጠቀጠቀጠ ሸንበቆ በራሱ ምን አቅም ኖሮት? እልቅ ድቅቅ፣ ስብር እንክትክት ያለውን ደካማ ኀጥዕ፣ መሲሁ እንደሚያቃና፣ እንደሚያበረታታ፣ እንደሚያጸና ነቢዩ ኢሳይያስ የሩቁን እጅግ አቅርቦ አይቷል። ለወደቀው ማኅበረ ሰብ፣ ኢሳይያስ የመጽናናትን ቃል ይናገራል፤ እስራኤል ነጻ ትወጣለች፤ ተበታትናም አትቀርም፣ እንደገናም ትደራጃለች፤ ተስፋ የተቆረጠባት አገር ሆና አትቀርም፤ የዛሉት ምርኮኞቿን የሚያበረታታ ኀይል ይመጣላቸዋል፣ ይሰጣቸዋልም እያለ ነቢዩ ሕዝቡን ያበረታታል። በፍጻሜው ግን ክርስቶስ ሰዎችን ከኅጢአት ነጻ አውጥቶ፣ በታላቅ ትድግናውና ቤዛነቱ ድኅነት እንደሚሰጣቸው የሚያመለክትና፣ ለኀጥዐን ፍጹም ቸርነትና ርኅራኄ እንደሚያደርግላቸው የሚያመለክት ክፍል ነው።
የሚጤስ ክር ምኑ ነው የማይጠፋው? ራሱስ ሊጠፋ የሚጤስ አይደለምን? የተቀጠቀጠ ሸንበቆ ምኑ ነው የማይሰበር? ያልጠቀጠቀጠ ሸንበቆ በራሱ ምን አቅም ኖሮት? እልቅ ድቅቅ፣ ስብር እንክትክት ያለውን ደካማ ኀጥዕ፣ መሲሁ እንደሚያቃና፣ እንደሚያበረታታ፣ እንደሚያጸና ነቢዩ ኢሳይያስ የሩቁን እጅግ አቅርቦ አይቷል። ለወደቀው ማኅበረ ሰብ፣ ኢሳይያስ የመጽናናትን ቃል ይናገራል፤ እስራኤል ነጻ ትወጣለች፤ ተበታትናም አትቀርም፣ እንደገናም ትደራጃለች፤ ተስፋ የተቆረጠባት አገር ሆና አትቀርም፤ የዛሉት ምርኮኞቿን የሚያበረታታ ኀይል ይመጣላቸዋል፣ ይሰጣቸዋልም እያለ ነቢዩ ሕዝቡን ያበረታታል። በፍጻሜው ግን ክርስቶስ ሰዎችን ከኅጢአት ነጻ አውጥቶ፣ በታላቅ ትድግናውና ቤዛነቱ ድኅነት እንደሚሰጣቸው የሚያመለክትና፣ ለኀጥዐን ፍጹም ቸርነትና ርኅራኄ እንደሚያደርግላቸው የሚያመለክት ክፍል ነው።
አዎን!
በሥጋ ሞቱ ሊያድነንና ሊቤዠን ወደዚህ ዓለም የመጣው ቅዱሱ መሲህ፣ መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በኀጢአት ለወደቅነው ለእኛ
የሕይወት ትንሣኤያችን ነው። በመምጣቱ ፈጽሞ አድኖናል፣ ተቤዥቶናል፣ አስታርቆናል፣
ከአባቱና ከእርሱ፣ ከመንፈስ ቅዱስም ጋር እንኖር ዘንድ የጽድቅ ብቃት ኾኖናል፤ እርሱ በበደላችንና በኀጢአታችን ሙታን የነበርነውን
(ኤፌ. 2፥1)፣ እጅግ ሊጠፋ እንደሚጤሰው ክር ልንጠፋ የደረስነውን፣ ደቅቀን እንደ ሸንበቆ ያለነውን፣ አንዳች ጥቅም ያልነበረንን
… የተጠጋጋን ብቸኛ መጠጊያ አምባችን ነው፤ ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታችንና መድኀኒታችን።
Monday, 12 November 2018
ቤተ ክርስቲያን፣ ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 3)
Please read in PDF
1.1. ጥንቈላ
ይህ ችግር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በግልጥ እንዳለ ይታወቃል፤ ግን አይደፈርም፣
ደፍረው የሚናገሩ ይገደላሉ፣ ይገለላሉ፣ ይተቻሉ፣ ይነቀፋሉ፣ ይወገዛሉ፤ ነገሩ ግን ሥር ሰድዷል፤ ከምንናገረው በላይ በቤተ ክርስቲያን
ስምና አከባቢ ተሰግስገው አሉ፤ ዓርማቸው፣ መለያቸው፣ መታወቂያቸው … ቤተ ክርስቲያኒቱ የእኔ በምትላቸው ንዋያትና ሰዎች ጭምር
ነው። መስተፋቅር፣ አንደርቢ፣ ሰብስቤ፣ “አስማት” … የሚባሉ የጥንቆላ ሥራዎች በብዛት የሚሠሩት በቤቱ ጥቂት በማይባሉ ቀሳውስትና
ደባትራን ነው። ይህን ያጋለጡ ብዙዎች አይሰደዱ ተሰደዋል፣ አይንገላቱ ተንገላተዋል፤ ይህ ሲኾን እማኝ ምስክር ከሚኾኑት መካከል
አንዱ ነኝ! ጠንቋይ ቀሳውስትን፣ ደባትራንን፣ መሪ ጌቶችን፣ መነኮሳዪይቶችን … በመቃወማቸው የተሰደዱ፣ የተዋረዱ፣ የተገደሉ …
ሰዎችን ከሚያውቁ ምስክሮች አንዱ ነኝ!
የእግዚአብሔርን እውነተኛ አስተማሪነት (ኢሳ. 30፥20) አለመቀበል፤ በትምህርቱም
አለመጽናት የሐሰት መምህራን ትምህርት ሾልኮ ለመግባት ሠፊ በር ይከፍታል (2ጴጥ. 2፥1)፤ በቤተ ክርስቲያናችን እንደ ቤተ ክርስቲያናችን
የመጻህፍት ጽህፈት ቀኖና መሠረት በቀለማት አጊጦ ከሚባዙትና ከቤተ ክርስቲያኒቱ መጻህፍት ጋር ታትሞ እኩል በየመጻህፍት መደብሩ
ከሚሸጡት መጻህፍት መካከል አንዱ ዐውደ ነገሥት የሚባለው የጥንቈላ መጽሐፍ ነው። መሥተፋቅር፣ አስማት የሚደግሙ፣ ሞራ ገላጮች፣
መናፍስት ጠሪ፣ ሙታን ሳቢዎች … እና ሌሎችም የጥንቈላ ሥራዎች ሁሉም ለማለት ሊያስደፍር በሚችል መልኩ የሚከናወነው ከደብተራ እስከ
ካህናት ባሉት የቤተ ክርስቲያኑቱ አገልጋዮች ነው።
Thursday, 8 November 2018
Saturday, 3 November 2018
ቤተ ክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 2)
Please read in PDF
ኹሌም የቤተ ክርስቲያንን ችግር
አንስተን ከብዙ ወገኖች ጋር በግልም በጋራም ስንወያይ፣ ውስጤን የሚነካኝና የሚያስጨንቀኝ ነገር ይህ ነው። ወደ ዋናው የችግሩ መንስኤ
መሄድን አንፈልግም። በደፈረሰው ወራጅ ላይ እንከራከራለን፣ የወራጁን ምንጭ የማጥራት ሥራ ላይ ለመረባረብ እንገፋፋለን እንጂ መሠረታዊውን
ችግራችንን፣ ከምንጩ ያፈነገጠውን ነገራችንን አጢነን፣ አስተውለን በልበ ሰፊነት ልናይ፣ ልንወያይ፣ በልበ ሰፊነት ተነጋግረን …
መፈለግንም ማድረግንም (ፊልጵ. 2፥13) ከሚሠራው ጋር ለመሥራትና ለመቃናት አንተባበርም። ምንጩ ሲጠራ ወራጁም እንደሚጠራ እናውቃለን
እንጂ አምነን ለመነሣት ለክፋት ጨካኞችና ለእግዚአብሔር ፍጹም ያደላን አይደለንም። ከዚህ የሚከፉት ይልቅ ያሉትን ችግሮች ብናይ
በአሁን ሰዓት በግልጽ ከሚታዩት ችግሮች አንዱና ዋናው፦
Sunday, 28 October 2018
ከ“ቄስ” በላይ መኮንንና ከኢዩ ጩፋ ጀርባ የቆመ የዘረኝነት ግንብ
Please read in PDF
በዘመናችን ባለው ክርስትና ውስጥ፣
እንደ ዘረኝነትና መናፍቅነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የተሰፋለት ነውር ኃጢአት ያለ አይመስልም። ኹለቱም መንፈሳዊ ካባ ለብሰው፣ ራሳቸውን
ሸሽገው፣ ሾልከው ከመካከላችን ገብተው አሉ። ከኀጢአት ኹነኛ ባሕርያት አንዱ እንዳይታወቅ ራሱን መሸሸግ ነው፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ባስተማረው የዘር ምሳሌ ላይ ጠላት እንክርዳድን የዘራው፣ “ሰዎቹ ሲተኙ” ነው፤ (ማቴ. 13፥25) ይህም ማለት ጠላት ዲያብሎስ መልካሙ
እርሻ መልካም ብቻ እንደ ኾነ እንዲዘልቅ ፈጽሞ አይፈልግም ማለት ነው።
Saturday, 27 October 2018
ከመጽሐፌ፣ ዘለላ ቁም ነገር
የጻፍኩት መጽሐፍ በጠቅላላ ስምንት ምዕራፎች አሉት፤
የገጽ ብዛቱ ደግሞ ከመጻፌ ምክንያት እስከ መግቢያ ያለውን ሳያካትት፣ 311 ነው፤ የመጽሐፉ ይዘት የእምነት እንቅስቃሴ አማኞች
ስለሚያምኑባቸው ዋና ዋና ኢ ክርስቲያናዊ አስተምህሮ በስፋት ያትታል፤ ከዚያ ውስጥ አንዱ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ አረዳዳቸው ጠማማና
ኢ ዐውዳዊ መኾኑ ዋነኛው ነው፤ ለዚህ “ዘለላ ቁም ነገሬ” እንደ አንድ ማሳያ የተጠቀምኹት፣ ኤሴክ ዊሊያም ኬንየን በአንድ መጽሐፉ
ዮሐ. 3፥16 ላይ “… በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ
ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፤” የሚለውን ቅዱስ ቃል ሲያብራራ እንዲህ ይላል፤ “ … እግዚአብሔር
አብ ዓለምን ስላፈቀረ አንድያ ልጁን ሰጥቶአል። ኢየሱስ ክርስቶስም ዓለምን እንዲሁ ስላፈቀረ ራሱን አሳልፎ ሰጠ። እኔም አኹን
ዓለምን ስላፈቀርኩ ራሴን አሳልፌ ሰጥቼአለሁ። ምንም ዐይነት ሂስና ስደት ይምጣ ልቤ በዓለም ላይ ምሬትን እንዲያስተናግድ
አልፈቅድም። በእነዚህ ሰዎች ላይ ጊዜዬን በከንቱ አጠፋሁ ለማለት ሲዳዳኝ በፊልጵስዩስ በጳውሎስና ሲላስ ላይ የደረሰውን
አስታውሳለሁ” ይለናል፤ (የእምነት እንቅስቃሴ - የዛሬዪቱ ቤተ ክርስቲያን ፈተና፤ ገጽ 38-41)።
Wednesday, 24 October 2018
“እንደ ኦሮሚያ ክልል ቤተ ክህነትን ማቋቋም እፈልጋለሁ”
ማሳሰቢያ - ረጅም ንባብ ነው!
እነ አባ ገዳ ተሾመ እንዲያው ዝም ብለው ብቻቸውን፣ “የኦሮሚያ ሲኖዶስ ይቋቋም” ለማለት አይደፍሩም፤ ደግሞም ሥልጣንም የላቸውም። ነገር ግን የራሷ “የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች እጅ” እንዳለበት እርግጠኛ ኾኖ መናገር ይቻላል። ለዚህ ደግሞ የነ“ቀሲስ” በላይ እጆች ረጅም ብቻ ሳይኾኑ፣ እሬቻዊ አምልኮ በግልጥ ከክርስትና ጋር ለመስፋት የሚጥሩ ናቸው። “ቄስቻው” በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ይንቀሳቀስ እንጂ ለቤተ ክርስቲያኒቱ እንጥፍጣፊ ፍቅርና ለክርስትና ደንታ እንደሌለው፣ የዛሬ ሦስት ዓመት በOBS የኦሮሚኛ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ በ“harka fuune” (ቤት ለእንቦሳ) በሚለው ዝግጅት ላይ ከጋዜጠኛ አብዲ ገዳ ጋር “ረዥም” ቃለ መጠይቅ ማድመጥ በቂ ማሳያ ነው። “የኦሮሚያ ሲኖዶስ የመቋቋም ጥንስስም” ጅማሮው የሰነበተ መኾኑን ማስተዋል አይከብድም፤ ይህን ቃለ ምልልስ ከሰማሁት በኋላ ሊያስተምርና ሊያወያይ እንደሚችል ስላሰብኩበት ተርጉሜው ለማቅረብ ወደድኹ። ይህን ቃለ ምልልስ አንብበው፣ ቃለ ምልልሱ በኋላ “ኦርቶዶክሳዊ ሃሳብ ነው” የሚሉ ይኖሩ ይኾንን? ብዬ መጠየቅ እፈልጋአለሁ፤ አይደለም የምትሉ ደግሞ እንግዲያው “ዘርን ወይም አንድን ክልል ማዕከል ያደረገ ሲኖዶስ” ጥንስሱ ዛሬ እንዳልኾነ፣ አባ ገዳ ተሾመም ኾኑ ሌሎች ይህን እንዲሉ አነሳሽ ኀይላት ከጀርባ እንዳሉ ማሳያ ይኾናል በማለት ነው። የ“ቄስቻው”ንም ማንነት በዚያውም መመልከት ተገቢ ሳይኾን አይቀረወም፤ መልካም ንባብ እላለሁ።
Saturday, 20 October 2018
Friday, 19 October 2018
ቤተ ክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 1)
Please read in PDF
መግቢያ
“ … በቤተ ክርስቲያን
መጻሕፍት ላይ ሂስ ማድረግ እንደ ክህደት ስለሚቈጠር ብዙ አስተያየት አልዳበረም። ይህ ባህል ቅዱስ መጽሐፍን ተመራመሩ የሚለው መሠረተ
ሐሳብ ተመራመርና እመን ከሚለው ንድፈ ሐሳብ በተቃራኒ እመን ግን አትመራመር ከሚል ንድፈ ሐሳብ ላይ ይመሠረታል።”[1]
በእርግጥ ዶ/ር ዲበኩሉ ዘውዴ ያቀረቡት ይህ ሐሳብ፣ “እንደ ኢትዮጵያ
ልምድ ስለ ፍትሐ ነገሥት ዝግጅትና የትርጉም ሥራ ላይ አብርሃም ወልደ ሐናናጥያን ምንም ሚና እንዳልተጫወተ እየታወቀ አለመተቸቱንና
እንደ ወረደ መቀበላችንን በግልጥ ለመናገር ወይም ለመተቸት በማሰብ ነው። እውነታው ግን ለፍትሐ ነገሥት ብቻ ሳይኾን፣ በጠቅላላው
አሁን ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ማለትም አስተምህሯዊ ችግሯን፣ አምልኳዊ ጉድለቷን፣ ሥነ ምግባራዊ ውድቀቷን
… በጐላና በተረዳ ጎኑ የሚያጸባርቅ ነው።
Sunday, 14 October 2018
ሥራ ፈቶችና ክፉ ሰዎች በደብረ ዘይቷ ቢሾፍቱ!
Please read in PDF
“ … አይሁድ ግን ቀንተው ከሥራ
ፈቶች ክፉ ሰዎችን አመጡ ሕዝብንም ሰብስበው ከተማውን አወኩ፥ ወደ ሕዝብም ያወጡአቸው ዘንድ ፈልገው ወደ ኢያሶን ቤት ቀረቡ፤
…” (ሐዋ. 17፥5)
በሐዋርያው በቅዱስ ጳውሎስ ኹለተኛ ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ እጅግ አስደናቂና
አሳዛኝ፣ ስደትና ደስታ፣ መከራና ዕረፍት፣ ድብደባና እርካታ ተስተውሎበታል። ቅዱስ ጳውሎስ በሄደበት ኹሉ የሚሰብከውን ወንጌል አሜን
ብሎ የተቀበለው አንዳች አካል አልነበረም፤ ከእጅግ ጥቂቶች በቀር፤ የመዳንና የጸጋውን ወንጌል ቅዱስ ጳውሎስ የሰበከው ብዙ ተቃዋሚዎችና
አሳዳጆች እረፍት እየነሡት ነው። ከሚሰብከው ወንጌል ጎን ለጎን ተመጋጋቢ ስደትና መከራ፣ እስርና እንግልት አለ! በተሰሎንቄ ከተማ
የገጠመው እንዲህ ያለ ነገር ነው።
Saturday, 13 October 2018
Friday, 12 October 2018
Saturday, 6 October 2018
Subscribe to:
Posts (Atom)



