በአንዳንድ የስልክ
ጥሪዎች ውስጥ የሚሰሙ ድምጾች ለዘላለሙ ከልብ ታትመው ይቀራሉ! 2009 ዓ.ም አንድ ሰንበት ሙሌ የተባለ ውድ ወዳጄ አንዲት እህት እርዳታ እንደምትሻ በስልክ ነግሮኝ፣ ስልኳን አቀብሎኝ እንዳገኛት ድልድይ ኾነን። የሄድኩት አንዲት ብቻዋን፣ ተስፋ ቆርጣ ራስዋን ለማጥፋት ዝግጅት አጠናቅቃ የመጨረሻ ኑዛዜዋን ልትነግረኝ ወዳለች አንዲት እጅግ ከሲታ ግን እጅግ ልጅ ወደ ኾነች ሴት ነው።
ለኹለት ሰዓት ተኩል ያህል ሳታቋርጥ እንባዋ እየተንዠቀዠቀ የደረሰባትን ሰቆቃ አወራችኝ። አዎን! የደረሰባት ሰቆቃና ግፍ ጆሮ ጭው ያደርጋል። መንፈሳዊ በሚባሉና በገዛ ቤተሰቦቿ የተፈጸመባት ግፍ የነቢዩ ኤርምያስን ዘመን ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ለመምከር አቅም አልነበረኝም፤ እንዲህ ያለ መራራ ነገር "ባልጠና አቅሜ" እንድሠማ ጌታ ለምን እንዳደረገኝ አላውቅም፤ ብቻ ጌታ ኢየሱስ በመንፈሱ ረዳኝ፤ ወደልቧ ተመለሰች፤ ቅዱስ ቃሉን ሰማች፤ ተመለሰች፤ ለመታነቅ ያዘጋጀችውን ገመድና የበጠበጠችውን መርዝ አውጥታ ጣለችው። ዛሬ መልካም ባልንጀሮች ነን።
ሌላ ታሪክ፤ መጽሐፌ ከታተመ ገና አንድ ወር አልሞላውም፤ በትምህርቱ ተጠልፈው የወደቁ ኹለት እህቶች ግን መመለሳቸውን፣ ጌታም እንደደረሰላቸው ስሰማ፣ በልቤ እንዲህ አልኹ፤ "መጽሐፉን የጻፍኹበት ዓላማዬ ተፈጸመ፤ መሻትና ምኞቴ የጠፉ እንዲድኑ፣ የባከኑ እንዲሰበሰቡ ነበርና፣ ኾነልኝ ... የኹለት ሰው መጥፋት ማለት የአንድ ቤተክርስቲያን መጥፋት ሲኾን የኹለት ሰው መገኘት ደግሞ የቤተክርስቲያን መገኘት ነው። ደስታዬ ተፈጸመ፤ ክብሩን ጌታዬ ኢየሱስ ይውሰድ።" አዎ! ደስታዬ ተፈጸመልኝ፤ ከንግዲህ መጽሐፉ ባይሸጥስ ምን ገዶኝ?!
ገና መጽሐፉን ሳታነቡ በስድብና በዛቻ፣ በተዋረደ ሞት "እንገድልሀለን" ያስፈራራችሁኝ "ወንድሞችና እህቶች" መሻቴ ተፈጽሞልኛልና ደስታዬ ድርብ ኾኖልኛል። በስሙ መነቀፍም የጠፋው ሰው ለክርስቶስ መገኘትም እጥፍ ደስታ ነውና! ከመጀመሪያውስ ዐላማዬ ለክርስቶስ ወንጌል ብቻ እንጂ መች ሌላ ነገር ኾነና?! በፍጹም አይደለምም! ጌታዬ ኢየሱስ ቢረዳኝ የተመለሱትም ሰዎች ፈቃዳቸው ከኾነ፣ በኹለተኛው እትምና በጡመራ መድረኬ የትምህርቱን መርዛማነትና ክርስቶስን የማይወድ መኾኑን አካትቼ የማቀርብ መኾኑን ቃል እገባለሁ፤ ክብር ለታረደው ግን ደግሞ ለቆመው በግ ለጌታ ኢየሱስ ይኹን፤ አሜን።
How can we get your book?
ReplyDeleteየሰራ እውነት የተናገረን ማን ይወደዋል ብለህ ነው ወንድሜ
ReplyDeleteThis comment has been removed by a blog administrator.
Delete0911044555 ወይም 0928724849 ወይም 0911393521 መደወል ይቻላል፡፡ ወይም 4 ኪሎ ዩንቨርሳል፣ ስቴዲየም የዕውቀት በር፣ ጌቱ ኮመርሻል ሕንጻ ኢማና መጻሕፍት መደብር ይገኛል፤ የጌታ ኢየሱስ ጸጋና ሰላም ይብዛልህ፤ አሜን፡፡
Deleteየሀሰት ና የሰይጣን ት፡ት ነው የብልፅግና ወንጌል።
ReplyDeleteልክ ብላቹዋል የአጋንት አገልጋዬች ናቸው ስለብልፅግና የሚሰብኩት ኢየሱስ ስጥኖል እስከ ማለት የደረሱ ደፋሮች ናቸው
ReplyDeletetebarek abeni
ReplyDelete