የጻፍኩት መጽሐፍ በጠቅላላ ስምንት ምዕራፎች አሉት፤
የገጽ ብዛቱ ደግሞ ከመጻፌ ምክንያት እስከ መግቢያ ያለውን ሳያካትት፣ 311 ነው፤ የመጽሐፉ ይዘት የእምነት እንቅስቃሴ አማኞች
ስለሚያምኑባቸው ዋና ዋና ኢ ክርስቲያናዊ አስተምህሮ በስፋት ያትታል፤ ከዚያ ውስጥ አንዱ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ አረዳዳቸው ጠማማና
ኢ ዐውዳዊ መኾኑ ዋነኛው ነው፤ ለዚህ “ዘለላ ቁም ነገሬ” እንደ አንድ ማሳያ የተጠቀምኹት፣ ኤሴክ ዊሊያም ኬንየን በአንድ መጽሐፉ
ዮሐ. 3፥16 ላይ “… በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ
ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፤” የሚለውን ቅዱስ ቃል ሲያብራራ እንዲህ ይላል፤ “ … እግዚአብሔር
አብ ዓለምን ስላፈቀረ አንድያ ልጁን ሰጥቶአል። ኢየሱስ ክርስቶስም ዓለምን እንዲሁ ስላፈቀረ ራሱን አሳልፎ ሰጠ። እኔም አኹን
ዓለምን ስላፈቀርኩ ራሴን አሳልፌ ሰጥቼአለሁ። ምንም ዐይነት ሂስና ስደት ይምጣ ልቤ በዓለም ላይ ምሬትን እንዲያስተናግድ
አልፈቅድም። በእነዚህ ሰዎች ላይ ጊዜዬን በከንቱ አጠፋሁ ለማለት ሲዳዳኝ በፊልጵስዩስ በጳውሎስና ሲላስ ላይ የደረሰውን
አስታውሳለሁ” ይለናል፤ (የእምነት እንቅስቃሴ - የዛሬዪቱ ቤተ ክርስቲያን ፈተና፤ ገጽ 38-41)።
ይታያችሁ እንግዲህ፣
ይህ ሰው ራሴን ለእናንተ አሳልፌ ሰጥቻችኋለሁ እያለን ነው¡ ለራሱ ነፍስ እንኳ የማይበቃው ሰው፣ “ለመላው ዓለም ዓለምን ስላፈቀርኩ
ራሴን ሰጥቻለሁ” ይለናል። ይህ ሰው፣ ጌታችን ኢየሱስ፣ “ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?” (ማር. 8፥37) በማለት
የተናገረውን የሚያምን ይመስላችኋል?! የቅዱስ ቃሉ ዐውድ አጣማሚ እንደኾነ አስተውሉ! እጅግ ደፋሮችና ዓመጸኞች ናቸው፤ የእኒህን
መርዝ ትምህርት ነው እንግዲህ፣ እነ በጋሻው ደሳለኝ፣ እነ ኃይሉ ዮሐንስ፣ እነ በረከት ዮሴፍ፣ እነ ጃፒ፣ እነ ዘላለም ጌታቸው
… “በአስባበ መገለጥ” ሊግቱን የሚፈልጉት።
ኬኔት ኮፕላንድ ደግሞ ማቴ. 6፥20ን ጌታ
እንዴት በራእይ እንዳብራራለት ሲናገር፦ “አንድ ከሰዓት በዴይቶ ኦሃዮ በነበረው ስብሰባ ጸሎት ላይ ሳለኹ ጌታ
ወደዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ትኩረቴን ሳበ። [ማቴ. 6፥20 ማለቱ ነው] ብል የማይበላው፣ ዝገት የማያጠፋው መዝገብ በሰማይ
ይኹንላችኹ የተባለው ይህ ዝገትና ጥፋት የዋጋ መጋሸብና የኢኮኖሚ ዝቅጠት ነው” አለኝ።” ይላል፤ እንግዲህ
አስተውሉ፤ ኹሉ ነገር ወደ ምድር ወርዷል፤ ሰማይና ሰማያዊ ሃብት ኹሉ ለምድራዊው ሊታዘዝ ሎሌ ኾኗል፤ ወደ ሰማይ አታስቡ፣ በሰማይም
ተስፋ የለም፣ ኹሉ ነገር ከምድር፣ ለምድር፣ በምድር ነው ይሉናል፤ እንኪያስ እኒህን የሚታገስ ምን አንጀት፣ ምን መንፈሳዊ ቅንአት
ይኖር ይኾን?
መጽሐፉ በውስጡ ብዙ መረጃዎቻቸውን በመጥቀስ ትምህርታቸውን ያጋልጣል፤ በመጽሐፍ
ቅዱስ ይመዝናል፤ ይጥላል፤ ያዋርዳልም፤ ለመጽሐፉ ቃል አለመታመናቸውን ይዘልፋል፤ የቅዱስ መጽሐፉን ቃል ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ያልቃል፤
ፊታችንን ወደ ቅዱስ ቃሉ ብቻ እንድናዞር አበክሮ ያስጠነቅቃል፤ የሰውን፣ የሥጋና የደምን ትምህርት አብዝቶ ይጠየፋል፤ ለቃሉ ብቻ
ያለውን ታማኝነት ያሳያል።
ውድ ወንድሞችና
እህቶች፣ አባቶችና እናቶች እኔም እንደ ቅዱስ ቃሉ ለመማር፣ ለመፈተሽ፣ ለመመርመር፣ ለመመዘን ዝግጁ ነኝ።
ይህን መጽሐፍ ማግኘት የምትፈልጉ አድራሻውን እንደገና ማሳወቁ አግባብ መስሎ
ታይቶኛል፤ ክፍለ አገርና በውጭው ዓለም ያላችሁ በብዙ የምትጠይቁኝ ለመድረስ እየጣርኹ ነው፤ ግን በአንድነት ተሰባስባችሁ በአንድ
ሰው ኃላፊነት ለመላክ እንዲመቸኝ ብታደርጉ እጅግ መልካም ነው። +251 911 04 45 55 ወይም +251 928 72 48 49
ወይም +251 911 39 35 21 ብትደውሉ ማግኘት ትችላላችሁ፤
አዲስ አበባ
-
አራት ኪሎ ዩንቨርሳል መጻሕፍት መደብር
-
ስቴዲየም የዕውቀት በር መጻሕፍት መደብር
-
ቦሌ ጌቱ ኮመርሺያል ኢማና መጻሕፍት መደብር
-
ፒያሳ በእምነት መንፈሳዊ መጻሕፍት መደብር
አዳማ
+251 912 21 52 96
አርሲ
ነጌሌ +251 916 50 60 88 ወይም +251 974 76 17 96
ሻሸመኔ
+251 968 65 90 93
ጅግጅጋ
- 0920438151 (በቅርብ ቀን)
አዋሳ
- አበራ መጻሕፍት መደብር ከመናኸርያ ፊት ለፊት
መቂ
+251 924 75 94 25
ሐረር
+251 906 77 14 42
ደብረ
ዘይት +251 920 37 63 68 ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ። ጌታ በነገር ኹሉ ማስተዋልን ያብዛልን፤ መንፈስ ቅዱስ የሐሰት መምህራንን
ልብ ወደንስሐ ይምራ፤ አሜን።
tru sra new aben tebarek
ReplyDeletetsega yibzalh wendme. berta tru metsaf new. agignche anbibewalew
ReplyDeleteGeta abzto ybarkh. tru sra new
ReplyDeleteeskahun kayehut leyet yale sra new. berta berata ....Geta bzih zemen yasnesah mrt wendm neh.
ReplyDeleteወቅታዊ ጉዳይ ማንሳትህ ለብዙ ሰው ከጥፋት እና ከኣታላይነት እንደሚያተርፍ እምነት ኣለኝ። እንዲህ አይነት ስራዎች እንዲበዙልን ጌታን እንማጸናለን
ReplyDeletetsega yibzalh. ejg yemiyanits sra new. betaaaam temrebetalw
ReplyDeleteይህን መጽሐፍ አይቼዋለሁ፡፡አንዳንድ ያልገቡኝ ነገሮች ቢኖሩም ብዙ አዳዲስ ነገሮችን አይቼበታለው፡፡በተለይ ብዙ ጥያቄዎችን መልሶልኛልና ወድጄዋለሁ፡፡ለሌሎች ሁለት ሰዎችም እንዲያቡ ጋብዣለሁ፡፡ከቻልኩ ግን ጥያቄዎችን ማቅረብ የሚቻልበት መንገድ ቢኖር መልካም ነው፡፡
ReplyDelete