Please read in PDF
“ … አይሁድ ግን ቀንተው ከሥራ
ፈቶች ክፉ ሰዎችን አመጡ ሕዝብንም ሰብስበው ከተማውን አወኩ፥ ወደ ሕዝብም ያወጡአቸው ዘንድ ፈልገው ወደ ኢያሶን ቤት ቀረቡ፤
…” (ሐዋ. 17፥5)
በሐዋርያው በቅዱስ ጳውሎስ ኹለተኛ ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ እጅግ አስደናቂና
አሳዛኝ፣ ስደትና ደስታ፣ መከራና ዕረፍት፣ ድብደባና እርካታ ተስተውሎበታል። ቅዱስ ጳውሎስ በሄደበት ኹሉ የሚሰብከውን ወንጌል አሜን
ብሎ የተቀበለው አንዳች አካል አልነበረም፤ ከእጅግ ጥቂቶች በቀር፤ የመዳንና የጸጋውን ወንጌል ቅዱስ ጳውሎስ የሰበከው ብዙ ተቃዋሚዎችና
አሳዳጆች እረፍት እየነሡት ነው። ከሚሰብከው ወንጌል ጎን ለጎን ተመጋጋቢ ስደትና መከራ፣ እስርና እንግልት አለ! በተሰሎንቄ ከተማ
የገጠመው እንዲህ ያለ ነገር ነው።
በተሰሎንቄ እንደ ገባ ያደረገው ነገር፣ እንደ ልማዱ ወንጌልን መመስከር
ነው፤ የቅዱስ ጳውሎስ ልማድ፣ “ክርስቶስ መከራ እንዲቀበልና ከሙታን እንዲነሣ ይገባው ዘንድ እያስረዳ፦ ይህ እኔ የምሰብክላችሁ
ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው” (ሐዋ. 17፥3) የሚለውን ወንጌል አጽንቶ መመስከር ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ከዚህ ውጪ ሌላ ልማድ ፈጽሞ
አልነበረውም። ልማድ ቋሚ ነገር ነው፤ የዘወትር ተግባር! የማያቋርጠው የፍቅር ዕዳው! ቅዱስ ጳውሎስ ከዚህ ዕዳ በቀር ሌላ አንዳች
ዕዳ የማንም የለበትም! ከሚመሰክረው ወንጌልና ለኢየሱስ ከሚኖርለት ሕይወት በቀር!
ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን በመመስከሩ ኹሉ በደስታ አልተቀበለውም፤ ካስተማራቸው
መካከል፣ “አንዳንዶቹ ተረድተው ከሚያመልኩም ከግሪክ ሰዎች ብዙ ከከበሩትም ሴቶች ጥቂቶች ያይደሉ፥ ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ቢተባበሩም”
(ቁ. 4) ሥራ ፈቶችና ክፉዎች ሰዎች ግን ቅዱስ ጳውሎስንና የሚመሰክረውን ወንጌል ይተባበሩ ዘንድ አልወደዱም። እናም ቅዱስ ጳውሎስን
በመቃወም ሳይረኩ ከተማውንም ጭምር አወኩ። እናም ሥራ ፈቶቹና አዋኪዎቹ፤ ክፉዎቹም ሰዎች ጳውሎስንና በወንጌል ያመኑትን ኹሉ ጐተቱ፤
ቀንተውም የክፋትን ሰዎች አነሣሱባቸው።
ወንጌል ያለ ተቃውሞ ተገልግሎ አያውቅም! ክርስቶስ ሰይጣንና ኀጢአት ባገነገነበት
ዝም ብሎ ተደላድሎ አይቀመጥም፤ ይልቁን ጠላት በበዛበት ወንጌሉ ተቃውሞን እያሸነፈ ድል ያደርጋል እንጂ። ሰዎች ወንጌልንና ወንጌላውያንን
ለማሰር፤ ለማስቆም፤ ለመቈጣጠር ይጥራሉ፤ ወንጌሉ ግን ወደረኛና ተገዳዳሪ ከተነሳበት እጥፍ ያለክልካይ ይበዛል፤ ይሰፋል። ጠላትና
አገልጋዮቹ ኹል ጊዜ የማያስተውሉት፤ ደጋግመው የሚሠሩት “ስህተት” ይህን ነው፤ ተቃውሞ፣ ተግዳሮት፣ ሁከት፣ ብጥብጥ … እኛን እንደሚያሳድገን፣
እንደሚያበዛን፣ እንደሚያሰፋን አያውቁም።
ጉባኤያችንን መጥተው ሲረብሹ፣ ክርስቶስን ለማክበርና ለማንገሥ፣ በአደባባይ
ለማወጅና ለማምለክ መሰብሰቢያችን ድረስ መጥተው ታውከው ለማወክ ሲጥሩ፣ እኛን ከፍ ከፍ እንደሚያደርጉን፣ ለብዙዎች እንደሚያስተዋውቁን፣
ያልከፈልናቸው የማስታወቂያ ሰሌዳዎቻችን፣ ሎሌዎቻችን እንደ ኾኑ አይረዱም። እንዴት ደስ ይላል! እኛ እኮ በተቃውሞ ውስጥ እግዚአብሔር
ያዘጋጀልን “ብዙ አገልጋዮች” አሉን! [ምርጥ ሎሌዎች - ዱካችንን እየተከተሉ ሰኮናችንን የሚናከሱ - ያዘገያሉ እንጂ ከድሉ ከተማ፣
ከጽዮን ተራራ አያስቀሩንም]! ተቃዋሚዎቻችን ሥራ ፈቶች ቢኾኑም የእኛን ሥራ በመሥራት፣ እኛን ለሌላው በማስተዋወቅ፣ የተሰበከውን
ወንጌል ደግመው በመናገር ሎሌዎቻችን ናቸው።
ዛሬ በደብረ ዘይቷ ቢሾፍቱ ላይ የኾነው እንደዛ ነው፤ ተቃዋሚዎቻችን መጥተው
ምርጥ ማስታወቂያ ሠሩልን፤ የምንሰብከውን ኢየሱስ አዩልን፤ የኢየሱስ ወዳጅ መኾናችንን መሰከሩልን፤ ሥራ ፈቶች ቢኾኑም ሥራችንን
ሠርተውልናልና እንወዳቸዋለን፤ እንጸልይላቸዋለን። በእርግጥ አንድ ነገር አንክድም፤ እነርሱም አይክዱም! ሕግ የማያከብሩ፣ ሕግ የማያግዳቸው
… ክፉዎች ናቸው፤ አዎን ደግሜ እላለሁ ክፉዎች ናቸው፤ በ2009 ዓ.ም ክረምት ላይ እኒሁ ሥራ ፈቶች በደብረ ዘይት በአንድ ጉባኤ
መካከል ተገኝተው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ዘርፈው ሄዱ፣ የዘረፉትንና ነጥቀው የወሰዱትን መጽሐፍ ቅዱስ ግን የቆሻሻ መጣያ ሥፍራ ጥለውት
ሄደው፣ በኋላ ላይ እንዲህ ብል በልቶት ተገኝቷል። እንግዲህ እነዚህ ናቸው ለቤተ ክርስቲያን እንቀናለን የሚሉት! እኒህ ናቸው መጽሐፍ
ቅዱስ የእኛ ነው የሚሉት! እኒህ ናቸው ከበሮ፣ ነጠላ፣ ቀሚስ፣ ጸናጽል፣ … ቅብርጥስ የእኛ ነው የሚሉት! እኒህ ናቸው …. ብቻ ግን መብሰላቸው ላይቀር እንጀት መፍጀታቸው
አይቀር፤ አይባልም! ግና ሰይጣን ቢፈራገጥም መውጣቱ መች ሊቀርለት!
እናምናለን! ወንጌል ከክርስቶስ ወደ ምድር የተጣለች እሳት ናት፤ “በምድር
ላይ እሳት ልጥል መጣሁ፥ አሁንም የነደደ ከሆነ ዘንድ ምን እፈልጋለሁ?” (ሉቃ. 12፥49) እንዲል፣ እሳቱን ጌታ በተቃዋሚዎቹ በደብረ ዘይት “ካራዎች” አስለኩሷልና
እጅግ ደስተኞች ነን! እኛን በመቃወማቸው ከእኛ እንደ ተለዩ አሳዩን! የወንጌል እሳት በመካከላችን በመንደዱ ለእኛ ምሕረት ኾኖልን
ለሌሎች የብስጭት፣ የንዴት፣ የቁጣ፣ የመንጨርጨር፣ የመንገብገብ … እሳት ኾኖባቸዋል። ጌታችን ኢየሱስ እንደ ተናገረው እሳት ወንጌል
ከነደደች ምን እናደርጋለን?! ደብረ ዘይት - ቢሾፍቱ ላይ እሳት ተለኩሷል፤ ላንቃውን ግን ጌታ በተቃዋሚዎች እጅ እንዲንቀለቀልና
እንዲታይ አድርጓል፤ ወንድሜ አዲስ ይርጋለም እንኳን ደስ አለህ፤ የደብረ ዘይት ምርጥ ወንድሞችና እህቶቼ፤ እናትና አባቶቼ እንኳን
ደስ አላችሁ!
ለካ ለከተማይቱ እንዲህ ታላቅ መፈራትና መደንገጥ ምልክት ናችሁን?! እናንተ
ታናሽ መንጋዎች! አባታችሁ የታመነ ነውና አንዳች አትፍሩ! አትደንግጡም! ሞትን የዋጠው፣ የታረደው ግን ደግሞ በአባቱ ቀኝ ያለው
ኢየሱስና መንፈሱ አብሯችሁ አለ! በክፉዎችና በሥራ ፈቶች ወንጌላችን ገና ይበዛል፤ ይሰፋልም!!! ጸጋና ሠላም ከኹላችሁ ጋር ይኹን፤
ተቃዋሚዎቻችን ሆይ! እንወዳችኋለን፤ ተግተን እንጸልይላችኋለን፤ እንማልድላችኋለን፤ አንድ ቀን እንድትመለሱ እናምናለን! አሜን!!!
እርሱ ግን ከሁሉ በላይ ነው
ReplyDeleteBadowch nachihu zm blachihu chefru amlakn atawukutm protestant kehadwech
ReplyDeleteኢየሱስ በዙፋኑ ሆኖ ሁሉን ያያል ደግሞም ግፈኞችን ይበቀላልና እናንተ ስራችሁን ስሩ!
ReplyDeleteተግዳሮቱ እንደ መብዛቱ እናንተም ገና ምድርን ትከድናላችሁ ያመናችሁት የታመነ ነው!!!!
ReplyDeleteየኛን እንጀራ በልታችሁ የኛን ውሃ ጠጥታችሁ
ReplyDeleteከጠገባችሁ በኋላ ከሀዲነታችሁ ሳያንሰን
ጭራሽ ለሀይማኖታቸው ተቆርቋሪዎቹን ወንድሞቻችንን ስራ ፈት ትላላችሁ በእውነት ያስተዝበናል
እኛ ምንለው ልብሳችንን አውልቃችሁ ስፈልጉ ራቁታችሁን ጨፍሩ እኛን አትምሰሉ ከኛ ራቁ።።።።።።
Aye menafeke endatastewelu ye Azeme menfesu yezuachukale
ReplyDeleteLe teyekachute teyakie melsune ezawe mesthafe kiduse laye semeleslachukhe endatamezazenu Ayene Lebonachuke Taweruale
Endatemelesu endatedenu ye DENGLE MARIAMEN melja kedachukale
Ye KIDUSANUNE kslekidan ena Berketen kedachukale
Ye KIDUSAN MELAYEKETEN teradsyenete ena Tebeka Kedachukale
Andachewen batekedu enkua tesfa yenorachukhe neaber
Mekenyatum wanawene ye Amaleketan Amelkae Ye Getochu Geta ye Negestate Neguse ye Sega ena Ye Neafse Fetary Alematune Be Kalue Fetro Yastena amelkae EYESUSE CHIRSTOSEN Amalje belachukhe ye kadachukhe mistere SELASSIEN yafalesachukhe yekadachukhe MENFESE KIDUSEN beye GUbayachukhe Endate endemetakalelu endemetsadebu ye matastewelu
Ye Davilose Lejenetachukhe be EYESUSE CHIRSTOSE LEGE neagie belo erasen be meshengle yemetenoru
Ye Hasawew menged Teragewoche nachukhe
Lebe yalew lebe yebele
Bezheche kale becha ke mesthafe kiduse woche mehonachukhe ena yezachute mesthafe yeteberze sew lematefate yetateme mekatele yalebete neaber newem
Aymanotune yelewete SEW ke MAYAMEN sew yelkhe yekefa new
Yeh maleate degmo Aganenete enkua Amelake endehone yamenalu tebelo ketestafew ke Aganentochu ye kefachukhe mehonachukhe becha enkua bastewalachukhe