Monday, 12 November 2018

ቤተ ክርስቲያን፣ ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 3)

Please read in PDF

1.1. ጥንቈላ
 ይህ ችግር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በግልጥ እንዳለ ይታወቃል፤ ግን አይደፈርም፣ ደፍረው የሚናገሩ ይገደላሉ፣ ይገለላሉ፣ ይተቻሉ፣ ይነቀፋሉ፣ ይወገዛሉ፤ ነገሩ ግን ሥር ሰድዷል፤ ከምንናገረው በላይ በቤተ ክርስቲያን ስምና አከባቢ ተሰግስገው አሉ፤ ዓርማቸው፣ መለያቸው፣ መታወቂያቸው … ቤተ ክርስቲያኒቱ የእኔ በምትላቸው ንዋያትና ሰዎች ጭምር ነው። መስተፋቅር፣ አንደርቢ፣ ሰብስቤ፣ “አስማት” … የሚባሉ የጥንቆላ ሥራዎች በብዛት የሚሠሩት በቤቱ ጥቂት በማይባሉ ቀሳውስትና ደባትራን ነው። ይህን ያጋለጡ ብዙዎች አይሰደዱ ተሰደዋል፣ አይንገላቱ ተንገላተዋል፤ ይህ ሲኾን እማኝ ምስክር ከሚኾኑት መካከል አንዱ ነኝ! ጠንቋይ ቀሳውስትን፣ ደባትራንን፣ መሪ ጌቶችን፣ መነኮሳዪይቶችን … በመቃወማቸው የተሰደዱ፣ የተዋረዱ፣ የተገደሉ … ሰዎችን ከሚያውቁ ምስክሮች አንዱ ነኝ!
    የእግዚአብሔርን እውነተኛ አስተማሪነት (ኢሳ. 30፥20) አለመቀበል፤ በትምህርቱም አለመጽናት የሐሰት መምህራን ትምህርት ሾልኮ ለመግባት ሠፊ በር ይከፍታል (2ጴጥ. 2፥1)፤ በቤተ ክርስቲያናችን እንደ ቤተ ክርስቲያናችን የመጻህፍት ጽህፈት ቀኖና መሠረት በቀለማት አጊጦ ከሚባዙትና ከቤተ ክርስቲያኒቱ መጻህፍት ጋር ታትሞ እኩል በየመጻህፍት መደብሩ ከሚሸጡት መጻህፍት መካከል አንዱ ዐውደ ነገሥት የሚባለው የጥንቈላ መጽሐፍ ነው። መሥተፋቅር፣ አስማት የሚደግሙ፣ ሞራ ገላጮች፣ መናፍስት ጠሪ፣ ሙታን ሳቢዎች … እና ሌሎችም የጥንቈላ ሥራዎች ሁሉም ለማለት ሊያስደፍር በሚችል መልኩ የሚከናወነው ከደብተራ እስከ ካህናት ባሉት የቤተ ክርስቲያኑቱ አገልጋዮች ነው።

Thursday, 8 November 2018

ነጠላ አስከባሪው!

ሕይወቱ በኮንሰርት በዘፈን ጨቅይቶ
ኀጢአት ነግሦ በʻርሱ ከጸጋ ደኽይቶ

Saturday, 3 November 2018

ቤተ ክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 2)

Please read in PDF

ኹሌም የቤተ ክርስቲያንን ችግር አንስተን ከብዙ ወገኖች ጋር በግልም በጋራም ስንወያይ፣ ውስጤን የሚነካኝና የሚያስጨንቀኝ ነገር ይህ ነው። ወደ ዋናው የችግሩ መንስኤ መሄድን አንፈልግም። በደፈረሰው ወራጅ ላይ እንከራከራለን፣ የወራጁን ምንጭ የማጥራት ሥራ ላይ ለመረባረብ እንገፋፋለን እንጂ መሠረታዊውን ችግራችንን፣ ከምንጩ ያፈነገጠውን ነገራችንን አጢነን፣ አስተውለን በልበ ሰፊነት ልናይ፣ ልንወያይ፣ በልበ ሰፊነት ተነጋግረን … መፈለግንም ማድረግንም (ፊልጵ. 2፥13) ከሚሠራው ጋር ለመሥራትና ለመቃናት አንተባበርም። ምንጩ ሲጠራ ወራጁም እንደሚጠራ እናውቃለን እንጂ አምነን ለመነሣት ለክፋት ጨካኞችና ለእግዚአብሔር ፍጹም ያደላን አይደለንም። ከዚህ የሚከፉት ይልቅ ያሉትን ችግሮች ብናይ በአሁን ሰዓት በግልጽ ከሚታዩት ችግሮች አንዱና ዋናው፦

Sunday, 28 October 2018

ከ“ቄስ” በላይ መኮንንና ከኢዩ ጩፋ ጀርባ የቆመ የዘረኝነት ግንብ

Please read in PDF

   በዘመናችን ባለው ክርስትና ውስጥ፣ እንደ ዘረኝነትና መናፍቅነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የተሰፋለት ነውር ኃጢአት ያለ አይመስልም። ኹለቱም መንፈሳዊ ካባ ለብሰው፣ ራሳቸውን ሸሽገው፣ ሾልከው ከመካከላችን ገብተው አሉ። ከኀጢአት ኹነኛ ባሕርያት አንዱ እንዳይታወቅ ራሱን መሸሸግ ነው፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባስተማረው የዘር ምሳሌ ላይ ጠላት እንክርዳድን የዘራው፣ “ሰዎቹ ሲተኙ” ነው፤ (ማቴ. 13፥25) ይህም ማለት ጠላት ዲያብሎስ መልካሙ እርሻ መልካም ብቻ እንደ ኾነ እንዲዘልቅ ፈጽሞ አይፈልግም ማለት ነው።

Saturday, 27 October 2018

ከመጽሐፌ፣ ዘለላ ቁም ነገር



 የጻፍኩት መጽሐፍ በጠቅላላ ስምንት ምዕራፎች አሉት፤ የገጽ ብዛቱ ደግሞ ከመጻፌ ምክንያት እስከ መግቢያ ያለውን ሳያካትት፣ 311 ነው፤ የመጽሐፉ ይዘት የእምነት እንቅስቃሴ አማኞች ስለሚያምኑባቸው ዋና ዋና ኢ ክርስቲያናዊ አስተምህሮ በስፋት ያትታል፤ ከዚያ ውስጥ አንዱ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ አረዳዳቸው ጠማማና ኢ ዐውዳዊ መኾኑ ዋነኛው ነው፤ ለዚህ “ዘለላ ቁም ነገሬ” እንደ አንድ ማሳያ የተጠቀምኹት፣ ኤሴክ ዊሊያም ኬንየን በአንድ መጽሐፉ ዮሐ. 3፥16 ላይ “… በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፤” የሚለውን ቅዱስ ቃል ሲያብራራ እንዲህ ይላል፤ “እግዚአብሔር አብ ዓለምን ስላፈቀረ አንድያ ልጁን ሰጥቶአል። ኢየሱስ ክርስቶስም ዓለምን እንዲሁ ስላፈቀረ ራሱን አሳልፎ ሰጠ። እኔም አኹን ዓለምን ስላፈቀርኩ ራሴን አሳልፌ ሰጥቼአለሁ። ምንም ዐይነት ሂስና ስደት ይምጣ ልቤ በዓለም ላይ ምሬትን እንዲያስተናግድ አልፈቅድም። በእነዚህ ሰዎች ላይ ጊዜዬን በከንቱ አጠፋሁ ለማለት ሲዳዳኝ በፊልጵስዩስ በጳውሎስና ሲላስ ላይ የደረሰውን አስታውሳለሁ” ይለናል፤ (የእምነት እንቅስቃሴ - የዛሬዪቱ ቤተ ክርስቲያን ፈተና፤ ገጽ 38-41)

Wednesday, 24 October 2018

“እንደ ኦሮሚያ ክልል ቤተ ክህነትን ማቋቋም እፈልጋለሁ”


  ማሳሰቢያ - ረጅም ንባብ ነው!

እነ አባ ገዳ ተሾመ እንዲያው ዝም ብለው ብቻቸውን፣ “የኦሮሚያ ሲኖዶስ ይቋቋም” ለማለት አይደፍሩም፤ ደግሞም ሥልጣንም የላቸውም። ነገር ግን የራሷ “የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች እጅ” እንዳለበት እርግጠኛ ኾኖ መናገር ይቻላል። ለዚህ ደግሞ የነ“ቀሲስ” በላይ እጆች ረጅም ብቻ ሳይኾኑ፣ እሬቻዊ አምልኮ በግልጥ ከክርስትና ጋር ለመስፋት የሚጥሩ ናቸው። “ቄስቻው” በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ይንቀሳቀስ እንጂ ለቤተ ክርስቲያኒቱ እንጥፍጣፊ ፍቅርና ለክርስትና ደንታ እንደሌለው፣ የዛሬ ሦስት ዓመት በOBS የኦሮሚኛ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ በ“harka fuune” (ቤት ለእንቦሳ) በሚለው ዝግጅት ላይ ከጋዜጠኛ አብዲ ገዳ ጋር “ረዥም” ቃለ መጠይቅ ማድመጥ በቂ ማሳያ ነው።  “የኦሮሚያ ሲኖዶስ የመቋቋም ጥንስስም” ጅማሮው የሰነበተ መኾኑን ማስተዋል አይከብድም፤ ይህን ቃለ ምልልስ ከሰማሁት በኋላ ሊያስተምርና ሊያወያይ እንደሚችል ስላሰብኩበት ተርጉሜው ለማቅረብ ወደድኹ። ይህን ቃለ ምልልስ አንብበው፣ ቃለ ምልልሱ በኋላ “ኦርቶዶክሳዊ ሃሳብ ነው” የሚሉ ይኖሩ ይኾንን? ብዬ መጠየቅ እፈልጋአለሁ፤ አይደለም የምትሉ ደግሞ እንግዲያው “ዘርን ወይም አንድን ክልል ማዕከል ያደረገ ሲኖዶስ” ጥንስሱ ዛሬ እንዳልኾነ፣ አባ ገዳ ተሾመም ኾኑ ሌሎች ይህን እንዲሉ አነሳሽ ኀይላት ከጀርባ እንዳሉ ማሳያ ይኾናል በማለት ነው። የ“ቄስቻው”ንም ማንነት በዚያውም መመልከት ተገቢ ሳይኾን አይቀረወም፤ መልካም ንባብ እላለሁ።
ጋዜጠኛው የቀሲስ በላይን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን የሥራ ድርሻ ከተናገረ በኋላ በቀጥታ ወደ ጥያቄ ያመራል።

Saturday, 20 October 2018

የዘፍጥረት አጭር ዳሰሳ





ከወንድሜ አዲስ ጋር የኦሪት ዘፍጥረትን የመጀመርያዎቹን ምዕራፎች እንዲህ አብረን አጥነተን ነበር!

Friday, 19 October 2018

ቤተ ክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 1)

Please read in PDF

መግቢ
   “ … በቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ላይ ሂስ ማድረግ እንደ ክህደት ስለሚቈጠር ብዙ አስተያየት አልዳበረም። ይህ ባህል ቅዱስ መጽሐፍን ተመራመሩ የሚለው መሠረተ ሐሳብ ተመራመርና እመን ከሚለው ንድፈ ሐሳብ በተቃራኒ እመን ግን አትመራመር ከሚል ንድፈ ሐሳብ ላይ ይመሠረታል።”[1]



      በእርግጥ ዶ/ር ዲበኩሉ ዘውዴ ያቀረቡት ይህ ሐሳብ፣ “እንደ ኢትዮጵያ ልምድ ስለ ፍትሐ ነገሥት ዝግጅትና የትርጉም ሥራ ላይ አብርሃም ወልደ ሐናናጥያን ምንም ሚና እንዳልተጫወተ እየታወቀ አለመተቸቱንና እንደ ወረደ መቀበላችንን በግልጥ ለመናገር ወይም ለመተቸት በማሰብ ነው። እውነታው ግን ለፍትሐ ነገት ብቻ ሳይኾን፣ በጠቅላላው አሁን ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ማለትም አስተምህሯዊ ችግሯን፣ አምልኳዊ ጉድለቷን፣ ሥነ ምግባራዊ ውድቀቷን … በጐላና በተረዳ ጎኑ የሚያጸባርቅ ነው።

Sunday, 14 October 2018

ሥራ ፈቶችና ክፉ ሰዎች በደብረ ዘይቷ ቢሾፍቱ!


Please read in PDF

“ … አይሁድ ግን ቀንተው ከሥራ ፈቶች ክፉ ሰዎችን አመጡ ሕዝብንም ሰብስበው ከተማውን አወኩ፥ ወደ ሕዝብም ያወጡአቸው ዘንድ ፈልገው ወደ ኢያሶን ቤት ቀረቡ፤ …” (ሐዋ. 17፥5)
   በሐዋርያው በቅዱስ ጳውሎስ ኹለተኛ ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ እጅግ አስደናቂና አሳዛኝ፣ ስደትና ደስታ፣ መከራና ዕረፍት፣ ድብደባና እርካታ ተስተውሎበታል። ቅዱስ ጳውሎስ በሄደበት ኹሉ የሚሰብከውን ወንጌል አሜን ብሎ የተቀበለው አንዳች አካል አልነበረም፤ ከእጅግ ጥቂቶች በቀር፤ የመዳንና የጸጋውን ወንጌል ቅዱስ ጳውሎስ የሰበከው ብዙ ተቃዋሚዎችና አሳዳጆች እረፍት እየነሡት ነው። ከሚሰብከው ወንጌል ጎን ለጎን ተመጋጋቢ ስደትና መከራ፣ እስርና እንግልት አለ! በተሰሎንቄ ከተማ የገጠመው እንዲህ ያለ ነገር ነው።

Saturday, 13 October 2018

መጽሐፌን ያሳተምኩበት ደስታዬ ተፈጸመ!

  በአንዳንድ የስልክ ጥሪዎች ውስጥ የሚሰሙ ድምጾች ለዘላለሙ ከልብ ታትመው ይቀራሉ! 2009 . አንድ ሰንበት ሙሌ የተባለ ውድ ወዳጄ አንዲት እህት እርዳታ እንደምትሻ በስልክ ነግሮኝ፣ ስልኳን አቀብሎኝ እንዳገኛት ድልድይ ኾነን። የሄድኩት አንዲት ብቻዋን፣ ተስፋ ቆርጣ ራስዋን ለማጥፋት ዝግጅት አጠናቅቃ የመጨረሻ ኑዛዜዋን ልትነግረኝ ወዳለች አንዲት እጅግ ከሲታ ግን እጅግ ልጅ ወደ ኾነች ሴት ነው።

Friday, 12 October 2018

ኮሽ ʻማይል መንግሥት!

Please read in PDF

ኮሽ ʻማይል መንግሥት፣ ስናፍቅ ስናፍቅ፤
ሰውነቴ አለቀ፣ ነፍሴም በመሳቀቅ…

Saturday, 6 October 2018

አንተን ካየሁ ወዲያ

Please read in PDF

በፍርሐት ቆፈን ተይዞ
አልጋው በድካም ተከቦ
በሠርጉ እያለቀሰ

Sunday, 30 September 2018

ነገረ ኢሬቻና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አበው!

Please read in PDF

   ማሳሰቢያ፦ ማንኛውም ሰው የፈለገውን እምነት የመከተል መብት ከያህዌ ኤሎሂም ተችሮታል፤ የወደደውንም “አምላክ”[እግዚአብሔርንም ኾነ ሰይጣንን] መከተል ይችላል፤  ታድያ ካመለክነው ዋጋችንን መቀበል ሳንዘነጋ!!!! ይህ ጽሁፍ የኢሬቻን አምልኮአዊ ሥነ ሥርዐት ለሚከተሉና ዋቄፈታን ሃይማኖታቸው ላደረጉ አልተጻፈም፤ ነገር ግን በክርስትና ውስጥ መስገው፣ ኢሬቻንና ዋቄፈታን ወደ ክርስትና አሹልከው ለማስገባት የሚጥሩትን ሥራቸውን ዕቡይ፤ መንገዳቸውን እኩይ ለማለት የተጻፈ ክርስቲያናዊ የተግሳጽ ጽሁፍ ነው!
ምክንያተ ጽሑፌ
   ሰሞኑን ሚድያውን ከሸፈኑት ነገሮች መካከል አንዱ፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አበውና አንዳንድ “ክርስቲያኖች” [በክርስትና ስም ያሉትን ኹሉ ይመለከታል]፣ “ዕጣን ዕጣንነታቸውን፤ ክርስቶሳዊ ክርስቶሳዊነታቸውን” ትተው፣ “እሬቻ እሬቻ፤ ዋቄፈታ ዋቄፈታ” መሽተታቸው ነው። እናም ይህ ተግባራቸው እጅግ ቈጥቁጦኛል፣ ለምንስ እንዲህ መኾን አስፈለገው? ብዬ እንድሞግት አስገድዶኛል። በምን መሥፈርት አንዳንድ አባቶች “የኢሬቻ የክብር ተሸላሚ እንደ ኾኑና፣ ለምን ዓላማስ እንዲህ ሊሸለሙ እንደ ተፈለገ፣ ኢሬቻ “ባሕላዊ ወሃይማኖታዊ መልክ” ሊይዝ እንዳለው [እንደ ያዘና ዋቄፈታ በሚለው ዐውድ፣ እንደ ክርስትናና እስልምና ሃይማኖቶች “አምላኩን ጠርቶ” ሲባርክ እያየን ነውና] እየታወቀና እየተሄደበት፣ በግልጽ ሃይማኖታዊ ቀኖናና ዶክትሪን እየተዘጋጀለት ባለበት በአኹኑ ሰዓት፣ ክርስትናን በተለይም ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን መታከክ ለምን አስፈለገ?፣ ከክርስትናና የክርስቶስ ጌትነትና አዳኝነት፣ ቤዛነትና ብቸኛ ዋጂነት በማይሰበክበት መድረክ ላይ፣ እኒህ አባቶች የስማቸው መጠራት፣ በተጨማሪም ጥቂት የማይባሉ ክርስቲያኖች በማምለኪያው ሥፍራ[1] መገኘታቸው አልኮሰኮሳቸው፣ አልከነከናቸው፣ አልቆጠቆጣቸው ይኾንን?” … የሚልና ብዙ የጥያቄ ማዕበሎች ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ ምክንያት ኾኖኛል።

Thursday, 27 September 2018

በጌታ ቸርነት መጽሐፉ ታተመ!


Please read in PDF
በጌታዬ ኢየሱስ፣ በአባቱ፣ በማኅየዊ መንፈስ ቅዱስ ጉልበትና አቅም፤ ደግሞም እንደ ፈቃዱ እነሆ ታተመ!
መጽሐፉን በግልም ኾነ ማከፋፈል ለምትፈልጉ +251911044555 ወይም +251920893099 መደወል ወይም abentek2@gmail.com በሚል ሜይል አድራሻ ማናቸውንም መጽሐፉን የተመለከተ አስተያየት መስጠት ይቻላል። ክብር ለታረደው፣ ደግሞም ሕያው ኾኖ ለቆመው በግ ለመሲሑ ኢየሱስ ይኹን፤ አሜን።

Tuesday, 25 September 2018

የእግዚአብሔር ኃይል

Please read in PDF

“የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።”
(1ቆሮ. 1፥18)
    ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ በኢትዮጵያውያን ዘንድ የታወቀ አንድ ጠንካራ አባባል አለው፤ “እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል” የሚል፤ ይህ ትምህርቱ እጅግ ጥልቅ ታላቅ መንፈስ ቅዱሳዊ ማስተዋልን የሚሻ አስደናቂ ትምህርት ነው። የትምህርቱ አስደናቂነት እግዚአብሔር ፍጥረትን እምሃበ አልቦ ሃበ ቦ (ካለ መኖር ወደ መኖር) እንዳመጣው፣ እንደ ቀድሞ ፍጥረትን ፈጥሮ በማስገኘት እንዳመጣበት አመጣጥ ያለ አይደለም። ይልቁን “ሕያው የኾነውን” የሰውን[አሮጌውን አዳም] በመስቀልና በመግደል አዲስና ልዩ ሕይወትን፣ ማለትም ለእርሱ ብቻ ሊኖር ያለውን ጠባይና ባሕርይ ገንዘብ ያደረገን አዲሱን ሰው በማስገኘት እጅግ አስደናቂ የማዳን ሥራን በመሥራት የኾነ እንጂ።