Thursday, 5 July 2018

ፊታችንን መልስ

Please read in PDF

ግፍ ደንደስ አወጣ፣ ዓመጽ ሥር ሰደደ፤
ቀንበር እንደ ጸና፣ መቃናት ሳይመጣ፣ ቀኑ ተዋገደ፤
ስል ኃጢአት ወረረን፣ ንቅዘታችን ታየ፤

Wednesday, 27 June 2018

“ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ” (ሉቃ. 13፥3)

   ይህንን ቃል የተናገረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ለመናገር ምክንያት የኾነው ደግሞ፣ የአይሁድ ራሳቸውን ንጹሕ አድርገው፣ ሌላውን ግን ፍጹም በደለኛ፤ ኃጢአተኛ አድርገው ማቅረባቸውን በታላቅ የተግሳጽ ቃል በመንቀፍ ነው። አይሁድ ራሳቸውን ንጹህና የተሻሉ አድርገው ለማቅረብ በሌላው ሰው ላይ የደረሰውን ነገር እንደ ታላቅ ማስረጃ አድርገው አቀረቡ። እናም፣ “ጲላጦስ ደማቸውን ከመሥዋዕታቸው ጋር ስላደባለቀው ስለ ገሊላ ሰዎች አወሩለት” (ቁ.1)። ጲላጦስ ይህን ነገር ለምን እንዳደረገ መጽሐፍ ቅዱስ ምክንያቱን አይነግረንም። ነገር ግን ጲላጦስ ይህን ነገር ሥልጣኑን ለማሰንበት ወይም የሮማን ሕግ ስለመሻራቸው ሲል አድርጐት ሊኾን ይችላል፤ በጭካኔው ወደር የለሽ ነበርና።
  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎቹ ያወሩለትን ነገር፣ “እነዚህ የገሊላ ሰዎች ይህ ስለ ደረሰባቸው ከገሊላ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ኃጢአተኞች የሆኑ ይመስሉአችኋልን?” (ቁ.2) በማለት፣ እጅግ ሞጋች ጥያቄን በማቅረብ መለሰላቸው። ደግሞም በተጨማሪ፣ “ወይስ በሰሌሆም ግንቡ የወደቀባቸውና የገደላቸው እነዚያ አሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሁሉ ይልቅ በደለኞች ይመስሉአችኋልን?” (ቁ.4) በማለት ያልተብራሩና እጅግ ግልጽ ያልኾኑ ድርጊቶችን ብቻ ተከትለው ፍርድን ለሚሰጡ ወገኖች ምክንዩ ጥያቄን አቀረበላቸው።

Wednesday, 20 June 2018

ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንና የ“ዲያቆን” ዳንኤል ክብረት የክፋት ሸፍጥ (ክፍል ፭)

Please read in PDF
በእስጢፋኖሳውያን ላይ የደረሰው መከራ
ካለፈው የበለጠ
34. ለየብቻ እየነጠላቸው በእስር መልክ ወደ እስላም ሃገሮች ሁሉ በመበተን[1] አንዳንዶችን በባርነት ሸጧቸዋል፤ በዚያም በጽኑ ጸዋተወ መከራ ውስጥ እንዲያልፉ አስደርጓቸዋል፤[2] [3]
“ ... የመንግሥቱ ምሥራቃዊ ወደ ሆነው ወደ እስላሞች ሀገሮች ይበትናቸው ጀመር። እዚያ በእሥራት፥ በግንድና በማነቆ (እያቆራኙ) ያስጨንቋቸው ነበረ። ደግሞ በማራቆት ሲቀልዱባቸው የአስኬማ ልብሳቸውን እየገፈፉ፥ አቧራ በላያቸው ላይ እያቦነኑ፥ የራስ ጠጉራቸው ሲላጩ እየነጩ፥ ያለምንም ምሕረት በበትር እየደበደቡ፥ ደግሞ በጦር ጫፍ አካላቸውን እየጓጐጡ፥ በእንደዚህ ያነ ሁኔታ ሲያሰቃዩዋቸው ብዙዎቹ ሰማዕትነታቸውን ፈጸሙ።” [4]
35. የላይና የታች ከንፈራቸውን በመግፈፍ ጥርሳቸውን ባዶ አስቀርቷቸዋል፤[5]
36. ስርናቸው አሰብሮ ደም በአፍንጫቸው እንዲጠጡ አስደርጓቸዋል፤[6]
37. ጢምና ጠጒራቸውን ያለ ውኃ በደረቁ አሸልቷቸዋል፤ አስነጭቷቸዋል፤[7]
38. አካላቸውን በጦር ወይም በስለት እንዲወጋ አድርጓል፤ ወግቶ በተበሳው ጠባሳ ስፍራ ጠጠር አስወትፏል፤[8]
39. ከቤተ መንግሥቱ በሚወጣ የሽንትና የሠገራ መተላለፊያ ውስጥ እንዲተኙ፣ ቈሻሻ እንዲፈስባቸውና እንዲከመርባቸው አስደርጓል፤[9]

Saturday, 16 June 2018

ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንና የ“ዲያቆን” ዳንኤል ክብረት የክፋት ሸፍጥ (ክፍል ፬)


በእስጢፋኖሳውያን ላይ የደረሰው መከራ
   “እብለክሙ ኦ ሕዝበ ክርስቲያን ምዕመናኒሃ ለማርያም ድንግል በክልኤ” ኵሉ ብዕሲ ዘተወክፈ ኪያሆሙ፥ ወዘተሳተፈ ምስሌሆሙ ወዘአንበሮሙ ውስተ ቤቱ ወኀበ ቤተክርስቲያን በውስተ ምድረ ርስቱ እሙኒ ሥዩም ይሠዐር ወይትበርበር ቤተ ንዋዩ፥ ወምድረ ርስቱ ይኩን ለባዕድ።
  ሊቃነ ካህናትኒ ወንቡራነ እድ ወኵሎሙ ሥዩማነ ቤተ ክርስቲያን ወመነኮሳትሂ ወኵሎሙ ሕዝብ ለእመ ተረክቡ እንዘ እኀብኡ ኪያሆሙ፥ ፈድፋደ ኩነኔ ላዕሌሆሙ። ሢመቶሙ ወምድረ ርስቶሙ ይኩን ለካልዕ እስመ ኮኑ ሱቱፋነ ምስሌሆሙ።
  ወእሙንቱሰ ደቂቀ እስጢፋ በአማን አይሁድ እሙንቱ እለ አብዩ ሰጊደ ለማርያም ድንግል በክልኤ ወለ መስቀለ ዋሕድ ወልድ ለእሙንቱሰ ኵነኔሆሙ ሞት።
   ወዘረከቦሙሂ ይኵንኖሙ በፅኑዕ ኩነኔ ወቀቲልሰ ኢይቅትሎሙ፤ አላ ይብጽሖሙ ውስተ ኩርጓኔነ ከመ ንሰማዕ ቃሎሙ። ወከመ ይኩን ፍትሕ ላዕሌሆሙ ወዘተረክበ። ብዕሴ እንዘ ይብሎ ሰላም ለእስጢፋዊ መክፈልቲ ምስለ እለ ተወክፋዎሙ ለደቀቂ እስጢፋ።”
የዚህ አማርኛ ትርጉም፦
“በኹለቱም ጊዜያት ድንግል የምትሆን የማርያም ምዕመናን የኾናችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ እንዲህ እላችኋለሁ። “ማናቸውም ሰው ሁሉ ደቂቀ እስጢፋን የተቀበለ ከእነርሱ ጋር የተባበረ በቤቱ ውስጥም ያኖራቸው ወይም በቤተ ክርስቲያኑና በርስቱም ምድር ያኖራቸው ቢገኝ፥ ሹመት ያለው ከኾነ ከሹመቱ ይሻር፥ ቤቱም ይዘረፍ ገንዘቡ ኹሉና ያለውም የምድሩ ርስት ለባዕድ ይሁን።
ሊቃነ ካህናት፥ ንቡረ ዕድ የቤተ ክርስቲያን ሹማምንትና መነኮሳትም ሁሉ ሕዝቡም ሁሉ እነርሱን ሲደብቋቸው ከተገኙ በእነርሱ ላይ ከፍ ያለ ቅጣት ይፈጸምባቸዋል። ሹመታቸውና የምድር ርስታቸው ለሌላ ይኹን። ከእነርሱ ጋር ተባብረዋልና ነው።
እነዚህ ደቂቀ እስጢፋ ግን ለድንግል ማርያምና ለአንድ ልጅዋ መስቀል መስገድን እምቢ ያሉ ናቸው፥ በእውነት አይሁድ ናቸው። የእነርሱ ቅጣት ሞት መሆን አለበት። ያገኛቸው ሁሉ በጽኑ መከራ ይቅጣቸው። ቃላቸውን ሰምተን በአደባባያችን ሸንጐ እንድንፈርድባቸው ወደ አደባባያችን ያምጣቸው እንጂ መግደልን ግን እርሱ ራሱ አይግደላቸው። እንደዚሁም ከደቂቀ እስጢፋ የሆነውን ሰው አግኝቶ ሰላምታ የሰጠው ሰው ሁሉ ዕድል ፈንታው ደቂቀ እስጢፋን ከተቀበሉ እንደሚደረግባቸው ይኾናል።”[1]  
   የእስጢፋኖሳውያንን መከራ መናገር በራሱ ያምማል፤ አሰቃቂነቱም ኹለንተናው በዲያብሎስ በተወረሰ ሰው የሚፈጸም እንጂ ሰብአዊ የኾነ ሰው እንኳ እንዲህ ሊያደርግ ፈጽሞ አይችልም። ሰው ለሰው ለመራራት ሰውነትን ማየቱ ብቻውን ይበቃዋል፤ ሰው በእንሰሳ ላይ እንኳ የማይፈጸም አሰቃቂ ተግባርን ከፈጸመ ግን ከሰውነት አንሷል ብሎ ደፍሮ መናገር ይቻላል። ታላቁ መጽሐፍ፣ “ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፤ የኀጥኣን ምሕረት ግን ጨካኝ ነው” (ምሳ. 12፥10) እንዲል፣ እውነተኛ መንፈሳዊ ልብ ያለው ሰው እንኳ በእግዚአብሔር መልክ ለተፈጠረው ሰው ለእንሰሳ እንኳ ይራራል። እናም ለእንሰሳ መራራት የሚቻለው ሰው፣ ለሰው መራራት ከተሳነው መንፈሳዊነቱ ደባይቷል ማለት ነው።

Thursday, 14 June 2018

አያሌ ዲያስፖራ ዛሬም ጥሙ፣ ረሃቡ፣ ናፍቆቱ ግብረ ሰዶማዊነት ነውን?!



    ጥቂት ያይደለው ዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ ማንነቴ ግብረ ሰዶማዊ ነው ይላል፤ የክፋት ጥጋችን መገለጫው ይህ ነው፤ እሳትን ከሰማይ አዝንም ልመናችን ይህ ነው፤ ነውር ይከበርልን፤ ዕድፈት ይጽደቅልን፤ ርኩሰት ይደንገግልን፤ ከእንሰሳነት ማነስ ይረጋገጥልን የሚል ዓመጸኝነት በምድራችን እንዲነግሥ እንዲህ ተግተው የሚሠሩ አሉ፤ ምድርን ካላረከሱ የማያርፉ፤ ግልሙትናና ሴሰኝነት፤ አመንዝራና ዝሙት ያላረካቸው ትውልድና ተፈጥሮን ካልተቃረንኩ ብለው ይሞግታሉ፤ ግብረ ሰዶማዊነት እንደ ቅድስና ሕጋዊ ይኹንልን፤ ተገፍተናልና አቁሙን የሚሉ ተማኅጽኖዎች እያየሉ መጥተዋል።

Tuesday, 12 June 2018

Namni nama malee Hafuraa miti! (kutaa 4ffaa)


 Kitaaboota Qulquloota yemmuu qorannuu Kakuu Duraanii keessattis ta’e kan Haarayaa keessatti hiikni isaani kan wal fakkaatu ta’u ni hubanna. Kutaan Haal qara waliigala Seera Umamaa; Namni Waaqayyo irraa malee namni ofii isaatiin Waaqayyo akka hintaane, Maddi namaatifi argamni namaas Waaqayyo irraa malee namni akka Waaqayyo durummaa(eternal)kan hinqabne ta’u ifatti ni kaa’u. keessattu jechootni “Bifa fi fakkaatti” jedhan hiikni isaani faalla’e (faalla ta’e) hiikama.

Monday, 4 June 2018

ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንና የ“ዲያቆን” ዳንኤል ክብረት የክፋት ሸፍጥ (ክፍል ፫)

Please read in PDF
ንጉሥ አለ መስገድ ከጥበብ መጉደል ነውን?

“ … የደረሰባቸው ነገር የደረሰባቸው በኹለት ምክንያት ነው፤ አንድ አባ እስጢፋኖስ ጥበበኛ ባለ መኾኑ ምክንያት ነው፤ ነገሥታቱ ላይ የነበረውን ስህተት ብቻ ከመንቀስና ጳጳሳቱ ላይ ብቻ የነበረውን ስህተት ከመንቀስ ይልቅ እነዚህ ዓይነት የሥነ መለኮት ክርክሮቹንና ነገሥታቱ ላይ ያሉ ተቃውሞዎች ኹለቱን አንድ ላይ ቀላቀላቸው፤ እነዚህ ኹለቱ ሲቀላቀሉ ጠላት አፈሩበት ማለት ነው …” (ዳንኤል ክብረት)

  ዳንኤል ክብረት፣ ለእውነተኞቹ ቅዱሳንና ሰማዕታት ያለውን ንቀትና የራሱን የታሪክ አልኰስኳሽነት በዚህ ንግግሩ ያለኃፍረት በአደባባይ ይገልጣል። ሰማዕታት፣ አላውያንና ጨካኝ ነገሥታትን፣ ገዢዎችን ፊት ለፊት መቃወማቸው የጥበብ መጉደል መንገድ እንደ ኾነ ሊሰብከን ይፈልጋል። “ስገዱልን” የሚሉ ፍጡራንን በመቃወም የሚመጣውን መከራና ከባድ ሰቆቃ ከነገረ መለኮት ጋር የሚቀላቀል “የአላዋቂ ጥበብ” አድርጐ ለማቅረብ ርምጥምጥ ሃሳቦችን ያቀርባል።
  ዳንኤልን፣ እስኪ እኒህን ጥያቄዎች እናንሳለት፤ ሦስቱ ሕጻናት ንጉሥ ናቡከደነጾር በዱራ ሜዳ ላይ ላሠራው ጣኦት፣ “… የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን … ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ” በማለት ፊት ለፊት በግልጥ መቃወማቸውና ከእሳት መጣላቸው ጥበበኛ ባለ መኾናቸው ነውን? (ዳን. 3፥17-18)፣ መርዶክዮስ ለአጋጋዊው ለሐመዳቱ ልጅ ሐማ አንገቱን ሰብሮ ባለ መስገዱ ምክንያት በሱሳ ግንብ ሥር ባሉ አይሁድ ኹሉ ላይ ሞት ማስፈረዱ ከጥበብ መጉደል ነውን? (አስ. 3፥2፤ 15)፣ ዮሐንስ ወንጌላዊ ለንጉሥ ድምጥያስ አልሰግድም በማለቱ በፈላ ዘይት ተቀቅሎ በፍጥሞ ደሴት መጣሉና በዚያ ለብዙ ዓመታት በእስር መቆየቱ ጥበበኛነት ባይታይበት ነውን? ቅዱስ ፓሊካርፐስ በትራጃን ዘመነ መንግሥት ንጉሡ ስገድልኝ ሲለው፣ “ሰማንያ ስድስት ዓመት ሳገለግለው አንድም ቀን ያልበደለኝን ጌታዬን ኢየሱስ ክርስቶስን አልበድልም” ብሎ በሕዝብ አደባባይ በእሳት ተቃጥሎ በሰማዕትነት መሞቱ ጥበበኛ አለ መኾንን፤ ከነገረ መለኮት ክርክር ጋር ቀላቅሎ [ተምታቶበት] ነውን? አግናጢዮስ ምጥው ለአንበሳ፣ አረመኔውን ንጉሥ ሊሠማ ባለመውደድ ለአንበሶች የምግብ ሲሳይ የኾነው በውኑ ጥበብ ጐድሎት ነውን? በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከ286 [አንዳንዶች ከ96 ዓ.ም ጀምሮ ያደርጉታል] ዓ.ም እስከ 315 ዓ.ም ድረስ ዘመነ ሰማዕታት ወይም የቤተ ክርስቲያን የስደት ዘመን እየተባለ ይጠራ በነበረበት ዘመን እነዚያ ድንቅ የቤተ ክርስቲያን ከዋክብት የታረዱት፣ ሰም ተቀብተው በሮማ አደባባዮች እንደ ጧፍ ቀልጠው የነደዱት፣ ለአንበሳ የተጣሉት፣ ቆዳቸውን እንደ በግ የተገፈፉት፣ በመንኩራኩር የተፈጩት … አንደኛና ዋነኛው ምክንያታቸው እኮ ለአላውያን ነገሥታት አንሰግድም፣ አንንበረከክም፣ በፊታቸውም አንደፋም በማለታቸው እንደ ነበር የዳንኤል ዐይኖች ምነው ማስተዋል ተሳናቸው? … ነው ወይስ ይህን የታሪክ ክፍል አልመረመረም?! ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደናል።

Friday, 1 June 2018

ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንና የ“ዲያቆን” ዳንኤል ክብረት የክፋት ሸፍጥ (ክፍል ፪)

Please read in PDF
   

   በየዘመናቱ ለቤተ ክርስቲያን እንቆረቆራለን፤ ለእርሷ ዘብ ቆመናል፤ ጠበቃዋ ነን … የሚሉ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን በመጻሕፍቶቿ ያልሸገገችውን ሕያው የታሪክ እውነትና የጥቁአንን [የተጠቁትን] የወንጌል ምስክርነት፣ እውነተኛ ሕይወታቸውንም ሊሸፋፍኑ፤ ሊያድበሰብሱ፤ የክፋት ልባቸውን ያለ መከልከል ገልጠው ሲያሳዩና አኹንም ሲያደርጉት ዕያየን ነው። ዳንኤል ክብረት፣ እስጢፋኖሳውያንን “መናፍቅ” ናቸው ለማለት የሚተጋውን ያህል፣ የተፈጸመባቸው ሰቆቃና መከራ ቅንጣት ታህል እንደ ማይሰቀጥጠው ንግግሮቹ ያሳብቃሉ። ለነገሩ መሞት፣ መዋረድ፣ ክፉን በክፉ አለማሸነፍ፣ መነቀፍ ሳይኾን መግደል፣ መሳደብ፣ መደብደብ … እንደ ሃይማኖትና መንግሥተ ሰማያት እንደ ሚያስወርስ “ምግባር ወይም ጽድቅ” በሚቆጠርበት የበዛ ማኅበረሰብ ባለበት፣ ዳንኤል ተቃራኒውን ቢያስብ ወይም ቢያስተምር እንጂ የደረሰባቸው ግፍ ባይገደው ምንም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም።

ደቂቀ እስጢፋኖስ ግድያ ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምኅሮ አንጻር እንዴት ይታያል?
    ይህን ርዕስ ማንሳት ቀላልና ምንም የማያደክም ሊኾን ይችላል፤ ምክንያቱም መግደል ግልጽ ኀጢአት ነውና፤ ነገር ግን ሰዎች መግደልን “ቅዱስና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ፍቅድ ሥልጣን እንዳለው” ለማድረግ የማይተረት ተረት፤ የማይደረት ድሪት የለም። “መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ” (ማቴ. 22፥29) እንዲል፣ ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ በመውጣት የምንወድቀውና የምንስተው እግዚአብሔር የተናገረንን በትክክል ሳናውቅ ስንቀር ነው። ሰውን መግደል ስህተት፣ ኀጢአት፣ ዓመጽ እንደ ኾነ እናውቃለን፤ ለሃይማኖታችን ክብር ወይም የሚቃወመንን ስንገድል እንኳን ሰው፣ እግዚአብሔር ራሱ እንዲቃወመንና ተዉ እንዲለን አንፈልግም፤ ለሃይማኖታችን በምናደርገው ማናቸውም ነገር እግዚአብሔር ራሱ የእኛ ሎሌ [የሃሳባችንና የድርጊታችን ተካፋይ] እንዲኾን እንፈልጋለን።

Monday, 28 May 2018

ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንና የ“ዲያቆን” ዳንኤል ክብረት የክፋት ሸፍጥ (ክፍል ፩)


ቂቀ እስጢፋኖሳውያንና የ“ዲያቆን” ዳንኤል ክብረት የክፋት ሸፍጥ (ክፍል ፩)
መግቢያ
   ዚህ ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የኾነኝ “ቀሲስ” ዳንኤል ክብረት የተባለ ሰው፣ በebs tv በአርአያ ሰብ(Who is Who) ፕሮግራም ላይ፣ በቀን 19/9/2010 ማታ 2፡00 ሰዓት ገደማ ላይ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንን በተመለከተ በሰጠው ቃለ ምልልስ፣ ፍጹም ሸፍጥና ክፋት የተሞላበትንና ከታሪክ እውነታ ያፈነገጠ ሃሳብን በማቅረቡ፣ እውነታውን ከቤተ ክርስቲያኒቱ መጻሕፍትና ከአባቶቿ አንደበት ማሳወቅ አስፈላጊ ኾኖ በመገኘቱና ነው።
   ለዚህም ጽሑፉ ከደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ታሪካዊ ዳራ ይልቅ እጅግ በአመዛኙ በእነርሱ ላይ የተፈጸመውና ቤተ ክርስቲያን በመጻሕፍቶቿ የያዘቻቸው እውነት ከቅዱሳት መጻሕፍት[1][ከመጽሐፍ ቅዱስ] አንጻር እንዴት ይዳኛል? ዳንኤል ክብረትስ ምን የተለየ ሃሳብን በደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ዙርያ ይዞ ብቅ አለ? ይዞ ብቅ የማለቱ እሳቤስ ምን መዘዝ አለው? ቅዱሳት መጻሐፍትስ እንዴት ይዳኙታል? ዳንኤልና ቅዱሳት መጻሕፍት ምን ያህል ጥብቅ ዝምድና አላቸው? ዳንኤል በማናቸው ምክንያትስ ቢኾን የሰው በአሰቃቂ ኹኔታ መገደል የሚገደው ነውን? … የሚሉና ሌሎች ተያያዥ ኹኔታዎችን በአጭሩ ለመዳሰስ እንሞክራለን።

Saturday, 26 May 2018

ከአጋንንት ምስክርነት?


ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣበት ዋና ዓላማ የዲያብሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድና (1ዮሐ.3÷8) በኃጢአት የታሰሩት ነጻ ወጥተው ህይወት እንዲሆንላቸው፤ እንዲበዛላቸውም ነው፡፡ (ዮሐ.10÷10)፡፡ ይህንን ለማድረግም ቀድሞ “ኃይለኛውን ሰይጣን ማሰር” እንደሚገባና ከዚያ በኋላ “ወደኃይለኛው ቤት በመግባት ቤቱን መዝረፍ” ማለትም ሰይጣንን በማሸነፍ አጋንንትን ማውጣት ፣በክፉ መንፈስ የሚሰቃዩትን፣ በኃጢአት ባርነት የተያዙትን በጽድቅ ነጻ በማውጣት ምርኮን መከፋፈል እንደሚገባ አስተምሮናል፡፡ ትልቁ የጌታ ምስራችና የአገልጋዮቹ ደስታ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት፣ ምስክርነትና የሥልጣን ቃል የአጋንንትና ግዛት በማስደድ መንግስቱን ወደሰዎች ልብ ግዛት ማቅረብ ነው፡፡

በቤቱ የተዘነጋ አባ ወራ

   ጽሐፍ ቅዱስ ወንድ አባ ወራ እንደ ኾነ ይነግረናል፤ “ባል የሚስት ራስ ነውና።” (ኤፌ.5፥23፤ 1ቆሮ.11፥3)፣ እንዲል። እናም ወራውን(ቤተሰቡን) በአግባቡ ማስተዳደር አለበት፤ “ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤ ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል?” (1ጢሞ.3፥4-5)። አባ ወራነት አስቀድሞ የወራ[በኦሮሚኛ ቤተሰብ ማለት ይኾንን?] ምስክርነት ያሻዋል፤ ቤተሰቡን የማይወድና ለቤተሰቡ ምንም ከበሬታ የሌለው አማኝም ኾነ አገልጋይ በውጭ ያለውን ዓለም በመላው እንደ ሚወድ ቢናገር ወይም ቢያሳይ ግብዝ ወይም አርቲስት እንጂ ሌላ ምንም ሊኾን አይችልም።
   የባል አባወራነቱ አስተዳደራዊ ነውና፣ ትልቅ ፍቅር የሚጠይቅ ነው። በትልቁም በትንሹም ውድ የኾነውን የባሎቻቸውን ፍቅር ያዩ ሚስቶች፣ ለባሎቻቸው እስከ ሞት በሚያደርስ ፍቅር እንደ ሚታመኑ ጥርጥር የለውም። ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን ፍቅር ዓይታ ለነፍሷ እንደ ማትሳሳ እንዲሁ፣ ሚስቶችም የአባ ወራቸውን “ደማቅ” ፍቅር ዓይተው ለባሎቻቸው የማይታመኑበት፣ ልጆችም አባታቸውን እንደ “ንጉሥ” የማያዩበትና የማያከብሩበት አንዳች ምክንያት አይኖርም።

Tuesday, 22 May 2018

ጌታችን ኢየሱስ ወደ ሰማያት ለምን ዐረገ? (የመጨረሻ ክፍል)

Please read in PDF

3.ሌላው አጽናኝ ወደ እኛ ይመጣ ዘንድ፤
  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ መስቀል ነፍሱን ስለ ሰው ልጆች አሳልፎ ሊሰጥ እጅግ በቀረበበት ሰዓት፣ ደቀ መዛሙርቱ እጅግ ማዘን ጀምረው ነበር፤ ተላልፎ እስከ ተሰጠባትና መስቀል ላይ እስከ ወጣበት ጊዜ ድረስ መከራው በሙሉ ያነጣጠረው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ነው። ነቀፌታውም፣ ስድቡም፣ ትችቱም፣ ጥላቻውም፣ መገለሉም፣ መሰደዱም፣ በመጨረሻም በመስቀል ከባድ መከራንም የተቀበለው ጌታችን ኢየሱስ ነው። ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን መከራው እነርሱንም እንደ ሚያገኛቸው አስቀድሞ አልነገራቸውም፤ ምክንያቱም በእርሱ ሕይወት ሲያልፍና ሲኾን የነበረውን ኹሉ ሲመለከቱ ነበርና። ከንግግር ይልቅ ሕይወት የማስተማር አቅሙ እጅግ ታላቅ ነውና!
 ነገር ግን ወደ ሰማያት ወደ አባቱ ሊሄድ ሰዓቲቱ እንደ ደረሰች ሲያውቅ፣ “እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደ ሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።” (ዮሐ.16፥1-2) በማለት፣ መከራው ለእነርሱም እንደ ማይቀር ነገራቸው። በጌታችን ኢየሱስ ላይ የወረደው የዓለሙ ኹሉ ጥላቻ በእነርሱም ይፈስሳል፤ የተገለጠ ንቀትም ፊት ለፊት ያገኛቸዋል፤ በዓለሙ ኹሉ ፊት እንደ ጉድፍ ይቆጠራሉ፤ ጌታቸው ባለፈባት የምጥ መንገድ እነርሱም ያልፉ ዘንድ አይቀርላቸውም። የመከራው ጫፍ ሰዎች እነርሱን ሲጠሉ፣ ሲያሳድዱ፣ ሲገድሉ … ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን የማቅረብ ያህል በጭካኔ ያደርጉባቸዋል። በዛሬ ዘመን ምን እየኾነ ይኾን? ሰዎች የእግዚአብሔር ሰዎች ነን እያሉ፣ በሃይማኖት ሽፋን ሰዎችን ለምን ይገድላሉ? ይጠላሉ? ያሳድዳሉ? የሰዎችን ስምስ በመረረ ጥላቻ ለምን ያጠፋሉ? …።

Saturday, 19 May 2018

ጌታችን ኢየሱስ ወደ ሰማያት ለምን ዐረገ? (ክፍል ፪)


2. ምስክርነታችንን እጅግ የታመነ ይኾን ዘንድ፤
   ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማያት ካላረገና ካልሄደ በቀር ምስክርነታችን ምሉዕ አይኾንም፤ ጌታችን ኢየሱስ ወደ ሰማያት ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን ምስክሮች እንደ ሚኾኑ ተናገራቸው፤ (ሐዋ.1፥8)፤ ምስክርነታቸው ከጌታ ኢየሱስ ለሠሙትና ላዩት ነገር ኹሉ ነው፤ (1ዮሐ.1፥1-3)፤ ካዩት ነገር ዋናውና አንዱ ደግሞ ዕርገቱ ነው። ቅዱሳን መላእክት ማረጉን ወዲያው ተናገሩት፣ “ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል” (ሐዋ.1፥11) በማለት። ጌታችን ኢየሱስ ወደ ሰማያት ወደ አባቱ ክብር ይገባ ዘንድ ዐርጓል፤ ስለዚህ “ትኩር ብላችሁ ወደ ሰማያት አትመልከቱ፤ በመመልከትም ጊዜን አታባክኑ፤ እስከ ምድር ዳርቻ ልታስተምሩ ገና ሰፊ በርና አገልግሎት አላችሁ” አሏቸው፤ አዎን! ሰማይ በዕርገቱ ሲከፈት፣ በምድር ደግሞ የአገልግሎት በር መርቆ ተከፈተ።
  የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ብዙ ተጠራጣሪዎችን ወደ እምነት መንገድ መልሷል፤ ቅዱስ ማቴዎስ እንዲህ ይለናል፣ “አሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ግን ኢየሱስ ወዳዘዛቸው ተራራ ወደ ገሊላ ሄዱ፥ ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ የተጠራጠሩ ግን ነበሩ።” (ማቴ.28፥16-17)፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማያት ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱ አምልከውታል፤ ስግደትም አቅርበውለታል። በሌላ ሥፍራም ወደ ሰማያት ሲያርግ እንደ ሰገዱለት ተጽፎ እናገኛለን፤ (ሉቃ.24፥52)። የባሕርይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ስግደትና አምልኮን ይቀበል ዘንድ ይገባዋል።

Thursday, 17 May 2018

ጌታችን ኢየሱስ ወደ ሰማያት ለምን ዐረገ? (ክፍል ፩)

Please read in PDf 

  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ማረጉ ለእኛ ክርስቲያኖች ዋስትናና ወደ ሰማያዊው ዓለም ለመፍለሳችን ታላቅ የማይናወጥ ምስክራችን ነው፤ ዕርገት ከክርስትና ዋና ትምህርቶችም እንደ አንዱ የሚቆጠርበት ምክንያቱና ዕርገቱን አለ መቀበልም ከዋናዎቹ መናፍቃን የማስቆጠሩም የማይካድ እውነታ ይኸው ነው። እናም ጌታችን አምላካችን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ሰማያት በክብር ማረጉ፣ ለእኛ ለክርስቲያን አማኞች ታላቅ ፋይዳ አለው። ከእኒህ ታላላቅ ፋይዳዎች ሦስቱን መጥቀስ እንችላለን፤ እኒህም፦