Wednesday, 20 June 2018

ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንና የ“ዲያቆን” ዳንኤል ክብረት የክፋት ሸፍጥ (ክፍል ፭)

Please read in PDF
በእስጢፋኖሳውያን ላይ የደረሰው መከራ
ካለፈው የበለጠ
34. ለየብቻ እየነጠላቸው በእስር መልክ ወደ እስላም ሃገሮች ሁሉ በመበተን[1] አንዳንዶችን በባርነት ሸጧቸዋል፤ በዚያም በጽኑ ጸዋተወ መከራ ውስጥ እንዲያልፉ አስደርጓቸዋል፤[2] [3]
“ ... የመንግሥቱ ምሥራቃዊ ወደ ሆነው ወደ እስላሞች ሀገሮች ይበትናቸው ጀመር። እዚያ በእሥራት፥ በግንድና በማነቆ (እያቆራኙ) ያስጨንቋቸው ነበረ። ደግሞ በማራቆት ሲቀልዱባቸው የአስኬማ ልብሳቸውን እየገፈፉ፥ አቧራ በላያቸው ላይ እያቦነኑ፥ የራስ ጠጉራቸው ሲላጩ እየነጩ፥ ያለምንም ምሕረት በበትር እየደበደቡ፥ ደግሞ በጦር ጫፍ አካላቸውን እየጓጐጡ፥ በእንደዚህ ያነ ሁኔታ ሲያሰቃዩዋቸው ብዙዎቹ ሰማዕትነታቸውን ፈጸሙ።” [4]
35. የላይና የታች ከንፈራቸውን በመግፈፍ ጥርሳቸውን ባዶ አስቀርቷቸዋል፤[5]
36. ስርናቸው አሰብሮ ደም በአፍንጫቸው እንዲጠጡ አስደርጓቸዋል፤[6]
37. ጢምና ጠጒራቸውን ያለ ውኃ በደረቁ አሸልቷቸዋል፤ አስነጭቷቸዋል፤[7]
38. አካላቸውን በጦር ወይም በስለት እንዲወጋ አድርጓል፤ ወግቶ በተበሳው ጠባሳ ስፍራ ጠጠር አስወትፏል፤[8]
39. ከቤተ መንግሥቱ በሚወጣ የሽንትና የሠገራ መተላለፊያ ውስጥ እንዲተኙ፣ ቈሻሻ እንዲፈስባቸውና እንዲከመርባቸው አስደርጓል፤[9]

40. ከዚህ ሁሉ ስቃይ በኋላ የተረፉትን ደግሞ፣ የሌሎቹን ወንድሞችና እህቶቻቸውን ሰቆቃና ጽኑ መከራ ወደ ውጭ ወጥተው እንዳይናገሩ በግድ አብሾ እንዲጠጡና አንዳንዴም ኮሶና የተለያዩ መድኃኒቶችን ከአቅማቸው በላይ እንዲወስዱ ወይም እንዲጋቱ በብዙ አስጨንቋቸዋል ወይም ሆዳቸው ተተርትሮ እንዲሞቱ አስደርጓል፤[10] [11]
41.  ፊታቸውን በጋለ ብረት አስተኩሷል፤[12]
42. እሳትን አንድዶ “አቃጥላችኋለሁ” በማለት፣ በወታደሮች ሰይፍና በጦሮች አስከብቦ በተደጋጋሚ አስፈራርቷቸዋል፤[13]
43. ገላቸው እንደ ቋንጣ እንዲበጣጠሱ አድርጓል፤[14] በቢላዋም አሳርዷቸዋል፤[15]
44.  በእሳት ነበልባል ውስጥ በማሳለፍ አስለብልቧቸዋል፤
 “ ... ከዚያ ወደ እሳቱ ውስጥ እንዲወስዷቸው [ወታደሮቹን] አዘዘ። ያነደዱት እሳት ትልቅ ቤት ያህል ነበረ። ነበልባሉ እንደ ደመና ወደ ላይ ወጥቶ ነበረ። ቅዱሳኑን እየገፈተሩ እንደታሰሩ ወስደው እዚያ አደረሷቸው። ... ንጉሡ ወታደሮቹ ጣር እንዲያበዙባቸው እንጂ ከእሳቱ ውስጥ ጨርሰው ለመግባት ሲፈልጉ በማነቆው (ይዘው) እንዲገቡ አይፈቅዱላቸውም። ለመውጣት ሲፈልጉ ደግሞ ከእሳቱ አቅርበው ያስጨንቋቸዋል። አንዳንዱ እግሮቹ ዓሣ በፍም (እንደ ሚጠበስ) ይጠበሳሉ፤ አንዳንዱን አንዱን በሌላው ላይ እየጣሉ እንደ ግንድ ይለበልቡታል። ከዚህ ጣር ይልቅ መሞትን ይመርጡ ነበረ። ግን ወታደሮቹ ይከለክሏቸዋል። ለመውጣት ሲሞክሩ፥ “ለመውጣት ከፈለጋችሁ ለንጉሡ ስገዱ፤ መምህራችሁንም ስደቡ” ይሏቸዋል።
   በእንደዚህ አደራጎት ብዙ አሰቃዩዋቸው። እነሱ ግን “ልጄ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ለመገዛት ከሄድክ ራስክን ለሥቃይ አዘጋጅ፤ ስትቸገር አታወላውል” ያለውን የነቢዩን ቃልና፥ “በትዕግሥታችሁ ነፍሳችሁን ታተርፋላችሁ” ያለውን የጌታን ቃል፥ በሐዋርያው ቃል ውስጥም፥ “ትዕግስት ፍጹም ሥራ አለበት” ያለውን እያስታወሱ ይኸንን ሁሉ ታገሱ።”[16]
45. ሴት መነኮሳዪያትን ደግሞ በጒጠት፣ በወስፌ፣ በምላጭ ምላሳቸውን መቁረጥና አፍንጫቸውን ከማስፎነን አልፎ ጡታቸውን አስቆርጧል፤[17] ከድካም የተነሣ ሲወድቁም መሬት ለመሬት እያስጐተተ ወደ ገበያው አደባባይ አስወጥቷቸዋል፤
“... አንዷን ትንሽ መነኵሲት ከወታደሮቹ አንዱ ብድግ አድርጎ ከመሬት ላይ ወረወራትና በእግሩ ቢረግጣት፥ እዚያ ሰማዕትነቷን ፈጸመች”[18]
46. ኹለንተናቸው በእሳት እንዲቃጠል አድርጓል፤[19]
47. በእሳት እንዲቃጠሉ አድርጐ ሳይረካ ሲቀር፣ በሴቶቹ መነኮሳዪያትና ምእመናት በብልቶቻቸው ውስጥ ፍህምና የጋለ ብረትን ያስጨምር ነበር፤
  ዱስ አባታችንን አባ በርተሎሜዎስን ብዙ አሠቃዩት። ከፍም ላይ ወረወሩት፤ የራሱ ጠጉር ነደደ፤ ሥጋው ተቃጠለ፤ ጭንቅላቱ አዠ። ሽምግልናው አላሳፈራቸውም፤ ግርማው አላስደነገጣቸውም፤ ሽበቱ፥ የዓይኖቹ ከባድነት፥ ቃለ መለኮት የሚናገሩ ደስተኛ ከንፈሮቹ፥ የአፉ ቃል እንቅስቃሴ፥ የእጆቹ ቅድስት በረከት አላሳዘኗቸውም። እሱ ግን በራስ ሺበት ጊዜ የጎልማስነት ጸጋ አግኝቶ ይኸንን ሁሉ ታገሰ። ...”[20]
“ ... መክብዩ የሚሏት አንዲት መበለት ነበረች። እንግዳ ተቀባይ፥ በምግባሯም ጥሩ የሆነች ነበረች። ወንድና ሴት ልጆች አሏት። ... ቅዱሳኑን ከቤቷ ታስገባቸው፥ አብራቸውም ለመሆን ትፈልግ ነበረ። ... ቅዱሳኑን እና እሷንም ከቤቷ ያዟቸው። እሷም እንዳለችው አደረገችው፤ (ቅጣቷን) ለተላኩት ከገንዘቧ ሰጠች፤ ልጆቿን አላሳዘነችም። ወስደው ለብቻዋ አቆሟት።
  ንጉሡ፥ “በእነሱ ዘንድ ምን አየሽ? ለምን ከነሱ ጋራ ተባበርሽ?” ብሎ ላከባት። “የእግዚአብሔርን መንገድ ስላገኘሁ ከነሱ ጋራ ተባበርኩ” አለችው። ደግሞ (እንድትመለስ) በብዙ ሸነገሏት፤ እምቢ አለቻቸው። ከቅዱሳኑ ጋራ ወደ እሳቱ ወሰዷትና እዚያ ብዙ አሰቃዩዋት። የንጉሡ ወታደሮች በብዙ ሰደቧት። በትር እያነሱ ደበደቧት። እጇን ይዘው ወዲያና ወዲህ እየጎተቱ ከእሳተ አጠገብ ጣሏት። ትንታጉን እያነሡ እላይዋ ላይ በመበተን አቃጠሏት። ደግሞ ፍም አንሥተው እልብሷ ላይ ጣሉት።
   ወታደሮቹ የመራሮች ውጤት ስለሆኑ እሷን ማሰቃየቱን ገብ አላደረጉም። (ሲወለዱ) የወጡበትን በር ሳያፍሩ እግሮቿን (በርግደው) ይዘው እስጋዋ ላይ የእሳት ትንታግ እያከታተሉ ጨመሩበት። ሥጋዋ እስኪነፍር ድረስ እየተፈራረቁ እንደዚህ አደረጉ። ቅዱሳኑ ያበረቷት ነበረ። እሷም በዚያ የቃጠሎ በሽታ(ሰማዕትነቷን) እስክትፈጽም ይኸንን ሁሉንም ታገሠች።”[21]
48. በእሳት ያቃጠሏቸውን ዐመዳቸው እንኳ እንዳይገኝ በወንዝ አስጨምሯል፤
49. ሳር አብልቷቸዋል፤[22]
50. በጆሮአቸው ጉንዳን አስጨምሮባቸዋል፤[23]
51.  አንገታቸውን በሰይፍ አስቀንጥሷል፤[24]
52. በግራኝ እጅ ሰዎች ዒላማ በማድረግም በጦርና በአንካሴ፣ በቀስት አስወድሮ ደረታቸውን አስተርትሯል፤[25]
53. ዐይናቸው በእሾኽ፣ በጋለ የብረት ወስፌ አስበጥቶ እንዲፈስ አድርጓል፤[26]
  “ … ቅዱሳኑን ያዛቸው፤ ወስዶ ከንጉሡ አደባባይ ሲያደርሳቸው ከሰቀላው ሰፈር አቆሟቸው። ለንጉሡ እንዲሰግዱ፥ መምህራቸውንም እንዲሰድቡ አዘዟቸው። ፩ዱ መርቆርዮስ የሚባለው ወንድም፥ “እኛ አንሰግድም፤ መምህራችንንም አንሰድብም፤ ቅዱስ ነው” አለ። ይኸንንም ወንድም ከንጉሡ ፊት ሲያቆሙት (እና ሲቀጡት) ይኸ አምስተኛው ነው፤ መጀመርያ፥ … ፶ ገርፈው … ሁለተኛ … ከአረሚዎች ብሔር ወስደውት ነበረ። ሶስተኛ ሲያቆሙት ቅጣቱ ብዙ ነበረ። አራተኛ … አፍንጫውንና መላሱን ቈርጠው ቋንጃውን አውጥተውበት ነበረ።  … አምስተኛ ጊዜ … ወታደሮቹ ታዝዘው ዓይኑን አወጡት። ብረት አግለው ከውስጡ ጨመሩት። አብረውት ያሉትንም እንደዚሁ አደረጉባቸው። …”[27]
54. በተደጋጋሚ ከእርሱ ዘንድ እንዲቀርቡ ከ30-35 ቀን የሚፈጀውን መንገድ እንዲመጡ አስገድዷቸዋል፤
55. አፄ ዘርዓ ያዕቀብ እስጢፋኖሳውያን በሐሰት እንዲወገዙ ብዙ ጥሯል፤ ባለ ማውገዙም ጳጳሱን እስከ ዕለተ ሞቱ ተቀይሞታል፤[28]
  “በነገሥታቱ ሥልጣን ላይ ተቃውሞ ያስነሣና የእነርሱን ስህተት ያጋለጠ፣ እንደ ፈጣ ነገሥታት ያልሰገደ ማንኛውም ሰው ያለምንም ርኅራኄና ይቅርታ በሕይወቱና በንብረቱ ይፈረድበታል፤ ከሐዲ፣ መናፍቅ፣ እግዚአብሔር ቀብቶ ላነገሠው ንጉሥ የማይሰግድ ተብሎ ይወገዛል”[29]
56. እስጢፋኖሳውያንን ፈልጎ ሰው እንዲያገኛቸው ሰው አስቀጥሮባቸዋል፤ ላገኛቸውም ሽልማትን ይሸልም ነበር፤[30]
 “ … ከዚያ ወደ ትግራይ አገረ ገዢ ሄደው ዐጋሜ ውስጥ ያሉትን ቅዱሳን እንዲይዛቸው የንጉሡን መልእክት ነገሩት። አገረ ገዢው ሰምቶ ከንጉሡ መልእክተኛ ጋራ (ሊፈልጋቸው) ሄደ። ቅዱሳኑ ካሉበት ሀገር ደርሰው እነሱን በመፈለግ ደከሙ። ከሀገሩ ሹማምንት ፩ዱን በግዛቱ ያሉትን ቅዱሳን እንዲይዝና እንዲሰጣቸው፥ (ይህን ቢያደርግ) በሀገሪቱ በሞላ የበለጠ ሹመት እንደሚሰጡት ቃል ገቡለት። እሱም በምክራቸው ተደልሎ ቅዱሳኑን በምድረ በዳና በየዋሻው ካሉበት ሄዶ ያዛቸው። መቼም የዚህ ዓለም ድኾች ሕጋቸው እንደዚህ ነው። የደከሙበትን ወሰዱባቸው።”[31]
57. በሐሰት ክስ በተደጋጋሚ ሲቀርብባቸው ተቀብሏል፤ ከሷቸዋልም፤ ለምሳሌ፦ የእስላም መስቀል አለ ብለዋል በሚል፤[32]
58. ሲሞቱ መቀበሪያ መቃብር በመከልከል በምድረ በዳ እንዲጣሉ አድርጓል፣ በጥሻ አስወርውሯል፣ ለአራዊት አሰጥቷል፣ በእሳትም እንዲቃጠሉ አድርጓል፤[33]
59. የተቀበሩትን ቅዱሳን አስወጥቶ በድንጋይ አጽማቸው እንዲወገር አድርጓል፤ [34]
  ይህን ኹሉ መከራ አድርሶባቸው አፄ ዘርዓ ያዕቆብ በመከራው ኹሉ አለመሸነፋቸው፤ እርሱም እነርሱን ባለማሸነፉ ጽናታቸው ሳያስደንቀው አይቀርም። እጅግ አስደናቂው ነገር በዚህ ኹሉ መከራ እንዳላሸነፋቸው ሲያይ፣ “የመከራውን ስቃይ የሚቀንስላቸው መድኃኒት ቢኖራቸውና ቢጠቀሙ ነው” በማለት አስፈትሿቸዋል፤
“ … እንደ ማይታዘዝለት ንጉሡ ሲረዳ፥ ቅጣት የሚያቃልሉበት መዳኒት አላቸው እንደሆነ ብሎ የቅዱሱንነ የልጆቹን የአስኬማ ልብስ እንዲፈትሹ ወታደሮቹን አዘዛቸው። ቀበቶዋቸውን ፈቱ፤ ቆባቸውንና የአስኬማቸውን ማረፊያ አወለቁ። (ምንም ነገር ሲያጡ) የሚሉት ጠፋባቸው።” እንዲል። [35]
እስጢፋኖሳውያን መከራውን ኹሉ ታገሱት እንጂ ሌላ ምንም ዓይነት መንገድ መጠቀማቸውን ታሪኮቻቸው አይናገሩም። ይልቁን ስለአባ እስጢፋኖስ እንዲህ ተብለ ተነግሯል፦
             “የቀበሮዎች ጩኸት አንበሳን እንደ ማይረብሸው እርሱም በፊታቸው በጽናት ቆመ።”[36]
  “የሥርዓት ንጉሥ” የተባሉትን፣ ንጉሥ ዘርዐ ያዕቆብን ቅዱስና እንከን አልባ አድርጐ፣ እስጢፋኖሳውያንን ግን “ጥበብ አልባና እልኸኞች፣ አላዋቂዎችና መናፍቃን” አድርጐ ማቅረብ፣ ጭፍንነትንና የታሪክን እውነት መካድና ከማመልከት በቀር ምንም የተለየ ምልከታ የለውም። የገዛ ልጆቹን እንኳ በአስባበ ቅንአትና ክብረ አምላክ ገድሎ መንግሥቱን ያጸናን አፄ፣ እንከን አልባ አድርጐ ጥብቅና እየቈሙ በሰማዕትነት የተጨፈጨፉትን የእውነት ምስክሮች ችላ ማለት ከቅዱስ ወንጌል ልብ ለመራቃችን ትልቅ ምስክር ነው። በአጭር ቃል ይህን አረመኔያዊ ድርጊት መስፍን ወልደ ማርያም(ፕሮፌሰር) እንዲህ ይገልጡታል፤
  “ከሰዎች ፊት ከሥልጣኔ በራፍ ላይ ደርሰን ከኋላችን የመጡ አልፈውን በአዳራሹ ሲገቡ እኛ አኹንም ከውጭ ቆመን መቅረታችንና በልመና የምንኖር መኾናችን የገዢዎቻችን የአፈና ተግባር የማይቀር ውጤት ሆኖ ነው። በታሪካችን ሁሌም በሕገ አራዊት እየተመራን፣ የሰውነት ሃብታችንን፣ አእምሮዓችንና መንፈሳችንን ታፍነን ኑሮዐችንን የምናሻሽልበት ዘዴ ለመፍጠር አልቻልንም። በሌላ በኩል ደግሞ፣ መንፈሳዊ ወኔ የነበራቸውና ሐሳባቸውንና እምነታቸውን ማንንም ሳይፈሩ በአደባባይ ለማውጣት የቻሉ እንደነ ደቂቀ እስጢፋኖስ የመሳሰሉ መገኘታቸው ከአፈናው ባሻገር ጭራሽ ባዶ አለ መሆናችንን ያሳየናል።”[37]
  እንግዲህ ዳንኤል ክብረት የእኒህ ቅዱሳንን መከራና ስቃይ እንደ ዋዛ በመመልከት ነው፣ የጥበብ መጕደል ውጤት እንደ ኾነ ሊናገር የደፈረው። ነገር ግን እንኳን መንፈሳዊ፣ የቱም ሰብዓዊ ኅሊና ያለው ሰው እንዲህ ባለው አስጨናቂና ከባድ መከራ “አመክንዮአዊ ምክንያት ባለማቅረብ ይሳለቃል” ብሎ አይጠብቅም። ይህን መከራ ማክፋፋት ከምን ልብ ሊመነጭ እንደ ሚችል መጽሐፍ ቅዱስን በማስተዋልና በልበ ሰፊነት ያጠና ብቻ ያስተውለዋል።
ይቀጥላል …



[1] ጌታቸው ኃይሌ (ፕ/ር) ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ “በሕግ አምላክ”፤ 2002 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬስ፤ ገጽ 190
[2] ዝኒ ከማሁ ገጽ 133፣ 174፤ ደቂቀ እስጢፋኖስና የደብረ ብርሃን ሸንጐ፤ ገጽ 35
[3] “ይህንንም የሚያደርገው “እስላሞቹ በብዙ መከራ አሰቃይተው እንዲያስተነፍሱለት ነው”፤” ጌታቸው ኃይሌ (ፕ/ር) ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ “በሕግ አምላክ”፤ 2002 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬስ፤ ገጽ 121
[4] ዝኒ ከማሁ ገጽ 114-115
[5] ብሩክ ገብረ ሊባኖስ (መምህር)፤ የሰው ያለህ፤ 2005 ዓ.ም፤ ሜልቦርን አውስተረሊያ፤ ማተሚያ ቤቱ ያልተጠቀሰ፤ ገጽ 59
[6] ጌታቸው ኃይሌ (ፕ/ር) ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ “በሕግ አምላክ”፤ 2002 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬስ፤  ገጽ 186
[7] ዝኒ ከማሁ ገጽ 133
[8] ዝኒ ከማሁ ገጽ 201
[9] ዝኒ ከማሁ ገጽ 170
[10] ዝኒ ከማሁ ገጽ 178፣ 207-208
[11]ይህን የሚያደርገው የሚፈልጋቸውን ነገሮች የሚያገኝባቸው እንደሆን በማሰብ ነው፤” (ጌታቸው ኃይሌ (ፕ/ር) ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ “በሕግ አምላክ”፤ 2002 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬስ፤ ገጽ 207
[12] ጌታቸው ኃይሌ (ፕ/ር) ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ  “በሕግ አምላክ” ፤ 2002 ዓ.ም ፤ አሳታሚ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬስ፤ ገጽ የሰው ያለህ፤ ገጽ 59
[13] ዝኒ ከማሁ ገጽ 138፣ 185፣ 211
[14] ዝኒ ከማሁ ገጽ 206
[15] ዝኒ ከማሁ ገጽ 204
[16] ዝኒ ከማሁ ገጽ 141
[17]ዝኒ ከማሁ ገጽ  215
[18] ዝኒ ከማሁ ገጽ 215
[19] ዝኒ ከማሁ ገጽ 141
[20] ዝኒ ከማሁ ገጽ 141
[21] ዝኒ ከማሁ ገጽ 142
[22] ዝኒ ከማሁ ገጽ 214
[23] ዝኒ ከማሁ ገጽ 214
[24] ዝኒ ከማሁ ገጽ 180
[25] ዝኒ ከማሁ ገጽ 187፣ 202
[26] ዝኒ ከማሁ ገጽ 177፣ 180
[27] ዝኒ ከማሁ ገጽ 177
[28] ጌታቸው ኃይሌ (ፕ/ር) ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ “በሕግ አምላክ”፤ 2002 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬስ፤ ገጽ 153፣
[29] ደቂቀ እስጢፋኖስና የደብረ ብርሃን ሸንጐ፤ ገጽ. 26
[30] ጌታቸው ኃይሌ (ፕ/ር) ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ “በሕግ አምላክ”፤ 2002 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬስ፤ ገጽ 111
[31] ዝኒ ከማሁ ገጽ 126
[32] ዝኒ ከማሁ ገጽ 178፣ 201
[33] ዝኒ ከማሁ ገጽ 114፣ 125፣ 174፣ 209
[34] ዝኒ ከማሁ ገጽ 172
[35] ዝኒ ከማሁ ገጽ 111፣ 209
[36] ገድለ አቡነ እስጢፋኖስ፤ ዘአሲራ መቲራ ገዳም፤ 1996 ዓ.ም፤ ገጽ 107
[37] ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም፤ ለ“ደቂቀ እስጢፋኖስ በሕግ አምላክ” መጽሐፍ መግቢያ የጻፉት

16 comments:

  1. እውነት ተናገር ታርኩ ዘርያዕቆብ በክርስቶስ አምላክነት ያመነ ክርስቲያን ከመጥፍት የታደግ ንጉስ ነው። ያነ ሀይ ባይል ዛሬ መሐመድ ነበር ስም

    ReplyDelete
  2. inante gin lemindinw le deqiqe Isxifanosawuyan indih yeteqoreqorachihu........timirtachew inde ke inante ke Lutherian yileyayal!!!!

    ReplyDelete
  3. ለምን ኦርቶዶክስ መስለሀ ምንፍቅና ትሰብካለሀ ተሰውሮ ማሳት የአባታችን የዲያብሎስ ነው ለምን በራሳችሁ ታፍራላችሁ በርግጥ ሲጠይቋችሁ መልስ ስለሌላችሁ እኛን መስላችሁ ልታምታቱ ትፈልጋላችሁ የፓስተራችሁ ካራቴ ሲመራችሁ በኛ ብራንድ መስበክ ጀመራችሁ ለማንኛውም እኛን ለማሳሳት ብላችሁ የመቤታችን አማላጅነት ርእስ በመፃፋችሁ ራሱ እመቤታችን ስለ እናንተ ታለቅሳለች ትለምንላችሀለች ታማልዳችሀለች እንደኔ ግን የአምላክ እናት ላይ ሽንቱን ሲሸና ወደ አውሬነት እንደተቀየረው እናንተን ደግሞ ምላሳችሁን እንደሁ ቢያደርግልኝ እመኛለሁ ከበላያችሁ የሰፈረውን ሰይጣን ምጠይቀው አዳምን 5500ዘመን ሲሞላ ከልጅ ልጅሀ ተወልጀ ነው ያለው ከልጅ ልጅሀ ተወልዶ የሚያድን አማላጅ ምትሉትን እልካለሁ ነው ያለው?አድንሀለሁ ያለው ማነው ያለው እየሱስ ነው እግዚአብሄር ነው ያለው?እየሱስ ተወልዶ ነበር እንዴ?ከፔንጤዎች ያደርክ ሰይጣን እስኪ መልስ?

    ReplyDelete
  4. May God bless you

    ReplyDelete
  5. ኸረ ውውውውው ተቃጠል ያቃጥልክ ክክክክክክ ውይ እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ

    ReplyDelete
  6. Amazing Wooooooooooow

    ReplyDelete
  7. በተቃውሞ አንዳች አትደንግጥ፡፡ዛሬም ሰው በመደብደብና በመግደል የሚያምኑ እኮ አሉ፡፡ገድለው ሰውን መስበክ የሚፈልጉ እኮ ብዙ ናቸው፡፡ለዚህ ነው ኦርቶዶክስ በአለም ፊት የምትወገዘው፡፡ቢያውቁ ኖሮ ክርስቲያን ክርስቲያንን አያሳድድም ነበር

    ReplyDelete
  8. geta lib yistih. nigusu endih ayadegm.tsadikina kidus nigus new.maryamn yemiwed.

    ReplyDelete
  9. አሜን ማራናታ...

    ReplyDelete
  10. Esun lemtechet moralun yet agegnehew..... አይ ሀራጥቃ ....

    ReplyDelete
  11. Anit Menafik kehadi yeSeyetan Gibir aberu Egziabeher yegesetseh!

    ReplyDelete
  12. ወዳጄ ማለት የምትፈልገውን በል እንጂ የሰውን ስም አትተች ምክንያቱም አንተ ምንም የለህምና ፡፡

    ReplyDelete
  13. ከእናንተ ዳንኤል። ጋ ለማውራት። የሚያስፈልገው የእግዚአብሔርን። ቃል ማወቅ ብቻ ነው እሱ የማያውቀውንና የሚያጣምመውን ቃል አውቆ ውሸታም ሆድ አምላኩ እንደሆነ። መንገር ነው የሚያስፈልገው። ያጣመመው ቃል ራሱ ይፈርድበታል ጌታችን እየሱስ። ክርስቶስ። ራሱ እንደተናገረው ማለት ነው

    ReplyDelete
  14. የጻፍከው እውነት ነው። እግዚአብሄር ይባርክህ።

    ReplyDelete
  15. ዘረ ያዕቆብ እሚባል አረመኔ ተረታሜ እንደ ቅዱስ ይታያል::

    ReplyDelete
  16. tebarek tru akerareb new

    ReplyDelete