Thursday, 14 June 2018

አያሌ ዲያስፖራ ዛሬም ጥሙ፣ ረሃቡ፣ ናፍቆቱ ግብረ ሰዶማዊነት ነውን?!



    ጥቂት ያይደለው ዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ ማንነቴ ግብረ ሰዶማዊ ነው ይላል፤ የክፋት ጥጋችን መገለጫው ይህ ነው፤ እሳትን ከሰማይ አዝንም ልመናችን ይህ ነው፤ ነውር ይከበርልን፤ ዕድፈት ይጽደቅልን፤ ርኩሰት ይደንገግልን፤ ከእንሰሳነት ማነስ ይረጋገጥልን የሚል ዓመጸኝነት በምድራችን እንዲነግሥ እንዲህ ተግተው የሚሠሩ አሉ፤ ምድርን ካላረከሱ የማያርፉ፤ ግልሙትናና ሴሰኝነት፤ አመንዝራና ዝሙት ያላረካቸው ትውልድና ተፈጥሮን ካልተቃረንኩ ብለው ይሞግታሉ፤ ግብረ ሰዶማዊነት እንደ ቅድስና ሕጋዊ ይኹንልን፤ ተገፍተናልና አቁሙን የሚሉ ተማኅጽኖዎች እያየሉ መጥተዋል።

ይህን ፎቶ ሳይ ውስጤን መግለጥ የማልችለው ቁጣና እንባ ተናንቆኛል፤ ብሔርተኝነትን ገና ማሸነፍ ላልቻለች አገር ሌላ ቀንበር የሚመኙላት አሉ፤ በአሜሪካ፣ በካናዳና በአውሮጳ ተቀምጠው ከዘርና ከወንዝ ብሔርተኝነት ያልተላቀቁና በዚህ ጸያፍ ሥራቸው ያልረኩ እልፍ ዲያስፖራዎቸው ሌላ የነውርና የኃጢአት የቤት ሥራ እያበጁልን ነው፤ ግብረ ሰዶማዊነት። ማን ይኾን ከትውልዱ ያስተዋለ?! ከምዕራቡ ዓለም አብያተ ክርስቲያናት ይልቅ ምነው የእነዚህ ነውረኞችና እጅግ ምድርን አስጨናቂ ኃጢአተኞች ድምጻቸው ጮኾ ይሰማል? አባቶች ጳጳሳት፣ ሰባክያን፣ ነገረ መለኮታውያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋይና ተማሪዎች፣ የሰባካ መንፈሳዊና የስብከተ ወንጌል አባላት፣ መጋብያን፣ ቆሞሳት፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት፣ አስተማሪዎች … ወዴት ናችሁ? ትውልድ በቁመቱ ልክ ወድቆ ምድር ፊቷን በርኩሰት ሳታጨማድድ ጨክናችሁ ተነሡ!!!

ዲያስፖራ ግብረ ሰዶማውያንም ሆይ! ምድሪቱን አታስጨንቋት፤ በንስሐ ተመለሱ፤ ጌታችን ኢየሱስን እንደ ገና እመኑት፤ ተቀበሉት፤ ዳኑበትም፤ በደሙም ታጥባችሁ ንጹ፤ ተቀደሱም፤ አገልጋዮችም ለትውልዱ እውነተኛውን የጽድቅና የመዳን ወንጌል ስበኩ፤ የወንጌሉን ቃል አሰምታችሁ ጩኹ፤ ሳትቆጥቡ ጩኹ! ጌታ እግዚአብሔር ምድራችንን ያስባት፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ ሆይ! እግዚአብሔር ይማራችሁ፤ ምሕረትን ያድርግላችሁ፤ አሜን።

11 comments:

  1. EGEZEHO MARINE CERESTOSE

    ReplyDelete
  2. እግዚኣብሔር ይጠብቀን።
    ግን የእውነት ሐበሻ እንዲህ ኣያደርግም። ፎቶው ተቀነባብሮ ይሆናል እንጂ።

    ReplyDelete
    Replies
    1. PRAY for Ethiopia! the beast is coming.

      check these site https://twitter.com/GayEthiopia

      Delete
  3. ያንች ሀሳብ ዘር እንቁላ ነዉ ይላል ያገሬ ሰዉ አገር ተረብሾ እነሱ አፍ አለን ብለዉ ይሄን ይተይኩ ማፈሪያ ሁላ

    ReplyDelete
  4. መጽሐፍ ቅዱስ በይሁዳ መልእክት ቁ፡7 ላይ እንደዚህ ይላል፤ "እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።" እንደዚሁ በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታዎች ግብረ ሰዶማዊነት ሐጥያት መሆኑ ተጽፏል።

    ReplyDelete
  5. Betam yasazenal Ethiopia kedest hager nat yehenen mekebel atechilm , atefekedim ,, endi yemiyaderegu Ethiopiawi mehonen menorem ayechilum may be American biwekel enji !!

    ReplyDelete
  6. Betam yasazenal Ethiopia kedest hager nat yehenen mekebel atechilm , atefekedim ,, endi yemiyaderegu Ethiopiawi mehonen menorem ayechilum may be American biwekel enji !!

    ReplyDelete
  7. yihe gn ewnet new?

    ReplyDelete
  8. Tshegay okubu አሉ በውጭው አለም ብዙዎች ፈልገውትም ይሁን ሳይፈልጉትም ቢሆን አሉ።

    ReplyDelete
  9. Tshegay okubu አሉ በውጭው አለም ብዙዎች ፈልገውትም ይሁን ሳይፈልጉትም ቢሆን አሉ።

    ReplyDelete
  10. እውነት ነው ብላችሁ ማመን ለተሳናችሁ አዎ ኢትዮጵያውያን ግብረሰዶማውያን አሉ በወጭው አላም እውነታውን እንዲህ ነው ብዪ ብእርግጠኝነት ባልናገርም ማለትም ፈልገውት ይሁን ተገደው የሚያስከትለውን ጉዳት ሳይረዱት ቀርተው ይሁን መናገር ባይችላልም አሁንማ ቁጥራቸው በመጨመር ላይ ነው ያለው እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጠብቃት ሀገሪቷን ለዛህም ነበር ባለፈው ኦባማ ወደሀግራችንና ወደኬንያ ሲመጣ አንስቶ ነበር የኢትዮጵያ መንግስት ያለውን በእርግጠኝነት መናገር ባልችልምግን ግን መለስ ከአንዋር መስኪድ ጀምራችሁ ታፔላውን ይዛችሁ ጊዮርጊስ በሰላም ከደረሳችሁ ጥያቄ የለውም ብሎ ነበር መሰለኝ ይየኬንያው መንግስት ከአሜሪካን ጋር የምንጋራው ባህል አለ ይፕማንጋራውም እንደዛው ነው ያለው የዩጋንዳው ደሞ መጽሀፍ ቅዱስም ሆነ ቁራን ላይ ስለሌለ እኔ ኦባማን ካገባሀ እፈቅዳለሁ ብሎዋል የየሀግሩን መሪዎች መናገር ግዜ ቢፈልግም ግን ብዙዎች ተቃውመዋል ሆኖም ግን በሀገራችንም ውስጥ አሉ ይፋ ስላልወጣ ነው እንጂ

    ReplyDelete