Tuesday, 8 March 2022

ኢየሱስ እስኪመጣ አሥር ዓመታት በጡመራ መድረክ አገልግሎት!

 Please read in PDF

እግዚአብሔር አምላኬ በብዙ ባበዛልኝ ጸጋ ተደግፌ፣ ላለፉት አሥር ዓመታት በጡመራ መድረክ (blog) አገልግያለሁ። ቅዱስ ጳውሎስ፣ “ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል።” (1ቆሮ. 3፥11-13) እንዲል፣ አገልግሎቴ አንድ ጊዜ በተመሠረተው መሠረት ላይ እንጂ፣ አዲስ ወይም ወይም ሌላ መሠረት በመመሥረት አልነበረም። ምክንያቱም አዲስ መሠረትን ብመሠረትና ከኢየሱስ የተለየ ወንጌልን ብመሰክር አገልግሎቴ በእሳት ሊበላ አለውና።

Monday, 7 March 2022

ከአምልኮተ ኢትዮጵያ ተጠበቁ!

 Please read in PDF

ብሔራዊ ቲያትር ላይ አድዋን አስመልክቶ በተዘጋጀው “ዝክረ አድዋ” መርሐ ግብር ላይ፣ “‘ከኦርቶዶክስ’ በቀር ሃይማኖት የለም!” ባዩ ዘበነ ለማ፣ “ሃይማኖቶችን አክብሮና ኢትዮጵያዊነትን አስመልኮ” መቅረቡ ይደንቃል! በትያትር ቤቱ አዳራሽ ያሉ ደግሞ፣ ጩኸታቸውና ጭብጨባቸው በትክክል “ምናባዊቷን ኢትዮጵያ” ተስላ እንጂ በእውን ሳያዩ በደንብ ይስተዋላል። ዘበነ ለማ ከተናገራቸው ንግግሮች ውስጥ እኒህ ደማቅ ትምክህቶች ጎልተው ይሰማሉ።


Wednesday, 2 March 2022

ጾሙ ተሐድሶ ያስፈልገዋል!

Please read in PDF

ጾም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አምልኮ ሲኾን፣ ክርስቲያን የኾነ ኹሉ በግልም ኾነ በማኅበር እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ ለማምለክና ወደ እርሱ ለመጸለይ፣ ይቅርታን ለመለመን፣ ስለ ተለያዩ ችግሮችና የልብ መሻቶች የእግዚአብሔርን ርዳታና ምላሽ ለማግኘት እግረ ልቡናውን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀናበት መንገድ ነው። እግዚአብሔር የሚፈልገው በትሕትና የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ በመኾኑ፣ ክርስቲያን በጾሙ ራሱን ከኀያሉ እግዚአብሔር እጅ በታች ስለሚያዋርድ፣ እንዲህ በእውነት ተዋርዶ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበውን አምልኮትና ጸሎትም እግዚአብሔር ስለሚቀበለው ችግሩ ይቃለላል፤ጥያቄውም ይመለሳል፤ (መዝ. 51፥17፤ 1ጴጥ. 5፥6)።

Saturday, 26 February 2022

ኑሮን በማስወደድ እንከብራለን ለሚሉቱ!

 Please read in PDF

“ችጋረኛውን የምትውጡ፥ የአገሩንም ድሀ የምታጠፉ እናንተ ሆይ፦ እህልን እንሸጥ ዘንድ መባቻው መቼ ያልፋል? የኢፍ መስፈሪያውንም እያሳነስን፥ ሰቅሉንም እያበዛን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እያታለልን፥ ድሀውን በብር ችጋረኛውንም በአንድ ጥንድ ጫማ እንገዛ ዘንድ፥ የስንዴውን ግርድ እንሸጥ ዘንድ ስንዴውን እንድንሸምት ሰንበት መቼ ያልፋል? የምትሉ እናንተ ሆይ፥ ይህን ስሙ።” (አሞ. 8፥4-6)

ታሪካዊ ዳራ!

ነቢዩ አሞጽ ያገለገለበት ጊዜ፣ በዳግማዊ ኢዮርብዓም የኋለኛው አጋማሽ ዘመን አከባቢ ነበር። በዚህ ዘመን ደግሞ የነበረው ብልጽግና፣ በማኅበራዊ ንቅዘት የተነወረ ነበር፤ ንቅዘቱና መበስበሱም እጅግ ተስፋፍቶ ነበር። በሌላ መልክ ደግሞ፣ እስራኤል በእግዚአብሔር መመረጥዋን ተገን በማድረግ፣ ብዙ በደልን ፈጽማ ነበር። እግዚአብሔርም በአሞጽ አንደበት በርግጠኝነት መመረጥዋን ተናገሮ (3፥2) ነገር ግን መመረጥዋ ብቻውን፣ ለእውነተኛው በረከትና መትረፍረፍ ዋስትና አለመኾኑንም ሲናገር እንሰማዋለን። ምክንያቱም ለተስፋው ቃልና ለተሰጣቸው ትእዛዝ መታዘዝና መጽናት አለባቸውና፤ “አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤” (ዘጸ. 19፥5) እንዲል።

Tuesday, 1 February 2022

ልሳን የማይናገሩ አልዳኑምን?

 Please read in PDF

አብ እንደ ወደደን፣ በክርስቶስ እንደ ዳንን፤ በመንፈስ ቅዱስም እንደ ታተምን በሥላሴ የድኅነት ሥራ ፍጹም እናምናለን!

መጽሐፍ ቅዱስ መዳንን ወይም ዳግመኛ መወለድን ወይም የዘላለም ሕይወትን በቀጥታ የሚያያይዘው፣ ከአዲስ ኪዳኑ ወርቃማ ቃል ማለትም፣ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤” (ዮሐ. 3፥16 ዐ.መ.ት) ከሚለው ጋር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ አለመጥፋትን ወይም ከዘላለም ሞት ማምለጫው በኢየሱስ ማመን ነው ይለናል።

Monday, 31 January 2022

ስለ ነነዌ፣ የእግዚአብሔርና የዮናስ ልብ!

Please read in PDF

እስራኤል በእግዚአብሔር ፊት እጅግ አስነዋሪ ኀጢአትን ሠራች። የሠራችውም ኀጢአት መቅደሱን የሚያረክስ፣ የእግዚአብሔርን አምልኮ በባዕዳንና በብዙ የአማልክት አምልኮ በመለወጥ በእግዚአብሔር ላይ ማመጽ ነበር። ከዚህ ዓመጿም እንድትመለስ፣ እግዚአብሔር አያሌ ቅዱሳን ነቢያትን ቢልክም፣ እስራኤል በልብዋ ከመኩራራት በዘለለ ወደ እግዚአብሔር ልትመለስ አልወደደችም። 

Sunday, 30 January 2022

ይምረረው ፈጽሞ

Please read in PDF

ይቅለል አይወደድ

እንደ ወይን ወዳድ ይኹን ፌዝና ቀልድ

ተሳልቀው ያጠልሹት

Thursday, 6 January 2022

መሲሑ ወደ ምድር የመጣበት ዋና ዓላማዎች!

Please read in PDF

በብሉይ ኪዳን ዘመን፣ እንደ ተናፈቀና እንደ ተቃተተለት የኖረ ታላቅ እውነት ቢኖር፣ ቅዱሱ መሲሕ ብቻ ነው። መሲሑን ሲፈልጉ ነቢያት አልታከቱም፤ አበው ፈጽሞ ዓይናቸው አልፈዘዘም፤ ያመኑ ሴቶች ሙታናቸውን በእምነት ለመቀበል አላመነቱም፤ ካህናት መሥዋዕትን ሲያቀርቡ ፈጽሞ አልተጠየፉም። እንደ ናፈቁት ኖረው፣ እንደ ናፈቁት ሞቱለት። ባያገኙት እንኳ፣ ምሳሌውን አገልግለው ለማለፍ ለቅንጣት እንደ ጉድለት አላሰቡም።

Friday, 31 December 2021

ኢየሱስን ብቻ!

ብቻ! የማያሳይ ከወዳጅ አግዝፎ

ብቻ! ማያጎላ ከአዝማድ አልቆ

Wednesday, 1 December 2021

ስህተትን ማን ያስተውላታል? (መዝ. 19፥12)

Please read in PDF

ኀጢአት አማኞች እንዳያስተውሉት ስለሚፈልግ፣ በጽድቅ መዝገብ ውስጥ ራሱን መደበቅ ይወዳል። አብዛኛኞቹ አማኞች ግን የተገለጠ ኀጢአትን አይተው ሲሸሹ፣ ራሱን ሊገልጥ የማይወደውንና ስውሩን ኀጢአትን ግን ሲዘፈቁበት አልያም “ኀጢአት አይደለም” ብለው ሲሞግቱ እንሰማቸዋለን። ከዚህ የተነሣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተሐድሶ እንዲመጣ የሚሹ አካላት፣ ዘወትር ሊያመለክቱ ከሚገባቸው ተግባራት አንዱ፣ ራሱን ሸሻጊውን፣ “እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ባለ ነገር በነውር ሊይዝ” (ኤፌ. 5፥27) ከሚተጋው ኀጢአት መጠበቅና ማስጠንቀቅ፤ ዘወትር አማኞች እንዳይረሱ ማሳሰብ ነው።

Thursday, 18 November 2021

“ወደ ኦርቶዶክስ አልተመለሱም፤ በዚህ መንገድም አይመለሱም!”

 Please read in PDF

ወደ ኦርቶዶክስ ተመልሰናል ባዮችና የኦርቶዶክስ “ቀናተኛው ማኅበረ ቅዱሳን”

የቀናተኞቹ ውይይት ዕጣሬ

በባለፈው ወር ”ወደ ኦርቶዶክስ ተመልሰናል“ ያሉ ወገኖች ብዙ ነጋሪት አስጐስመዋል፤ ከበሮ አስመትተዋል፤ እንቢልታ አስነፍተዋል። ነገር ግን ያስነፉትን እንቢልታ፤ ያስመቱትን ከበሮ፤ ያስጐሰሙትን ነጋሪት ያህል፣ ተቀባይነትን ሳይኾን “ማኅበረ ቅዱሳን የተባለ ‘ኦርቶዶክሳዊ’ ቀናተኛን” በሚገባ አስቀሰቀሰባቸው እንጂ አልጠቀማቸውም። “ተመላሾቹ”፣ እንዲመለሱ መንገድ ያደላደለላቸው ሰው፣ “የማኅበራዊ ሚዲያ አቅም እንዲጠቀሙ በብዙ እንደ መከራቸው ይታመናል፤” ግን ውጤቱን አለመመዘናቸውና በተቀደደ ቦይ መፍሰሳቸው ሊመጣ ያለውን ናዳ አለማስተዋላቸው ወለል አድርጎ ያሳያል።





Thursday, 11 November 2021

በደስታ ካልተገዛህለት!

 Please read in PDF

ቅጥር እንዳትቀጥር፣ እንዳታበጅ መስመር

ሚዛን ቱንቢው ይቅር፣ ብላ ጠጣ ጨፍር

በቅንብብ አትኑር፣ ባ’ጥር አትከበብ

Wednesday, 3 November 2021

መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፲፭)

Please read in PDF

ካለፈው የቀጠለ …

ከዚህ በታች ያሉት ዐሳቦች፣ ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምራቸው ታላላቅ እውነቶች ናቸው። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት፦

1.  የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት ከመዳናችን ፈጽሞ ነጥለን ልናየው አንችልም። በቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት እንዳስተዋልነው፣ ከክርስቶስ ጋር የአካል አንድነት የሚኖረን በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት ብቻ ነው። በመንፈስ ቅዱስ የሚጠመቀው አማኝ፣ ሕያውና ቅድስት የኾነችውን የቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚካፈልና አማኞችን ወደዚህ ፍጹም አንድነት ለመጨመር የሚከናወን ታላቅ መንፈሳዊ ሥራ ነው።



Friday, 29 October 2021

በገንዘብ ብዛት አትችሏትም!

Please read IN PDF

ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት፤ እርሱ ብቻ ደግሞ ራስዋ ነው። የሚያምርና የተንቆጠቆጠ ካቴድራል አልያም ጽርሐ ወንጌል ላይኖራት ይችላል። አማኞቿ ጥልቅ ድኾች፣ ደምግባት አልባ፣ ያልተማሩ ገበሬዎች አልያም ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ቢኾኑም፤ በክርስቶስ ፊት እኩልና አንድ፤ ኹሉም ለክርስቶስ በኵራት ናቸው። በጌታ ቤት ታላቅና ታናሽ የለምና!

በአንድ ቀን የወደቀ የለም!

Please read in PDF

ስሕተትን ማን ያስተውላታል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ። (መዝ. 19፥12)

ሔዋን ከእባብ ጋር በማይጠቅምና በማያንጽ ወሬ መዘግየቷ ዋጋ አስከፍሎአታል (ዘፍ. 3፥1-6)፤ የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ሳዖል ውድቀቱ የጀመረው፣ ትንሽ ከምትመስል ነገር ግን አደገኛ ከኾነ ክፉ የባልንጀርነት ቡድን ውስጥ መሳተፉ ነው (1ሳሙ. 14፥2-3)፤ ጅማሮው መልካም የነበረው ያ ንጉሥ በፍጻሜው፣ ጠንቋይ እንደ ፈለገ፣ ለእግዚአብሔር እንዳልታዘዘ ክፉ ሞት ሞተ፡፡ ሳምሶንን የሚያህል ብርቱ አገልጋይ፣ የመውደቁና የመንኮታኮቱ ጅማሮ፣ ሶምሶንም ወደ ተምና ወረደ፥ በተምናም ከፍልስጥኤማውያን ልጆች አንዲት ሴት አየ። (መሣ. 13፥1) ከምትል ቀላል ሐረግ ነው፡፡