Monday, 29 January 2018
Monday, 22 January 2018
የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፱
ሰዎች ክርስቶስን ይመስላሉ ስንል፦ የአዲስ
ኪዳን ምንባባት ይህን አባባል በግልጥ ወስነው አስቀምጠውታል፤ ይኸውም፦ (1ዮሐ.3፥2፤ ሮሜ.8፥29፤ ፊል.3፥21፤ 1ቆሮ.15፥49) በእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ፣ ሰው ከእግዚአብሔር ስለተካፈላቸው የቅድስናና የግብረ
ገብነትን ባሕርይ እንጂ ሰው ፍጹም አምላክ ስለመኾኑ የሚያመለክቱ አይደሉም፡፡ ከፍጥረታችንም ሰው መኾን እንጂ፣ መለኮት የመኾንም
ኾነ ወደዚያ የማደግ አንዳች ምክንያት የለንም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም በዚህ ረገድ የሚያስተምረን አንዳች ትምህርት የለውም፡፡
በዚህ ምድርም
ኾነ ከሙታን ትንሣኤ በኋላ በሚኖረን ሕይወት ከእግዚአብሔር ጥገኝነት ፈጽመን መላቀቅ አንችልም፡፡ ደግሞም፣ “We are
independent”[1] “እኛ ነጻ፤ ከምንም ነገር ኢ ጥገኛ ነን” ማለት አይቻለንም፡፡ መጠጊያ ጥጋችን እግዚአብሔር ብቻ ነውና፡፡
እኛ በራሳችን በዚህ ዓለም ብቻችንን ለመኖር የሚያበቃን ሐለዎታዊ ሕይወትን አላገኘንም፤ አልተሰጠንምም፡፡ የሕይወት እስትንፋስን የሰጠን የሰማይ አምላክ ነው እንጂ፡፡
Monday, 15 January 2018
የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፰
·
1ቆሮ.3፥16፦ “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ
ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?” በሚለው ቅዱስ ቃል ውስጥ፣ የእምነት እንቅስቃሴ መምህራን “ቤተ መቅደስ”
የሚለውን በመውሰድ፣ የሥጋን አገልግሎት የማደርያነት ብቻ እንጂ ዘላለማዊ ወይም ከሰውነት ኹለንተና አንዱ አለመኾኑን ለመሞገት ያቀርቡታል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ክፍል እየተናገረ ያለው፣ ስለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ማለትም በጥቅሉ ስለጉባኤው የመንፈስ
ቅዱስ ማደርያ ስለመኾናቸው ነው፡፡ ከክፍሉ ዓውድ እንደምንረዳው እየተናገረ ያለው አንድን ሰው ሳይኾን በጠቅላላ ተደራስያን የኾኑትን
የቆሮንቶስን ቤተ ክርስቲያን አማኞች ነውና፡፡ ክፍሉን እንደምናስተውለው፣ ከሰው የሥጋ ሰውነት ጋር በመያያዝ የተነገረ አይደለም፡፡
Saturday, 6 January 2018
ታቹን አልርመጥመጥ!
መንቁር አፉን ነቅሎ
ጥፍሩን ኹሉ ጥሎ
ክንፉን እንኳ ሳይቀር ፍጹም አስወግዶ
በመለወጥ ሂደት መግል ቁስሉን ሽሮ
ዳግመኛ እስኪታይ በከፍታ በሮ
Wednesday, 3 January 2018
የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፯
Please read in PDF
ዛሬም በቀጣይነት የሰውን ሰው-ነት በመካድ ለሚያስተምሩት የስህተት አስተምሮአቸው የሚያነሷቸውን ጥቅሶች በማንሣት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሾችን እንሰጣለን፡፡
ዛሬም በቀጣይነት የሰውን ሰው-ነት በመካድ ለሚያስተምሩት የስህተት አስተምሮአቸው የሚያነሷቸውን ጥቅሶች በማንሣት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሾችን እንሰጣለን፡፡
·
2ቆሮ.5፥1 ፦ ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ
ሥፍራ ሰው-ነታችንን “ምድራዊ ድንኳን” በማለት ይጠራዋል፡፡ ድንኳን ጊዜያዊ መኖርያ እንደኾነ እንዲሁ፣ ይህ የለበስነው ሥጋችንም
በምንኖርበት ጊዜያዊ ዓለም ኗሪ፣ ለድካም ተጋላጭ፣ ሙስና መቃብር የሚያገኘው ነው፤ ስለዚህም ሥጋ መንፈሳዊ አካልን ሊለብስ ዳግም
እስኪነሣ ድረስ በሞት ዓረፍተ ዘመኑ ይገታል፡፡ “የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰው-ነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል”
(2ቆሮ.4፥16) እንዲል፣ ይህ እንደድንኳን ያለው ጊዜያዊ ማደርያችን የኾነው ሰው-ነታችን፣ ይለወጣል፣ ይጠፋል፣ ይታደሳል፣ በክርስቶስ ኢየሱስ
ከማይጠፋውና ሊሻር ከማይችለው ከሚኾነው ዳግም ትንሣኤ የተነሣ መንፈሳዊ አካልን ይለብሳል፡፡
Thursday, 28 December 2017
የማይለወጠው ዥንጉርጉሩ ነብርና የኢትዮጲያዊ መልክ
ነቢየ እግዚአብሔር ኤርምያስ፦ “በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ
ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? በዚያን ጊዜ ክፋትን የለመዳችሁ እናንተ ደግሞ በጎ ለማድረግ ትችላላችሁ፡፡”
(ኤር.13፥23) በማለት፣ ስለይሁዳ ኃጢአት በከባድ ወቀሳ ይናገራል፡፡ ነቢዩ ኤርምያስ ይሁዳ ተጠራርጋ በእግዚአብሔር ፍርድ
ልትጠፋ እንዳለች በእግዚአብሔር ስለተረዳ፣ ሚስትን ከማግባትና ልጆችንም ከመውለድ ተከልክሏል፤ (ኤር.16፥1-4)፡፡ ትዳር
ብቻም ሳይኾን ወዳጆቹም እጅግ ጥቂቶች ነበሩ፤ አኪቃም (26፥24)፣ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስና (39፥14) ኢትዮጲያዊው
አቤሜልክ ናቸው (38፥7)፤ የክፋቱ ጠጣርነት ከሰው በብዙ ስላገለለው ረጅም ዘመኑን ያሳለፈው በሐዘን ነው፡፡
የይሁዳ ኃጢአቶች የተገለጡና ለኹሉ የታዩ ነበሩ፤ “ይሰርቃሉ፥
ይገድላሉ፥ ያመነዝራሉ፥ በሐሰትም ይምላሉ፥ መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም ይገፋሉ፥ በቅዱሱም ስፍራ ንጹሕ ደምን ያፈስሳሉ፥
ስሙም በተጠራበት በቤተ መቅደሱ በፊቱ ቆመው፦ ይህን አስጸያፊ የሆነ ነገርን ሁሉ አላደረግንም ብለው ይክዳሉ፣ ስሙ የተጠራበት
ቤት በዓይናቸው ፊት የሌቦች ዋሻ አደረጉት፣ የቀደሙት አባቶቻቸው እግዚአብሔርን ተዉ፣ አመነዘሩ፣ አማልክት ያልሆኑትን ለራሳቸው
አማልክትን አድርገው፣ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ አመለኩአቸውም ሰገዱላቸውም፥ ያስቈጡትም ዘንድ በሰገነታቸው ላይ ለበኣል
አጠኑ፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቍርባን አፈሰሱ፣ ሕጉንም አልጠበቁም፤ እንዲኹም እነርሱም ከአባቶቻቸው ይልቅ ክፉ
አድርገዋል፤ እነሆም፥ ሁላቸውም እንደ ክፉ ልባቸው እልከኝነት ሄደዋል እርሱንም አልሰሙትም” (7፥1-11፤ 16፥11፤ 20፤
22፥9፤ 23፥10፤ 32፥29፤ 44፥2፤ 23)፡፡ በዚህ ኃጢአታቸው እግዚአብሔርን ፈጽመው አስቆጥተውታል፡፡
Tuesday, 26 December 2017
በጋሻው “አፍንጫው ሲነካ[ስሙ ሲነሣ]፣ ዓይናችኹ ላላቀሰ” ኹሉ!
Please read in PDF
በግልጽ አንድ ያልተግባባነው ነገር አለ፤ የሐሰት ትምህርትን መቃወምና የሐሰት መምህራንን አለመቀበል የወንጌል ልብ አለመያዝ ወይም በወንድም ላይ መፍረድ ማለት አይደለም፡፡ ለበጋሻው ሳልራራለት ቀርቼ አልነበረም የሐሰት ትምህርቱን የተቃወምኩት፡፡ “አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥ አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ፤” (ይሁ.22-23) የሚለውን የቅዱስ ይሁዳ ቃልም ፈጽሞ ጠፍቶኝ ወይም ተዘንግቶኝ አይደለም፡፡
ብናስተውል፣
የሐሰት ትምህርትን እንደቃሉ መቃወም እውነተኛ አማንያን እንዲጠበቁና እንዲጠነቀቁ ማድረግ ብቻ ሳይኾን፣ ሐሰተኛውን መምህር እንዲመለስ
ተግሳጻዊ በኾነ መንገድ “የመማጸንም ሥራ” ነው፡፡ ትምህርቱን ስንቃወም ሰውየውን[የሐሰት አስተማሪውን] ከመጥላት ጋር አይደለምና፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ የነበረውን የታወቀውን አመንዝራ ሰው፣ “ … እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው”
ሲል፣ ከጥላቻና መዳኑን ካለመፈለግ አንጻር ሳይኾን፣ “ መንፈሱ በጌታ
በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ” ነው፤ (1ቆሮ.5፥5)፡፡
Monday, 11 December 2017
Thursday, 7 December 2017
የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፮
መጽሐፍ ቅዱስ ሰው ሥጋም መኾኑን ቢናገርም፣ የቃል እምነት አገልጋዮች ግን
ይህን እውነት ከዓውድ ውጪ አጥምመው “ሰው መንፈስ ነው ለማለት” የሚጠቅሷቸው ጥቅሶች አሏቸው፡፡ ዋና ዋናዎቹን ከዚህ በታች እያነሣን፣
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሽ እንሰጥበታለን፡፡
·
ዘፍ.1፥26-27 እና 2፥7፦ እኒህን
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በባለፉት ጊዜያት በተደጋጋሚ ተመልክተናልና የቀደሙትን ክፍሎች እንድትመለከቱ በመጋበዝ አልፌዋለሁ፡፡ “ሰዎቹ”
ሰውን “መንፈስ ነው” ለማለት ከሚጠቅሷቸው ጥቅሶች መካከል መኾናቸውን ግን ማስታወስ እወዳለሁ፡፡
·
ዮሐ.3፥1-13፦ ሰውን አመናፋሾቹ
የሐሰት መምህራን ከዘፍጥረት መጽሐፍ ቀጥለው የሚንደረደሩት ወደዚህ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ክፍል ነው፡፡ እንግዲህ ቅዱሳን መጻሕፍትን
በየዓውዳቸው ለማያጠና ተማሪ፣ “እምነትና በጎ ሕሊናውን ያስጥሉታል፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር እንዲጠፋ ያደርጉታል፤”
(1ጢሞ.1፥19)፡፡ ስለዚህ “ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ እንደማይችሉ ሞኞች ሴቶች፣ ከተነዳላቸው ወደየሞት
ወጥመዳቸው ሰተት አድርገው ያስገቡታል፤ እኛ ግን ስለምንሰማው ነገር ልንጠነቀቅ፤ ባለማስተዋልም ልንዘለል አይገባንም፤ (2ጢሞ.3፥6-7)፡፡
Monday, 4 December 2017
መልዐከ መዊዕ አባ የማነ ብርሐን ካሳሁን አፈርንሎት!
Please read in PDF
በቀን 24/3/10 8:30 ገደማ
በሻሸመኔ ከተማ
ማኅበረ ኢየሱስ
ባዘጋጀው ጉባኤ
ላይ ቀሚሳቸውን
ለብሰው መስቀላቸውን
ጨብጠው እንደጉባኤው
እድምተኛ ከሌሎች
ቀሳውስት፣ ዲያቆናትና
ሰንበት ተማሪዎች
ጋር በመኾን
ልክ ጸሎት
በሚጀመርበት ሰዓት
ዱላና ድንጋይ
አስጨብጠው ወደመድረኩ
በመውጣት የያዙትን
መስቀል ወደኪስዎ
ከትተው ድብደባ
ባርከው በማስጀመርዎ
አፈርንሎት!
እርስዎን የማውቅዎ በ2004 ዓ.ም እኔ በወንጌል ጉዳይ ተከስሼ በእርስዎ ፊት ቀርቤ በብዙ ጩኸት ይከሱኝ ከነበሩት ከሳሾች በተሻለ ለዘብተኝነት ሲናገሩ ሰምቼዎ ነበር፤ የዚያኔ ጌታ ልብዎን "ለወንጌል አለዝቦ የሥጋ ልብ" እንዲያደርግልዎ በልቤ ማልጄዎት ነበር፤[ዲያቆን ለአባ ቆሞስ መጸለይ ያልተለመደ ቢኾንም¡] ዳሩ ግን ልብዎ ደንድኖ ጆሮዎ ከመስማትና ከማስተዋል ችላ ብሎ፣ በአመጸኝነትና በማን አለብኝነት የእርስዎን የግብር ልጆች አስከትለው በመምጣት፣ ወንጌል ሊማማሩ የተሰበሰቡትን የገዛ ልጆችዎን፣ "ተሳስተዋል ቢሉ መክረው አስተምረው መመለስ ወይም ባይቻልዎ ከእርስዎ ለሚሻል አባት ማስመከር ሲገባዎ" እጅና እግር ሰንዝረው ተማትተው ደም በማፍሰስዎ አፈርንልዎት!
እርስዎን የማውቅዎ በ2004 ዓ.ም እኔ በወንጌል ጉዳይ ተከስሼ በእርስዎ ፊት ቀርቤ በብዙ ጩኸት ይከሱኝ ከነበሩት ከሳሾች በተሻለ ለዘብተኝነት ሲናገሩ ሰምቼዎ ነበር፤ የዚያኔ ጌታ ልብዎን "ለወንጌል አለዝቦ የሥጋ ልብ" እንዲያደርግልዎ በልቤ ማልጄዎት ነበር፤[ዲያቆን ለአባ ቆሞስ መጸለይ ያልተለመደ ቢኾንም¡] ዳሩ ግን ልብዎ ደንድኖ ጆሮዎ ከመስማትና ከማስተዋል ችላ ብሎ፣ በአመጸኝነትና በማን አለብኝነት የእርስዎን የግብር ልጆች አስከትለው በመምጣት፣ ወንጌል ሊማማሩ የተሰበሰቡትን የገዛ ልጆችዎን፣ "ተሳስተዋል ቢሉ መክረው አስተምረው መመለስ ወይም ባይቻልዎ ከእርስዎ ለሚሻል አባት ማስመከር ሲገባዎ" እጅና እግር ሰንዝረው ተማትተው ደም በማፍሰስዎ አፈርንልዎት!
Saturday, 2 December 2017
የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፭
ü
ዘፍጥ.2፥7
ይህ ክፍል የምዕ.1 ሌላ እይታ ወይም ማብራሪያ እንጂ ከስድስቱ ቀናት ውጪ ቀጣይ ታሪክን በራሱ የያዘ አይደለም፡፡ የፍጥረትን
ታሪክ በተመለከተ ከሁለት አቅጣጫ በመመልከት ወይም የምዕ.1ን የአፈጣጠር ሁኔታ ለማብራራት የተቀመጡ እንጂ፣ ሁለት የተለያዩ ዘመናት
ታሪኮችና ክስተቶች አይደሉም፡፡ ይህ ደግሞ የቅዱሳት መጻሕፍት ባሕርይ ነው፡፡ ለምሳሌ፦ አንድ ሰው “ከመሬት ተነሥቶ” አራቱ ወንጌላት
ይበዛሉና ይቀነሱ ቢል፣ ጤናማ ሃሳብ ነው ብለን አንቀበለውም፤ ምክንያቱም የአንዱን የጌታችን ኢየሱስን ትምህርትና ሕይወት ከአራት
ወንጌላውያን እይታ አንጻር አይተው አስፍረውታልና በደስታ ተቀብለነዋል፡፡ በዘፍ.1 እና 2 ላይም አንድን የፍጥረት ታሪክ በሁለት
እይታ መስፈሩን ማስተባበል አንችልም፡፡
አልያ ግን አሁንም ሌላ ጥያቄ ልናነሳ እንችላለን፤
“እግዚአብሔር ፍጥረትን በስድስት ቀን ፈጥሮ አልጨረሰም” ወደሚል አንድ እንግዳ ጫፍ ይወስደናል፡፡ ስለዚህ ምዕ.2 የምዕ.1 ማብራሪያ
ወይም ሌላ እይታ ነው፡፡[1]
ይህንንም እንዲህ በአጭሩ ማሳየት እንችላለን፤
ü
ስለሰማይና ምድር፦
v
ምዕ.1፥1-2 በአጭሩ፣ “በመጀመሪያ
እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ፡፡ ምድርም ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም
መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር” ይላል፤
·
ምዕ.2፥4-6 ላይ ይኸንኑ
ሲያብራራ፣ “እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ
ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው፡፡ የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ገና አልነበረም፤ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ገና አልበቀለም
ነበር፣ እግዚአብሔር አምላክ ምድር ላይ አላዘነበም ነበርና፥ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም፤ ነገር ግን ጉም ከምድር ትወጣ
ነበር፥ የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር” ይላል፡፡
Wednesday, 29 November 2017
የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፬
ሰው መንፈስ ነውን?
ሰው ሥጋና ነፍስ ወይም ሥጋና መንፈስ
ነው፤ የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት የብልጥግና ወንጌል[1] መምህራን፣
“ሰው መንፈስ ነው፤ ነፍስ አለው፤ በሥጋ ውስጥ ያድራል፡፡”[2] በሚለው
ፍጹም ክህደት ደምድመውታል፡፡ “ሰው መንፈስ ነው” የሚለው ትምህርታቸውን የሚያስተምሩበት ዓላማቸው ኋላ ላይ አግተልትለው ከሚያመጡት
“ፈጣጣ ክህደት” አንጻር እንጂ ወዲያው አይገባንም፡፡ በአጭሩ “ሰው መንፈስ ነው” የሚሉበት ዋና ዓላማቸው ሥጋ ለባሹን ሰው፣
“እግዚአብሔር ለማድረግ” ከሚባዝን ከንቱ ምናባዊ ቅዠት የተነሣ ነው፡፡ ይህንን በድፍረት ኢትዮጲያዊው የቃል እምነት መምህሩ ኃይሉ
ዮሐንስ እንዲህ ይላል፦
“ … አዎ ልክ እንደእግዚአብሔር ነን[ኝ] በሚለው እስማማለሁ፤ ምን ማለት ነው ይህ? መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ማስረጃዎች አሉኝ፤ በመጀመርያም የምሄደው ዘፍ.1፥26-28 ያለውን በመጥቀስ ነው፤ … ያ መልክና አምሳል ሙሉ ለሙሉ እግዚአብሔርን
እንድንመስል ያደርገናል የሚል አመለካከት አለኝ፡፡ ግን “detail” መሄድ ቢያስፈልግ ጌታችን ኢየሱስ ስለራሱ የተናገራቸው
ነገሮች ትዝ ይሉኛል፤ በዮሐ.14፥8 ላይ … “እኔና አብ አንድ ነን” ያለበት ሃሳብ በእኔ አመለካከት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ደግሞ ሰው ነው፤ በእኔ አመለካከት የሌላውን ሰው አመለካከት ልጋፋው አልችልም፡፡
ጌታ ኢየሱስ “እኔና አብ አንድ ነን” ካለ፣ ታላቅ ወንድማችን እንደዛ ካለ፣ እኛ ደግሞ ከአባታችን ጋር አንድነታችንን መናገር
እንችላለን፤ ምክንያቱም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው እኛም ደግሞ የእግዚአብሔር ልጆች ነን፡፡
|
Saturday, 25 November 2017
Monday, 20 November 2017
የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፫
2. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰውነቱ የተናገረውንና
የተነገረለትን ልክ ለመለኮቱ እንደተነገረ ተቆጥሮ ሲካድ እንመለከታለን፡፡ ለዚህም እንደዋቢ አድርገው የሚጠቅሱት፣ “የክርስቶስን
ከዘላለም የእግዚአብሔር ልጅ አለመኾኑን” ሁለት ሃሳቦችን በአንድነት በመስፋት ነው፡፡ እንዲህ በማለት፦ “አብና ወልድ
…እኩል አይደሉም፤ አብ ወልድን ይበልጣል፤ … ገብርኤል እንዳለው ስሙ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፤ ከዛ በፊት አባታችን ነው፤ ሌላ
ማስረጃ በዕብ.2 ላይ “ልጆቹ በሥጋና በደም እንደሚካፈሉ እርሱም እንዲሁ በሥጋና በደም ተካፈለ፤ ማን ተካፈለ? አባታቸው፡፡ ስሙ
የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል በሚል የእግዚአብሔር ልጅ ብሎታል፤ ከዛ በፊት ልጅ አልነበረም ወይ? ልጅ አልነበረም፤ አባታችን ነው፡፡
አባትና ልጅ መሆንም አይችልም፡፡ … ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘለዓለም ልጅ ከነበረ ለዘለዓለም ከአብ ያንስ ነበር ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም
ሥጋ የለበሰው መች እንደኾነ እናውቃለንና፤ ሥጋ የለበሰው የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ከድንግል ማርያም በተወለደበት ጊዜ ነው ልጅ
የኾነው፡፡ ያን ጊዜ “officially”[በግልጥ ወይም በይፋ ለማለት ይመስላል] እግዚአብሔር የነበረው ሥጋ ሲኾን፣ አብ ከእኔ
ይበልጣል፤ ብታምኑስ አብ ከእኔ ይበልጣል ብሏል፤ አብ ስለሚበልጠው እንደውም በሁሉ ነገር ይጸልይ ነበር እንደማንኛውም ሰው፤ እርሱ
ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ነው ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ከኾነ “somehow”[እንደምንም]
የኾነ ቦታ ተወልዷል ማለት ነው፤ …የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር አይደለም፡፡”[1]
በማለት፡፡
“ኢየሱስ ከአብ ጋር አይተካከልም” ለማለት መናፍቃኑ የሚጠቅሱት
ጥቅስ፣ በእውኑ ክፍሉ እነርሱ እንደሚሉት ሃሳባቸውን ይጋራልን? እውን ቃሉ እነርሱ እንደሚሉት የኢየሱስን የመለኮታዊ “ታናሽነት” ይናገራልን?
የጌታችን ኢየሱስ ልጅነት ወይም አባቴ ብሎ መጥራቱ የእርሱን አምላክ አለመኾንን ያመለክታልን? ዓውዱስ ያንን የሚል ነውን? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
መለኮታዊ ክብር እንደሌለው የሚያመለክት ነውን? … እና ሌሎችንም ተያያዥ ጥያቄዎችን በማንሳት መመርመር ይኖርብናል፡፡
“አብ ከእኔ ይበልጣል” የማለቱ ምክንያት
ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ እጅግ በተደጋጋሚ የክርስቶስ
ኢየሱስ ጌታችንን ከአብ ጋር ተካካይነት ሲገልጥልን አይተነዋል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደአባቱ
እንደሚሄድ በተናገራቸው ጊዜ ልባቸው ታውኳል፣ (ዮሐ.14፥1)፣ ደግሞም ፈርተዋል፤ (ቁ.27)፡፡ ስለዚህ መፍራትና መሸበር
እንደሌለባቸው በሚያጽናና ቃል ተናገራቸው፡፡ እንደውም የእርሱ ወደአብ መሔድ የተሻለ መኾኑን ስለሁለት ምክንያት ተናገራቸው፤
(1) “ለዘላለምም
ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤”(ቁ.15-16)፣ (2) ጌታችን ኢየሱስ ወደአባቱ በመሄዱ አብ እርሱን ያከብረዋል፤
(ዮሐ.17፥5)፡፡ ደቀ መዛሙርቱ እኒህን ታላላቅ ምክንያቶች ያስተዋሉ አይመስሉም፡፡ ስለዚህም ለራሳቸው እጅግ ከማሰብ የተነሣ በራሳቸው
ሃሳብና ኀዘን ውስጥ ተዋጡ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ እነርሱ በዚህ ዓይነት ድብልቅልቅ ስሜት ውስጥ እያሉ፣ “የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ
አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር” በማለት ተናገራቸው፡፡ ይህንንም ስለሁለት ነገር ተናግሯቸዋል፡፡ እኒህም፦
Thursday, 16 November 2017
የብልጽግና ወንጌል፣ ከጌታችን ኢየሱስ ያልኾነ ልዩና እንግዳ ወንጌል - ክፍል ፪
ክፍል
አንድ
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መለኰታዊ ማንነት መካድ፣ በእምነት እንቅስቃሴ
መምህራን ዘንድ እጅግ የታወቀና እንግዳ ያልኾነ ነገር ነው፡፡ ምንም እንኳ በትምህርቶቻቸው መካከል በኢየሱስ ክርስቶስ “እንደሚያምኑ”
ቢናገሩም፣ ነገር ግን እናምናለን የሚሉትን ሲያብራሩትና ሊያስተምሩት ሲነሡ ግን በትክክል ሲክዱት ይስተዋላል፡፡ በእርግጥም፣ የኑፋቄ
መምህራንን ከምንለይበት መንገድ አንዱ፣ በደፈናው እናምናለን የሚሉትን የትኛውም ትምህርታቸውን፣ “እስኪ አብራሩት” ሲባሉ፣ ኑፋቄያቸው
ወለል ብሎ ይታያል ወይም ከመጽሐፍ ቅዱስ በተቃርኖ ይቆማል፡፡
ስለጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውም ትምህርት
እንዲህ የሚል ነው፦
“ኢየሱስ መለኮታዊ መኾኑን ያወቀውና
ያገኘው በውስጡ መኖሩን ፈልጐ ካገኘ በኋላ ሲኾን፣ ይህንንም በማወቁና ፈልጎ በማግኘቱ እጅግ ታላቅ አስተዋይ ሰው ነው፤ … ራሱም
በአንደበቱ፣ “የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር” (ዮሐ.14፥28) ብሏልና፣ ከአብ
ያንሳል፡፡ ሰው ብቻ ኾኖ እንጂ አምላክ በመኾን ፈጽሞ አልመጣም፡፡ ደግሞም በማናቸውም ሥፍራ ራሱን “እኔ አምላክ ነኝ” ብሎ
አልገለጠም፡፡”
|
በማለት ይናገራሉ፡፡ ይህ ትምህርታቸው
የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በግልጥ የሚክድ ነው፡፡
በዚህ ትምህርታቸው ውስጥ ክርስቶስን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስን በመቃረን
ብዙ ኑፋቄያት ተሰግስገው እናያለን፡፡ በዋናነትም ብንጠቅስም፦
Subscribe to:
Posts (Atom)