Monday, 17 February 2025

ሕይወት ቴቪን "የእውነት ቃል አገልግሎት" ሊታደግ?

 Please read in PDF

መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ቃል፣ “አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል።” (1ቆሮ. 15፥33) ይላል። “አትሳቱ” የሚባለው ለሚያውቁና ለተረዱ አማኞች ነው። የሚባልበትም ምክንያት፣ የሚያስቱና የሚያሳስቱ ስላሉ ነው። ከክፍሉ እንደምንረዳው በቆሮንቶሳውያን መካከል ትንሣኤ ሙታንን በመናቅና በማቃለል፣ ሕይወትን፤ ዕለታዊ ኑሮን ከመብልና ከመጠጥ ጋር ብቻ ያያያዙትን “አማኞች” ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ካሉት መራቅና ኅብረታቸውን መተው እንደሚገባ ይናገራል። ምክንያቱም ክፉ ባልንጀርነት የመልካሙን ዐመል ስለሚያጠፋ ነው ይለናል። ከበላተኛ ከጠጪ ወይም የሆድን ነገር ብቻ ከሚያወሩ ጋር መዋል፣ ትንሣኤ ሙታንን እንድንንቅ ያደርጋሉና። በሌላ ንግግር የማይገባ ግንኙነት እንደ ጭንቁር እንደሚባላ ማስተዋል እንችላለን።

 

ድኅነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው

 


Tuesday, 11 February 2025

Fayyisuun kan Waaqayyooti!

                         Ani garuu sagalee galataatiin,
                         aarsaa siif nan dhi'eessa;
                        wanta ani wareeges nan baasa;
                       fayyisuun kan Waaqayyoo ti! (Yonas 2:10)



 

Monday, 10 February 2025

ከአንድ ዐይነትነት የመንፈስ አንድነት ይበልጣል።

 Please read in PDF

ዶግማና ቀኖና የማያሳስባቸውና የማያስጨንቃቸው፣ አንድ ላይ ያሉ አንድ ዐይነት “ኅብረቶች” ብዙ ናቸው። የሕይወት ልምምድና የኑሮ ዘይቤ ግድ የማይሰጣቸው፣ በጋራ ግን "መንፈሳዊ የሚመስል ኅብረት" ያላቸው ጀማዎች፣ በዘመናችን እንደ አሸን የፈሉ ናቸው። በአንድ ወቅት ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ተስማምተው አንድ ኾነው ነበር፣ ቅዱስ ጳውሎስን ለመክሰስ፤ ነገር ግን አንድነታቸው የትንሣኤ ሙታን የዶግማ ጥያቄ ሲነሣ፣ ብትንትናቸው ወጣ፤ “... ይህንም ባለ ጊዜ በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን መካከል ጥል ሆነ ሸንጎውም ተለያየ።” (ሐ.ሥ. 23፥7) እንዲል።

Friday, 31 January 2025

ወደ አዲስ ኪዳናዊ የመመለስ ተሐድሶ ያስፈልገናል!

 Please read in PDF

ከዚህ ቀደም የጻፍኹትን ልጥቀስ፣

“ተሐድሶ፣ “ሐደሰ” ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን፣ ትርጕሙ “አዲስ አደረገ” የሚለውን ትርጕም ታሳቢ ያደርጋል። በተገብሮ (Passive) “ተሐድሰ” ከሚለው ቃል ደግሞ፣ “ተሐድሶ” የወጣ ሲኾን፣ ትርጕሙ “አዲስ ኾነ” ማለት ነው። ስለዚህም ስያሜው ድርጊትን እንጂ ተቋማዊነትን ወይም አደረጃጀትን ፈጽሞ አያመለክትም።” [1]

Monday, 27 January 2025

ተሐድሶም አብሮ እንዳይገፋ!

Please read in PDF

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ጥር ፲፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ የቤተክርስቲያ መብትና ጥቅም ለማስከበርና 

የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጥብቅ እየሠራች መኾኑን በራሷ የትስስር ገጾች አመልክታለች። ቤተክርስቲያኒቱ በተለይም፣

“ ... ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አካላት መብትና ጥቅሟን የሚነኩ

* በአስተምህሮቿ

* በዕምነቷ

* በንዋያተ ቅድሳቶቿ ላይ መሰረታቸውን ያደረጉና ትዕግስቷን የሚፈታተኑ ክብርና ሉአላዊነቷን የሚዳፈሩ እኩይ የትንኮሳ ተግባራት እየተፈጸመባት ይገኛል ...”

በማለት ገልጻለች።

Saturday, 25 January 2025

ጥበብ ልቆ ታየ

Please read in PDF 

የጠቢባን ምክር የአስተዋዮች ጥበብ

የኀያላንና ባላባቶች መዝገብ

የብርቱዎች ትምክህት የብዙዎች ክብር

Monday, 6 January 2025

እረኞችና ሰብዓ ሰገል

 Please read in PDF

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከቅድስት ድንግል መወለድ፣ ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ ያልተሰማ እጅግ አስደናቂ ምስጢር ነው። ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስ ኢየሱስ ሲወለድ፣ ሊቀራረቡ የማይችሉ አካላት በአንድነት ተገናኝተዋል። ኀጢአት በሰዎች መካከል ልዩነትን አድርጎአል፤ ባለጠጋና ድኃ፤ ታላቅና ታናሽ፤ አዋቂና መሃይም፤ አለቃና ምንዝር፤ ጌታና ሎሌ፤ ጥቁርና ነጭ፤ ገዢና ተገዥ … በሚል።

Monday, 30 December 2024

በተሰቀለው ክርስቶስ ወንጌል አናፍርም!

 Please read in PDF

እናውቃለን፤ ዕርቃንና ወንጀለኛ በሚሰቀልበት መስቀል ላይ መሰቀል፣ ልዕለ ኃያል አምላክ ሲኾን በፍጡራን እጅ መያዙና ፍጹም መከራን ፈቅዶና ወድዶ በ“ሽንፈት” መቀበሉ ውርደት ነው፤ በሰው ዓይንም ሲታይ፣ የሚያሳፍር እንጂ የሚያኰራ አይደለም። እንዲህ ያለውንም ነገር “የምሥራች!” ብሎ መናገር ተቀባይነትና ተከታይን የሚያስገኝ ነገር አይደለም። ቅዱስ ጳውሎስ ይህን በሕዝብ ዘንድ እምብዛም ተቀባይነት የሌለውን ወንጌል በይፋ፤ በድፍረት ሰበከ!

Wednesday, 4 December 2024

የቄሣር ኮሪደር!

Please read in PDF 

በአጭር ቃል፣ በ58 ዓ.ም አከባቢ ነግሦ የነበረው የሮም ቄሣር ኔሮን፣ የሮምን ከተማ ከግማሽ በላይ በእሳት አነደዳት። ያነደበበት ምክንያቱ ከተማይቱ ስለ ደበረችው፣ ሌላ አዲስ ከተማ መገንባት ያመቸው ዘንድና ቃጠሎውን በክርስቲያኖች በማላከክ በኋላ በዚህ ሰበብ፣ ክርስቲያኖችን ለማሳደድና ለመግደል ይመቸው ዘንድ ነው። አባ ጎርጎርዮስ እንዲህ በማለት ይገልጹታል፣

“ … ብዙ ወንጌል መልእክተኞችን የፈጀው ኔሮን ቄሳር ነው።ለነገሩ መነሻ ያደረገው የሮምን መቃጠል ነው። ርግጥ በዘመነ መንግሥቱ አጋማሽ ላይ የሮም ከተማ በእሳት ጋይታለች። ያቃጠለው ማን እደ ኾነ አልታወቀም። ክርስቲያኖችን አሳጥ ለማጥፋት ኔሮን ራሱ ነው ያደረገው የሚሉ አሉ።”

Friday, 29 November 2024

በኢየሱስ አንደራደርም!

 Please read in PDF

ኢየሱስ የማናፍርበት ወንጌላችን ነው፤ ወንጌል ክርስቶስ ባይኖርበት “የምሥራች!” ተብሎ ሊሰበክ አይችልም፤ የቆምነው፤ ያለነው፤ የምንኖረው፤ የምንንቀሳቀሰው… እግዚአብሔር በክርስቶስ ካትረፈረፈው ጸጋ የተነሣ ነው፡፡ ያለ ክርስቶስ ምንም ነን፤ ርሱ በምንም ነገራችን ውስጥ የገባ ምሉዕ አምላክና ሰው ነው፡፡

Thursday, 28 November 2024

ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ¡? – (የመጨረሻ ክፍል)

 Please read in Pdf

መጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣኑ “ሲገሰስ”!

መጽሐፍ ቅዱስ የክርስትና ዋና ማዕከልና የትምህርቶቹም ኾነ የልምምዶቹ መሠረት ነው። ይህ እንዲኾን ያደረገው ዋናው ምክንያት ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊው ሥልጣን ራሱ እግዚአብሔር ስለ ኾነ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የትኛውንም ትምህርት ወይም መጽሐፍ ይዳኛል፤ ይመዝናል እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ከርሱ ውጭ በኾነ ትምህርትም ኾነ መጽሐፍ ፈጽሞ አይመዘንም፤ አይመረመርም።

Wednesday, 27 November 2024

ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ¡? - ክፍል አንድ

 Please read in PDF

የምዩጣኑ ጥርስ ያገጠጠ ውሸት!

መንደርደሪያ

ጃንደረባው የተባለ ሚድያ የሠራውን ቪድዮ፣ ተመልክቼአለኹ፤ አሰላስዬዋለኹም። ብዙ ሰዎች ደውለውልኝ የምጽፍበትን መንገድ ሲያመላክቱኝ፣ ከነገሩኝ ሰዎች ተጽዕኖዎች ነጻ ልወጣ እንዲገባኝ ከራሴ መክሬአለሁ። በተለይም ደግሞ አንዳንድ ነገሮች፣ በቀጥታ ከእኔ ጋር የሚያያዙ በመኾናቸው ይህን ጽፌአለሁ። እጅግ በጣም አስነዋሪ ውሸቶችን ደግሞ ለማጋለጥ ስል፣ በግል የተደረጉ የውይይት ቅጂዎችን ለመጠቀም ተገድጄአለኹ።

Tuesday, 12 November 2024

ጳጳሳቱና መታደስ የሚያስፈራቸው “ኦርቶዶክሳውያን”!

 Please read in PDF

ከኦርቶዶክሳውያን ጥቂት ጳጳሳትና መምህራን መካከል፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ጠንከር ያሉ የተሐድሶ ድምጾች በተለያየ መንገድ እየተሰሙ ነው። በባለፉት ወራት ፓትርያርክ አባ ማትያስ እንደ ተናገሩት፣

ምዕመናን ገንዘባቸውን የሚሰጡት ለሃይማኖት ማስፋፊያ እንጂ ለዘረፋ አይደለም።

በማለት የሙስናና የገንዘብ መውደድ ነገር ሥር የሰደደ መኾኑን ጠቁመዋል። በመቀጠልም ጳጳስ አብርሃም እንዲህ አሉ፣

ቤተ ክርስቲያን የሙሰኞች ዋሻ ኾናለች የሚለው ዘርፈ ብዙ ፍርጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንጂ ሲቀንስ አይታይም … ይህን አስነዋሪ ድርጊት እያወገዝን እውነትን ተላብሰን ከሙሰኞች የጸዳችና የከበረች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለተተኪው ትውልድ ልናስተላልፍ ይገባል።

በማለት ጠንከር ያለ ድምጽ አሰምተዋል።