መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ቃል፣ “አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት
መልካሙን አመል ያጠፋል።” (1ቆሮ. 15፥33) ይላል። “አትሳቱ” የሚባለው ለሚያውቁና ለተረዱ አማኞች ነው። የሚባልበትም ምክንያት፣
የሚያስቱና የሚያሳስቱ ስላሉ ነው። ከክፍሉ እንደምንረዳው በቆሮንቶሳውያን መካከል ትንሣኤ ሙታንን በመናቅና በማቃለል፣ ሕይወትን፤
ዕለታዊ ኑሮን ከመብልና ከመጠጥ ጋር ብቻ ያያያዙትን “አማኞች” ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ካሉት መራቅና ኅብረታቸውን መተው እንደሚገባ
ይናገራል። ምክንያቱም ክፉ ባልንጀርነት የመልካሙን ዐመል ስለሚያጠፋ ነው ይለናል። ከበላተኛ ከጠጪ ወይም የሆድን ነገር ብቻ ከሚያወሩ
ጋር መዋል፣ ትንሣኤ ሙታንን እንድንንቅ ያደርጋሉና። በሌላ ንግግር የማይገባ ግንኙነት እንደ ጭንቁር እንደሚባላ ማስተዋል እንችላለን።
Monday, 17 February 2025
ሕይወት ቴቪን "የእውነት ቃል አገልግሎት" ሊታደግ?
Tuesday, 11 February 2025
Fayyisuun kan Waaqayyooti!
Monday, 10 February 2025
ከአንድ ዐይነትነት የመንፈስ አንድነት ይበልጣል።
ዶግማና ቀኖና የማያሳስባቸውና የማያስጨንቃቸው፣ አንድ ላይ ያሉ አንድ ዐይነት “ኅብረቶች” ብዙ ናቸው። የሕይወት
ልምምድና የኑሮ ዘይቤ ግድ የማይሰጣቸው፣ በጋራ ግን "መንፈሳዊ የሚመስል ኅብረት" ያላቸው ጀማዎች፣ በዘመናችን
እንደ አሸን የፈሉ ናቸው። በአንድ ወቅት ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ተስማምተው አንድ ኾነው ነበር፣ ቅዱስ ጳውሎስን ለመክሰስ፤ ነገር
ግን አንድነታቸው የትንሣኤ ሙታን የዶግማ ጥያቄ ሲነሣ፣ ብትንትናቸው ወጣ፤ “... ይህንም ባለ ጊዜ በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን
መካከል ጥል ሆነ ሸንጎውም ተለያየ።” (ሐ.ሥ. 23፥7) እንዲል።
Friday, 31 January 2025
ወደ አዲስ ኪዳናዊ የመመለስ ተሐድሶ ያስፈልገናል!
ከዚህ ቀደም የጻፍኹትን ልጥቀስ፣
“ተሐድሶ፣ “ሐደሰ” ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ
ሲኾን፣ ትርጕሙ “አዲስ አደረገ” የሚለውን ትርጕም ታሳቢ ያደርጋል። በተገብሮ (Passive) “ተሐድሰ” ከሚለው ቃል ደግሞ፣
“ተሐድሶ” የወጣ ሲኾን፣ ትርጕሙ “አዲስ ኾነ” ማለት ነው። ስለዚህም ስያሜው ድርጊትን እንጂ ተቋማዊነትን ወይም አደረጃጀትን ፈጽሞ
አያመለክትም።” [1]
Monday, 27 January 2025
ተሐድሶም አብሮ እንዳይገፋ!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ጥር ፲፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ የቤተክርስቲያ
መብትና ጥቅም ለማስከበርና
የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጥብቅ እየሠራች መኾኑን በራሷ የትስስር ገጾች አመልክታለች።
ቤተክርስቲያኒቱ በተለይም፣
“ ... ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አካላት መብትና ጥቅሟን የሚነኩ
* በአስተምህሮቿ
* በዕምነቷ
* በንዋያተ ቅድሳቶቿ ላይ መሰረታቸውን ያደረጉና ትዕግስቷን የሚፈታተኑ ክብርና ሉአላዊነቷን የሚዳፈሩ
እኩይ የትንኮሳ ተግባራት እየተፈጸመባት ይገኛል ...”
በማለት ገልጻለች።
Saturday, 25 January 2025
Monday, 6 January 2025
እረኞችና ሰብዓ ሰገል
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ
ከቅድስት ድንግል መወለድ፣ ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ ያልተሰማ እጅግ አስደናቂ ምስጢር ነው። ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስ ኢየሱስ
ሲወለድ፣ ሊቀራረቡ የማይችሉ አካላት በአንድነት ተገናኝተዋል። ኀጢአት በሰዎች መካከል ልዩነትን አድርጎአል፤ ባለጠጋና ድኃ፤
ታላቅና ታናሽ፤ አዋቂና መሃይም፤ አለቃና ምንዝር፤ ጌታና ሎሌ፤ ጥቁርና ነጭ፤ ገዢና ተገዥ … በሚል።
Monday, 30 December 2024
በተሰቀለው ክርስቶስ ወንጌል አናፍርም!
እናውቃለን፤ ዕርቃንና ወንጀለኛ
በሚሰቀልበት መስቀል ላይ መሰቀል፣ ልዕለ ኃያል አምላክ ሲኾን በፍጡራን እጅ መያዙና ፍጹም መከራን ፈቅዶና ወድዶ በ“ሽንፈት”
መቀበሉ ውርደት ነው፤ በሰው ዓይንም ሲታይ፣ የሚያሳፍር እንጂ የሚያኰራ አይደለም። እንዲህ ያለውንም ነገር “የምሥራች!” ብሎ
መናገር ተቀባይነትና ተከታይን የሚያስገኝ ነገር አይደለም። ቅዱስ ጳውሎስ ይህን በሕዝብ ዘንድ እምብዛም ተቀባይነት የሌለውን
ወንጌል በይፋ፤ በድፍረት ሰበከ!
Wednesday, 4 December 2024
የቄሣር ኮሪደር!
በአጭር ቃል፣ በ58 ዓ.ም አከባቢ ነግሦ የነበረው የሮም ቄሣር ኔሮን፣ የሮምን ከተማ ከግማሽ በላይ በእሳት አነደዳት። ያነደበበት ምክንያቱ ከተማይቱ ስለ ደበረችው፣ ሌላ አዲስ ከተማ መገንባት ያመቸው ዘንድና ቃጠሎውን በክርስቲያኖች በማላከክ በኋላ በዚህ ሰበብ፣ ክርስቲያኖችን ለማሳደድና ለመግደል ይመቸው ዘንድ ነው። አባ ጎርጎርዮስ እንዲህ በማለት ይገልጹታል፣
“ … ብዙ ወንጌል መልእክተኞችን የፈጀው ኔሮን ቄሳር ነው።ለነገሩ መነሻ ያደረገው የሮምን መቃጠል ነው። ርግጥ በዘመነ መንግሥቱ አጋማሽ ላይ የሮም ከተማ በእሳት ጋይታለች። ያቃጠለው ማን እደ ኾነ አልታወቀም። ክርስቲያኖችን አሳጥ ለማጥፋት ኔሮን ራሱ ነው ያደረገው የሚሉ አሉ።”
Friday, 29 November 2024
በኢየሱስ አንደራደርም!
ኢየሱስ የማናፍርበት ወንጌላችን ነው፤ ወንጌል ክርስቶስ ባይኖርበት “የምሥራች!” ተብሎ ሊሰበክ አይችልም፤ የቆምነው፤ ያለነው፤ የምንኖረው፤ የምንንቀሳቀሰው… እግዚአብሔር በክርስቶስ ካትረፈረፈው ጸጋ የተነሣ ነው፡፡ ያለ ክርስቶስ ምንም ነን፤ ርሱ በምንም ነገራችን ውስጥ የገባ ምሉዕ አምላክና ሰው ነው፡፡
Thursday, 28 November 2024
ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ¡? – (የመጨረሻ ክፍል)
መጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣኑ
“ሲገሰስ”!
መጽሐፍ ቅዱስ የክርስትና ዋና ማዕከልና የትምህርቶቹም ኾነ የልምምዶቹ መሠረት ነው። ይህ እንዲኾን ያደረገው ዋናው ምክንያት ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊው ሥልጣን ራሱ እግዚአብሔር ስለ ኾነ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የትኛውንም ትምህርት ወይም መጽሐፍ ይዳኛል፤ ይመዝናል እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ከርሱ ውጭ በኾነ ትምህርትም ኾነ መጽሐፍ ፈጽሞ አይመዘንም፤ አይመረመርም።
Wednesday, 27 November 2024
ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ¡? - ክፍል አንድ
የምዩጣኑ ጥርስ ያገጠጠ
ውሸት!
መንደርደሪያ
ጃንደረባው የተባለ ሚድያ የሠራውን ቪድዮ፣ ተመልክቼአለኹ፤ አሰላስዬዋለኹም። ብዙ ሰዎች ደውለውልኝ የምጽፍበትን
መንገድ ሲያመላክቱኝ፣ ከነገሩኝ ሰዎች ተጽዕኖዎች ነጻ ልወጣ እንዲገባኝ ከራሴ መክሬአለሁ። በተለይም ደግሞ አንዳንድ ነገሮች፣
በቀጥታ ከእኔ ጋር የሚያያዙ በመኾናቸው ይህን ጽፌአለሁ። እጅግ በጣም አስነዋሪ ውሸቶችን ደግሞ ለማጋለጥ ስል፣ በግል የተደረጉ
የውይይት ቅጂዎችን ለመጠቀም ተገድጄአለኹ።
Tuesday, 12 November 2024
ጳጳሳቱና መታደስ የሚያስፈራቸው “ኦርቶዶክሳውያን”!
ከኦርቶዶክሳውያን
ጥቂት ጳጳሳትና መምህራን መካከል፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ጠንከር ያሉ የተሐድሶ ድምጾች በተለያየ መንገድ እየተሰሙ ነው። በባለፉት
ወራት ፓትርያርክ አባ ማትያስ እንደ ተናገሩት፣
“ምዕመናን ገንዘባቸውን የሚሰጡት ለሃይማኖት ማስፋፊያ እንጂ ለዘረፋ አይደለም።”
በማለት የሙስናና
የገንዘብ መውደድ ነገር ሥር የሰደደ መኾኑን ጠቁመዋል። በመቀጠልም ጳጳስ አብርሃም እንዲህ አሉ፣
“ቤተ ክርስቲያን የሙሰኞች ዋሻ ኾናለች የሚለው ዘርፈ ብዙ ፍርጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየተባባሰ እንጂ ሲቀንስ አይታይም … ይህን አስነዋሪ ድርጊት እያወገዝን እውነትን ተላብሰን ከሙሰኞች የጸዳችና የከበረች
ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለተተኪው ትውልድ ልናስተላልፍ ይገባል።”
በማለት ጠንከር ያለ
ድምጽ አሰምተዋል።
Friday, 8 November 2024
“መናፍቅ በመባሌ እጅግ ደስ ይለኛል”
“… በሥጋ ካየነው ያናድዳል፤ የሞተልንን
አምላክ በመከተል፣ ቅዱስ ጳውሎስ “እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔም ምሰሉ” ባለው መንገድ ከሄድን ያስደስታል፡፡
ምክንያቱም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ … በአባቱ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ተዋርዶአል፡፡ … ርሱ ምን የልተባለው ነገር አለ?
ዋናው ክሱ እኮ በሃይማኖት ነው፤ በሃይማኖት መከሰስ ማለት መናፍቅ ነው ተብሎ ነው፡፡ … ሰንበትን ሻረ፣ የእግዚአብሔር ልጅ
ነኝ አለ፣ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካከለ ብለው ነው፤ ያ ለነርሱ መናፍቅነት ነበረ … ርሱ ያልተባለው ምን አለ? …
ቅዱስ ጳውሎስ ምን ያልተባለው አለ? አስቀድሞ የብሉይ ኪዳን ዋና ጠበቃ ነበረ … ኋላ መንፈስ ቅዱስ አገኘውና ቀየረው፣ ጌታም
ምርጥ ዕቃዬ አለው፡፡ እነዚያ ግን መናፍቅ ነው ያሉት … በተለይ በነገረ ድኅነት እንዲህ መባሌ እጅግ ደስ ይለኛል፡፡”
(ብጹዕ አቡነ በርናባስ ከመለሱት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ)



.jpeg)





