ከአዲስ ኪዳን አገልጋዮች የተደነቀ የንግግር ችሎታ የሌለውና ነገር አቅንቶ መናገር የማይችለው (ከብሉይ ኪዳኑ ጥልቅ አዋቂና ልዩ ተናጋሪው አጵሎስ አንጻር ሲታይ) በጸጋው ያገለገለ ሐዋርያ እንደጳውሎስ ያለ አይመስልም፡፡ ጸጋውን፣ አለዋጋ የተሰጠውን ሐብትና መልካም ስጦታም አስቦ በሥጋ ለመመካት ለአንዲት ሰዐት በመዘናጋት ያዋለ አይደለም፡፡
የጌታ የትንሣዔውን ኃይል ለእርሱ እንዴት እንደተገለጠ ሲናገር፥ "
… ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ።እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም”፤ (1ቆሮ.15÷8-11)፡፡

