ቅድስት ድንግል ማርያም መኖርያዋና እድገቷ የዛብሎን ነገድ ድርሻ በምትሆነው በተራራማዋ ሐገር በገሊላ ናዝሬት ከተማ እንደሆነና ጌታ ኢየሱስንም በዚያ ፀንሳ በኋላም እንዳሳደገችው ታላቁ መጽሐፍ ይነግረናል፤ (ሉቃ.1÷26-27፤2÷39-50)፡፡ ናዝሬት በብሉይ ኪዳን ካልተጠቀሱት ከተሞች አንዷ ስትሆን ብዙ የማትታወቅም ነበረች፡፡ በሐዲስ ኪዳንም ከተማይቱ ምንም አይነት በጎ ገጽታ አልታየባትም፡፡ ይልቁን ከተማይቱ ፈጽሞ ተስፋ የተቆረጠባትና አንዳች መልካም ነገር አይገኝባትም የተባለችም ናት፤ (ዮሐ.1÷47)፡፡
ጌታ እግዚአብሔር ከፈቀደበትና ከወደደበት ሥፍራ መልካም ሰዎችን እንደሚያስነሳ ታላላቆቹ የአይሁድ ህግ አዋቂና የኃይማኖት መሪዎቹ እንኳ ፍጹም ስተው በነበረበት (ዮሐ.7÷41)፣ ናዝሬት ዝክረ ስሟ በተረሳበት ዘመን የናዝሬቱን ኢየሱስ የወለደች እመቤታችን በዚህች ከተማ በንጽዕናና በድንግልና ተጠብቃ ትኖርባት ነበር፡፡ እጅግ በተሸለሙ ደናግላን መካከል ራስን ለእግዚአብሔር ቀድሶ ለይቶ ማኖር አይከብድ ይሆናል(በራስ ብቃትና ንቃት ግን አይደለም!!!!) ነገር ግን በአመጸኞችና በክፉዎች በአመንዝሮች መካከል ራሰን በድንግልና ለመልካሙ ለእግዚአብሔር ፈቃድ መለየት እጅግ ከባድ ነው፡፡
በኢየሩሳሌም በታላቁ መቅደስ የሚኖሩ ፈሪሳውያንና ህግ አዋቂዎቹ አካላቸው እንጂ መንፈስና ልባቸው ያለው ካለመታዘዝ ዱር ውስጥ ነበር፡፡ በሙሴ ወንበር ተቀምጠው የማያደርጉትን እየተናገሩ፣ የማይኖሩትን እየሰበኩ፣ ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ እየጫኑ ለራሳቸው ግን በጣት መንካት ተጠይፈው የመበለቲቱን ቤት ይዘርፋሉ፣በአስራቱ ቀልተው በበኩራቱ ደምቀው ይኖራሉ፤ (ማቴ.23÷1-4)፡፡
ኢየሩሳሌምንና መቅደሱን ለሚያይ ሰው ብዙ ቅዱሳንና አገልጋዮች ያሉባቸው ይመስላሉ፡፡ ነገር ግን ጌታ አይኖቹ የተመለከቱት ወደኢየሩሳሌምና መቅደሷ ሳይሆን ወደገሊላዊቷ ናዝሬትና ወደድንግል ማርያም ነበር የተመለከተው፡፡ ሰው እንደሚያይ እግዚአብሔር አያይም፡፡ በኢየሩሳሌም ሕጉ ይነበባል፣ ቃሉ በየቀኑ ይተረተራል፣ መሥዋዕቱና የእህል ቁርባኑ አንድም ቀን ቀርቶ አያውቅም ነገር ግን እግዚአብሔር ከመስዋዕቱ በፊት ምህረትና ይቅርታን ነው የወደደው፡፡ እግዚአብሔር ሐገር አቋርጠን በምናቀርበው አገልግሎታችን፣ ሱባኤያችን፣ ጸሎታችን፣
ስዕለትና መዝሙራችን አይረካም፡፡ እርሱ እንደ ቅድስት ድንግል ለአንዱ ሙሽራ ለክርስቶስ በህይወት ድንግልና ያለእድፍና ያለነውር ከኃጢአት ርቀን ሙሽሪት ሆነን እንድንታጭለት አስቀድሞ ይሻልና፤ (2ቆሮ. 11÷2፤ ኤፌ.5÷27)፡፡
የዛሬዎቹ አብያተ ክርስቲያናት እንደ ኢየሩሳሌምና መቅደሷ ለአገልግሎታቸው እንጂ ለቅድስናቸው የሚጨነቁ አይደሉም፡፡ ከሰዐታት እስከ ቅዳሴ፣ ከመዝሙር እስከ ስብከቱ፣ ከበገና እስከክራሩ፣ ከነጠላ እስከካባው፣ ከቀሚሱ እስከመጎናጸፊያው … ምንም ነገር አልጎደለም ግን የሕይወት ንጽዕናና ቅድስናችን ልብና መንፈሳችን ከጥላሸት ይልቅ በኃጢአት ጠልሽቷል፡፡እግዚአብሔር በነጭ ነጠላና ባማረ ካባ አይሸነገልም ባማሩ ስብከቶችና መዝሙሮችም አይደለልም፡፡
እግዚአብሔር መልካም ነገርን ከመቅደሱ በማጣቱ ፈጽሞ አዝኗል፤ (ማቴ.23÷37-39)፡፡ በዚህም ኢየሩሳሌምና መቅደሷም እንደሚፈርሱ ተናገረ፤ (ማቴ.24÷1-3)፡፡ የተሰጠንን የንስሐ ዘመን ካልተጠቀምንበት ጌታ እግዚአብሔር መቅረዛችንን ከፊታችን ያነሳዋል፡፡ ኢየሩሳሌምና መቅደሷ የተሰጣቸውን የንስሐ ዕድል ስላልተጠቀሙ አሻራቸው እስከማይገኝ ድረስ ፈጽመው ፈርሰዋል ጠፍተዋል፡፡
ከሚጠበቀው ሲጠፋ ከማትጠበቀዋ ከናዝሬት ጌታ ሰው አገኘ፡፡ ገሊላዊቷን ድንግል ማርያምን፤ በቤቱ ከሚኖሩት ሳይሆን በሩቅ ካለችው፣ ከመልካሞቹ መካከል ሳይሆን ከክፉዎቹ፣ ከታላላቆቹም ሳይሆን ከትሁታኑ ከነአረጋዊው ዮሴፍ መካከል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገኘች፡፡ እግዚአብሔር በቤቱ ላሉት ብቻ ሳይሆን በሩቅም ላሉት አባትና አምላክ ነው፡፡ እናንተ ዛሬ በቤቱ ያላችሁ (ብዙ ጊዜም ከልክ አልፋችሁ … አህዛብ፣ መናፍቅ፣ አረማዊ… እያላችሁ የምትሳደቡ) እግዚአብሔር የበረሀ ወይራ የተባሉትን የሩቆቹን ከዋናው ዛፍ ግንድ ጋር በአንድ አጣብቆ ፍሬ እንዲሰጥ ማድረግ ይቻለዋልና ቅርንጫፎች ሆይ በልባችሁ አትታበዩ፤ (ሮሜ.11÷17-25)፡፡ እግዚአብሔር ከድንጋዮችም (ከአሕዛብና ካላመኑት መካከል)ለአብርሐም ልጆች ሊያስነሳለት ይችላልና ደግሜ እላለሁ በልባችሁ አትታበዩ፤ (ማቴ.3÷9-10)፡፡
ቸርነቱን አትዘንጉ ፈራጅ ነውና ፍርዱንም ቸል አትበሉ ምህረቱ የበዛ አምላክ ነውና፡፡እንኪያስ አስተውሉ!!! ገሊላዊቷ ድንግል በዚያ ክፉ ሥፍራ እንኳ ታምና መኖሯን እዩ!!! ይህች እናት በጸሎቷም እንዲህ አለች፦
"ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤ … ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤"(ሉቃ.1÷51)፡፡
እናንተ በኢየሩሳሌም በመቅደሱና በቤቱ የምትኖሩ በልባችሁ አትመኩ ጌታ በናዝሬት ምርጥ ሰው አለውና፡፡ ይልቁን በከንቱ ለተመካችሁበትና ሌሎችን ለናቃችሁበት፤ ለገፋችሁበትም ዘመናችሁ ንስሐ ግቡ፡፡
ጌታ ሆይ ማስተዋልህን አብዛልን፡፡አሜን፡፡
Thank you my brother. God bless you so much. what your doing is amazing just keep going what ever you are doing now.you don't know how much I love your daily bread.
ReplyDeleteGod be with you.
ዲያቆን!! አንተ ለምትናገረዉ ነገር እንዲሄድልህ ስለፈለክ ብቻ በቤቱ ያደገችዉን ድንግል (በቤቱ ከሚኖሩት ሳይሆን በሩቅ ካለችው) ብለህ ትናገራለህ ማስተማሩ ጥሩ ሆኖ ሳለ ነገር ግን በማስተዋል ቢሆን መልካም ነዉ ፡፡በተረፈ እግዚአብሄር ፀጋዉን ያሳድርብህ ሚስጥራትንም ይገለጥልህ፡፡
ReplyDeletetebarek
ReplyDeleteAYE MEKEBATRE DENGELE MARIAME ANTE ENDALKWE KWECHE AYEDELECHEM KEDESETE BATEKERESETEYANE ASETEMEREWA DENEGLE MARIAME EDEGETEWA BEBATE MEKEDESE NWE ATEKEBATRE EWENTENE SEBKE
ReplyDeleteegzeabher tsegawen yabzaleh degme elalew tebarek,,,"BeEyerusalem higu yenebebal kalu. beyekenu yeterekal meswetuna ye hilu kurban 1dim ken kerto ayawkim neger gin kemeswatu befit mihretina yekirtan new yewdedew" tsegawin yabzalik amen kale hiwetin yasemak
ReplyDeletekale hiwot yasemah Tsegawen yabzaleh
ReplyDelete