Friday, 24 May 2019
Monday, 20 May 2019
በሕማሙና በትንሣኤው ዙርያ የነበሩ ምስክሮች (ክፍል ሦስት)
Please read in PDF
3. ማርያም መግደላዊት፦ የክርስቶስ ከሙታን ትንሣኤ መካከል በእውነት መነሣት የክርስትና ዋና ማዕከል ነው፤ በመስቀል ላይ ቤዛ ኾኖ መሰቀሉ በእውነት ለኃጢአተኞች መኾኑና የቤዛነት ክፍያውም መረጋገጡን የሚያበስረው ከሙታን መካከል መነሣቱ ነው፤ “እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ” ክርስቶስ ከሙታን መካከል ተነሥቶአል፤ (ሮሜ 6፥4፤ 7፥6፤ ሐዋ. 2፥24፤ 2ቆሮ. 5፥17፤ ኤፌ. 4፥22፤ ቈላ. 3፥10)። ጌታ ኢየሱስ ከሙታን መካከል ባይነሣልን፣ “ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት፤ እስከ አሁን ድረስ በኃጢአታችሁ አላችሁ” (1ቆሮ. 15፥17) እንደ ተባለ፣ ከኃጢአታችን ሳንላቀቅ እስከ አኹን እንደ ተጣባን፣ የሙጥኝ ብለን እየኖርን አለን ማለት ነው። ክብር ይኹንለትና እርሱ ግን የኀጢአት ዋጋችንን በሥጋው መከራ በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶ ከፍሎልን፣ ዋጋችንም የጸደቀና የተረጋገጠ መኾኑን በትንሣኤው አጽንቶልናል።
3. ማርያም መግደላዊት፦ የክርስቶስ ከሙታን ትንሣኤ መካከል በእውነት መነሣት የክርስትና ዋና ማዕከል ነው፤ በመስቀል ላይ ቤዛ ኾኖ መሰቀሉ በእውነት ለኃጢአተኞች መኾኑና የቤዛነት ክፍያውም መረጋገጡን የሚያበስረው ከሙታን መካከል መነሣቱ ነው፤ “እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ” ክርስቶስ ከሙታን መካከል ተነሥቶአል፤ (ሮሜ 6፥4፤ 7፥6፤ ሐዋ. 2፥24፤ 2ቆሮ. 5፥17፤ ኤፌ. 4፥22፤ ቈላ. 3፥10)። ጌታ ኢየሱስ ከሙታን መካከል ባይነሣልን፣ “ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት፤ እስከ አሁን ድረስ በኃጢአታችሁ አላችሁ” (1ቆሮ. 15፥17) እንደ ተባለ፣ ከኃጢአታችን ሳንላቀቅ እስከ አኹን እንደ ተጣባን፣ የሙጥኝ ብለን እየኖርን አለን ማለት ነው። ክብር ይኹንለትና እርሱ ግን የኀጢአት ዋጋችንን በሥጋው መከራ በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶ ከፍሎልን፣ ዋጋችንም የጸደቀና የተረጋገጠ መኾኑን በትንሣኤው አጽንቶልናል።
Tuesday, 14 May 2019
Wednesday, 1 May 2019
“መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል” (ዮሐ. 10፥11)
Please read in PDF
ወንጌላዊው
ዮሐንስ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እረኝነት እጅግ አድምቆ ከሚያሳዩ ትምህርቶች አንዱንና ሰፊውን ጠቅሶ ጽፎልናል፡፡ ምዕራፉ ስለ
እረኝነት ብዙ ነገር የምንማርበት ቢኾንም፣ አንዱን ዘለላ ብቻ መዝዘን ለመማማር ወደድን፤ እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ የማኖሩን ወይም
አሳልፎ የመስጠቱንና ስለ በጎቹ ማናቸውንም ዋጋ ከፍሎ የሚያድን ስለ መኾኑ የተነገረውን አንድ አንቀጽ፡፡
በምድረ እስራኤል እረኝነት የተወደደ ተግባር ነው፤ በተለይም የበግ እረኝነት፡፡
በብሉይ ኪዳንም ኾነ በአዲስ ኪዳን ብዙ ጊዜ ከእረኝነት ጋር በተያያዘ በጎች ሲጠቀሱ፣ መልካም እረኞችም ለበጎቻቸው ባላቸው እንክብካቤና
ጠባቂነት፣ ታዳጊነትም ሲመሰገኑ እናያለን፤ ልክ እንዲሁ ደግሞ ምንደኛና ሙያተኛ እረኞችም ለሚጠብቋቸው እረኞች ባላቸው ተላላነትና
ዝንጉነት፣ እንዲሁም ጥቅመኛ ብቻ ስለ መኾናቸው እየተነሳ ሲወቀሱና ሲዘለፉ፣ ፍርድንም ሲቀበሉ እንመለከታለን፡፡
Saturday, 27 April 2019
የኢየሱስ የቀብር ሥነ ሥርዓት (ዮሐ. 19፥38-42)
Please read in PDF
“ኢየሱስን በዚያ አኖሩት” (ዮሐ. 19፥42)
ወንጌላዊው
ዮሐንስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ኹሉን አዋቂና ተቈጣጣሪ አድርጐ ያቀርበዋል፤ (ዮሐ. 2፥25፤ ኢየሱስ እንደሚሞት ያውቃል (ዮሐ.
12፥23፤ 13፥1)፣ እንዴት እንደሚሞት ያውቃል ( 12፥33)፣ መች እንደሚሞት ያውቃል (ዮሐ. 17፥1)፣ መከራውን ኹሉ ብቻውን
መቀበል እንደሚፈልግ ፈቃዱን ገልጦአል (18፥4)፣ ጊዜው ሳይደርስ እንዳይሞትም ያውቃል (11፥54)፤ ኢየሱስ ሥጋን የለበሰ ደካማ
መሲሕ ኾኖ ቢገለጥም ነገር ግን ኹሉን አዋቂና ተቈጣጣሪ ጌታ ነው። በእርግጥም የሞተው በአጋጣሚ አይደለም፣ እያወቀና ከትልቅ ፍቅሩ
የተነሣ ስለሚወደንና ስለሚያፈቅረን ነው።
Monday, 22 April 2019
እጅግ ረክሷልና!!!
Please read in PDF
ዓመት ሙሉ ታስሮ ባመቱ መፈታት
ወራት ሙሉ ወድቆ አንድ ቀን መነሳት
ለጊዜው መቆጠብ ለወራት መፈንጨት
በፋሲካ ሰሞን አማኝ አማኝ መሽተት
Wednesday, 17 April 2019
በሮተር ዳሙ ካቴድራል - ጣዖት አምልኮ?
Please read in PDF
ሕዝቅኤል
እስራኤልን ሲመለከታት በኀጢአት የተጨማለቀች አመንዝራ ሴትን ትመስላለች፤ ታማኝነቷን ያጐደለች ፍቅረኛ ናት፣ ከሕፃንነት ጀምሮ ቢከታተላትም፣
ከተጣለችበት ቢያነሣትም፣ “በተወለድሽ ጊዜ በዚያው ቀን እትብትሽ አልተቈረጠም ንጹሕም ትሆኚ ዘንድ በውኃ አልታጠብሽም፥ በጨውም
አልተቀባሽም በጨርቅም አልተጠቀለልሽም። በተወለድሽበት ቀን ከሰውነትሽ ጕስቍልና የተነሣ በሜዳ ላይ ተጣልሽ እንጂ ከዚህ አንዳች
ይደረግልሽ ዘንድ ዓይን አልራራልሽም፥ ማንም አላዘነልሽም።” (ሕዝ. 16፥4-5) ከተጣለችበት አንሥቶ በብዙ ምሕረቱ ቢታደጋትም
እርሷ ግን “ … አንቺም አደግሽ ታላቅም ሆንሽ፥ በእጅጉም አጌጥሽ፤ ጡቶችሽም አጐጠጐጡ ጠጕርሽም አደገ፥ ነገር ግን ዕርቃንሽን
ሆንሽ፥ ተራቍተሽም ነበርሽ።” እንዲል ፈጽማ አመንዝራ መንገድን ተከተለች።
Monday, 15 April 2019
ኒቆዲሞስ - ከዳግም መወለድ ይልቅ ኢየሱስ ይልቃል!
Please read in PDF
የሳምንቱ ስያሜ ኒቆዲሞስ ነው። የሚነበበው የወንጌል ንባብ ደግሞ ዮሐ. 3፥1-21 ነው። ክፍሉ በኢየሱስና በየአይሁድ መምህር በኾነው በኒቆዲሞስ ንግግር የደመቀ ኾኖ፣ የክፍሉ ዋና መልእክቱ ግን የኒቆዲሞስ መምህር መኾን ወይም የዳግም መወለድ ጉዳይ ብቻ አይደለም። እውነት ነው! በክፍሉ የኒቆዲሞሰ ታሪክ ተመዝግቧል፤ የዳግም ልደት ትምህርትና ጥልቅ ማብራሪያም አለ፤ ዋናው የወንጌሉ መልእክት ግን ይህ አይደለም።
የሳምንቱ ስያሜ ኒቆዲሞስ ነው። የሚነበበው የወንጌል ንባብ ደግሞ ዮሐ. 3፥1-21 ነው። ክፍሉ በኢየሱስና በየአይሁድ መምህር በኾነው በኒቆዲሞስ ንግግር የደመቀ ኾኖ፣ የክፍሉ ዋና መልእክቱ ግን የኒቆዲሞስ መምህር መኾን ወይም የዳግም መወለድ ጉዳይ ብቻ አይደለም። እውነት ነው! በክፍሉ የኒቆዲሞሰ ታሪክ ተመዝግቧል፤ የዳግም ልደት ትምህርትና ጥልቅ ማብራሪያም አለ፤ ዋናው የወንጌሉ መልእክት ግን ይህ አይደለም።
Friday, 12 April 2019
ራሴን ያየሁበት ምስል
Please read in PDF
ይህን
ምስል ስመለከት ኹለት የተቃረኑ ሃሳቦች ወደ ውስጤ መጡ፤ አንደኛው የካቶሊኩ ፖፕ ስለምን እንዲህ ራሳቸውን አዋረዱ? ምን ይኾን
ልቡናቸውን የነካው? ከአራት መቶ ሺህ በላይ በጦርነት የተፈጁትና ያለቁት የኑብያ ልጆች [ሱዳናውያን] አንጀታቸውን አድብነው፣ ጉበታቸውን አፍርሰው፣ በመሪር እንባ በፊታቸው ድቅን
ብለውባቸው ይኾንን? የዓለም መገናኛ ብዙሃን እንኳን ሊዘግበው ሊመለከተው ያልወደደውን የኑብያን ልጆች [የሱዳናውያንን] ሰቆቃ በአካል
ሄደው ተመልክተውት ራሳቸውን ስተው ይኾንን? እንዲህ በማድረጋቸውስ “የሱዳኑ መሪ” ልቡ ይሰበር ይኾንን? የመቶ ሺህዎቹ የኑብያ
ልጆች ኅሊናውን አልገደለው፣ ልቡን አላደነደነው ይኾንን? የፖፕ ፍራንሲስ “ውርደት” የራሱ “ውርደት” እንደ ኾነው ይሰማው ይኾንን?!
በመላ ዘመኑ የኑብያዋ የሱዳን መሪ የእኒህን ፖፕ ድርጊት መዘንጋት ይቻለው ይኾን? ስል ...
Sunday, 7 April 2019
በጎና ክፉ ባሪያ (ሉቃ. 19፥11-27)
Please read in PDF
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ዋቢ ያደረገው ዓቢይ ጾም፣ የጾሙ ሳምንታት በየራሳቸው
ስያሜ አላቸው፤ ስያሜዎቹን የሰየመው “የዜማ ደራሲው” ያሬድ ሲኾን፣ የጌታ ኢየሱስን ሕይወቱንና ትምህርቱን ከወንጌላት በመውሰድ
የሰየማቸው ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኢ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የኾኑ ብዙ ትምህርቶች ያሉትን ያህል፣ ከጅማሬአቸው
መልካም የነበሩና አኹንም ድረስ በመልካም ምሳሌነት የተያዙን አንጥሮ፣ በመጽሐፉ ቃል መዝኖ መቀበል ደግሞ ለእኛ ለአማንያን የተተወ
ነው። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተገኘውን ኹሉ እንድንቀበል ሳይኾን በመጽሐፍ መዝነን እንድንቀበል ቃሉም መንፈሱም ይመክሩናልና።
የዚህኛው ሳምንት ስያሜ ገብር ኄር ይባላል፤ ትርጉሙም መልካም ወይም ትጉህ
ባርያ ማለት ነው፤ ይህ ስያሜ ደግሞ የተወሰደው ከማቴ. 25፥14-30 ወይም ከሉቃ. 19፥12-27 ካለው የወንጌል ክፍል ነው፤
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ክፍል የተናገረው ለሞቱ ወደ ኢየሩሳሌም እየወጣ በነበረበት ወራት ነው፤ በተናቁትና በተገፉት፣ በኢየሩሳሌማውያን
ፈጽመው በማይወደዱት ገሊላውያንና መንደሮቿ መካከል የቆየውና የነበረው ጌታችን ኢየሱስ፣ አሁን ለሞቱ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቷል። በገሊላ
የነበሩት እጅግ የተናቁ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ኃጢአተኞችና በኢኮኖሚም ደረጃ እጅግ ዝቅ ያሉ፣ ከፍተኛ የሥነ ልቡና ጫናም የነበረባቸው
ሰዎች ጭምር፤ ኢየሩሳሌም ደግሞ በሕጉ የሚመኩና የሚመጻደቁ፣ አግላይና ናቂ፣ ትእቢተኞችና ራሳቸው ብቻ የመሲሑ ተቆርቋሪ እንደ ነበሩ
አድርገው የሚያስቡ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውን የበዙባት ከተማ ነበረች።
Sunday, 31 March 2019
ደብረ ዘይት - “መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው?” (ማቴ. 24፥3)
Please read in PDF
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ
ዘይት ተራራ ተቀምጦ ሳለ፣ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው መጥተው የነገረ ዳግም ምጽአቱን ምልክቶች ጠይቀውታል፡፡ ጌታ ኢየሱስና ደብረ
ዘይት እጅግ “የተሳሰሩ” ናቸው፤ “እንደ ልማዱ ወደ ደብረ ዘይት ሄደ” (ሉቃ. 22፥39) በተደጋጋሚ ጌታችን ኢየሱስ ወደ ደብረ
ዘይት ተራራ ለጸሎትና በዚያውም ለማደር ይሄድ ነበር፤ (ዮሐ. 8፥1-2)፡፡ በዚያ አድሮ ማለዳ ማለዳ ከደብረ ዘይት ተነሥቶ አገልግሎትን
ይጀምራል፡፡ “ድኃው” ኢየሱስ፣ ቤት ያልነበረው ኢየሱስ (ሉቃ. 9፥58) የጸሎት ስፍራውንና ማደሪያውን ያደረገው በደብረ ዘይት
ነበር፡፡
Saturday, 30 March 2019
Sunday, 24 March 2019
መጻጉዕ - ፈዋሹ እግዚአብሔር
Please read in PDF
“እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና” (ዘጸ. 15፥26)
እስራኤል ከግብጽ ምድር ሲወጡ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በጸናች እጁ
በተዘረጋች ክንዱ፤ በተአምራት አሻግሮአቸዋል፤ ባሕሩን ከተሻገሩ በኋላ ሙሴ ሕዝቡን ይዞ ለሦስት ቀናት የተጓዘው ወደ ሱርም ምድረ
በዳ ነው፤ በዚያ ምድረ በዳ ላይ ሕዝቡ ውኃ ማግኘት አልቻሉም፤ ቀጥለው ወደ ማራ ቢመጡም የማራ ውኃ እጅግ መራራ ነበርና መጠጣት
አልቻሉም፤ ከዚህ የተነሣ ታላቁን ተአምራት፣ ድንቁን ነገር በኤርትራ ባሕር ዳርቻ ላይ የተመለከቱት እስራኤል፣ ባዳናቸውና በታደጋቸው
አምላክ መታመንን ትተው፣ “ሕዝቡም፦ ምን እንጠጣለን? ብለው በሙሴ ላይ አንጐራጐሩ” (ዘጸ. 15፥24)። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር
ለመነ፣ ያህዌ ኤሎሂም እንዳዘዘውም አደረገ፤ ውኃውም ጣፈጠ።
Tuesday, 19 March 2019
ምኩራብ
Please read in PDF
አይሁድ ወደ ባቢሎን በምርኰ በወረዱ ጊዜ የቀደመው ኪዳን “የአምልኮ ማዕከል” ከኾነው ከመቅደሱ ተለያዩ፤ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር በሦስተኛው ዙር የምርኰ ማጋዝ በአካል ወደ ኢየሩሳሌም በመምጣት ኢየሩሳሌም ገለበጣት፤ መቅደሷንም አፈረሰ፤ ከመቅደሱ ንዋየ ቅዱሳቱንም ዘረፈ፤ እስራኤልን ሙሉ ለሙሉ ባድማ አደረጋት።
አይሁድ ወደ ባቢሎን በምርኰ በወረዱ ጊዜ የቀደመው ኪዳን “የአምልኮ ማዕከል” ከኾነው ከመቅደሱ ተለያዩ፤ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር በሦስተኛው ዙር የምርኰ ማጋዝ በአካል ወደ ኢየሩሳሌም በመምጣት ኢየሩሳሌም ገለበጣት፤ መቅደሷንም አፈረሰ፤ ከመቅደሱ ንዋየ ቅዱሳቱንም ዘረፈ፤ እስራኤልን ሙሉ ለሙሉ ባድማ አደረጋት።
እናም የኪዳኑ ሕዝብ እስራኤል በምርኰ ሳሉ አምልኮ “ናፈቁ”፤
ከኢየሩሳሌም በቀር በሌላ ስፍራ [በባቢሎን ጭምር] መቅደስ መሥራት ባይቻላቸው፣ በዚያው በምርኰ ባሉበት ምድር ኾነው
የሚሰባበሰቡበትንና በዋናነትም ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚያነቡበትን፣ በንባብም የሚያመልኩበት ምኩራብ፣ በቁጥር አነስ ያሉ ሰዎችን
ሊይዝ በሚችል መልኩ በሕዝቡ መካከል ሠሩ፤ እናም በምርኰ ምድር ኾነው በንባብ እግዚአብሔርን ለማምለክ፣ ሊታዘዙትም ምኩራብን
ለሕዝቡ አቅራቢያ በኾነበት ስፍራ ተግተው ሠሩ።
Wednesday, 13 March 2019
Subscribe to:
Posts (Atom)





