Saturday, 31 August 2024

“ኑ ወደ ኦርቶዶክስ ተመለሱ!” ለምትሉን!

 Please read in PDF

ኦርቶዶክሳዊው ተሐድሶ እያየለና በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትን እያገኘ ሲመጣ፣ በቃላት በማባበል፣ በጥቅምና በክብር በማማለል፣ መልሰን አናወግዛችሁም በሚል የተስፋ ቃል በመስጠት … እየቀረበልን ያለው ጥያቄ፣ “ኑ! ወደ ኦርቶዶክስ ተመለሱ!” ሚል ነው። ከዚህ በታች የምናስቀምጣቸው ጠንካራ ምክንያቶች የመመለስና ያለ መመለስን ጥያቄ ትርጕም ይሰጡታል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወደ ኋላ ስለ መመለስ በማስጠንቀቂያ አዘል ከተጻፉ መልእክቶች አንዱ፣ የዕብራውያን መልእክት ነው። የሐዋርያት ሥራን መጽሐፍ ስናጠና እንደምናስተውለው፣ አስቀድሞ ክርስትናን ለተቀበሉ አይሁድ የመጀመሪያዎቹ የቤተ ክርስቲያን ዓመታት እጅግ አስቸጋሪዎች ነበሩ። በእነዚህ ጊዜያት ክርስትና በአጭሩ የአይሁድ ሃይማኖት ኾኖ ነበር። ከ120ው የጌታ ቤተ ሰቦች (ሐ.ሥ. 1፥15) ጀምሮ ኹሉም በአንድነት ያመልኩና ያገለግሉ የነበረውም በአይሁድ ቤተ መቅደስ ውስጥ ነበርና፤ (ሐ.ሥ. 2፥46፤ 3፥1፤ 5፥42)።

Sunday, 18 August 2024

የ“ታቦር” ስብከቴን ቀይሬአለኹ!

 Please read in PDF

ጌታችን ኢየሱስ ክብረ መንግሥቱን የገለጠበት፤ ማንነቱን ለደቀ መዛሙርቱ ያሳየበት የክብሩ ተራራ እውነት እጅግ አስደናቂ ነው። ጌታ፣ በፊልጶስ ቂሣርያ፣ “ለብቻውም ሲጸልይ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩና፦ ሕዝቡ እኔ ማን እንደ ኾንሁ ይላሉ? ብሎ ጠየቃቸው።” (ሉቃ. 9፥18) ደቀ መዛሙርቱ ሲመልሱ፣ የነቢያትን ስም በመጥራት እንዲኹም ከነቢያት አንዱ ነህ ይላሉ ብለው መለሱ። ቀጥሎም፣ “እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።” (ሉቃ. 9፥20) “ጴጥሮስም መልሶ፦ ከእግዚአብሔር የተቀባህ ነህ አለ።”ቅዱስ ጴጥሮስ ይህን ታላቅ እውነት በመመለሱ፣ “ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።” (ማቴ. 16፥17) በማለት የጴጥሮስን ዕድለኝነት ጌታችን መሠከረለት።

Wednesday, 31 July 2024

ለእውነተኛ ተሐድሶ ኦርቶዶክስን አይጠቅማትም!

 Please read in PDF

ከጥቂት ዓመታት ወዲህ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከተደረጉ “ፖለቲካዊ የቤተ ክርስቲያን ውሳኔዎች” አንዱ፣ ሰዎች በቋንቋቸው ወንጌል ሊማሩ ይገባል የሚል ነበር፤ በዚህ ዐሳብ ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ “በወንጌል ልብ” በተደጋጋሚ ይጠይቁ ከነበሩ ሰዎች መካከል አንዱ በመኾኔ፣ በጥያቄው ፍጹም እስማማለኹ። ነገር ግን መልሱ የተሰጠውና በተግባር ላይ የዋለው ፍጹም መንፈሳዊ ባልኾነ መንገድ ባለ መኾኑ ሳዝን ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት እጽናናለኹ!


Sunday, 28 July 2024

የፓሪስ ኦሎምፒክ ሴሰ*ኝነት፣ ሰዶ*ማ*ዊነት፣ በጌታ እራት ሲሳ*ለቁ!

 

“ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥”
(ሮሜ 1፥22)

በዘመናት መካከል ዓለምና ሥርዓትዋ፤ ሰይጣንና ሠራዊቱ ለእግዚአብሔርና ለሥራው ኹሉ ጠላትነታቸውን ደብቀው አያውቁም። ቅዱሱ መጽሐፍ፣ የዚህ ዓለም ሰዎች፣ “... የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት እየ ለወጡ ...”(ሮሜ 1፥25) በጥበባቸው ደንቆሮዎች እንደ ኾኑ በግልጥ ይናገራል።


Friday, 19 July 2024

ስለ ኦርቶዶክስ በልቤ ያለ ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት!

 Please read in PDF

ከልጅነቴ ያደግኹት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነው፤ የተጠመቅኹት፤ የቆረብኹት፤ በቅንአትና በትጋት ያገለገልኹት … በዚያ ነው። በዚያ የነበረኝ አገልግሎት በዕውቀትም በቅናትም እንደ ነበር ብዙዎች ምስክሮቼ ናቸው። የክብሩንና የትንሣኤውን ወንጌል በትክክል ስረዳና ስመሰክር ግን ብዙዎች ተቃወሙኝ፤ እናም አብረኸን ልትኾን አይገባም ሲሉኝና ሲገፉኝ ወጣኹ።

Friday, 5 July 2024

ወርቅ ሲደብስ!

 

ጳጳሱ ቅዱሳት መጻሕፍትን አላነበቡምን?

ጳጳሱ ለማርያም ያላቸው አስተምኅሮ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ በተቃራኒ የቆመ ነው፤ እንዲህ ያለ ነገር በርግጥ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ “የታወቁ መምህራን” የሚናገሩት ነው፤ ከዚህ ቀደም ዲያቆን ኃይሌ፣ “እመቤታችን ማማለድ አይደለም አፍርሳን መሥራት ትችላለች” ብሎ መናገሩንና ለዚህም ምላሽ መስጠታችን ይታወሳል፡፡ ለምን ኾን ብለው ማርያምን በማግነንና በማስመለክ፣ እግዚአብሔርንና ስሙን መሳደብ እንደሚፈልጉ አላውቅም፤ እግዚአብሔርንና እግዚአብሔር በልጁና በመንፈሱ የሠራውን ሥራ ባለማወቃቸውም እጅግ እደነቃለሁ!

Tuesday, 2 July 2024

ጌታ ኦርቶዶክስን በወንጌል ሊጎበኝ እያሰበ ቢኾንስ?

Please read in PDF

“የስብከተ ወንጌል”ና “የመንፈስ ቅዱስ ቀን”

በኹለቱ ተቋማት ዕይታ!

በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማርቆስ አማካኝነት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ሰኔ 24ን “የስብከተ ወንጌል” ቀን ብላ ሰይማለች፤ ዓላማውንም ጳጳሱ እንዲህ ብለው ያስረዳሉ፣ “የስብከተ ወንጌል ቀን ሲባል ስብከተ ወንጌል የሌለበት ቀን የለም። የወንጌልን ቀን ማክበር የተፈለገበት ዕውቅናን ለመስጠት ነው፤ ይበልጥ በትውልዱ አእምሮ … ዛሬ የወንጌል ቀን ብሎ እንዲያዘክረው እንዲያከብረው … ሕፃናት ጭምር እንዲያውቁት ነው ትልቁ ዓላማው።” መሪ ቃሉም፣ “በወንጌል ተልእኮ ትውልዱን መታደግ” የሚል እንደ ኾነ ተጠቅሶአል።




Sunday, 9 June 2024

ሰኔ 16 ቃለ አዋዲ፤ ሰኔ 23 ማኅበረ አኀው አይቀርም!

 

“ዘወትር እየተገናኘን ርስ በርሳችን እንበረታታ እንጂ አንዳንዶች ማድረግ እንደ ለመዱት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም የጌታ መምጫ ቀን መቃረቡን እያስታወሳችሁ ይህን ነገር በይበልጥ አድርጉ።” (ዕብ. 10፥25)

የዕብራውያን አማኞች፣ መንፈሳዊ ኅብረትን ስደትን ከመፍራት የተነሣ ተወት አድርገው ነበር፤ እናም ብዙዎች ወደ መንፈሳዊ ኅብረቶች ከመሄድ ይልቅ፣ በየቤቶቻቸው ተቀምጠው ነበር። ሌሎች ደግሞ አይሁድና አሕዛብ በአንድነት ኅብረት ሊያደርጉ አይገባቸውም የሚለውን ትችትና ነቀፋ በመፍራት ኅብረት ከማድረግ አፈግፍገው ነበር። ነገር ግን እኒህና ሌሎች በቂ የሚመስሉ ምክንያቶች ቢኖሩም፣ ከመንፈሳዊ ኅብረት መታጎል ወይም መቅረት ፍጹም ትክክል አይደለም።



Jajjabina isa Waaqayyoo (kutaa 1ffaa)

 

Sunday, 2 June 2024

ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፲፪)

 Please read in PDF

ካለፈው የቀጠለ …

2.   ጹም ፍቅርእግዚአብሔርም[ሥላሴ] ፍቅር ነው (1ዮሐ. 4፥16)፤ ይህ ፍቅር፣ ፍጥረት ከመፈጠሩ በፊት በሥላሴ ዘንድ ያለ ነው፤ ጌታችን ኢየሱስ፤ “ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ … ።” (ዮሐ. 17፥24) ብሎ ሲናገር፣ አብና ወልድ ከዘላለም ጀምሮ ይዋደዱ እንደ ነበርና አብም ለወልድ የሚሰጠው ክብር እንዳለ ያሳየናል። “አባት ልጁን ይወዳል” እንዲል (ዮሐ. 3፥35)።



Wednesday, 29 May 2024

የድል መንገድ!

 Please read in PDF

መስቀልና ትንሣኤ ሊነጣጠሉ የማይቻላቸው፣ የክርስትና የአንድ ሳንቲም ኹለት ገጽታዎች ናቸው። መስቀሉ ውርደትን፣ ሽንፈትን፣ አለልክ ዝቅ ማለትን በውስጡ የያዘ ቢኾንም፣ ድል መንሣትን፣ ሙሉ ለሙሉ የተፈጸመ ወይም የተጠናቀቀ የኅጢአት ክፍያን (ዮሐ. 19፥30)፣ ጠላትን ጠርቆ ከመንገድ ማስወገድን ኹሉ (ቈላ. 2፥14) አጭቆ የያዘ፣ የክርስትና እጅግ አስደናቂ መንገድ ነው።

Sunday, 19 May 2024

ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፲፩)

 Please read in PDF

ገረላሴንጥናታችንስተምረናል?

1.   ሥሉሳዊ አንድነትበሥላሴ ዘንድ ፍጹም አንድነት አለ፤ አንድነታቸውም ፍጹም የኾነና እንከን አልባ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ፣ የጌታችን ኢየሱስን ንግግር ሲናገር እንዲህ አለ፤ “እኔና አብ አንድ ነን።” (ዮሐ. 10፥30)። ጌታችን ኢየሱስ ይህን ሲናገር፣ አብ በእርሱ፤ እርሱም በአብ በማይለያይ ዘላለማዊ መለኮታዊ አንድነት አብረው መኖራቸውን ማስተዋል ይቻላል።



Sunday, 5 May 2024

በእውነት አገኘችው!

 

በድኑን በሽቱ ልትቀባው ሽታ

በብርቱ ስትፈልግ ተርባ ተጠምታ

አጽንታ በትጋት በድቅድቅ ጨለማ

የሴትነት ፍርሃት ኹሉን ተቋቁማ ...

Saturday, 4 May 2024

Fiixaan Baheera!

 Fannoo irra nuuf oolu isaatiin gatiin cubbuu keenyaa guututti kafalameera; foon uffatee nuuf du'u isaatiin hamannaan seexanaa kammiyuu nurraa ka'eera; dadhabaa fakkaatee fannoo irratti mul'atuus inni Gooftaan keenya Yasuus du'a fi awwaala mo'achuun hunda Goonfateera! Ameen!