የእውነት ቃል አገልግሎት፣ የእምነት እንቅስቃሴ አጋፋሪ ትምህርት ነው። የእምነት
እንቅስቃሴ ትምህርቶቹ ኹሉ ሰውንና ራስን ወደ ማላቅ፤ ሰውን አምላክና አንዳች ልዩ ኃይል በውስጡ እንዳለ የሚያሞኙ፣ የሚያጃጅሉ፣ በምኞት የሚያስጎመጁና የሚያነኾልሉ
“የከንቱ ከንቱ፤ ከንቱ ከንቱ ስብከቶችና ትምህርቶችን” የታጀለ አስተምህሮ ነው። ትምህርቶቻቸው ማዕከሉ ክርስቶስ መዳረሻውና ፍጻሜው
የእግዚአብሔር መንግሥት መስፋት አይደለም።
Thursday, 20 May 2021
የእውነት ቃል አገልግሎትና የእምነት እንቅስቃሴ ተመሳሳይነት!
Wednesday, 19 May 2021
ጌታ ኢየሱስ ነቢይም ነው!
ሊቀ ነቢያት ሙሴ እስራኤልን በተናገረው የስንብት ንግግሩ፥ “አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል እርሱንም ታደምጣለህ” (ዘዳግ. 18፥16) በማለት፥ ለጊዜው ከእርሱ በኋላ ለሚነሱ ለሌሎች ነቢያት ሲናገር በፍጻሜው ግን በትንቢት መልክ ስለሚመጣው መሲሕና ትንቢቱ በእርሱም የተፈጸመ መኾኑን እናያለን። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ አምስት ሺህ ወንዶችን ባሳመነበት (ሐዋ. 4፥4) የኢየሩሳሌም ስብከቱ በጌታ ኢየሱስን ትንቢቱ በትክክል መፈጸሙን ጠቅሶ አብራርቶታል።
Tuesday, 18 May 2021
Saturday, 15 May 2021
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፰)
ካለፈው የቀጠለ …
እምነት፦ ሰው፣ በእግዚአብሔር ላይ ያለውን መደገፍ ከሚገልጥበት መንገድ አንዱና ተቀዳሚው
እምነት ነው። እግዚአብሔር ለዘላለም እርሱም፤ ቃሉም ታማኝ ነው (2ጢሞ. 2፥13፤ ቲቶ 3፥8)። አማኝ እግዚአብሔር በተናገረው
ቃሎቹ ላይ ፍጹም መደገፉ እርሱ እምነት ነው። እኛ በእግዚአብሔር ላይ ጥገኞች ነን፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር የፍጥረቱ አካል አይደለም፤
ይልቅ ፍጥረቱን ብቻውን ፈጥሮአልና እርሱ ከፍጥረቱ እጅግ የተለየና ምጡቅ ነው። ፍጥረት በእርሱ ይደገፋል፣ የእርሱን መግቦት ይጠባበቃል፤
እግዚአብሔር ግን በፍጥረቱ ፈጽሞ አይደገፍም።
Wednesday, 12 May 2021
ከኦርቶዶክስ ውጭ ያለ መጤ ነው?
ከንቱ ትምክህት!
ማኅበረ ቅዱሳንና አንዳንድ የኦርቶዶክስ ሰባክያን፣ ስለ ክርስትና ሲያወሩ፣
ክርስትናን ራሳቸው ጠፍጥፈው የሠሩትና ለዓለም የናኙት ይመስላሉ። እነርሱ በግብዝነት የሚመኩትን ያህል ክርስትና የሰበኩት፣ የመንግሥቱን
ወንጌል ለዓለሙ የናኙት የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት እንኳ እንደ እነርሱ ፈጽሞ አይመኩም፤ አይገበዙምም። እጅግ በጣም የሚያስደንቀው
ነገር፣ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ አባ ሰላማ፣ ኢትዮጵያዊ እንዳልኾነ የሚያውቁ እጅግ ጥቂቶች ናቸው። እንዲያውም ከታወቁት የቤተ ክርስቲያን
ታሪክ ጸሐፍት አንዱ፣ ቅዱስ ማቴዎስ የተገደለው በኢትዮጵያ ምድር እንደ ኾነ ይነግረናል። ክርስትና አገር በቀል ቢኾን፣ ክርስቲያን
በኢትዮጵያ ምድር ባልተገደለ!
Saturday, 8 May 2021
ግንቦት ልደታና የሕይወት ትዝታዬ!
የዛሬ አሥራ ሰባት ዓመት ገደማ፣ ነፍሴ ከግንቦት አንድ አምላኪያን እጅ ያመለጠችበት ቀን ነው። በዚያን ቀን፣ በአርሲ ነጌሌ ሶጊዶ ማርያም ቤተ ክርስቲያን በዓለ ንግሡ ላይ ላገለግል ተጠርቼ በዚያ ነበርኩ። “የተሸሸገ ጣዖት” በሚል ርዕስ፣ የያዕቆብ ሚስት ራሔል ጣዖትን መሸሸጓንና በዚህም የደረሰባትን በማንሳት አንስቼ አገለገልሁ፤ እኛም ይህን ማድረግ እንደሌለብን ብርቱ ማስጠንቀቂያ በማኖር ጭምር። ነገር ግን በዚያን ቀን ሳስተምር፣ ከታቦቱ ጎን ትምህርቴን ቆሞ ይሰማ የነበረ፣ የገጠር ከተማይቱ ጠንቋይ ደም በሰረበ ዓይኖቹ ይመለከተኝ ኖሯል።
Thursday, 6 May 2021
ይድረስ እንደ እኔ ለነበራችሁ ኹሉ!
እኔ!
በአጭር ቃል፣ እኔ ትላንትና የክርስቶስን መካከለኝነት ነቅፌ የማርያምን መካከለኝነት አስተምር ነበር፤ የክርስቶስን መካከለኝነት ያስተምሩና ይሰብኩ የነበሩትን ነቅፍ፣ ሰድብ፣ በብርቱ ቃል ተች፣ አዋርድ ነበር። እኔ በማደርገው ንግግርና ድርጊት ሰዎች እስኪሸማቀቁ ድረስ ለብዙዎች የመሰናከልና የመውደቅ ምክንያት ነበርኩ። ማርያምን በዝማሬ አምልኬአለሁ፤ ወደ እርሷ ጸልይ፤ በስሟም እማጠን፣ አማልጂኝ ብዬም እለምናት ነበር። ለስእሏ እሰግድ፣ ለስሟም ስዕለት አስገባ፣ በመላእክት፣ ቅዱሳን ተብለው በሚጠሩ ፍጡራን ሰዎችና ቊሳት ኹሉ ስም አምልኮ እፈጽም፣ እግዚአብሔር ሩቅ እንደ ነበር፣ መዳንን በግል ጥረት ማግኘት እንደሚቻል ለዚህም ገዳም ለገዳም እንከራተትም … ነበር።
Tuesday, 4 May 2021
Saturday, 1 May 2021
የሕማም ሰው
ነቢዩ ኢሳይያስ ስቁዩንና መከራ ተቀባዩን መሲሕ፣ “ደዌን የሚያውቅ የሕማም ሰው” ብሎ ይጠራዋል (ኢሳ. 53፥3)። መሲሑ መከራን የማይቀበልና ሕመም ተጠያፊ አይደለም፤ ይልቁን ሐዋርያው ጳውሎስ፣ “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ መኾኑን” (ፊልጵ. 2፥8) በግልጥ ተናገረ። መሲሑ ለመታመም የፈቀደ፣ ለመድቀቅ የወደደ፣ ለመዋረድ ክብሩንና ጥቅሙን ኹሉ በፈቃዱ የተወ፣ እግዚአብሔር ነፍሱ የተደሰተችበት ጻድቅ ባሪያ ነው (ኢሳ. 53፥11)።
Friday, 30 April 2021
Marii - Nuuf jecha Fannoo irra Oolmaa Gooftaa Yesuus!
"Yommuu bakka Qaraaniyoo jedhamu ga'anitti achitti isa fannisan;" (Luqa. 23:33)
Wednesday, 28 April 2021
Saturday, 24 April 2021
Saturday, 17 April 2021
ኒቆዲሞስና ነገረ ዳግም መወለድ
ኒቆዲሞስ፣ ኢየሱስን እጅግ በብዙ ከሚንቁት ፈሪሳውያን ወገንና ከአይሁድ አለቆች መካከል አንዱ የነበረ ሰው ነው። በዚያ ዘመን ፈሪሳዊ መኾን ሕጉን እንጠብቃለን፤ ሕጉን በመጠበቅም እንጸድቃለን ለሚሉ ሃይማኖተኞች ብርቱ ትምክህት ነው። ፈሪሳውያን ለሕጉ እጅግ ቀናተኞች ከመኾናቸው የተነሣም፣ ከመካከላቸው ቀራጮችንና ኀጢአተኞችን ፍጹም በማግለል ራሳቸውን እንደ ፍጹም ጻድቃን ይቈጥሩ ነበር።
Thursday, 15 April 2021
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፯)
ካለፈው የቀጠለ …
ጽድቅ፦ “ጽድቅ” የሚለው ቃል የአማርኛ ተካካይ ትርጉሙ፣ “ሕግን መፈጸም፣ እንደ ሕግ መኖርና መመራት፣ ትክክለኛነት፣ እውነት፣ ቀጥተኛ፣ ፍትሓዊ፣ በጎ ምግባር” ማለት ነው። አለቃ ኪዳነ ወልድም በመዝገበ ቃላቸው ሲተረጕሙ “እውነት፣ ርግጥ፣ ቅንነት”።[1] ይላሉ። ይህም በቀጥታ ከእግዚአብሔር ባሕርይ ወይም ከፍጹም ትክክለኛነቱ ጋር የሚገናኝ ነው። ሰው ኀጢአተኛ ስለ ኾነ የእግዚአብሔርን ጽድቅ መፈጸም አይችልም። በተለይ ደግሞ ከመዳን ትምህርት ጋር አያይዘን ስናነሳው እንዲህ ማለት እንችላለን፤ ሰው መጽደቅ የሚችለው ከእግዚአብሔር ልጅ ከክርስቶስ የቤዝወት ሥራ የተነሣ ብቻ ነው።
Tuesday, 13 April 2021
አባባይ “shows”
የስህተት መምህራን “የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ ምን ያህል የጽድቅ አገልጋዮች እንደሚመስሉ” (2ቆሮ. 11፥13-14)፣ ምን ያህል ውስጠ ተኵላነታቸውን ደብቀው የበግ ለምድ እንደሚለብሱ (ማቴ. 7፥15) … ጃፒ ከኬፋ ሚደቅሳ ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ ጥሩ ማሳያ ነው[በእርግጥ እንዲህ ዓይነት አባባይ ቃለ መጠይቆች፣ ከዚህ በፊት ብዙ ተደርገዋል]።


