ካለፈው የቀጠለ …
ጽድቅ፦ “ጽድቅ” የሚለው ቃል የአማርኛ ተካካይ ትርጉሙ፣ “ሕግን መፈጸም፣ እንደ ሕግ መኖርና መመራት፣ ትክክለኛነት፣ እውነት፣ ቀጥተኛ፣ ፍትሓዊ፣ በጎ ምግባር” ማለት ነው። አለቃ ኪዳነ ወልድም በመዝገበ ቃላቸው ሲተረጕሙ “እውነት፣ ርግጥ፣ ቅንነት”።[1] ይላሉ። ይህም በቀጥታ ከእግዚአብሔር ባሕርይ ወይም ከፍጹም ትክክለኛነቱ ጋር የሚገናኝ ነው። ሰው ኀጢአተኛ ስለ ኾነ የእግዚአብሔርን ጽድቅ መፈጸም አይችልም። በተለይ ደግሞ ከመዳን ትምህርት ጋር አያይዘን ስናነሳው እንዲህ ማለት እንችላለን፤ ሰው መጽደቅ የሚችለው ከእግዚአብሔር ልጅ ከክርስቶስ የቤዝወት ሥራ የተነሣ ብቻ ነው።
ሰዎች የራሳቸውን ጽድቅ የሚያቆሙበት ጊዜ አለ፤ የሰው ጽድቅና የእግዚአብሔር
ጽድቅ ፈጽሞ አንድ አይደሉም፤ ሰዎች የእግዚአብሔርን ጽድቅ ባለማወቅ፣ በራሳቸው የሚያቆሙት ጽድቅ እንዳለ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ
ይናገራል (ሮሜ 10፥3)፤ ጌታችን ኢየሱስ እንዳስተማረንም፣ ሰዎች “እየጾሙና እየጸለዩ ወይም መልካም ሥራ እየሠሩ” ከእግዚአብሔር
ጽድቅ ተቃራኒ ሊኾኑ ይችላሉ፤ (ሉቃ. 18፥9-14)። የሰው ጽድቅ ያለ እግዚአብሔር፣ ራሱን የሚያጸድቅና እጅግ ራሱን ከፍ በማድረግ
የሚታበይና የሚገበዝ ነው። በገዛ ራስ መልካም ሥራ መመካት፣ እርሱ የራስ ጽድቅ ነውና።
የእግዚአብሔር ቃል ግን መዳንን በተመለከተ በግልጥ፣ “ጸጋው
በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።” (ኤፌ.
2፥8-9) በእርግጥም፣ “እንግዲህ
ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ።” እንዲል። ይህም፣ “ … በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት
የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥ እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የኾነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ
ነው፤” (ሮሜ 3፥21-22፤ 9፥16)። “እንግዲህ
ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የኾነ ጽድቅ ነው፤” (ሮሜ 9፥30)
“የእግዚአብሔር ጽድቅ
ኀጢአተኞችን በማጽደቅ ይገለጣል፤ ለአንዳንዶች እግዚአብሔር በሁሉን ቻይነቱና በፍቅሩ መሠረት ለኀጢአተኛ እንዲሁ ይቅር ማለት የሚችልይ
ይመስላቸዋል። ይህ ግን ሕጉን መጣስና የባሕርዩን ጽድቅ መካድ ነው፤ ዘዳ. 25፥1፤ 32፥4፤ 2ጢሞ. 2፥13። እንግዲህ ኀጢአተኛውን
በምን መሠረት ያጸድቃል (ሮም 4፥5)? ለኀጢአተኛው የራሱን ልጅ ደም ማስተስረያ አድርጎ በማቆም ሕጉን ፈጸመና ኀጢአተኛውን ሲያጸድቅ
ጽድቁን አሳየ፤ አጸናውም፤ ሮም 3፥25-26። ይህ ጽድቅ የሚቈጠረው በጻድቅ ልጁ ለሚያምኑ ሁሉ ነው፤ ክርስቶስ ጽድቃቸው ነውና፤
ኤር. 23፥6፤ 1ቆሮ. 1፥30-31፤ 2ቆሮ. 5፥21።”[2]
ጽድቅ የእግዚአብሔር ብቸኛ ገንዘቡ ነው፤ የሰው ልጅ ለእግዚአብሔር ጽድቅ ባለመታዘዙ፣
ከእግዚአብሔር ጽድቅ ተራቈተ፤ ተኰነነ። ስለዚህም ሰው ከእግዚአብሔር በመለየቱ ከጽድቅ ተራቆተ፤ እናም እግዚአብሔር ሰውን ለማጽደቅ
ከራሱ ባሕርይ የተነሣ እንጂ ከሰው ማንነት[ኀጢአተኝነት ወይም ሞራላዊ መልካምነት] ጋር የተያያዘ መኾኑን መጽሐፍ ቅዱስ አይነግረንም።
“ዲካኢኦ የሚለው
የአዲስ ኪዳን ቃል ተመሳሳይ ትርጉም አለው። ይኸውም ከሚከተሉት እንደምንረዳው “ጻድቅ ነህ” ብሎ ማወጅ ነው። 1/ በብዙ ቦታዎች
ሌላ ትርጕም ሊኖረው አይችልም፤ ሮሜ 3፥20-28፤ 4፥5-7፤ 5፥1 ገላ. 2፥16፤ 3፥11፤ 5፥4። 2/ ከኩነኔ ጋር ተቃራኒ
በመኾን ተቀምጧል፤ ሮሜ 8፥33፡ 34። 3/ እርሱን በመተካት የዋሉትም ቃላት ያው የሕግ አሳብ አላቸው ዮሐ. 3፥18፤ 5፥24፤
ሮሜ 4፥6፡7፤ 2ቆሮ. 5፥19። ስለዚህ የእነዚህ ቃላት ጥናት የሚነግረን በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉማቸው ልብን በመቀየር ጻድቅ ማድረግ
ሳይኾን “ጻድቅ ነህ” ብሎ ማወጅ ነው ማለት ነው።”[3]
ጽድቅ ወይም መጽደቅ እግዚአብሔር ለእኛ የሚቈጠርልን የክርስቶስ የመስቀል ወይም
የቤዝወት ሥራ ነው። ይህም እግዚአብሔር በክርስቶስ እኛን የሚቀበልበት ልዩ የማዳን መንገድ ነው። እግዚአብሔር እኛን “ጻድቃን ናችሁ”
ብሎ የተቀበለበት መንገድ፣ የክርስቶስን ጽድቅ ሰጥቶን ወይም ለእኛ ቈጥሮልን ነው። ይህንም ኹላችን የተቀበልነው ክርስቶስ በመስቀል
ላይ የሠራልን ሥራ በማመን ብቻ ነው። “እንደዚህ በእምነት እንጸድቅ ዘንድ ሕግ ወደ ክርስቶስ
የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆኖአል፤ እምነት ግን መጥቶአልና ከእንግዲህ ወዲህ ከሞግዚት በታች አይደለንም።” (ገላ. 3፥24-25)። በእርግጥም ለኀጢአተኞች የእግዚአብሔር የጽድቅ አዋጅ
ይገባናል!
“ጸጋ በአጠቃላይ አነጋገር እግዚአብሔር ዓለሙን
እንዲኹ ከመውደዱ የተነሣ አንድ ልጁን ለዓለም መድኃኒት አድርጐ መስጠቱን የገለጸበት የፍቅሩና የምሕረቱ የሥራ ውጤት ነው። (ዮሐ.
1፥12-18፤ 3፥16፤ 1ዮሐ. 4፥7-12)። በሕግና በክርስቶስ ጸጋ በመምጣቱ ያመኑትን እንዲሁ አጽድቋቸዋል (ሮሜ 3፥21-26)።
እንግዲህ የጸጋ መነሻ ምንጩ ከእግዚአብሔር ፍቅርና ከማዳን ሥራው ነው፤ … በክርስቶስ ያመኑ ሁሉ ጸጋ በጸጋ እንደ ኾኑና ጸጋም
በእጅጉ እንደ በዛላቸው … በጥንተ ተፈጥሮ የወደቀውንም ሰው በአዲስ ተፈጥሮ አድኖታል”[4]
እንግዲህ ስለ ጽድቅ በጠቅላላ እንዲህ ማለት እንችላለን፤
1.
የጽድቅ ምንጭ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው፤ (ሮሜ 3፥24፤ ቲቶ 3፥7)፣
2.
የጽድቅ መሠረት የክርስቶስ ሞት ነው (ሮሜ 3፥25-26፤ 5፥9፤ 2ቆሮ.
5፥21፤ ገላ. 3፥13)፣
3.
የጽድቅ መገኛ የክርስቶስ መታዘዝ ነው፤ (ሮሜ 5፥18-19፤ 10፥4፤ 1ቆሮ.
1፥30-31)፣
4.
የጽድቅ መንገድ እምነት ነው፤ (ሮሜ 3፥28፤ 4፥5፤ 5፥1፤ ፊልጵ. 3፥8-9)፣
5.
የጽድቅ መግለጫ መልካም ሥራ ነው፤ (ገላ. 4፥4-6፤ ኤፌ. 2፥8-10)[5]።
የ“መድሎተ ጽድቅ ጸሐፊ” የጽድቅ ትርጕም ስህተቱ
“የመድሎተ
ጽድቅ ጸሐፊ” ጽድቅ በሥራ ይገኛል ብላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች የሚባለው፣ ሐሰት እንደ ኾነና
ቤተ ክርስቲያን ያለ እምነት በሥራ ብቻ ይጸደቃል ብላ አታምንም፣ አታስተምርም ይላል።[6] ይህን ለማጽናትም፣
“በወንጌል ስለሚገኘው የመዳን ጸጋ፣ … “እምነት” ያለው ወንጌልን መኾኑ ግልጽ ነው።”[7] ብሎ ተናግሮአል። ነገር ግን ይህ አባባሉ በአደባባይና በግልጽ በቤቱ ውስጥ
ከሚታየው እውነታና ከሚሰበከው ጋር እርስ በእርሱ ሲጋጭ ይታያል። ምክንያቱም የትኛውም ኦርቶዶክሳዊ ገዳም ለገዳም የሚሄደው፣ በሙታን
ስም የሚዘክረው፣ የሚጾመው … ለመጽደቅ እንደ ኾነ አይክድም፤ እንዲያውም የአንዳንድ ሙታን ኪዳናት ሰው ከማጽደቅ ባለፈ ቀጥታ መንግሥተ
ሰማያትን የሚያስወርሱ ናቸው።
“የመድሎተ
ጽድቅ ጸሐፊ”ም ኾኑ ማኅበረ ቅዱሳን[8]፣ በክርስቶስ ሞትና
ትንሣኤ የታወጀውንና በእምነት የሚገኘውን ዘላለማዊ ጽድቅ በአንድም ቦታ ሲጠቅሱት አንመለከትም። እንዲያውም “የመድሎተ ጽድቅ ጸሐፊ” ይህን ለመቃወም ርቆ ሲሄድ እንመለከተዋለን፤
ሰው የሚጸድቀው በእምነት ነው እንጂ በእምነት ብቻ አይደለም ይለናል።[9] ጸሐፊው የመጽደቅንና
የመቀደስን ትምህርቶች እርስ በእርስ ሲያላትምና ሲያጋጭ እንመለከተዋለን። ሰው በእምነት ይጸድቃል ማለት ሌላ ትርጕም የለውም፤ በእምነት
ብቻ ይጸድቃል ማለት ነው፤ “ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር
ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው።”፤ “እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን
እንያዝ፤” እንዲል (ገላ. 3፥11፤ ሮሜ 5፥1) እንዲል።
“የመድሎተ
ጽድቅ ጸሐፊ” እንደ ተረጐመው፣ ለመጽደቅ እምነትና ሥራ በአንድነት የግድ ያስፈልጋል ብሎ የተናገረውን የሚደግፍ አንዳችም የመጽሐፍ
ቅዱስ ክፍል የለም። እግዚአብሔር ሰውን በክርስቶስ ለማጽደቅ ሰው ያለበትን ኹኔታ አልተመለከተም። እግዚአብሔር ሰውን ያጸደቀው በክርስቶስ ስጦታነት ነው። ሰው ግን ከጸደቀ በኋላ ሊቀደስና ሊታመን፤ ሊታዘዝ አይገባውም የሚልም
የመጽሐፍ ቅዱስም ትምህርት የለም። እኛን ለማጽደቅ በክርስቶስ ስጦታነት የተቀበለን ያው እግዚአብሔር ደግሞ እንቀደስም ዘንድ ጸጋውን
ያድለናል። በሌላ ንግግር እንጸድቅ ዘንድ የመዳንን እምነት የሚሰጠን ያው እግዚአብሔር (2ጴጥ. 1፥1)፤ እንቀደስና የመንፈስ ፍሬን
እናፈራ ዘንድም እምነትን ይሰጠናል፤ (ገላ. 5፥22)።
ይቀጥላል …
[1] አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሐፈ ሰዋስው
ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፤ ገጽ ፯፻፵፮
[2] ቄስ ኮሊን ማንሰል፤ ትምህርተ እግዚአብሔር
2ኛ እትም፤ 1999 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ንግድ
ማተሚያ ድርጅት፤ ገጽ 199
[3] ሉውስ
በርከኾፍ(ፕሮፌሰር)፤ የትምህርተ መለኮት ጥናት፤
ገጽ 200
[4] አበራ
በቀለ(ሊቀ ጉባኤ)፤ ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት፤
ገጽ 234፡ 236
[5] ኮሊን
ማንሰል(ቄስ)፤ ትምህርተ ክርስቶስ፤ ገጽ 356-357
[6] ገጽ 183
[7] ገጽ 189
[9] ገጽ
188
May the LORD be your guide & strength for days to come!!!!!
ReplyDeleteአንተ ሉሲፈር ነገር ነህ
ReplyDeleteመድሎተ ኦርቶዶክሳዊት ፅድቅ ቢሆን የመፅሐፉ አርዕስት፣ ባላከራከረም ነበር፤ምክንያቱም ለአባ እከሌ ፀበል ፀዲቅ የሚቆላው አሻሮ የሸተተው፣ 7 ትውልዱ የኦርቶዶክስ ገነት ይገባል የሚልም ዝሆን ወለደ ተረትም በመኖሩ ነው፤አሁን የምናየው መከራ ምንጩ የኦርቶዶክስ ተረት ለመሆኑ 100% እርግጠኛ ነኝ።
ReplyDeleteስለ ፅድቅና ቅድስና ምንም የማታውቀው ኦርቶዶክስ፣ ከዕድር የዘለለ ዋጋ እንደሌላት መታወቅ አለበት፤50ሚሊዮኖች አባላት ያሉት ትልቁ በኢትዮጵያ ዕድር ስሙ፦' ኦርቶዶክስ ተዋህዶ 'ይባላል፤period !!
"የራሷ ሲያርባት የሰዉ ታማስላለች" አንተ ራስህ ገና መች አመንክና!
ReplyDeleteተሀድሶ ደነገጥክ
ReplyDeleteወደህ ነው የምታነባት እየመረረህ ትውጣታለህ ።ደ/ን ያረጋል አበጋዝ እድሜህን ያርዝመው።ላለለማዎቅ ጥረት ሢያደርጉ አዕምሯቸውን ለማይረባ ነገር አሣልፎ ሠጣቻው ተብለዋልና ሑሌም አንተን መሠል ሠዎች ክርሥቶሥን እየገደሉ ፅድቅ የሠሩ ይመሥላቸዋል።
ReplyDeleteምን ነው አቅሙ ካለ መጽሐፍ አትጽፍምና አናነብልም ስንት አመት ደከማችው እስካሁን ግን ወፍ የለም ።
ReplyDeleteለመደሎተ ጽድቅ ፩ ምላሽ የሚሆን ነገር ሳትመልሱ
መደሎተ ጽድቅ ቅጽ ፪ ና ፫ ከች ብሎባችዋል ።
የተሃድሶ መናፍቃን #የነጭለባሽ__መናፍቃን እሳት እራት #መደሎተ__ጽድቅ ቅጽ ፩,፪,ና ፫
ግን አንብበው ታውቃለ?
ይህን የማንበብ አቅም ያለ እራሱ አይመስለኝም ፤ አይደለም መልስ የመስጠት?
ሰውየው ከባድ ነው!አንጎልህን አዞረብህ አይደል የባጥ የቆጡን አስቀባጠረህ ምን ዋጋ አው ቀባጥረህ ትቀራለህ!!
ReplyDeleteምነው? ከላይክ ላይ ያለው አጋንንት ነው መሰለኝ የጮከው።መድሎተ ጽድቅ የተሃድሶ መዶሻ ነውና አናት አናትክን ያለህጊዜ አንገሸገሸህ አጋንንቱ ራሱ ሲጮክ ያየሁት መሰለኝ።አይዞህ ምን ታረገዋለህ ሊቃውንት እንዲህ ያስጮሁሃል።ባይሆን ህዝብ እንዳትረብሽ ሆነህ ነው መጮክ እሽ።እኔ ግርም ሚለኝ ሲጨንቃችሁ ጊዜ በየ መንገዱ እና በየ አስፓልቱ ምትጮሁት ነገር ሃሃሃሃ.......ለማንኛውም አጅሬ ሰይጣን በነፃ ምጨፍርበት ሰው አግኝቻለሁ ብሎኛል ና አይዟቹህ እንዳታስቀይሙት እሽ።እኔ ስራየን ሚሰራልኝ ስላገኘሁ እረፍት ወጥቻለሁ ብሎኛል።ሰዓቱን እንዳትሸርፉበት በደንብ እንድታገለግሉት እሽ።ዋጋችሁን እንደሆን ይከፍላችኋል ስጋት አይግባችሁ።እሱ ላገልጋዮቹ በጣም ታማኝ ነው እሽ አይዟችሁ በርቱልኝ በደንብ ጩሁለት ወንጌልንም ስበኩለት የኢየሱስንም ማማለድ ስበኩለ እሽ አደራ ብሏችኋል።በሰላም በጤና ወደ እርሱ ይውሰዳችሁ መንግስተ ሲኦልንም ያውርሳችሁ።
ReplyDeleteመናፍቅ ፃፈ አልፃፈ አይገርምም
ReplyDeleteእራስ ምታት ለቀቀባችሁ ሉተር ገበሬ ሰው አይድውለም ነው ያለው ክዶ ዲቁና የለም ፓስተር አቤኔዘር
ReplyDeleteሀሀሀሀሀ ጮማ ነህ የምር ገና ምንም አላወቅህም
ReplyDeleteመድሎተ ስሑት አንተ ነህ።
ReplyDeleteስራ ፈት ፓስተር አቤኔዘር ተኩላው የሆነች ነገር ጣል ሲደረግልህ ያሾርኻል ደግሞ
ReplyDeleteከአለት ጋር ነው የተጋጨህው ወዳጄ አንድንም ሁለትም ደርሶኛል ሰሞኑን ደግሞ እሰልሳለሁ ። የአባቶቻችን ትምህርት ካለበት አምጥቶ አስጎንጭቶናል ላንተና ለመሰሎችህ ግን ስታሳዝኑ
ReplyDeleteዝም ብለህ ብታምን ይሻልህ ነበር:: አማራጩ እሱ ብቻ ነው
ReplyDeleteአዛባ ዴዴም ካላወክ ጠይቀን ።
ReplyDeleteዳቆን ነህ እንጅ ዕውቀትህ የዲያቆን አይደለም። ቱልቱላ መናፍቅ
ReplyDeleteእሺ የአዳራሽ አርበኛው ቀን በቀን እየደነስን እየጨፈርን እየዘለልልን እናመልከዋለን በ አለማዊ ዘፈን !!!!!!
ReplyDeleteጤና ቢስ ቅዠታም !💀💀💀 ሲጀመር ኢየሱስን ታውቀዋለህ! በጭፈራ በካራቲስትና በጫጫታ መሰለህ ? በስሙ መነገድና በእርሱ መኖር ይለያያሉ! ይሁዳምኮ ኢየሱስ ኢየሱስ እያለ ይከተለው ነበር ። ሲጀመር ከቅዠትህ ውጣ ። ሰው ሁን ። አስተውል ጌታ ጌታ ማለትኮ ሰይጣንም ይላል ። Back to Orthodox as your preachers!
ReplyDeleteድልብ መናፍቅ የሉተር ቡችላ ዝምብለህ አሳማህን ዋጥ የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች
ReplyDelete