Wednesday, 19 May 2021

ጌታ ኢየሱስ ነቢይም ነው!

 Please read in PDF

ሊቀ ነቢያት ሙሴ እስራኤልን በተናገረው የስንብት ንግግሩ፥ “አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል እርሱንም ታደምጣለህ” (ዘዳግ. 18፥16) በማለት፥ ለጊዜው ከእርሱ በኋላ ለሚነሱ ለሌሎች ነቢያት ሲናገር በፍጻሜው ግን በትንቢት መልክ ስለሚመጣው መሲሕና ትንቢቱ በእርሱም የተፈጸመ መኾኑን እናያለን። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ አምስት ሺህ ወንዶችን ባሳመነበት (ሐዋ. 4፥4) የኢየሩሳሌም ስብከቱ በጌታ ኢየሱስን ትንቢቱ በትክክል መፈጸሙን ጠቅሶ አብራርቶታል።

     ጌታ ክርስቶስን ነቢይ ነው ስንል፦

1.  በአባቱ ፈቃድ የተላከና ፈቃዱን ሊፈጽም የመጣ መሆኑን ያሳየናል።

የዕብራውያን መልዕክት ጸሐፊ ሙሴንና ጌታ ኢየሱስን ሲያነጻጽር  “ሙሴስ በኋላ ስለሚነገረው ነገር ምስክር ሊሆን በቤቱ ሁሉ እንደ ሎሌ የታመነ ነበረ፥ ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታመነ ነው፤ …” በማለት ያስቀምጣል (ዕብ.3፥5-6)። ሙሴ “እርሱን የሚመስል ነቢይ የለም” እስኪባል ቤተ እስራኤልን ምሳሌነት ባለው ቅንነት የመራ፤ ታማኝና ቅዱስ የነቢይ ሎሌ ነበረ (ዘዳግ. 34፥10፤ ዘኍ. 12፥7)። ሙሴ የተመረጠውና እንዲህ የተከናወነለት በያህዌ ፈቃድና እርሱም “ያለና የሚኖረውንም” አምላክ ፈቃድ ስለታዘዘ ነው (ዘጸ. 3፥1፤14)።

  እንደ ልጅ በቤቱ የታመነው ጌታ ኢየሱስ ደግሞ በነቢይነቱ በአባቱ ፈቃድ የተላከና የአባቱንም ፈቃድ የፈጸመ ነው። እንደ ነቢይ የአባቱን ፈቃድ ፈጽሟል ስንል፦

1.1.  ቃሉን ተናግሯል

     የነቢያት ትልቁ ሥራ የእግዚአብሔርን ቃል ሳይጨምሩና ሳይቀንሱ እንደተነገራቸው ለህዝቡ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” ብለው መናገራቸው ነው።(አሞ.1፥3 ፤ ሚክ. 3፥8) ጌታ ኢየሱስ ግን ነቢይ ሆኖ አገለገለ ብንልም እንደ ነቢያት “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” አላለም፤ እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ነውና “እኔ ግን እላችኋለሁ ወይም እውነት እውነት እላችኋለሁ” አለ እንጂ፤ (ማቴ. 5፥22፤ 28፤ 32፤ 34፤ 39፤ 44 …  ዮሐ. 6፥32 ፤ 47፤ 53 ጥቂት ማሳያዎች ናቸው።) ነቢያት “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” ያሉት እርሱን ነው፤ እርሱ ግን መለኰታዊ ክብሩን በሥጋ ሸፍኖ በተገለጠ ጊዜ ግን “እኔ አላችኋለሁ” አለ።

“ኢየሱስ ነቢይ ነው”  የሚለውን ትምህርት አንዳንዶች “አምላካዊ ክብሩን የሚቀንስ” ሌሎች ደግሞ “ፍጡር ነው” ለሚለው አስተምህሮአቸው የድጋፍ ሃሳብ አድርገው ያቀርባሉ። ነገር ግን እርሱን ነቢይ ነው ማለታችን በመሢሃዊ አገልግሎቱ አባቱንና እኛን በማገልገሉ ስላደረገው እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት የለውም።

   እንኪያስ፦ በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑ እንዲህ ተብሎላቸዋል፦

“ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ … ” (1ዮሐ. 5፥1)

የመወለዳችን፤ የእርሱም ልጆች የመባላችን ምስጢሩ እንዲህ ብለን ማመናችን ነውና እንዲህ እናምናለን፤ እንታመናለን። አሜን ወአሜን።

(አቤንኤዘር ተክሉ (ዲያቆን)፤ ኢየሱስ ማን ነው?፤ ያልታተመ፤ ከገጽ 141-153 የተቀነጨበ)

5 comments:

  1. ሉቃስ 24
    ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
    ¹⁹ እርሱም፦ ይህ ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት፦ በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፤

    ²⁷ ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።

    ReplyDelete
  2. እኔ የሚገርመኝ እራሱጌታ ለደቀመዝሙሮቹ እንዲህ አላቸዉ ሰዎችማንይሉኛልብሎጠየቃቸው እነሱም መለሱለት ሙሴ ነው የሚሉአሉኤልያስነው የሚሉአሉ እኩሌቶቹ እንደመናቆች አምላክነቱንተጠራጥረው አማላጅነውየሚሉት ከነቢያትአንዱነውየሚሉአሉ ብለውመለሱለት ጌታክርስቶስ መለሠና እናንተስማንትሉኛላችሁአላቸው ቅዱስጴጥሮስ አንተ የሕያውእግዚአብሔርልነህ ብሎሲመሰክር ጴጥሮስሆይመንፈስቅዱስገለጸህእንጅከስጋናከደምሐሳብአይደለምአለው እንግዲህ እራሱ እኔ ክፉዎች አይሁድ መናፍቆችእነበግዋሻው እነደሚሉት አዎነቢይነኘአላለም ስለዚህይሄእውነቱእያለ ሌላመቀባጠር ምንአስፈለገ ።

    ReplyDelete
  3. GOD bless you for sharing Abiny I can't wait for these book to be published. May the SPIRIT be your guide and strength for days to come!!!!!

    ReplyDelete
  4. እከካም ጴንጤ እንዳንተ በዱቄትና በዘይት እምነት የሚለውጥ አይደለም ።

    ReplyDelete
  5. አይደክሜውና ሆዳሙ ፓስተር አቤኔዘር ተኩላው

    ReplyDelete