ዘነበ ወላ፣ ሰሞኑን ሥራና ምናኔን አስመልክቶ የሰጠው አስተያየት በብዙ ኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ጥርስ አስነክሶበታል። ብዙ ኦርቶዶክሳውያን የሰላ ትችት ሲሰነዘርባቸው፣ ችግሮቻቸውንና ስህተቶቻቸውን ከማረቅ ይልቅ፣ ቤተ ክርስቲያንን ለማዋረድ የሚነገር አድርጎ ማሰብ፣ “ልጅ እናቷን ምጥ አታስተምርም” የሚል አጉል ፈሊጥ መጥቀስ፣ ዛሬ መጥታችኹ ቤተ ክርስቲያንን ወንጌል ልትሰብኳት፣ ችግሯን ልታመለክቱ አትችሉም … የሚሉ አያሌ አሉታዊ ምላሾች ይቀርባሉ። ይህን ስንል ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማዋረድ የሚሠሩ የሉም ማለት አልችልም። ይኹንና ደግመን ደጋግመን መናገር የምንፈልገው፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ወደ እውነተኛ የወንጌል ጐዳና እስክትመለስና በመካከልዋ ያለውን “ዕድፍና ጉድፍ” እስክታስወግድ ድረስ “የተሐድሶ ድምጽ” ማሰማታችንን አናቆምም!
Saturday, 14 September 2024
Wednesday, 11 September 2024
ዘመን የተጨመረልን በመግቦቱ ነው!
የእግዚአብሔር መግቦት እጅግ አስደናቂ ነው። ጌታ ፍጹም መጋቢ ስለ ኾነ
በፍጥረት መካከል አድልዎ ሳያደርግ የሚተገብራቸው አያሌ መግቦቶች አሉ፤ ቅዱሳት መጻሕፍትን ዋቢ አድርገን ምሳሌ ብንጠቅስ፦ “ርሱ[እግዚአብሔር] በክፎዎችና በበጎዎች
ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።” (ማቴ. 5፥44)፣ እንዲኹም እግዚአብሔር አምላክ ጋብቻን ባርኮ
ለመላለሙ በአምላካዊ መግቦቱ መስጠቱን እናስተውላለን፤ (ዘፍ. 2፥24፤ ማቴ. 19፥4-5)።
Tuesday, 10 September 2024
Wednesday, 4 September 2024
የቁባቱን በድን የቆራጠው ካህን! (መሳ. 19-20)
በእስራኤል ልጆች ታሪክ ውስጥ አያሌ አስከፊ ተግባራት ተከናውነዋል፤ ዛሬ
የምናየው ይህ አንዱ ነው፤ “በዚያም
ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ በሌለበት ጊዜ በተራራማው በኤፍሬም አገር ማዶ የተቀመጠ ሌዋዊ ነበረ፤” (መሳ. 19፥1) ይላል፣ በመሳፍንት
መጽሐፍ ውስጥ ከተቀመጡት የብንያም ሰዎችን የሥነ ምግባር ብልሹነትና በምላጭ ጫፍ ላይ መቆማቸውን ከሚያሳዩት ታሪኮች አንዱን
ለመተረክ ሲነሳ።
በርግጥ ሌዋዊው ካህን ቁባቱን ፍለጋ ከኤፍሬም ወደ ቤተልሔም መሄዱ፣ ከአንድ
ሚስት በላይ ማግባቱን ያሳያል፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ያለው ተግባር አልነበረም፤ በተጨማሪም፣ እግዚአብሔር
ለእስራኤል ልጆች መሳፍንትን የሰጠው፣ ርሱ ብቻውን በነርሱ ላይ ሊነግሥ ነበር። ነገር ግን ለጌታ ከመታዘዝ ይልቅ፣ የሃይማኖት
መሪዎቿ ድካምና ኃጢአት እያየለባቸውና እየባሰባቸው ሲሄድ በተደጋጋሚ እንመለከታለን።
Saturday, 31 August 2024
“ኑ ወደ ኦርቶዶክስ ተመለሱ!” ለምትሉን!
ኦርቶዶክሳዊው ተሐድሶ እያየለና በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትን እያገኘ ሲመጣ፣ በቃላት በማባበል፣ በጥቅምና በክብር በማማለል፣ መልሰን አናወግዛችሁም በሚል የተስፋ ቃል በመስጠት … እየቀረበልን ያለው ጥያቄ፣ “ኑ! ወደ ኦርቶዶክስ ተመለሱ!” ሚል ነው። ከዚህ በታች የምናስቀምጣቸው ጠንካራ ምክንያቶች የመመለስና ያለ መመለስን ጥያቄ ትርጕም ይሰጡታል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወደ ኋላ ስለ መመለስ በማስጠንቀቂያ አዘል ከተጻፉ
መልእክቶች አንዱ፣ የዕብራውያን መልእክት ነው። የሐዋርያት ሥራን መጽሐፍ ስናጠና እንደምናስተውለው፣ አስቀድሞ ክርስትናን
ለተቀበሉ አይሁድ የመጀመሪያዎቹ የቤተ ክርስቲያን ዓመታት እጅግ አስቸጋሪዎች ነበሩ። በእነዚህ ጊዜያት ክርስትና በአጭሩ
የአይሁድ ሃይማኖት ኾኖ ነበር። ከ120ው የጌታ ቤተ ሰቦች (ሐ.ሥ. 1፥15) ጀምሮ ኹሉም በአንድነት ያመልኩና ያገለግሉ
የነበረውም በአይሁድ ቤተ መቅደስ ውስጥ ነበርና፤ (ሐ.ሥ. 2፥46፤ 3፥1፤ 5፥42)።
Sunday, 18 August 2024
የ“ታቦር” ስብከቴን ቀይሬአለኹ!
ጌታችን ኢየሱስ ክብረ መንግሥቱን የገለጠበት፤ ማንነቱን ለደቀ መዛሙርቱ
ያሳየበት የክብሩ ተራራ እውነት እጅግ አስደናቂ ነው። ጌታ፣ በፊልጶስ ቂሣርያ፣ “ለብቻውም ሲጸልይ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር
ነበሩና፦ ሕዝቡ እኔ ማን እንደ ኾንሁ ይላሉ? ብሎ ጠየቃቸው።” (ሉቃ. 9፥18) ደቀ መዛሙርቱ ሲመልሱ፣ የነቢያትን ስም
በመጥራት እንዲኹም ከነቢያት አንዱ ነህ ይላሉ ብለው መለሱ። ቀጥሎም፣ “እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።” (ሉቃ.
9፥20) “ጴጥሮስም መልሶ፦ ከእግዚአብሔር የተቀባህ ነህ አለ።”ቅዱስ ጴጥሮስ ይህን ታላቅ እውነት በመመለሱ፣ “ኢየሱስም መልሶ
እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።” (ማቴ.
16፥17) በማለት የጴጥሮስን ዕድለኝነት ጌታችን መሠከረለት።
Wednesday, 31 July 2024
ለእውነተኛ ተሐድሶ ኦርቶዶክስን አይጠቅማትም!
ከጥቂት ዓመታት ወዲህ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ
ከተደረጉ “ፖለቲካዊ የቤተ ክርስቲያን ውሳኔዎች” አንዱ፣ ሰዎች በቋንቋቸው ወንጌል ሊማሩ ይገባል የሚል ነበር፤ በዚህ ዐሳብ
ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ “በወንጌል ልብ” በተደጋጋሚ ይጠይቁ ከነበሩ ሰዎች መካከል አንዱ በመኾኔ፣ በጥያቄው ፍጹም እስማማለኹ።
ነገር ግን መልሱ የተሰጠውና በተግባር ላይ የዋለው ፍጹም መንፈሳዊ ባልኾነ መንገድ ባለ መኾኑ ሳዝን ዳሩ ግን በእግዚአብሔር
ሉዓላዊነት እጽናናለኹ!
Sunday, 28 July 2024
የፓሪስ ኦሎምፒክ ሴሰ*ኝነት፣ ሰዶ*ማ*ዊነት፣ በጌታ እራት ሲሳ*ለቁ!
Friday, 19 July 2024
ስለ ኦርቶዶክስ በልቤ ያለ ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት!
ከልጅነቴ ያደግኹት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነው፤ የተጠመቅኹት፤ የቆረብኹት፤ በቅንአትና
በትጋት ያገለገልኹት … በዚያ ነው። በዚያ የነበረኝ አገልግሎት በዕውቀትም በቅናትም እንደ ነበር ብዙዎች ምስክሮቼ ናቸው።
የክብሩንና የትንሣኤውን ወንጌል በትክክል ስረዳና ስመሰክር ግን ብዙዎች ተቃወሙኝ፤ እናም አብረኸን ልትኾን አይገባም ሲሉኝና
ሲገፉኝ ወጣኹ።
Friday, 5 July 2024
ወርቅ ሲደብስ!
ጳጳሱ ቅዱሳት መጻሕፍትን አላነበቡምን?
ጳጳሱ ለማርያም ያላቸው አስተምኅሮ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ
በተቃራኒ የቆመ ነው፤ እንዲህ ያለ ነገር በርግጥ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ “የታወቁ መምህራን” የሚናገሩት ነው፤ ከዚህ ቀደም
ዲያቆን ኃይሌ፣ “እመቤታችን ማማለድ አይደለም አፍርሳን መሥራት ትችላለች” ብሎ መናገሩንና ለዚህም ምላሽ መስጠታችን
ይታወሳል፡፡ ለምን ኾን ብለው ማርያምን በማግነንና በማስመለክ፣ እግዚአብሔርንና ስሙን መሳደብ እንደሚፈልጉ አላውቅም፤
እግዚአብሔርንና እግዚአብሔር በልጁና በመንፈሱ የሠራውን ሥራ ባለማወቃቸውም እጅግ እደነቃለሁ!
Tuesday, 2 July 2024
ጌታ ኦርቶዶክስን በወንጌል ሊጎበኝ እያሰበ ቢኾንስ?
“የስብከተ ወንጌል”ና “የመንፈስ ቅዱስ ቀን”
በኹለቱ ተቋማት ዕይታ!
በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማርቆስ አማካኝነት፣ የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ሰኔ 24ን “የስብከተ ወንጌል” ቀን ብላ ሰይማለች፤ ዓላማውንም ጳጳሱ እንዲህ ብለው
ያስረዳሉ፣ “የስብከተ ወንጌል ቀን ሲባል ስብከተ ወንጌል የሌለበት ቀን የለም። የወንጌልን ቀን ማክበር የተፈለገበት ዕውቅናን
ለመስጠት ነው፤ ይበልጥ በትውልዱ አእምሮ … ዛሬ የወንጌል ቀን ብሎ እንዲያዘክረው እንዲያከብረው … ሕፃናት ጭምር እንዲያውቁት
ነው ትልቁ ዓላማው።” መሪ ቃሉም፣ “በወንጌል ተልእኮ ትውልዱን መታደግ” የሚል እንደ ኾነ ተጠቅሶአል።
Sunday, 30 June 2024
Sunday, 9 June 2024
ሰኔ 16 ቃለ አዋዲ፤ ሰኔ 23 ማኅበረ አኀው አይቀርም!
“ዘወትር እየተገናኘን ርስ
በርሳችን እንበረታታ እንጂ አንዳንዶች ማድረግ እንደ ለመዱት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም የጌታ መምጫ ቀን መቃረቡን
እያስታወሳችሁ ይህን ነገር በይበልጥ አድርጉ።” (ዕብ. 10፥25)
የዕብራውያን አማኞች፣ መንፈሳዊ ኅብረትን ስደትን ከመፍራት የተነሣ ተወት አድርገው ነበር፤ እናም ብዙዎች ወደ መንፈሳዊ ኅብረቶች ከመሄድ ይልቅ፣ በየቤቶቻቸው ተቀምጠው ነበር። ሌሎች ደግሞ አይሁድና አሕዛብ በአንድነት ኅብረት ሊያደርጉ አይገባቸውም የሚለውን ትችትና ነቀፋ በመፍራት ኅብረት ከማድረግ አፈግፍገው ነበር። ነገር ግን እኒህና ሌሎች በቂ የሚመስሉ ምክንያቶች ቢኖሩም፣ ከመንፈሳዊ ኅብረት መታጎል ወይም መቅረት ፍጹም ትክክል አይደለም።
Sunday, 2 June 2024
ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፲፪)
ካለፈው
የቀጠለ …
2. ፍጹም ፍቅር፦ እግዚአብሔርም[ሥላሴ] ፍቅር ነው (1ዮሐ. 4፥16)፤ ይህ ፍቅር፣ ፍጥረት ከመፈጠሩ በፊት በሥላሴ ዘንድ ያለ ነው፤ ጌታችን ኢየሱስ፤ “ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ … ።” (ዮሐ. 17፥24) ብሎ ሲናገር፣ አብና ወልድ ከዘላለም ጀምሮ ይዋደዱ እንደ ነበርና አብም ለወልድ የሚሰጠው ክብር እንዳለ ያሳየናል። “አባት ልጁን ይወዳል” እንዲል (ዮሐ. 3፥35)።
















