Please read in PDF
ይህ ጽሑፍ በ2008 ዓ.ም አጋማሽ
ላይ በአንድ ሌላ የጡመራ መድረክ ላይ በብዙዎች የተነበበ ነው! መልእክቱ ዛሬም ደማቅ ስለ ኾነ በድጋሚ እንዲቀርብ ኾኖአል!
ቃሉን የተናገረው በወርቀ ደሙ የዋጀንና ያዳነን መድኅን አለም ኢየሱስ
ክርስቶስ ነው። ደቀ መዛሙርቱ በፈሪሳውያንና በሄሮድስ እርሾ ክፉ ኃጢአት በመዋጥ እንዳይጠፉ ባስጠነቀቃቸው ጊዜ፣ እነርሱ ግን ከማስተዋል
ዘግይተው እንጀራ ባለመያዛቸው እንደ ተናገረ አስበው ተነጋገሩ። ጌታ ያየላቸው ዘላለማዊውን ዐሳብ ነው። እነርሱ ግን ገና በሥጋ
አዕምሮ ነበሩና ስለ ቍሳዊውና ተበልቶ እዳሪ ስለሆነው እንጀራ አሰቡ። እርሱ ስለመንፈሳዊው ነገር ይነግራቸዋል እነርሱ ግን የሚናገራቸውን
እንኳ በወግ አያስተውሉም።